Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ኸይሩል ከላም ለሁሉም avatar
ኸይሩል ከላም ለሁሉም
ኸይሩል ከላም ለሁሉም avatar
ኸይሩል ከላም ለሁሉም
Қайта жіберілді:
Islamic avatar
Islamic
🌺ፍጠኑ ፍጠኑ በጣም ቀላል ነው🌺
📚📚📚📚📚
የማታ እና የቀን መላእክት የሚሰበሰቡበት ሰላት የትኛው ነው


ትክክለኛውን መልስ ሲነኩ🖇 ሊንክ🖇 ይሰጣችኋል !!!

Islamic Wave :::::::::::::〖 @sudii20 〗
19.04.202519:11
ምዕራፍ ሁለት
#ተጅዊድ_በአማረኛ_ከሶስተኛው_እትም

🔴ክፍል ሁለት🔴 ( 2️⃣ )

#የአረበኛ_ፊደላቶች (حُرُوفُ الْعَرَبِيَّة)

♦ቁርኣንን ወይም ዓረበኛ ቋንቋን ለማንበብም ሆነ ለመፃፍ የአረብኛ ፊደላትን ማወቅ
/መለየት የግድ ነው።
የአሏሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ንግግር የሆነውን ቁርኣን በምዕራፎች በአንቀፆች በቃላቶችና በፊደላቶች የተዋቀረ ሆኖ እናገኛለን።
ሆኖም ግን ምዕራፎችን አንቀፆችን እና ቃላቶችን በትክክል ለመናገር ያስችለን ዘንድ ፊደላትን በትክክል ማወቅ
አስፈላጊና ግዴታም ነው።
ወደ ዝርዝሩም ከመግባታችን በፊት

📌ድምፅ ማለት ምን ማለት ነው?

📌ፊደል ማለትስ ምን ማለት ነው?

↪ድምፅ ማለት ፦⤵
በሀይል በመነካካት ወይም በመለያየት የሚገኝ የአየር ግጭት ሲሆን ከሰውም ከግዑዝም ይገኛል ::

↪ፊደል ማለት ደግሞ ⤵
በመናገሪያ አካል ላይ በመጋጨት የሚገኝ ድምፅ ነው።
ፊደላትም የሚነገሩት በጉሮሮ፣በምላስ፣በከንፈር ነው።
ቀጣይ ምዕራፎች ላይ በሰፊው ተዳሰዋል።

#የአረብኛ ፊደላትን አወቅን የሚባለው በጥቂቱ የሚከተሉትን ሦስት ነጥቦችን ስናውቅ ነው።
እነሱም፦
📌• 1⃣ኛ,ብዛታቸውን

📌• 2⃣ኛ,ቅርፃቸውን

📌• 3⃣ኛ,ድምፃቸውን

1⃣ኛ_ብዛታቸው ፦⤵
የአረበኛ ፊደላት ብዛትን በተመለከተ በሁለት የሚከፈል ሲሆን ፦

🔹🔸አንደኛው፡
#ድምፃቸው የሚታወቁ የአረብኛ ፊደላት (حُرُوفُ الْهِجائِيَّةُ)

🔹🔸ሁለተኛው፦
#ቅርፃቸው የሚታወቁ የዓረበኛ ፊደላት (حُرُوفُ الْأ بْجدية)ናችው።

↘በድምፃቸው የሚታወቁ የአርበኛ ፊደላት 29 ሲሆኑ እነሱም⤵

ا   ب    ت     ث     ج    ح   خ    د    ذ    ر     ز   س     ش  ص   

ض    ط    ظ   ع   غ    ف    ق    ك    ل    م     ن   و   ه      لا  ي 

በቅደም ተከተል ያስቀመጡትም ነስር ቢን ዓሲም አል_ለይሢዩ (نصر بن عاصم اليثي )
የሚባሉ ታላቅ የቋንቋ ምሁር ነበሩ።
የሞቱትም በ90 አመተ ሂጅራ ነው። 
በዚህ ቀደም ተከተል ያስቀመጡትም የፊደላትን መመሳሰልን ተከትሎ ሲሆን ተመሳሳይ ቅርፅ ያላቸውን ፊደላት በቀላሉ ለመለየት ነጠብጣቦች ተጠቅመዋል።

#ማስገንዘቢያ
ቀደምት ዐረቦች በተመሳሳይ ፊደላቶች ላይ ምንም አይነት ነጥብጣቦችን አይጠቀሙም ነበር።

#ጥልቅ_እውቀት
ሀምዛህ (ء) በቀደምት ዐረቦች ጊዜ ቅርፅ አልባ የነበረች ፊደል ስትሆን በድምፅ ደረጃ ግን ትታወቅ ነበር።
ሀምዛ የምትታወቀው በአሊፍ ( ا ) ቅርፅ ነበር።
የኋላ ኋላ ግን ኸሊል ቢን አህመድ አል ፈራሂዲዩ (خليل بن أحمد الفراهدي) (ረሒመሁሙሏህ) የተባሉ ታላቅ የቋንቋ ሊቅ የራሷ የሆነ ቅርፅ እንዲኖራት አድርገዋል። ቅርጿም ዓይን ፊደል ጋር በመውጫ ስለሚቀራረቡ የዓይንን (  ع  )ራሷን በመቁረጥ ለሀምዛህ (  ء  ) ቅርፅ ትሆን ዘንድ አበርክተዋል (  ء   )      (   ع   )
አሊፍን (  ا    ) ሀምዛን (  ء  )  ወክላ የምትመጣ ስትሆን ከመጨረሻው ቀደም ብላ የምትገኘዋን ላም አሊፍ ደግሞ አሊፍን ወክላ የምትመጣ ናት። በዚህ ምክንያት ድምፃቸው የሚታወቁ የዓረበኛ ፊደላት 29 ይሆናሉ።

↪ ቅርፃቸው የሚታወቁ (حروف الأبجدية )
ቅርፃቸው የሚታወቁ የዓረብኛ ፊደላት ብዛት ደግሞ 28 ሲሆኑ ቅደም ተከተላቸው፦
↪አሁን ባለው የዓረብኛ ቅደም ተከተልና አቀማመጥ አሊፍ መሳቢያ ፊደሏን ወክላ የምትመጣ ስትሆን ሀምዛ ደግሞ የራሷ ቅርፅ ኖሯት እናገኛለን።
ሰለዚህ ሁሉም ፊደላቶች  የራሳቸው የሆነ ቅርፅና ድምፅ ያላቸው ሲሆን
#ብዛታቸው_አሊፍን_ሳናስወግድ_29_ይሆናሉ

ا   ب    ت     ث     ج    ح   خ    د    ذ    ر     ز   س     ش  ص   

ض    ط    ظ   ع   غ    ف    ق    ك    ل    م     ن   و   ه      ء  ي 

2⃣ኛ,ቅርፃቸው
የዓረብኛ ፊደላትን በትክክል አወቅን ከሚያስብሉን ነጥቦች መካከል ቅርፃቸው ይገኝበታል።
ቅርፃቸውን ለይተን ማወቅ ወሳኝ ነገር ነው። ቅርፃቸውን ማወቅ ሲባል ነጠላ ሆነው የሚኖራቸውንም ሆነ በቃል በተለያዩ ቦታዎች ሲገቡ የሚኖራቸውን ቅርፅም ጭምር ነው።
በቅርፅ አንድ አይነት ሆነው በነጥብ የሚለያዩ ፊደላቶች በርካታ ናቸው። እነዚህን ፊደላቶች በትክክል ማወቅ ተገቢ ነው ። የሚከተሉት ሰንጠረዦች የዐረብኛ ፊደላት ነጠላ ሆነውና በቃል በተለያዩ ቦታዎች ሲገቡ የሚኖራቸው ቅርፅ የሚያሳይ ነው። ሰንጠርዡን ከተጅዊድ በአማረኛ ሶስተኛው እትም ላይ ገፅ 32-33 ማግኘት ይቻላል።

ከአረበኛ ፊደላቶች ውስጥ በቀኝም በግራም ቅጥያን የሚቀበሉ ፊደላቶች ያሉ ሲሆን በቀኝ ብቻ የሚቀበሉም ፊደላቶች አሉ።
በቀኝ ብቻ የሚቀበሉ ፊደላቶች የሚከተሉ ፊደላቶች
እነሱም፦   ا    د   ذ   ر  ز   و   ء  ናቸው ።
ከነዚህ ውጭ ያሉት ፊደላቶች በቀኝም በግራም ቅጥያን የሚቀበሉ ፊደላቶች ናቸው።

3⃣ኛ,ድምፃቸው⤵
የዓረብኛ ፊደላትን በትክክል አወቅን ከሚያስብሉን ነጥቦች መካከል ዋነኛው ድምፃቸው ነው።
ድምፃቸውን ለይተን ማወቅ ወሳኝ ነገር ነው።
ድምፃቸውን ማወቅ የሚያስፈልገው አንዱን ፊደል ከአንዱ ፊደል ለይተን እንድናውቅ እና እንድንለይ ነው። የፊደሉ ድምፅ የሚለካው በመውጫ ቦታውና በባህሪው ሲሆን መውጫ ቦታቸውንና ባህሪያቸው በሚከተሉት ምዕራፎቹ በሰፊው ተዳሷል። የሚከተሉትን ምዕራፎች ተጅዊድ መፅሀፍ 3ኛው እትም ላይ ታገኟቸዋላችሁ ኢንሻ አሏህ
ክፍል ሶስት ይቀጥላል...........
በቴሌግራም ለመከታተል፦
https://t.me/ibnumuhammed1433
https://t.me/ibnumuhammed1433
18.04.202506:30
20.04.202516:53
የተጅዊድና የቁርኣን ንባብ ህጎች



“ተጅዊድ” የሚለው ቃል ጥሬ ትርጉም ማሻሻልና ትክክለኝነት እንደ ማለት ነው። አንድን ነገር በ“ተጅዊድ” ሰራኸው ማለት የመጨረሻ ውብና በጣም ትክክል አድርገህ ሰራኸው ማለት ነው። ይህ በቋንቋ ደረጃ ያለው ትርጉም ሲሆን በቁርኣን ንባብ ህግ ሳይንስ መሰረት ተጅዊድ ማለት የቁርኣን አነባብ ሳይንስን የሚመለከት ሆኖ ትክክለኛ አነባበብና የቁርኣን ፊደላትን፣ ቃላትን፣ አንቀፆችን ትክክለኛ ድምፀታቸውንና አነባበባቸውን ጠብቆ ማንበብ ነው። ቃሉ በቋንቋ ደረጃ እና በቴክኒክ ደረጃ ያለው ትርጓሜ ያላቸው ግንኙነት ግልፅ ነው። በቋንቋ ደረጃ ያለው ትርጓሜ ተግባራትን በትክክል መስራትን የሚመለከት ሲሆን በቴክኒካል ትርጓሜው (ኢስጢላህ) ቁርኣንን በአግባቡ መቅራት (ማንበብ) ማለት ነው።

በመጀመሪያዎቹ የኢስላም ዘመናት ከኢስላም ፈጣን መስፋፋት በኋላ- በተለይም አረብ ያልሆኑ ሙስሊሞች መሀል- ለቁርኣን ተማሪዎች ማጣቀሻ የሚሆን የተጅዊድ ህግጋት መጽሐፍት ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኘ። ስለዚህም ቁርኣንን በተጅዊድ ማንበብ ለሚፈልጉ ሁሉ መነሻ (ማጣቀሻ) የተጂዊድ መጽሐፍት ማየቱ ተገቢ ሆነ። ይህ ማለት ግን ያለ አስተማሪ እገዛ ቁርኣንን በተጅዊድ መጽሐፍ እገዛ ብቻ ማንበብ ይቻላል ማለት አይደለም። ብቸኛና ልዩ የሆነ ሰነድን መሰረት ያደረገና የተቀናጀ የተጅዊድና የቁርኣን ንባብ አስተምህሮት ታሪካዊ ሂደቱን እንደጠበቀ ለተማሪዎች እየተሰጠ ይገኛል። በዚህም ሰነድን መሰረት ባደረገው አስተምህሮት መሰረት ተማሪዎች ሙሉ ቁርአኑን በልባቸው (በቃላቸው) ሙሉ የተጅዊድ ህጎቹን ጠብቀው ከመነሻው እስከ መድረሻው ቁርኣን የማስቀራት ፍቃድ ባለው ብቁ የቁርኣን አስተማሪ ላይ ቁርኣንን በማንበብ ቁርኣን የማንበብ የማስተማር ፍቃድ ይሰጣሉ። ይህ ፍቃድ “ኢጃዛ” ተብሎ ይታወቃል። ትክክለኛ የሆነ ኢጃዛ ከነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጀምሮ እስከ ግለሰቡ ድረስ የነበሩ ፍቃዱ የተሰጣቸውንና የሚሰጡ ግለሰቦችን ስም ዝርዝር የያዘ ነው።

በሙሁራን ትርጓሜ መሰረት ተጀዊድ ማለት፣ ሁሉንም የቁርኣን ፊደሎች ከትክክለኛ ቋሚ መውጫ ቦታዎች ማውጣት እንደዚሁም ተለዋዋጭ የሆኑትን ፊደላትም እንደየሁኔታዎች አስገዳጅነት ከትክክለኛ ቦታቸው ማውጣት ነው። ቋሚ ቦታዎች በሚለው ማመላከት የተፈለገው ፊደላት ከዚህ ቦታቸው ካልወጡ በስተቀር በትክክለኛ ድምፀት ሊቀሩ እንደማይችሉ ለማሳየት ነው። ተለዋዋጭ ባህሪ ያላቸው ፊደላት የተባሉት ፊደላቱ በሚያርፋባቸው ሀረካ፣ ከተቀመጡበት ቦታ፣ ከሌሎች የድምፀት ባህሪያቸውን ሊቀያይሩ ከሚችሉ ፊደላት ጋር ያላቸው አቀማመጥ ቅደም ተከተል ጋር ተያይዞ ድምፀታቸው የሚቀያየሩ ናቸው።

ዋና ዋና ተጠቃሽ የተጅዊድ መጽሐፎች የቁርኣን ማንበብን አስፈላጊነት እና አነባብ ስርዓት በማስተዋወቅ የትክክለኛ አነባበብ ስርዓት ቅድመ ሁኔታዎች፣ ቁርኣንን በተጅዊድ መቅራት ከኢስላማዊ ህግጋት አንፃር እንዴት እንደሚታይና የቁርኣን አነባበብ ዓይነቶች ከአነባበብ ፍጥነት አንፃር በስንት እነደሚከፈሉ በማስተማር ትምህርታቸውን ይጀምራሉ። ከላይ የተገለፁት ትርጓሚዎች በግልፅ እንደሚያስቀምጡት የተጅዊድ ዋናው አካል ቁርኣንን በአግባቡ ማንበብ ነው። ይህም በሚከተሉት መሰረታዊ ነጥቦች በጥልቀት ይዘረዘራል።

    የፊደላት መውጫ ቦታ (መኻሪጀል ሁሩፍ)
    የፊደላት ባህሪያት (ሲፈቱል ሁሩፍ)
    ሌሎች የተጅዊድ ህጎች፡- ለምሳሌ የተወሰኑ ፊደሎች በቃል ውስጥ ያረፉበት ቦታና በዙሪያቸው ካሉ ቃላቶች አንፃር የድምፀት ለውጥ መቀየር ይከሰትባቸዋል። ሳድስ የሆኑ “ሚም” እና “ኑን” ፊደሎችን ህግ እዚህ ላይ ለአብነት መጥቀስ ይቻላል (አህካሙ ኑን ወልሚም አስ-ሳኪናህ)።

የሥነ-ድምፅ (Phonetics) ተማሪዎች እነዚህ ርዕሰ አንቀፆች የተለመዱና ከትምህርታቸው ጋርም ተመሳሳይ ሆነው ያገኟቸዋል። ለምሳሌ የ “ኢድጋም” ጭብጥ ሀሳብ ውህደት (Assimilation) ከሚለው የሥነ-ድምፅ ጭብጥ ሃሳብ ጋር ይመሳሰላል።

ቁርኣን በሚነበብበት ጊዜ የተጅዊድን ህጎች ጠንቅቆ ማየቱ ግዴታ መሆኑን የተጅዊድ ሙሁራን ይገልፃሉ። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

وَرَتِّلِ الْقُرْآنَ تَرْتِيلًا

“ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ።” (አል-ሙዘሚል 73፤ 4)

አንቀፁ ቁርኣንን በዝግታና አላህን በመፍራት ማንበብንና የሚሳበውን በመሳብ (መድ አል-ሙዱድ) የሚያጥረውን በማሳጠር (ቀስር አል-ቁሱር) መቅራትን ይገልፃል። ከላይ የተጠቀሰው አንቀፅ በትዕዛዝ መልክ (ዐምር) የተነገረ በመሆኑ የተጅዊድን ግዴታነት (ዋጂብ) ያመለክታል። ከዚህ ውጭም አንቀፁ ሊያመላክት ያለመው ሌላ ሀሳብ የለም። (አል-መርሳፊ፣ ሂዳየቱል ቃሪእ ኢላ ተጅዊድ ፊ ከላም አል-ባሪ)

ከጥንታዊያን የተጅዊድ ሙሁራኖች መካከል አንዱ የሆኑት ኢማም ኢብኑል ጀዘሪ “ቱህፈቱል አጥፋል” በሚለው ታዋቂ የጀማሪዎች ተጅዊድ መፅሐፋቸው እንደገለፁት “የተጅዊድን ህግ ማጥናቱ ግዴታ ነው። እነዚያ ይህን ህግ ሳያዩ ቁርኣንን አላግባብ የሚያነቡ ሰዎች ወንጀል እየፈጸሙ ነው። ቁርኣንን ያወረደልን አላህ (ሱ.ወ) ነው። የተተላለፈልን ደግሞ በተጅዊድ ህግ መሰረት ነው። ስለሆነም ተጅዊድን ማጥናት ግዴታ (ዋጅብ) ነው።” ይላሉ።

ይሁንና ሌሎች ሙሁራኖች የቁርኣን ቃላቶች በትክክል እስከተነበቡ ድረስ፣ ስህተት እስካልሆኑ ድረስ፣ የተጅዊድን ህግ መከተሉ ይወደዳል (ሙስተሃብ) እንጂ ግዴታ (ዋጂብ) አይደለም ይላሉ። የሆነ ሆኖ ቁርኣንን በተቻለ አቅም በአግባቡ ለማንበብ መሞከር በሁሉም ሙስሊም ላይ ተገቢ የሆነ ነገር ነው። ዓኢሻ (ረ.ዐ) ከነቢያችን (ሰ.ዐ.ወ) ይዘው እንደዘገቡት፡-

“ቁርኣንን ፍፁም ቆንጆ አድርጎ የሚቀራ ከተከበሩ ታማኝ መላኢካዎች ጋር ነው። ቁርኣንን እየከበደውና እየተንገታገተ የሚቀራ ሰው እጥፍ ምንዳ ይመነዳል።” (ቡኻሪና ሙስሊም)

ተጅዊድ አላህ (ሱ.ወ) ቁርኣንን ከየትኛውም ብረዛ የተከላከለበት አንዱ መገለጫ ነው። የተጅዊድ መጽሐፎች በምንቃኝበት ጊዜ ለጥቃቅንና ዝርዝር የቁርኣን የአነባበብ ስልቶች የተደረገውን ትልቅ ጥንቃቄ እናያለን። ይሄ ሁሉ የሚያመላክተው ከዛሬ 14 ክፍል ዘመናት በፊት በነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ ቁርኣን ይነበብበት በነበረው መልኩ ዛሬም ምንም ሳይቀየር እንደሚነበብ ነው። የሰነድ ሰንሰለትን መሰረት ካደረገው የቁርኣን አነባበብ ያለመበረዝ ዋስትና በተጨማሪም ከፍተኛ ጥራትንና ትክክለኝነትን ባረጋገጠ መልኩ የተጅዊድ ህጎች ከአንድ ተውልድ ወደ ሌላ ትውልድ በተግባራዊ አነባበብ ስልት ቃል በቃል ይተላለፋሉ።

በአጠቃላይ ተጅዊድ ከመነሻው ቁርኣንን ለማገልገልና ከብረዛ ለመጠበቅ ከተቋቋሙት ሳይንሶች አንዱ ነው። ሌሎች በዚህ መስክ እንደ ቂራኣት (የአነባብ አይነቶች) እና አር-ረስም ወድ-ዶብጥ (የቁርኣን አጻጻፍ) ተጠቃሽ የቁርኣን ሳይንሶች ናቸው።

*
https://t.me/Almahir333
19.04.202519:11
🔹ክፍል_አንድ 1⃣

✅መኻሪጀል_ሑሩፍ [مخارج الحروف]

#መኻሪጁል_ሁሩፍ (የፊደላት መውጫዎቹ) እና ሲፋቱል ሑሩፍ (የፊደላት ባህሪዎች)
ከተጅዊድ ክፍሎች ውስጥ ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
መጀመሪያ መኽረጅ ማለት በዐረብኛ ቋንቋ
#መውጫ_ቦታ  ማለት ነው።

እንደ ተጅዊድ ምሁራኖች ደግሞ
#ፊደላቶች_የሚወጡበት_ግልፅ_የሚሆኑበት_እና_ከሌሎች_ፊደላቶች_የሚለዩበት
ማለት ነው።
የፊደላት መውጫ በቁጥር የሚገለፁ ሲሆን የተጅዊድ ምሁራኖች በፊደለት መውጫ ቁጥር ላይ የተለያዩ አቋሞች አሏቸው። ከነዚያም ውስጥ።

1⃣.አስር (🔟) ናቸው የሚለው ነው።
ይህ አቋም ከተጅዊድ ሊቅ ተቀዳሚ የሆኑት
#ኢማም_ኸሊል_ቢን_አህመድ_አል_ፈራሂዲይ ረሒመሁሏህ ናቸው።

2⃣.አስራ ስድስት (16) የሚለው ነው።
ይህ አቋም
#የኸሊል_ቢን_አህመድ ደረሳ የሆኑት
#የሲበወይሂ መዝሀብ ነው 

3⃣አስራ ሰባት (17) የሚል ነው።
ይህ አቋም የእውቁ ኢማም_ሙሀመድ_ኢብኑል_ጀዘሪይ ረሕመቱሏሂ ዓለይህ ሲሆን ኢማም ኢብኑል ጀዘሪ ረሕመቱሏሂ ዓለይህ አስራ ሰባት ያደረጓቸው ከኸሊል ቢን አህመድ አል ጀውፍን በመውሰድና ከሲበወይሂ ደግሞ 16 መውጫዎችን በመውሰድ 17 ሰባት አድርገዋቸዋል። በዚህ ስራቸውም በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አግኝተዋል። እንዲሁም ሲሉ ገልፀውታል ፦

مخارخ الحروف سبعة عشر .......على الذ يختاره من اختبر
የፊደላት ድምፅ የሚፈጠረው በአስራ ሰባት የልሳነ አካላት (ስፍራዎች) አንደሆነ በመስኩ የተካኑ ምሁራን ተናግረዋል (አስቀምጠዋል)። ይላሉ

የዚህ መፅሀፍ ፀሀፊም  ተመራጭ የሆነውን እና የብዙ ቁራኦች መዝሀብ የሆነውን
#የኢማም_ሙሀመድ_ቢን_ጀዘሪይ_  አቋም ይካተታል።
ከላይ የተጠቀሰውን የአስራ ሰባቱን (17) መውጫዎች በአምስት (5)ጠቅላላ መውጫዎች ተካተው እናገኛለን።
እነርሱም ጠቅላላ መውጫዎች ወይንም መኻረጁል ዓምማህ ተብለው በአምስት ይከፈላሉ ።
እነሱም:- ⤵

📌1⃣አል_ጀውፍ

📌2⃣አል_ሐልቅ

📌3⃣አል_ሊሳን

📌4⃣አል_ሸፈታን

📌5⃣አል _ኸይሹም

↪️የፊደላት_መውጫዎቹን_በቀላሉ_ለማወቅ

ከመሳቢያ ፊደላቶች ውጭ የማንኛውንም ፊደል መውጫ ቦታን ለማወቅ፦
ማወቅ የምንፈልገውን ፊደል ሱኩን ወይንም ሸዳህ በማድረግ፣ ማወቅ ከምንፈልገው ፊደል በፊት የፈለግነውን ሐረካ በመጠቀም ሀምዘተል ወስልን ማስገባት፣ ከዚያም ፊደሉን ማንበብ፣ ድምፁ የሚያርፍበት ቦታ የፊደሉ መውጫ ሁኖ እናገኛለን።

➡ምሳሌ :- (  أمْ  )   (  أقْ  )   (  أدْ  )

የመድ (መሳቢያ) ፊደላትን መውጫ ቦታ ለማወቅ፦
በአሊፍ ላይ ፈትሓ የሆነ ፊደልን በማስቀደም በ ያ ላይ ከስራ የሆነ ፊደል በማስቀደም፣ እንዲሁም በዋው ለይ ደግሞ ዶምማ የሆነ ፊደልን በማስቀደም ማንበብ፣
ከዚያም ድምፁ የሚያቋርጥበት ቦታ የፊደሉ መውጫ ሆኖ እናገኛለን ።
ይህ ከተጅዊድ በአማረኛ ከ3ኛው እትም የተወሰደ ነው። ኢንሻ አሏህ
ክፍል ሁለት ይቀጥላል........
https://t.me/ibnumuhammed1433
18.04.202506:18
اللهم صلي وسلم علي نبينا محمد
20.04.202516:49
ለአስማ ቢንት አቡበክር ረዲየሏሁአንሃ ''የነቢዩ ﷺ ሶሃቦች ቁርዓንን ሲሰሙ እንዴ ነበር?'' ተብለ ተጠየቀች
''دمَع عينهم وتقشعِر جلودهم،كما نعتهم الله''
''አይኖቻቸው ያነባሉ ቆዳዎቻቸው ይኮማተራሉ ልክ አሏህ እንደገለፃቸው ብላ መለሰች

እኔ ኣንቺ ኣንተስ❓
ጭራሽ ልናለቅስ ሰውነታችን ሊኮማተር ይቅርና ቁርዓን ከፍተን ወሬ እናወራለን አብዛኞቻችን ቁርዓንን ምናነበውም ጁምዓ ቀን እና በአመት ኣንዴ ረመዷን ላይ ነው አሏህ ያገራለትና ያዘነለት ሲቀር 

አሏህ ልባችንን ያፅዳልን የቁርዓን ሰዎች ያድርገን ቁርዓን ከሚመሰክርላቸው እንጂ ከሚመሰክርባቸው አያድርገን🤲🤲
ልክ እንደ ዝናቡ ሁን ይላሉ ዓረቦች

ልክ እንደ ዝናቡ ሁን
ሊመጣ ባለ ሰዓት መምጣቱን ይናገራል
በመጣ ሰዓት ፍጥረቱን ይጠቅማል
በሄደ ሰዓት ጥሩ አሻራ ጥሎ ይሄዳል
በጠፋ ሰዓት .....ደግሞ ይናፍቃል
        
@HayrulNew
18.04.202506:18
اللهم صلي وسلم علي نبينا محمد
Қайта жіберілді:
Islamic avatar
Islamic
መሳቅ😅 ለምትፈልጉ ብቻ!!!
በቅርብ ጊዜ ተከፍቶ በጣም ተወዳጅነት ያተረፈውን ቻናል ተጋበዙልኝ🤩
👇
19.04.202514:57
ፈገግታ ሱና ነው 😁

  ❤️ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ ዓ ወ)  ጨዋታ ላይ የማይጎረብጡ ምቹ ሰው ናቸው!
አንድ እለት ከሰሃባዎቻቸው ጋር ተቀምጠው ተምር እየበሉ ጨዋታ ይዘዋል…… ከፊታቸው የተቀመጠ አንድ ሰሃባ ሊቀልዳቸው ፈልጎ ተምሩን ይበላና የተምሩን ፍሬ እሳቸው በልተው ካስቀመጡት የተምር ፍሬ ጋር ሳያዩት ያስቀምጠዋል… አሁንም ይበላና ፍሬውን ከሳቸው ፊት ይጨምረዋል……
መጨረሻ ላይ "ያ ሩሱለላህ፣ ዛሬ ያለ ወትሮዎ ብዙ ተመገቡኮ" አላቸው……
እሳቸውም ዝቅ ብለው ከፊታቸው ያሉትን የተምር ፍሬ ሲመለከቱት በዛባቸው(ተከምሯል)😁……
ሰውየው ወደተቀመጠበት ቦታ ሲመለከቱ ምንም የተምር ፍሬ የለም… ሁሉም ያለው ከሳቸው ፊት ነው……
ረሱልም(ሰዐወ) ነገሩ ፈገግ አሰኛቸውና እንዲህ አሉት…
«የኔ ይህን ሁሉ ተምር መብላት ብቻ ሳይሆን ያንተ ከነ ፍሬው መዋጥህም ይገርማል» 😁😁😁     
                       صل الله عليه وسلم
                   (ﷺ)❤️(ﷺ)❤️(ﷺ)


.
Көрсетілген 1 - 11 арасынан 11
Көбірек мүмкіндіктерді ашу үшін кіріңіз.