Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ avatar

MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™

አስተሳሰባችንን ለመጠበቅ፣
አዕምሯችንን በአዎንታዊ ሀሳቦች ለማነፅ፣
ወደ ከፍታው የሚያሻግሩ ምክረ ሀሳቦችን ለማጋራት ለሁላችን የተዘጋጀ ቻናል ነው።
@mikreaimro

ይቀላቀሉን ዘንድ በአክብሮት ተጋብዘዋል!
ለወዳጅዎ ማጋራትዎን እንዳይረሱ!
🏠Welcome to your Home! 🏘
Personal Contact: @epha_aschalew
Insta: instagra.com/epha_aschalew
TGlist рейтингі
0
0
ТүріҚоғамдық
Растау
Расталмаған
Сенімділік
Сенімсіз
Орналасқан жері
ТілБасқа
Канал құрылған күніMar 14, 2021
TGlist-ке қосылған күні
Aug 21, 2024
Қосылған топ

Telegram арнасы MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ статистикасы

Жазылушылар

40 706

24 сағат
14
0%Апта
98
-0.2%Ай
65
-0.2%

Дәйексөз индексі

200

Ескертулер1Каналдарда қайта жазылу0Каналдарда ескерту1

1 жазбаның орташа қамтуы

656

12 сағат1 1380%24 сағат656
68.7%
48 сағат2 3370%

Қатысу деңгейі (ER)

0.76%

Қайта жазылды3Пікірлер0Реакциялар8

Қамту бойынша қатысу деңгейі (ERR)

0%

24 сағат0%Апта0%Ай0%

1 жарнамалық жазбаның қамтуы

656

1 сағат47071.65%1 – 4 сағат467.01%4 - 24 сағат33250.61%
Каналға біздің ботымызды қосып, осы каналдың аудиториясын біліңіз.
24 сағаттағы жазбалар саны
1
Динамика
1

Рекордтар

23.01.202523:59
41.3KЖазылушылар
30.11.202423:59
450Дәйексөз индексі
26.03.202523:59
2.2K1 жазбаның қамтуы
27.03.202514:19
2.2KЖарнамалық жазбаның қамтуы
19.11.202423:59
50.00%ER
26.03.202521:13
5.40%ERR
Жазылушылар
Цитата индексі
1 хабарламаның қаралымы
Жарнамалық хабарлама қаралымы
ER
ERR
OCT '24JAN '25APR '25

MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ танымал жазбалары

22.04.202513:29
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
01.04.202519:57
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
30.03.202520:32
መፅሐፍ ከተወደደ አንባቢ ይጠፋል!
ምክንያቱም የመግዛት አቅም የለውምና!!

ይሄን መሰረት በማድረግ
የተለያዩ መፅሐፍ በ Pdf  ድርሰቶች አጫጭር ታሪኮችን የሚያዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል
ልጠቁማችሁ!!!

ስሙ እንማር ይሰኛል !!
ቀኖትን እያረመ ማታዎትን እያደመቀ ምርጥ ምርጥ መፅሀፎች ይጋብዛቸዋል ።
100%ትወዱታላችሁ


https://t.me/Enmare1988
https://t.me/Enmare1988
27.03.202509:50
ስሜታችሁን አትስሙ!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
የትኛውም ምቾት መነሻው ለጊዜያዊ ስሜት መገዛት ነው። ስሜት ከመቅፅበት ይቀያየራል፣ ውስጣችሁ ወዲያው ወዲያው ይላወሳል፣ አንዴ ይደሰታል አንዴ ያዝናል፣ አንዴ ዘና ይላል አንዴ ይደብረዋል። ሁሉም ስሜቶች መነሻ አላቸው፣ ምክንያት ይኖራቸዋል። ምክንያታቸው ምንም ቢሆን ስሜታችሁን አምናችሁ እርሱን የምትንከባከቡ ወይም ከዛ ስሜት ለመውጣት የምትጠብቁ ከሆነ እንዴትም የገዛ ህይወታችሁ ላይ ስልጣን ሊኖራችሁ አይችልም። ገዢያችሁ ስሜታችሁ ሳይሆን እናንተ መሆን አለባችሁ፣ መሪያችሁ ወቅታዊ ሙዳችሁ ሳይሆን ውስጣዊ ፍላጎትና ማንነታችሁ መሆን አለበት። ራሳችሁን ማባበል አቁሙ። ሲከፋችሁ ዓለም ሁሉ እንደምትከፋ ማሰብ አቁሙ፤ እናንተ ስትደሰቱ ዓለም ሁሉ እንደምትደሰት ማሰብ አቁሙ። የእናንተ ስሜት ለዓለም ምኗም አይደለም። ሃዘንን እስከ ጥግ ታዩታላችሁ፣ የድብርትን ጣሪያ ትነኩታላችሁ፣ ብቸኝነት ደጋግሞ ያሰቃያችኋል፣ በዛው ልክ በአንድ ወቅት የዓለማችን ቁጥር አንድ ደስተኛ ሰው ትሆናላችሁ፣ ህይወት በፈገግታ ትቀበላችኋለች፣ ዓለም እጅ ነስታ ታስተናግዳችኋለች። የስሜት መውጣት መውረድ ሁሌም አለ። ነገር ግን ስሜታችሁ መሪያችሁ እንዳልሆነ አስተውሉ።

አዎ! ስሜታችሁን አትስሙ! ማንን መስማት ነፃ እንደሚያወጣችሁ ጠንቅቃችሁ እወቁ። ስልጡን ሰው በዋናነት የሚሰለጥነው ስሜቱ ላይ ነው፣ ሃይለኛ ሰው አስቀድሞ የራሱ የሚያደርገው ጥበብ የስሜት ብልህነት የተሰኘውን ጥበብ ነው። አንተ ሳታውቅ ስሜትህ መርቶ አዘቅት ውስጥ እንዲከትህ አትፍቀድለት። አልቃሻ ሰው ስሜቱን ከማሸነፍ በላይ ተደብቆት ሊያመልጠው ይጥራል፣ ልፍስፍስ ሰው ሃላፊነቱን ላለመወጣቱ ወቅታዊ ስሜቱን ይወቅሳል። የትም ሒዱ የት ከሃላፊነታችሁ በላይ ስሜታችሁን የምታስቀድሙ ከሆነ ውድቀት መገለጫችሁ መሆኑ አይቀርም። ሰው ናችሁና መቼም ቢሆን ሁሌም የተስተካከለ ጥሩ ስሜት ሊሰማችሁ አይችልም። ስሜታችሁን እየመጣ እንደሚሄደው ሰው ቁጠሩት ይመጣል ይሔዳል እንደገና ይመጣል እንደገና ይሔዳል እናንተ ከሰለጠናችሁበት ሔዶ እንደሚቀረው ሰው በዛው በሔደበት ይቀራል። ለራሳችሁ ከልክ በላይ ርህራሔ አታሳዩ። መጨከን ካለባችሁ ጨክንቡት፣ ማሰቃየት ካለባችሁ አሰቃዩት። እሹሩሩ እያላችሁ የማትፈልጉትን ልፍስፍስ ማንነት አትፍጠሩ። አጉል ርህራሔ መደምደሚያው ቂልነት እንደሆነ አስተውሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! በምናብህ ውስጥ ያለው ዓለም የተለየ ነው፣ ስሜትህም እንዲሁ የተለየ ነው። የትኛው ስሜት በምናብህ ውስጥ ወደተፈጠረው የተለየ ዓለም እንደሚወስድህ ጠንቅቀህ እወቅ። ማንንም ለመርዳት ከመፍጨርጨርህ በፊት ራስህን መርዳት፣ ራስህ ላይ መሰልጠን፣ ስሜትህን መምራት እንዳለብህ አስተውል። ሰውነት ብዙ ደካማ ጎኖች አሉት። በአንዲት ቅፅበት ሙሉ ህይወትህ ሊቀየር ይችላል። ማጣት የስቃይ ሁሉ መነሻ ነው፣ ድህነት ከሰው ሁሉ በታች ያደርጋል፣ ድምፅ እያለህ ድምፅ አልባ ያደርግሃል፣ አዋቂ ሆነህ እንደአላዋቂ ያኖርሃል። የዛሬ ማጣትህ ልብህን እንዳይሰብረው ተጠንቀቅ፣ ይልቅ ዘመንህን በሙሉ በማጣት ስትዳክር መቆየትህ ያሳስብህ። አሁን የድህነት ተምሳሌት መሆንህ አያስጨንቅህ፣ ይልቅ እድሜ ልክህን የድህነት መጫወቻ መሆንህ ያስጨንቅህ። ስሜትህን በአዎንታዊነት ከመነዘርከው ሃብትህ ነው፣ በአሉታዊነት ካዳመጥከው ግን መጥፊያህ ነው። በስሜትህ ቁጥጥር ስር በመውደቅ ባርነትን አትለማመድ። ስሜትህ ጥሩ ሆነም አልሆነም፣ በሰዓቱ ተደሰትክም አዘንክም ጥርስህን ነክተህ መስራት ያለብህን ስራ ስራ። ከስሜትህ በላይ የሚያነግስህ ምግባርህ እንደሆነ አስተውል።
ግሩም ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
31.03.202506:12
ሶስቱ ማንነቶቻችን!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
ከስነ-ልቦና እይታ አንጻር ሶስት አይነት ማንነት እንዳሉን ማሰብ እንችላለን፡-

1. ራሴ “እንዲህ ነኝ” ብዬ የማስበው

እኔ በራሴ ላይ ያለኝ ተጽእኖ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህ ከሆነበት ምክንያቶች ዋነኛው ብዙውን ጊዜ ከራሴ ጋር ስለማሳልፍና ብዙ ነገሮችን ለራሴ የመናገር እድሉ ስላለኝ ነው፡፡ ይህ ልቀይረውና ሌላ አማራጭ ልፈልግለት የማልችለው እውነታ በመሆኑ በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡ በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ራሴው በእኔው ላይ ከለጠፍኩበት ዋጋ አልፎ በመዝለቅ ወደ ትክክለኛው መስመር እስከሚገባ ድረስ ትክክለኛ መለኪያን እንዳላዳበርኩ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የሰውነቴ ዋጋ የማይለዋወጥ እንደሆነና እኔው በፈቃዴ ግን የተለያዩ የዋጋ ተመኖች እንዲለጠፉብኝ መፍቀድ እንደምችል ማስታወስ የግድ ነው፡፡

2. ሰዎችና ሁኔታዎች “እንዲህ ነህ” ብለው የሚነግሩኝ

ሰዎች ካለማቋረጥ መልእክትን ወደ እኛ ይልካሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቃል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሁኔታ፡፡ በተለይም የመደብ ልዩነት ከባህሉ ጋር ተገምዶ በሚገኝበት እንደኛው አይነት ማሕበረሰብ ውስጥ ጀርባችንን፣ የወቅቱ ሁኔታችንን፣ ያለንና የሌለንን በመደመርና በመቀነስ ካለማቋረጥ ማንነታችን ላይ ተመን ይለጥፋሉ፡፡ ይህ ዋጋ ደግሞ አንዴ ከፍ ይላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅ ይላል፡፡ ይህንን ሁኔታ በተገቢው ሚዛናዊነት የማስተናገዱ ግዴታ እኔው ላይ ነው ያለው፡፡ ሰዎች በእኔ ላይ የሚለጣጥፉት የዋጋ ውጣ ውረድ በማንነቴ ላይ ተጽእኖ የሚያመጣው እኔው ራሴ ስፈቅድለት ብቻ እንደሆነ ማስታወስ የግድ ነው፡፡ 

3. እውነተኛውና ትክክለኛው ማንነቴ

እውነተኛው ማንነቴ ማለት እኔው በራሴ ላይ ወይም ደግሞ ሌሎች ሰዎች የለጠፉብኝ ተመን (Price) ሳይሆን ሰው በመሆኔ ከፈጣሪ የተሰጠኝ ዋጋ (Value) ነው፡፡ ይህ የመጨረሻ ስልጣን ያለውና ሁሉንም ትቼ ላምነው፣ ላሰላስለውና ልለማመደው የሚገባኝ እውነት ነው፡፡ ይህ የማንነቴ ዋጋ በምንም ሁኔታ ሊቀንስም ሆነ ሊጨምር አይችልም፡፡ ይህንን ዋጋ በጥረቴ ልጨምረውም ሆነ ላሳድገው አልችልም፡፡ ለዚያ ሊቀነስም ሆነ ሊጨመር ለማይችለው ከፈጣሪዬ ለተቀበልኩት የከበረ ዋጋ ላለው ማንነቴ የሚመጥን አመለካከትና የኑሮ ዘይቤ የመከተሌ ሁኔታ ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡

እንግዲህ አንድ ሰው በራሱ ማንነት ላይ ያለው ዋጋ የተዛባ መሆኑን ለማወቅ ካሉን መመዘኛዎች መካከል አንዱ በችግሮቹ ላይ ያለውን አመለካከት በማጤን ነው፡፡ የተቃኘና ትክክለኛ ራስ-በራስ ምልከታ ያለው ሰው እለት በእለት በሚገጥመው ችግሩ ላይ ያለውም ምልከታ ሚዛናዊና አዎንታዊ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ችግር ሲገጥመው የወደቀ አመለካከት ያለው ሰው በቅድሚያ በራሱ ላይ ያለው አመለካከት አለመስተካከሉን አመልካች ነው፡፡

የኑሯችሁ ሁኔታ በተለዋወጠ ቁጥር በማንነታችሁ ላይ ያለችሁን አመለካከትና ለራሳችሁ የምትሰጡትን ግምት አትለዋውጡ፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፉም የማንነታችሁ ዋጋ ያው ነው!
/የማንነትህ መለኪያ መጽሐፍ/
ግሩም ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
06.04.202508:33
ማንም በሌለበት!
፨፨፨/////////፨፨፨
ማንም የለም፣ ማንም አይጠብቅህም፣ ማንም የምትደገፈው፣ ማንም የምትተማመንበት ሰው የለህም። ለራስህ እውታውን ንገረው። ሰውን ስትጠብቅ የባከኑ ውድ ጊዜህን አስታውስ። ብቻህን የምታደርገው ነገር፣ ለብቻህ የምትወስነው ውሳኔ፣ ማንም ሳያይህ የምታደርገው፣ ለማንም ሰይሆን ለእራስህ ብለህ የምትፈፅመው ጀብድ እርሱ ነው ከመሬት አንስቶ ከፍታ ላይ የሚያስቀምጥህ፣ እርሱ ነው ዋጋህን የሚጨምረው፣ እርሱ ነው የተለየ ሰው የሚያደርግህ። ብችህን ስትሆን ምን ታደርጋለህ? ማንም በሌለበት ደጋግመህ የምታከናውነው ተግባር ምንድነው? ተደብቀህ የት ትሔዳለህ፣ ምን ትሰራለህ? ምንስ ታያለህ?

አዎ! ጀግናዬ..! በዛ በጨለማ ማንም በሌለበት፣ ጠያቂ በማታገኝበት፣ አይዞህ ባይ አበርታች፣ በሃሳብም ሆነ በገንዘብ የሚደግፍህ በሌለህ ሰዓት ምን እያደረክ ነበር? ስለሆነብህ እያማረርክ ወይስ ምሬትህን ለመቀየር ጠንክረህ እየሰራህ? ብቸኝነትህን እየረገምከው ወይስ እራስህን ለመገንባት እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀምከው? እድለኛ እንዳልሆንክ እያሰብክ ወይስ ሁኔታውን ለመቀየር እየተፋለምክ? ብቻህን ስትሆን የሚኖርህ ማንነት ያንተ ትክክለኛው ማንነት ነው። አንተና ፈጣሪ ብቻ የምታውቁት የግል ሚስጥርህ ይኖራል። በገባህ ልክ እለት እለት ለብቻህ የምትፋለምለት ሃሳብ ይኖርሃል። "ብቻዬን ነኝ፣ ሰው የለኝም፣ የሚያግዘኝ አላገኘውም፣ የማደርገው ነገር በማንም ተቀባይነት አላገኘው፣ ማንም አላመነበትም።" ብለህ አታቆመውም።

አዎ! ብቻህን ስትሆን ስለምታደርገው እያንዳንዱ ነገር ተጠንቀቅ፣ ማንም በሌለበት ወደአዕምሮህ ስለሚመጣ ሃሳብ ደጋግመህ አስብ። በሰዎች መከበብ ትርፉ መዘናጋት እንደሆነ እወቅ፣ ከዚህም ከዛም በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ ቃላት መዋከብ ትርፉ አጉል መኮፈስ ወይም ተሰብሮ መቅረት እንደሆነ አስታውስ። ከቻልክ ለብቻህ ስለራስህ ጊዜ ሰጥተህ አስብ፣ ስላለህበት ሁኔታ፣ ስለምትፈልገው፣ ስለአላማህ፣ ስለልማድህና ስለግል አቋምህ ጠንቅቀህ መርምር። በመዋከብ ጊዜ አታጥፋ፣ እዚም እዛም እየተገኘህ ዋጋህን አታሳንስ፣ በገዛ ፍቃድህ ብኩን አትሁን። ለራስህ ጊዜ ይኑርህ፣ ትኩረትህን እራስህ ላይ አድርግ፣ አንተ ሳትቀየር ውጪው እንዲቀየር መጠበቅ አቁም፣ ማንም ላይ አንድ ጣትህን ስትቀስር የቀሩት አራቱ ወዳንተ እንደሚያመለክቱ አስተውል። እራስህ ላይ ስራ፣ እራስህን አሻሽል የቀረው በጊዜው እንዲስተካከል ተወው።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
//• በብልሀት ብቻ ህይወታቹን ኑሯት •//

አላግባብ የአስተዳደራችሁትን (manage ያላደረጋችሁትን ወይም mismanage ያደረጋችሁትን) ነገር ቀስ በቀስ ታጡታላችሁ፡፡

በእጃችሁ ያለው የገንዘብ መጠን በዛም አነሰም፣ በትክክል manage ካደረጋችሁት ትጠብቁታላች፣ ታባዙትማላችሁ፡፡ አለዚያ ግን ቀስ በቀስ ከእጃችሁ ይወጣል፡፡

የእኔ ናቸው የምትሏቸው ቤተሰቦች፣ ቀድሞውኑ (by default) የእናንተ ስለሆኑ ብቻ የትም አይሄዱም ብላችሁ ችላ ካላችኋቸውና ግንኙነታችሁን በትክክል manage ካላደረጋችሁት ትዳርም ሆነ የቅርብ ቤተሰብ ሁኔታ ቀስ በቀስ ከእጃችሁ መውጣት መጀመሩ አይቀርም፡፡


የምትመሩትና የምታስተዳድሩት የሰው ኃይልም ሆነ ሕዝብ በትክክል ካላስተዳደራችሁት (mismanage ካደረጋችሁት) አብሮነቱንና አጋርነቱን ቀስ በቀስ እያጣችሁት መሄዳችሁ አይቀርም፡፡

የጀመራችሁት ንግድ (business) ትንሽም ሆነ ትልቅ፣ በትክክል manage ካደረጋችሁት ታሳድጉታላች፡፡ ካላደረካችት ደግሞ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለ ይሄዳል፡፡

እያለ መርሁ ከብዙ ዘርፎች አንጻር እውነታነቱ ያው ነው፡፡

አንድን ነገር በትክክል manage ማድረግ ማለት፣ ትክክለኛውን መርህ መከተል፣ በእቅድ መኖር፣ ስህተት ሲኖር ቶሎ ማረም እና የመሳሰሉትን አስፈላጊ ሂደቶች ተግባራዊ ማድረግ ማለት ነው፡፡

ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
29.03.202519:27
ዓለምን አትመኑ!
፨፨፨///////፨፨፨
አማኝ "አማኝ ነኝ" ብሎ አያወራም። የትኛውም አማኝ መገለጫው ስራው ነው። በማን እንደምታምኑ አስተውሉ። ዓለምን ወይስ የዓለሙን ፈጣሪ እያመናችሁ ነው? ለማን ተገዝታችኋል? ለዓለም ብልጭልጮች ወይስ ለህያው ፈጣሪ? እምነታችሁን በቃል መናገር አይጠበቅባችሁም። ተግባራችሁን ብቻ አይታችሁ ማወቅ ትችላላችሁ። የፈጣሪን ህግጋት ያለማወቅ ችግር የለብንም የምንገዛው ግን ለዓለም ህግ ነው፤ ፈጣሪ ከእኛ ምን እንደሚፈልግ እናውቃለን እኛ ግን የምናደርገው ዓለም ከእኛ የምትፈልገውን ነው። ዓለም ስህተት ስንሰራ ትስቃለች ፈጣሪ ግን ያዝናል፣ ዓለም ትክክለኛ ተግባር ስንፈፅም ቦታ አትሰጠንም አምላክ ግን ደስ ይሰኝብናል። ዘወትር አንድ አይነት ህይወት መኖር ከሰለቻችሁ ከምንም በፊት እምነታችሁን መርምሩ። በአንዴ ለሁለት ጌታ መገዛት አይቻልም። ምርጫችሁ አንድና አንድ ነው እርሱም በተግባር የምትኖሩት ህይወት ነው። ሰው ደስታውን ያሳድዳል በዚህም መንገድ የዓለም ወጥመድ ውስጥ ይገባል። ዓለም የዲያብሎስ መፈንጫ በሆነችበት ዘመን ልባችሁን አጥብቃችሁ ጠብቁ።

አዎ! ዓለምን አትመኑ! ልባችሁን ዛሬ ታይቶ ለሚጠፋ፣ አሁን አግኝታችሁ ለምታጡት ደስታ አትክፈቱት። በእምነታችሁ ልክ የፈተናን ብዛት ታያላችሁ፣ ውስጣችሁ ባለው አመለካከት ምክንያት ሰላማችሁ እየተመዘነ ይመጣል። ምድር ላይ ብዙ ግርግር ታያላችሁ ነገር ግን አንዱም ውስጣችሁን አያረጋጋም፣ ዓለም ላይ ብዙ ወሬዎችን ትሰማላችሁ ነገር ግን አንዱም ነፍሳችሁን አያሳርፈውም። በዚህ ሰዓት ልባችሁ ምን ይላችኋል? አሁን ስሜታችሁ እንዴት ነው? ዛሬን ሳትኖሩ ሩቅ ማለም አቁሙ፣ እንዲሁ ባልተጨበጠ ምኞት መቃዠት አቁሙ። ዓለም አሳይታ የምትነሳችሁን እድል የሙጥኝ በሉ፣ ከፈጣሪ ጋር የሚያጣላችሁን የትኛውንም ተግባር ከውስጣችሁ አስወጡ። ዓለምን ስትከተሉ የሰይጣን መጫወቻ እንደምትሆኑ አስተውሉ። አወቃችሁም አላወቃችሁም ዓለማዊ ጫወታ ካታለላችሁ ነፍሳችሁ በብዙ እጥፍ እየተጨነቀች ነው። ነፍሱን የሚጨቁን ሰው ደግሞ መንፈሱን ሊያረጋጋ አይችልም። ወደድንም ጠላንም ለዓለም ግዞት እየተገዙ ከፀፀትና ከሰው ሰራሽ ህመም ነፃ መሆን አይቻልም።

አዎ! ጀግናዬ..! የፈጣሪህ አምሳያ የሆነውን ህሊናህን አስበው። ከገዛ ህሊናህ በላይ ዳኛ የለህም፣ ውስጥህ ካለው እምነት ውጪ የሚመራህ ነገር የለም። ወሩን ሙሉ የምትሰራው በወሩ መጨረሻ ለምታገኘው ደሞዝ ነው። ማንም ቅድሚያ ደሞዝ ሰጥቶህ አያሰራህም። የህይወትን ፍሬም የምታገኘው አስቀድመህ አምነህ በሰራህበት ነገር ነው። የቀደመ እምነትህ እየነዳ እዚህ አድርሶሃል፣ የዛሬው እምነትህም እየመራህ የተለየ ስፍራ ያደርስሃል። ዓለምን አምነህ አትሸወድ፣ ሰው ተከትለህ ጉድጓድ አትግባ። ሰው ነፃ አያወጣህ፣ ዓለም ነፃ አታወጣህም፣ ሃብትና ዝና ነፃ አያወጡህም። ሁለንተናዊው ነፃነትህ ያለው አምላክህ ላይ ያለህ እምነትህ ውስጥ ነው። ስጋዊውን መንገድ መርጠህ ትወድቃለህ እውነተኛዋ የነፍስ መንገድ ደግሞ ዳግም ታነሳሃለች። የቀደመ እምነትህን ፈትሽ፣ መከራ ሲበዛብህ በማን ልታልፈው እንደምትችል እወቅ። እያንዳንዱ የህይወት መንገድህ ውስጥ ያመንክበት አካል ጣልቃገብነት እንዳለ አስተውል። ዓለምን አትመን፣ እውነተኛውን ሰማያዊ አባትህን ተከተል።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
04.04.202518:02
እራስህን ገንባ!
፨፨፨//////፨፨፨
"ሌሎች ያላደረጉት ነገር አያሳስብህ።
ዋጋ ያለው አንተ የምታደርገው ነው።"
-Napoleon Hill

ብዙ ጊዜ የምትመለከታቸው ሰዎች የተግባር ሰዎች ላይሆኑ ይችላሉ፣ አካባቢህ ከስራ ወሬን በሚያስበልጡ ሰዎች ሊሞላ ይችላል፣ ያንተን ህይወት በእነርሱ ስንፍና ትለካውም ይሆናል ነገር ግን ሌሎች ያላደረጉት ነገር እኔም ባደረግው ለውጥ አያመጣም ከሚለው እሳቤ ውጣ። እነርሱ ስላላደረጉት ያጡት ነገር ይኖራል፣ እነርሱ የተግባር ሰው ባለመሆናቸው፣ ዋጋ ለመክፈል ባለመድፈራቸው፣ አደጋን በመፍራታቸው ምን እንደጎደላቸው አስተውል። ስኬቱንም ሆነ ውድቀቱን በቅርብህ ካሉ ሰዎች የምትማር ከሆነ ትርጉም ያለው ህይወት የማትኖርበት ምክንያት የለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ማንም ያመነበትን ያደርጋል፤ አንተም እንዲሁ። ከማቀድ አለማቀድን፣ ካማድረግ አለማድረግን፣ ከመጀመር አለመጀመርን፣ ከመጨረስም አለመጨረስን ከሚመርጡ ሰዎች እራስህን ነጥል። የእነርሱ አለማድረግ፣ የእነርሱ አለመቀየር፣ የእነርሱ አዲስ ነገር አለመፍጠር፣ የእነርሱ ባሉበት መቆየት አንተን አያሳስብህ፤ ባንተ ህይወት ላይ አንዳች ነገር የሚጨምረው፦ የእነርሱ አለማድረግ ሳይሆን ያንተ ተሽሎ አድርጎ መገኘት ነው፤ የእነርሱ ጀምሮ ማቆም ሳይሆን ያንተ ጀምሮ መጨረስ ነው፤ የእነርሱ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ያንተ በተስፋ መሞላት ነው፤ የእነርሱ በስንፍና መመላለስ ሳይሆን ያንተ በጥንካሬ መንቀሳቀስ ነው።

አዎ! ማንን እንደምትከተል ጠንቅቀህ እወቅ፣ በማን መርህ፣ በማን አቋም እንደምትመራ በሚገባ ለይ። በቅርበት የምታገኛቸው ሰዎች በራሳቸው መንገድ ይሰሩሃል፣ ረጅም ጊዜ አብረሃቸው የምታሳልፈው ሰዎች የህይወትህ መሪዎች ናቸው። ቁብነገር ያለው፣ ዋጋህን የሚጨምር፣ በለውጥና በእድገት የተቃኘ ህይወት ለመኖር ጥራት ያላቸው ብርቱና ጠንካራ ሰዎች ያስፈልጉሃል። ስለሃገሪቷ ተስፋ ማጣት እያወሩ ተስፋቢስ ከሚያደርጉህ፣ ስለስራቸው አለማስደሰት እየተነተኑ ለስራህ ያለህን ጥሩ አመለካከት ከሚቀይሩ፣ ተምረው ከማያስተምሩህ፣ ለራሳቸው ዋጋ ሰጥተው ያንተንም ዋጋ ከማይጨምሩ ሰዎች ራቅ፣ በተገነባ አካባቢ ውስጥም እራስህን ገንባ
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
25.03.202518:06
በራሳችሁ ተገደቡ!
፨፨፨/////////፨፨፨
የተሳሳተ ውሳኔ መወሰን ከፈለጋችሁ ብዙ ሰው ጠይቁ፣ ትክክለኛ ውሳኔ መወሰን ከፈለጋችሁ ራሳችሁን ጠይቁ። ብዙ ሰው ስላማከራችሁ የሚቀርላችሁ ውድቀትም ሆነ የምታመልጡት የተሳሳተ ውሳኔ የለም። ሰው ሲበዛ ሀሳብ ይበዛል፣ ሀሳብ ሲበዛ የግል አቋም ይሸረሸራል፣ ይግል አቋም ሲሸረሸረ የተሳሳተ ውሳኔ ይወሰናል። ምንያህል የሚያውቁትን ሰው በሙሉ አማክረው ተክክለኛ የሚጠቅማቸውን ውሳኔ የወሰኑ ሰዎችን ታውቃላችሁ? እናንተስ በምንም ነገር ዙሪያ ውሳኔ ማሳለፍ ስታስቡ ብዙ ሰው የማማከር ልማድ አላችሁ ወይስ በእራሳችሁ ትወስናላችሁ? ብዙ ሰው መደገፍ አቋም አልባ ልፍስፍስ እንደሚያደርግ አስታውሱ። በራሳቸው የሚተማመኑ፣ የማያወላዳ አቋም ያላቸው ሰዎች በምን ዙሪያ ማንን ማማከር እንዳለባቸው፣ ማንስ የተሻለ ሀሳብ ሊሰጣቸውና የበለጠ ሊያበረታታቸው እንደሚችልም ጠንቅቀው ያውቃሉ። የምታማክሩትን ሰው ካልመረጣችሁ መጨረሻ ላይ ምራጭ ሆናችሁ የምትቀሩት እናንተ ናችሁ።

አዎ! በራሳችሁ ተገደቡ! አቋም ይኑራችሁ፣ ለየትኛውም ውሳኔያችሁ ሃላፊነት መውሰድን ተለማመዱ። ውሳኔያችሁ ትክክል የሚሆነው ሰው ስላበዛችሁ ሳይሆን ማማከር ያለባችሁን ጥቂት ሰው ማወቅ ስለቻላችሁ ነው። መንገድ ጠፍቷችሁ ስትጠይቁ አላውቅም ማለት እየቻለ በማያውቀው አቅጣጫ የሚጠቁማችሁ ሰው በበዛበት በዚህ ጊዜ ብዙ ሰው አማክሬ የምፈልገውን ሀሳብ አገኛለሁ ብላችሁ አታስቡ። ስለማያውቀው ነገር አላውቅም ማለት ውርደት የሆነበት በጣም ብዙ ሰው አለ። በአላዋቂነት ተሞልቶ በአዋቂነት ሽፋን የሚመላለስ ብዙ ሰው አለ። አንዳንድ ውድቀትህን በጉጉት ይጠብቅል አንዳንዱም እንዲሁ አይነ ውሃህ አይጥመውም። ከምንም በላይ ተግባርን እመኑ። አንዳንድ ሰዎች በከንከራቸው ሱካርን በልባቸው መርዝን እንደሚያስቀምጡ አስታውሱ። የምትጠጓቸው ሰዎች ወይ ትንሿን የተስፋ ጭላንጭል ሙሉ ያደርጓታል አልያም ከነጭራሹ ያጠፏታል። እያላችሁ ካልሆነ ሳይኖራችሁ ለማይቀርባችሁ ሰው ብላችሁ የችግራችሁን ክብደት ከፈጣሪ ደብቃችሁ ሰው ጋር አትሩጡ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሰው ህመምም መድሃኒትም ነው፣ እግዚአብሔር ግን መድሃኒት ነው። ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብትሆን፣ አጣብቂኝ ውስጥ ብትገባ፣ ነገሮች ቢመታቱብህ፣ ለውሳኔ ብትቸገር እንዲሁ ግራ ቢገባህ ወደምታውቀው ሰው ሁሉ ከመሮጥህ በፊት ከእግዚአብሔር አምላክህ ጋር ተወያይ፣ በፀሎት በልመና ፈጣሪህን አማክረው፣ በትክክለኛው መንገድ ይመራህ ዘንድ ተማፀነው። ወደድክም ጠላህም ህይወትህ የእያንዳንዱ ውሳኔዎችህ ጥርቅም ውጤት ነች። ለመወሰን ስታንገራግር እሷም ታንገራግራለህ፣ እራስህን አጠንክረህ በድፍረት ስትወስን አሷም ታደፋፍርሃለች። በፈጣሪህ እገዛ የራስህን ጉዳይ ለራስህ ለመወሰን ደፋር ሁን። አንድ ነገር አስታውስ ትክክለኛ ውሳኔ ለመወሰን የተሳሳተ ጊዜ የለም። የውሳኔ ሰው ሁን፣ ሃላፊነት ውሰድ፣ መማር ካለብህም ቶሎ ወስነህ ከተሳሳተ ውሳኔህ ተማር።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን!
SUBSCRIBE NOW! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊💪
05.04.202510:30
ሰላሜ በዝቷል!
፨፨፨//////፨፨፨
ከራስ ጋር ንግግር፦ "በቀደመው ዘመን አንተ በሌለህበት ህይወት፣ አባትነትህን በሸሸውበት፣ ልጅነቴን በካድኩበት፣ ውለታህን በዘነጋውበት፣ ጥበቃህን ቸል ባልኩበት፣ አብሮነትህን ባልፈለኩበት በዛ ክፉ ዘመን አንተ ያው ሩህሩህ ጌታ ደግ አባት ነበርክ እኔ ግን እኔ አልነበርኩም። መታመኛዬ ዓለም ነበረች፣ መደበቂያዬ ዳንኪራው፣ ሱሱና ክፋቱ ነበር። የሆንኩልህን አላውቅም ያደረክልኝ ግዛ እጅግ ብዙ ነው፣ ያደረኩልህ ምንም ነው ያደረክልኝ ቁጥር ስፍር የለውም። እስከ ጥግ ወደሀኛል፣ እስከመጨረሻው ምረሀኛል፣ በይቅርታህ ጥፋቴን ሽረህልኛል፣ የጠፋው ልጅህን ወደቤትህ መልሰሀኛል፣ ዓለም የናቀችውን፣ ነውር ያረከሰውን፣ ጥፋት መገለጫው የሆነውን ባሪያህን ከከፋው አጥፍቶ ጠፊነት፣ መጨረሻ ከሌለው የስቃይ ህይወት ታድገሀዋል።

አዎ! ባንተ ሰላሜ በዝቷል፣ ባንተ ነፍሴ ተረጋግታለች፣ ባንተ ህይወቴ ሙሉ በርቷል፣ ባንተ ውስጤ ፈክቷል፣ ደምግባቴ ተመልሷል፣ ክብሬ ከፍ ብሏል፣ ባንተ ከድካሜ ሁሉ አረፍኩ፣ እንግልቴ ሁሉ ጠፋ፣ ንፁውን ፍፁም ደስታም ካንተ አገኘውት። አባትነትህ ምነኛ ፍፁም ነው? ርህራሔህ ምነኛ ድንበር አልባ ነው? መውደድህስ ቢሆን ምን ይሆን ገደቡ? ወደህ ፈቅደህ ወደእቅፍህ ጠርተሀኛል፣ ፈልገህ አለኝታ ሆነሀኛል፣ ሳትጠየፈኝ ዝቅ ብለህ አንስተሀኛል። አንድ ዘላለም የምኮራበት ነገር ቢኖር ያንተ የእግዚአብሔር አምላኬ ልጅ በመሆኔ ነው። ማንም በሌለበት በድቅድቁ ጨለማ አልያም በሃሩሩ በረሃ ብገኝ እንኳን አንተ አብረሀኝ እንዳለህ አውቃለሁና አንዳች አልፈራም፣ ፍቅርህ ከልቤ፣ ማዳንህም ከማንነቴ ተዋህዷልና ሁሌም ኩራቴ ነህ፣ ዘወትር መመኪያዬ መጠጊያዬም ነው። እወድህ ዘንድ የማንም ፍቃድ አልሻም፣ አክብሬህ እከብር ዘንድ መርጬህም እመረጥ ዘንድ አንዳች ግፊት አንዳች ግዴታ የለብኝ። አምላኬ እወድሃለሁ፤ አባቴ አከብርሃለሁ።"

አዎ! ጀግናዬ..! ከምድራዊ ህይወት እረፍትን መጠበቅ፣ ከዓለም ንብረትና ዝና እንዲሁ ከደካማው የሰው ልጅ ፍፁም ሰላምን መፈለግ ድክመት ነው። ከአባትህ ቤት መጥፋትህን አስብ፣ ከመገናኛችሁ መራቅህ ይታወቅህ፣ ከበረከቱ መጉደልህ ይግባህ። ስለምን ነገ የሚጠፋውን የዓለም ጌጥ ፍለጋ ያለእረፍት ትደክማለህ? ስለምን ቦሃላ በትሹ በሚሰበረው ሰውነትህ ትመካለህ? ስለምን ጊዜ በሚሰጥህ እግዚአብሔርም ባስረከበህ ስልጣን ልጆቹን ትበድላለህ? ስለምን ስህተትህን እንደ መልካም ስራ፣ ጥፋትህንም እንደ ጀብድ ትደጋግማለህ? ወደ ፈጣሪህ እቅፍ ተመለስ፣ ወደቤቱ ቅረብ፣ ዝቅ ብለህ ተማፀነው፣ ክብርን ከእርሱ አግኝ፣ ፍፁም ሰላምህን ከእርሱ ውሰድ። ፍቅሩን ተረዳ፣ ማዳኑን ተመልከት፣ እለት እለት ከበረከቱ ተካፈል፣ ውስጥህን አድስ፣ በመኖርህ ተደሰት።
ፍፁም ሰላማዊ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
04.04.202507:49
አንድ ነገር ከመጀመራችሁ በፊት!
፨፨፨፨፨፨///////////////፨፨፨፨፨፨
ከማንኛውም ሰው ጋር ባላችሁ ንክኪ ሊያሳባችሁና ጥንቃቄ ልትወስዱ የሚገባችሁ ነገር ቢኖር የአጀማመራችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ሁኔታው የንግድ አጋርነት፣ የፍቅር ግንኙነት፣ ትዳር፣ የስራ ሁኔታም ሆነ ሌላ ማሕበራ ጉዳይ፣ የትክክለኛ አጀማመርን ሕግ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት አንድን ነገር የጀመርንበት ሁኔታ በቀጣይነቱና በአጨራረሱ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ስላለው ነው፡፡

አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት . . . 

1. ከፍጻሜው ተነሱ
ከፍጻሜው መነሳት ማለት የምትጀምሩትን ነገር እስከወዲያኛው በማሰብ ወደየት ልትወስዱት እንደምትፈልጉ፣ ምን ያህል ርቀት እንዲሄድ እንደምትፈልጉና ከነገሩ ምን ውጤት እንደምትጠብቁ በሚገባ በማሰብ መጀመር ማለት ነው፡፡ የቅርብ እይታ፣ አጭርና ስንኩል ጉዞን ይፈጥራል፤ ረጅም እይታ ደግሞ ረጅምና ስኬታማ ጉዞን ይሰጠናል፡፡

2. የመነሻ ሃሳባችሁን አስተካክሉ
የመነሻ ሃሳብን ማስተካከል ማለት ከአንድ ሰው ጋር አንድን ነገር ስትጀምሩ ያንን ነገር ለምን ለመጀመር እንደፈለጋችሁ የመነሻ ሃሳባችሁን ለይታችሁ በማወቅ ሃሳቡ ጤናማና ትክክለኛ መሆኑን ማወቅ ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር የምትጀምሩት ለማይሆንና ለተዛባ ምክንያት ከሆነ ጅማሬው ላይ ምንም ያህል ተለሳልሳችሁና ተግባብታችሁ ብትቀራረቡም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መበላሸቱ አይቀርም፡፡

3. የሚጠበቀውን ነገር ግልጽ አድርጉ
የሚጠበቀውን ነገር (Expectations) ግልጽ ማድረግ ማለት እናንተ ከሰዎቹ የምትጠብቁትን፣ እነሱ ደግሞ ከእናንተ የሚጠብቁትን ነገር በግለጽ መነጋገርና የጋራ ግንዛቤና ተግባቦት መፍጠር ማለት ነው፡፡ ትልቁ የሕብረተሰባችን አለመግባባትና መንስኤው አንዱ ከሌላው ምን እንደሚጠብቅ በግልጽ ከመነጋገር ይልቅ ሁኔታውን በስሜት ጀምሮ እግረ-መንገድ እየፈጠሩና ግራ እየተጋቡ የመሄድ ጉዳይ ነው፡፡
ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
06.04.202518:17
ሙከራን ልመዱ!
፨፨፨////////፨፨፨
አዳዲስ ነገሮች ውስጥ ምን አለ? ከፍረሃታችሁ ጀርባ ምን የሚጠብቃችሁ ይመስላችኋል? ሃሳባችሁን እንዴት እውን ማድረግ ትችላላችሁ? ከተስፋና ከእምነት የትኛውን ይበልጥ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ? የአኗኗር ዘይቤ (lifestyle) በራሱ ህይወት ነው። የምንኖረው ህይወት እንደ ልማድ ከምናደርጋቸው ተግባሮች የተለየ አንድምታ የለውም። አብዝተን የምንገኝበት ስፍራ፣ ደጋግመን የምናደርገው ነገር፣ ረጅም ጊዜ አብረናቸው የምናሳልፋቸው ሰዎች፣ ብዙ ሰዓት የምናከናውነው ተግባር ህይወታችን ነው። ማናችንም ብንሆን እግዚአብሔር እስከፈቀደ ድረስ እንኖራለን፣ በፈጣሪ እገዛ ብዙ ከባድ ነገሮችን አልፈናል ወደፊትም እናልፋለን። የእያንዳንዱን የህይወት ስጦታዎች ጠዓም፣ የእያንዳንዱን አዲስ ተግባሮች ክብደት መለካት ደግሞ የሁላችንም ግዴታ ነው።

አዎ! ሙከራን ልመዱ! እራሳችሁን ለአደጋ ማጋለጥ ተለማመዱ፣ ለመውደቅ ደፋር ለመነሳትም ፈጣን ሁኑ። የምትኖሩትን ህይወት ከቁጪት ነፃ አድርጉት። የምንፈልገውን ህይወት ለመኖር በሰዓቱ የማያስደስተንንና የማይመቸንን ተግባር እንደምንወደውና እንደተመቸን አድርገን የመስራት ግዴታ አለብን። እራስን ምቾት መንሳት ደስ አይልም፣ እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ያስፈራል፣ አውቆ እራስን መፈተን ያስጨንቃል ነገር ግን ከዚህ ቀደም ያልተገኘን ውጤት ያስገኛል፣ ከዚህ በፊት ያልተደረሰበት ስፍራ ያደርሳል፣ ታይቶ የማይታወቅ ዓለም ውስጥ ይከታል። አንድ ቦታ ቆማችሁ ከምትጨነቁ ሁሉን በመሞከር እራሳችሁን ግራ አጋቡ፣ በፍረሃታችሁ ታስራችሁ ከምትቀሩ በየደረጃው ፍራሃታችሁን ተጋፈጡት፣ ዘመናችሁን በሙሉ በስጋትና በማንአለብኝነት ከምታሳልፉ ለገዛ ህይወታችሁ ሃላፊነት ውሰዱ። ከእያንዳንዱ የህይወት ክስተቶቻችሁ ስትማሩ፣ ከየትኛውም ችግራችሁ ለመውጣት ስትሞክሩ እግረመንገዳችሁን እራሳችሁን እያሻሻላችሁና የሚያኮራ ማንነትን እየገነባችሁ ትመጣላችሁ።

አዎ! ጀግናዬ..! የበዪ ተመልካች አትሁን ተቀላቅለህ የሚበሉትን ብላ፣ የሚሞክሩትን ሞክር፣ የሚያደርጉትን አድርግ። ባለህበት ቆመህ የሚፈጠር ተዓምር የለም፣ በየአቅጣጫው ተንቀሳቀስ፣ እንዳቅምህ እራስህን ፈትነው፣ ተስፋህን ለመጨበጥ፣ እምነትህን ተግባራዊ ለማድረግ በትንሹ ወደፊት ተራመድ፣ በልክህ ጥረትህን ጨምር። ማድረግ እንደምትችል እያወክ ምንም ነገር ሳታደርገው እንዳያመልጥህ። ሁሉም ቦታ መገኘት፣ ሁሉንም መሞከር  ብክነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን በእቅድና በአለማ ሲፈፀም ግን ትልቁ ህይወት ቀያሪ ክስተት ይሆናል። አቅሙ እንዳለህ ታውቃለህ፣ የውስጥህን ፍላጎት ተረድተሃል፣ ምን ስታደርግ ምን እንደምታገኝ ግልፅ ነው። ካልሞከርክ ግን ዛሬም ነገም ውጤት አልባ እውቀት ተሸክመህ ትቀራለህ። ሙከራን የአኗኗር ዘይቤህ አንድ አካል አድርገው፣ አዲስ ነገርን የመጋፈጥን ድፍረት እንደ ግል አቋምህ አራምደው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
26.03.202518:51
አዳማጭ ሁኑ!
፨፨፨/////፨፨፨
ለአፍታ ዝም ብላችሁ አካባቢያችሁን ቃኙ፣ አስተውሉ፣ ዞር ዞር ብላችሁ ተመልከቱ፣ መስማት የምትችሉትን ነገር ከልብ አዳምጡት። በየቦታው ጩሀት አለ፣ የህመም፣ የሲቃ ድምፅ አለ፣ ትርጉም አልባ ግርግር አለ፣ ብዙ የተጨነቁ ነፍሳት አሉ፣ ብዙ ውስጣቸው የቆሰለ፣ ስቃይ ያደከማቸው፣ ተስፋ የራቃቸው መጮህም ማውራትም ያልቻሉ ምስኪን ነፍሳት አሉ። ዝም ብላችሁ አዳምጡ። ንግግሩን ብቻ ሳይሆን መንፈስንም ማዳመጥ ሞክሩ፣ ገፅታን፣ ስሜትን፣ ተግባር ከልባችሁ ማስተዋል ጀምሩ። ዓለም ያለማቋረጥ የሚጮህ እንጂ አዳማጭ የላትም፣ የሰው ልጅ የሚፈልገው ወረኛን ሳይሆን የሚያዳምጠውን ነው። ጫጫታ በዝቷል፣ እዚም እዛም አለመግባባት ተስፋፍቷል፣ ሁሉም ተናጋሪ ሆኗል፣ ሁሉም በየፊናው ወከባ ይፈጥራል፣ አቋሙን በግድ ለማራመድ ይጥራል። በሁካታ ብዛት የሚጨነቁ ነፍሳትን የሚያስብ የለም፣ በትርምሱ መሃል ልባቸው ስለሚያነባ ነፍሳት የሚያስታውስ የለም። አብዛኛው ችግር ፈጣሪ ለሌላው ያዘነ፣ አብዛኛው የግርግሩ ባለቤት ለህዝብ የሚያስብ፣ የሰው ችግር የሚያስጨንቀው ይመስላል። ነገር ግን የወገኑን ጩሀት እንደተረዳ ከማስመሰሉ በፊት ውስጡን እንኳን በቅጡ አያውቀውም።

አዎ! አዳማጭ ሁኑ! በቅድሚያ ወደራሳችሁ ተመለሱ፣ ለራሳችሁ ጉዳይ ቅድሚያ ስጡ፣ ውስጣችሁን አዳምጡት፣ ሁኔታችሁን መርምሩ፣ ፍላጎታቸውን አጥኑ። ከልብ የማዳመጥን ልማድ ስትገነቡ ማስተዋል ትጀምራላችሁ፣ ከሸንጎ ፍርድ ትቆጠባላችሁ፣ ከእያንዳንዱ እርምጃችሁ በፊት ደጋግማችሁ ታስባላችሁ፣ ችግር በበዛበት ዓለም የመፍትሔ ሰው ሆናችሁ ብቅ ትላላችሁ። የምታዳምጡት የምትናገሩት አጥታችሁ፣ እውቀት አንሷችሁ ወይም ፈርታችሁ አይደለም። ይልቅ ከመናገራችሁ በላይ ትርፋማ የሚያደርጋችሁ፣ ይበልጥ ጥበብን የሚያድላችሁ፣ ተጨማሪ ግበዓትን የሚያጎናፅፋችሁ ማዳመጣችሁ እንደሆነ ስለገባችሁ ነው። ሰዎች ስላሉበት ሁኔታ ሊያወሯችሁ ቢፈልጉ ከልብ ጆሮ ስጧቸው፣ በሙሉ ሰውነታችሁ አዳምጧቸው፣ ትኩረታችሁን እነርሱ ላይ አድርጉ። ማዳመጥ በእራሱ እራሱን የቻለ የስነስልቦና የህክምና ዘርፍ (therapy) እንደሆነ እወቁ።

አዎ! ጀግናዬ..! አትዋከብ፣ እዚም እዛም አትበል፣ ነፍስህን አታስጨንቃት፣ የጫጫታው አድማቂ፣ የትርምሱ መሪ አትሁን። ሰከን በል፣ ተረጋጋ፣ ወደራስህ ተመለስ። አንተ እራስህን ካላዳመጥክ ማን እንዲያዳምጥህ ትፈልጋለህ? አንተ እራስህን ካልተመለከትክ ማን ይመለከትሃል? እራስህን አስታውስ። የዓለም ግርግር አያታልህ፣ የምታየው ጌጥና ጫወታ ከፈጣሪህ ጋር ያለህን ግንኙነት አያበላሽ። ከእግዚአብሔር በቀር ምንም ነገር እንደነበረ አይቀጥልም፣ ምንም ነገር ቋሚ አይደለም። ዛሬ የምትጓጓለት የተመቻቸ ህይወትም ቢሆን በእጅህ ሲገባ የሆነ ጊዜ ምንም እንደሆነ ይገባሃል። ከየአቅጣጫው ጩሀትና ዋይታ ሲበረታ አዳማጭ የመፍትሔ ሰው ያስፈልጋልና እራስህን ለእርሱ አዘጋጅ። ማንንም ከመከተልህ በፊት ከስሜት በላይ ሆነህ፣ ከጥላቻና ከፍርጃ ርቀህ ልብ ገዝተህ አዳምጥ። አንተም ተምታተህ ሰዉን አታምታታ። አዳምጥ፣ እወቅ፣ መርምር፣ ችግር ፈጣሪ ሳይሆን ችግር ፈቺ፣ የሁካታ መሪ ሳይሆን የመፍትሔ ሰው ሆነህ ተገኝ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫✨
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

🔺🔻በYouTube ቤተሰብ ስለሚሆኑ እናመሰግናለን!
SUBSCRIBE NOW! 👇
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊💪
Жойылды30.03.202523:19
27.03.202520:16
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
Көбірек мүмкіндіктерді ашу үшін кіріңіз.