Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
አዲስ ነገር መረጃ avatar
አዲስ ነገር መረጃ
አዲስ ነገር መረጃ avatar
አዲስ ነገር መረጃ
10.05.202511:33
ከእውቅናየ ውጭ ምንም አይነት የውጭ ግንኙነት ማካሄድ ትክክል አይደለም - የትግራይ ክልል የጊዜያዊ አስተዳደር

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከእውቅናየ ውጭ በክልሉ ምንም አይነት የውጭ ግንኙነት ማካሄድ ትክክል አይደለም፣ አደገኛም ተግባር ነው ሲል ትላንት ሚያዚያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አሳሰበ፤ በምንም መንግድ “ተቀባይነት የለውም” ሲል አስጠንቅቋል።

ክልሉ “ከፌዴራል መንግስት ጋር ብቻ ሳይሆን ከማንኛውም ሃይል ጋር ያሉትን ልዩነቶች በሰላማዊና ህጋዊ መንገድ ለመፍታት የተቻለውን ሁሉ ጥረት ማድረግ ተገቢ ነው ብሎ እንደሚያምን” ያስታወቀው ጊዜያዊ አስተዳደሩ “ነገር ግን እስትራቴጂው፣ አላማውና ስልቱ የማይታወቅ ምንም አይነት የውጭ ግንኙነት ማድረግ ትክክል አይደለም” ሲል ገልጿል።

ይህ አይነቱ አካሄድ “ትግራይን መንግስት አልባ ሆና ስጋት እንዲነግስ የሚያደርግ፣ ክልሉ አንድ ማዕከል እንዳይኖረው የሚያደርግ አደገኛ ተግባር ነው” ሲል ኮንኗል፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር “እንዲህ ዓይነቱን ተግባር በማንኛውም ሁኔታ እንደማይቀበለው ሊታወቅ ይገባዋል ሲል” አስጠንቅቋል።


@Addis_News
@Addis_News
10.05.202509:47
የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ሰራተኞች ስራ የማቆም እርምጃ ሊወስዱ ነው

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ገቢ ማመንጫ ኢንተርፕራይዝ ሰራተኞች ለረጅም አመታት ሲጠይቁ የነበረው የደሞዝ ማሻሻያ ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ 1156/2011 አንቀፅ 160(2) መሰረት ህጋዊ ስራ የማቆም እርምጃ ሊወስዱ መሆናቸው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ኢንተርፕራይዙ የመንግስት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የገቢ ማስገኛ ድርጅቶችን ለማቋቋም ባወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደምብ በመቋቋም የተለያዩ የንግድ እና ገቢ ማስገኛ ስራዎችን ሲሰራ የቆየ ነው።ይሁንና የኢንተርፕራይዙ ሰራተኞች ከ2008 ዓ/ም ጀምሮ አንድም ግዜ የደሞዝ ጭማሬ እንዳልተደረገላቸው ለመሠረት ሚድያ ተናግረዋል።

የኢንተርፕራይዙ ሰራተኞች ውሳኔያቸውን ለትምህርት ሚኒስቴር፣ ለጤና ሚኒስትር እና ለዩኒቨርስቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መቅደስ ዳባ እንዲሁም ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ማሳወቃቸው ታውቋል።በተመሳሳይ ከሰሞኑ የጤና ባለሙያችም "ጥያቄያችን ይመለስ" በሚል የመብት እና የጥቅም ጥያቄ በማንሳት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች ድምፅ እያሰሙ መሆናቸው ይታወቃል።

እነዚህ የጤና ባለሙያዎችም ለመንግስት ምላሽ መስጫ ቀን ሰጥተው እየጠበቁ ሲሆም ምላሽ ካላገኙ እስከ ስራ ማቆም የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስዱ እያሳወቁ ይገኛሉ።


@Addis_News
@Addis_News
"በጣም ቀሽም ተማሪ ነበርኩ ኳስ ግን በጣም ጥሩ ተጨዋች ነበርኩ" የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ "ተማሪ ሳለሁ ከኳስ ዉጪ ትምህርት ትዝ ብሎኝ አያዉቅም ነበር" ብለዋል።

"ከኳስ ሌላ ክፍል ገብቶ መዉጣት ምናምን ነበር። በጣም ቀሽም ተማሪ ነበርኩ ኳስ ግን በጣም ጥሩ ተጨዋች ነበርኩ" ብለዋል።

@Addis_News
@Addis_News
09.05.202518:31
‹እኔም አንተም አንቺም ሁላችን ለወገን የሚጠቅም ሃሳብ፣ ልምድ፣ የህይወት ተሞክሮ አለን። ለማገልገል ቅንነት እንጅ ካሰቡበት ስኬት መድረስ ግደታ አይደለም!› ።  በዚህ CHANNEL የማይዳሰስ ሃሳብ የለም፤ በህጋዊ መንገድ ከሃገር መውጫ መንገዶች፣ ስለ አዳድስ ቴክኖሎጅዎች አጠቃቀም፣ ሥራ ፈጠራና የቢዝነስ ሃሳብ ማጋራት እና ሌሎች ወቅታዊና ሃገራዊ ሁነቶች ይዳሰሳሉ። ኑ! እናንተም ሃሳባችሁን ለውይይት አቅርቡ፤ ልምዳችሁን አጋሩ፤ ኑ! አብረን እንሥራ፣ ማህበረሰባችንን እናገልግል።
ውጭ መሄድ ለምትፈልጉ በተለይ ገብታችሁ ተመልከቱ ❗️👇👇👇
https://youtu.be/_xHfBzmYOX8
https://www.youtube.com/channel/UCN7VWSigN5zfJJEe9ReV1fw?sub_confirmation=1
ኑ! እንወያይ፡ ማህበረሰባችንን እናገልግል።
09.05.202516:36
09.05.202514:01
ድምፃዊ አስጌ በኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር በወጣበት መግለጫ

ድምፃዊዉም መግለጫ አውጥቷል....

አስጌ:- የሀገር ካስማ ምስክር ነው!!..

በመጀመሪያ ደረጃ  ፣ ጽሑፌ ላይ "ሁሉም ሴቶች" የሚል የለም። ምንም አማርኛ አራተኛ ቋንቋዬ ቢሆንም "ሴቶች" ስል ከአንድ በላይ ፣ መሆናቸውን እንጂ "ሁሉም" ማለት እንዳይደለ ፣ ጠንቅቄ አውቃለሁ።

ሲቀጥል ፣ አታብድም እንጂ ፣ አታፈቅርም ፣ የሚል ፅሑፍም በየትኛውም የፊት ገጽ(ማህበራዊ ሚዲያ) ላይ አላጋራሁም።

እንዲያውም ፣ ለሴቶች ድምጽ ፣ መሆኔን ነው የማውቀው ፣  ዓለም ያልመሰከረላቸውን ፣ ጥንካሬ ነው የመሰከርኩላቸው።

ወንድ ልጅ ፣ ሴት ልጅ ፣ ጥላው ስለሄደች(ስለተከዳ) ብቻ ፣ ሰማይ የተዘጋበት ፣ ሊመስለው ይችላል ፣ አቅሉን ሊስት ፣ ሊያብድ እና ፣ ጨርቁን ጥሎ ፣ ጎዳና ሊወጣ ይችላል። ለዚህም ፣ እስከዛሬ ትመጣለች እያለ ፣ በተስፋ የሚጠብቀውን ፣ መንገድ ላይ ቆሞ ፣ መንገድ የጠፋውን ፣ እሷን ፍለጋ ራሱን ያጣውን ፣ ወንድማችንን ማየት በቂ ነው።

ሴቶች ጋር ግን ፣ እንዲህ ዓይነት ነገር ፣ ዕምብዛም አይታይም። ይሄ ደግሞ ፣ ጥንካሬያቸውን እና ልዩ ፍጡር መሆናቸውን ፣ ነው የሚያሳየው። ከዚህ ተነስቼ ነው ፣ ሴት ልጅ ፣ በፍቅር አታብድም የምለው። ለምን አያብዱም ትለናለህ ፣ እናብዳለን ብላችሁ ፣ የምታብዱ ሴቶች ፣ እደግመዋለው አታብዱም ፤ እንድታብዱም አልፈልግም ፤ እኔ የልጄ(ሴት) አባት ፣ የእናቴ(ሴት) ልጅ ነኝ። ማበድም ደግሞ ፣ የፍቅርም የጀግንነትም ፣ መገለጫም አይደለም'ና ፣ የወሰድኩባችሁ ክሬዲት ካለም ፣ በይፋ መልሼአለሁ🙌 ፣ ይቅርታዬንም እነሆ።🙏🏽
 
ለሚመለከተው ግን ፣ አንድ ነገር ፣ ማለት ፈልጋለሁ፤

ተደፍረው የተገደሉ ፣ ሕፃናትን ፣ ዶሴ አቧራ ፣ ሳናራግፍ ፤💔🙌
📍📚አክሱም ላይ ፣ በሂጃብ ምክንያት ፣ ከትምህርት ገበታ ፣ ስለታገዱ ሴቶች ፣ ዝምታችንን ሳንሰብር ፤

📌በትግራይ ጦርነት ጊዜ ፣ ከ15 እስከ 49 ዓመት ዕድሜ ክልል ፣ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች ፣ 10% የሚሆኑት ሲደፈሩ ፣ ያልነበርን ፣
(ለቀነኒ አዱኛ ወዳጆች እና ቤተሰብ መጽናናትን እመኛለሁ)💔🙌 ፣

"አታብዱም" ተባልን ተብሎ ፣ መግለጫ ማውጣት ፣ ከየት ተማርን ፣ እንዴት ቻልንበት ፣ ሞራሉንስ ከየት አገኘን ማለት እወዳለሁ።

ግና ግን ፣ ለሴት ልጅ ያለኝን ፣ ፍቅር'ና ክብር ፣ በልጄ : በእናቴ እና ፣ ዙሪያዬ ባሉ ፣ እንዲሁም ፣ በቅርበት ፣  በሚያውቁኝ ሴቶች ፣ ማየት ፣ ማረጋገጥ ፣ ይቻላል ፤ "የሀገር ካስማ" (ለሴቶች እኩልነት የተሰራ ሙዚቃ) ምስክሬ ነው።

በመጨረሻም ፣ በነፃ ሀሳባችን ፣ በአማርኛችን ፣ በመልካችን እና በመጣንበት አቅጣጫ ፣ ለማሸማቀቅ የሚደረገውን ፣ የትኛውንም ተግባር'ና እንቅስቃሴ እቃወማለሁ🙌 ፣ አመሰግናለሁ!!

አሁንም ኑና እሰሩኝ ሴት በፍቅር አታብድም (ድምፃዊያን አስገኘው ደንደሾ)።

@Addis_News
@Addis_News
10.05.202510:00
በሞስኮው ከትራኦሬ ጋር ፎቶ ለመነሳት ጥቁሩም ነጩም በዚህ መልኩ ሲጣደፉ ታይተዋል።

ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ በሩሲያ በዓል ላይ ከታደመ በኋላ ከተናገረው

"ሩሲያ በ ድል የተቀዳጀችበትን 80ኛ ዓመት በሚከበርበት ታላቅ ሰልፍ እና የአበባ ጉንጉን አቀማመጥ ላይ በመታደም ለሶቪየት ጦር እና ለተባባሪ ወታደሮች ክብር ሰጥቻለሁ።  ይህ ታሪካዊ ድል ሀገራችን እና የAES ኮንፌዴሬሽን (Alliance of Sahel States) በፀረ ሽብርተኝነት እና ኢምፔሪያሊዝም ላይ የምናደርገውን ጦርነት በማንኛውም ዋጋ ለማሸነፍ ባለን ጽኑ ቁርጠኝነት እምነት እንዲኖረኝ ያነሳሳኛል።  በቡርኪናፋሶ እና በሩሲያ ፌዴሬሽን መካከል ያለውን የጋራ ተጠቃሚነት አጋርነት በደስታ እቀበላለሁ" ሲል ተደምጧል።

@Addis_News
@Addis_News
10.05.202509:31
🇪🇹🇷🇺 የሩሲያ መንግሥት በኢትዮጵያ አዳዲስ የሎጂስቲክስና የትራንስፖርት ፕሮጀክቶችን ለመጀመር እንደተዘጋጀ ገለፀ

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ከ80ኛ ዓመት የድል በዓል ጎን ከሩሲያ ፕሬዝዳንት የዓለም አቀፍ ትብብርና ትራንስፖርት ዘርፍ ልዩ አማካሪና ተወካይ ኢጎር ሌቪቲን ጋር ውይይት አድርገዋል።

ርዕሰ ብሔሩ የኢትዮጵያ እና ሩሲያ ግንኙነት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይበልጥ እያደገ መምጣቱን በውይይቱ ወቅት ተናግረዋል።

ሀገራቱ በሎጂስቲክስና ትራንስፖርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል።

Via berbir

@Addis_News
@Addis_News
"ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይና አመራሮች ከሀኪሞቻችን እንማር" -  ታዬ ደንደዓ

የቀድሞው የሰላም ሚኒስትር ታዬ ደንደዓ ምን አሉ?

"ፀረ-እውቀት ቁማርተኞች ዛሬም እውነቱን አልተረዱም። ስለኮሪደር፣ ስለሪዞርትና ስለፓርክ እያወሩ ለመኖር የተቸገረውን ለማታለል ሲሞክሩ አያፍሩም።

ኢትዮጵያ እኮ የቄስ ሞገሴና የመሬት ደላላ ብቻ አይደለችም።

እኛ በልቶ ማደር፣ የኤሌክትሪክ ታሪፍ መክፈል፣ ልብስ መቀየርና ልሎች የህይወት ጉዳዮች የቸገረን የኢትዮጵያ ሀኪሞች፣ መምህራን፣ ወታደሮች፣ ሠራተኞችና የከተማ/ገጠር ነዋሪዎች የዳቦ እንጂ የመዝናኛ ጥያቄ የለንም።

ስለዚህም የፓርክና የኮሪደር ቁንጅና አያምረንም።

ኢትዮጵያውያን በአጠቃላይና አመራሮች በተለይ ከሀኪሞቻችን እንማር። ከብሔር፣ ከሃይማኖትና ከአከባቢ አጥር ወጥተን በነፃነት፣ በፍትህ፣ በሰላምና በወንድማማችነት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለጋራ እናተኩር።

ችግሩ ለሁላችንም የህልውና  አደጋ ነውና በመርህ እንተባበር" ብለዋል።

Via : zena ethiopia

@Addis_News
@Addis_News
09.05.202518:16
በከፍተኛ የዳኞች ስራ መልቀቆያ ሳቢያ በተፈጠረ የዳኞች እጥረት መዝገቦች በታቀደው ልክ እልባት አላገኙም ሲል የደቡብ ወሎ ዞን አስታወቀ

የዞኑ ፍርድ ቤቶች የ9 ወር ስራ አፈፃፀም ግምገማ በደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን የከፍተኛ ፍርድ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት እና በዞኑ የሚገኙ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንቶች እና የዋና ስራ ሂደት አስተባባሪዎች በተሳተፉበት ተካሂዷል። የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እቅድ ዝግጅትና በጀት ክትትል ባለሙያ አቶ መሀመድ ሰይድ የዞኑን ፍርድ ቤቶች የ2017 ዓ.ም  የ ዘጠኝ ወር  የስራ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡ በከፍተኛ ፍርድቤት ከቀረቡት የፍታብሄር ጉዳይ 3ሺ937 መዝገቦች ቀርበው 2ሺ758 መዝገቦች እልባት ሲያገኙ በወንጀል ጉዳይ 1ሺ432 መዝገቦች ቀርበው 884ቱ ውሳኔ አግኝተዋል፡፡ 

በአጠቃላይ በፍታብሄርና በወንጀል 5ሺ369 መዝገቦች ቀርበው 3ሺ642 መዝገቦች እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል።በተመሳሳይ በዞኑ የወረዳ ፍርድ ቤቶች 49ሺ993 የፍታብሔር መዝገቦች ቀርበው 45ሺ772 መዝገቦች ውሳኔ አግኝተዋል። ከዚህ በተጨማሪ በወንጀል ጉዳይ 6ሺ435 መዝገቦች ቀርበው 6ሺ128 መዝገቦች ውሳኔ ተሰጥቶባቸዋል። የፀጥታ ችግር መኖር፣ የተከሳሽን የምስክር አቀረረብ ክፍተትና በተለይም በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ በርካታ ዳኞች ከመልቀቃቸው ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የዳኛ እጥረት በታቀደው መጠን መዝገቦችን እልባት ላለመግኘታቸው እንደ ዋነኝ ምክንያት ተጠቅሷል።

ውሳኔ የሚያገኙ መዘግብት የእድሜ ቆይታን በተመለከተ ውሳኔ ካገኙ መዛግብቶች በከፍተኛ ፍርድ ቤቱ 84 በመቶ ፤በወረዳ ፍርድ ቤቶች ደግሞ 98 በመቶ ከስድስት ወር በታች በሆነ ጊዜ እልባት ያገኙ መሆናቸው ተገልጿል። የፍርድ ጥራትን በተመለከተ በከፍተኛ ፍ/ቤት ታይቶ በጠቅላይ ፍ/ቤት የመፀናት ምጣኔ ስንመለከት ውሳኔ ካገኙ 2ሺ382 መዝገቦች ውስጥ 1ሺ468 መዝገቦች ፀንተዋል፡፡  ከወረዳ ፍ/ቤቶች እልባት አግኝተው ለከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበው እልባት ካገኙ 2ሺ575 መዝገቦች ውስጥ 1ሺ364ዎቹ የፀኑ መሆናቸው ብስራት ሬድዮ ያገኘው መረጃ ያሳያል።

@Addis_News
@Addis_News
09.05.202516:36
እግዚአብሔር ይመስገን !!!

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት በዚህ መልኩ ተከብሮ ውሏል፤

መልዕክቱን ያድምጡት👇
07.05.202511:34
መንግስት የጤና ባለሙያዎች ላቀረቡት ጥያቄ በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ የ ኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር አሳሰበ

የጤና ባለሙያዎች ከደሞዝ ጭማሪ እና ጥቅማጥቅም ጋር ተያይዞ ለሚያነሱት ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ የቅድመ ስራ ማቆም አድማ ሰልፎችን በመላው ኢትዮጵያ እያካሄዱ መሆኑን ተከትሎ የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ማህበር፤ መንግስት ለጥያቄያቸው በአስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ አሳሰበ። የባለሙያዎቹ ንቅናቄም "አገሪቱን እና ማህበረሰቡን በማይጎዳ መልኩ" መከናወን እንዳለበት አፅንዖት ሰጥቷል።

ማህበሩ ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ፤ "በጤና ባለሙያዎች የተነሱት ጥያቄዎች ተገቢ በመሆናቸው መንግስት አፋጣኝ መፍትሄዎችን መስጠት አለበት" ብሏል።  “መንግስት በጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን ችላ ማለቱን እንዲያቆም እና ለሀገሪቱ ችግር ከመፍጠሩ በፊት ተገቢውን ትኩረት እና ምላሽ እንዲሰጥ” አጥብቆ አሳስቧል።

ማህበሩ እነዚህን ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እና ከፍተኛ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በተገቢው ህጋዊ መንገድ ማቅረቡን ገልጾ፤ ይሁን እንጂ "የጤና ባለሙያዎች የሚያነሱት ጥያቄ በአፋጣኝና በተገቢው መንገድ ምላሽ ስላልተሰጠው የጤና ባለሙያዎች በተለያዩ መንገዶች መብታቸውን እየጠየቁ ነው" ሲል ገልጿል።


@Addis_News
@Addis_News
10.05.202509:59
#ግመል በመርፌ ቀዳዳ ስትሾልክ አሳየው

በማቴ. 10÷3 እንደተጻፈው አባቱ እልፍዮስ ይባላል፡፡ በሉቃስ 6÷16 ደግሞ ሐዋርያው “ታዴዎስ ልብድዮስ”፣ “የያዕቆብ ልጅ ይሁዳ” እየተባለም ተብሎ ሲጠራ እናያለን፡፡ ጌታችን ከሐዋርያት አስቀድሞ ይህን ቅዱስ ታዴዎስን እንደ መረጠው መጽሐፈ ስንክሳር ይናገራል፡፡ እርሱም በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን በመስበክ ከአይሁድና ከአረማውያን ወገን ብዙዎችን ወደ ክርስትና መልሶ አጥምቋል፡፡ አንድ ቀን ወደ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሦርያ ለስብከተ ወንጌል ሲሔድ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጐልማሳ አምሳል ተገልጦ “ወዳጄ ታዴዎስ ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” ብሎ ሰላምታ ሰጥቶት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስም እንደ አባትነቱ ወደ ሦርያ አብሮት ሔዶ ነበረ፡፡ ከከተማዋ አጠገብ ሲደርሱም አንድ ሽማግሌ በሮችን ጠምደው ሲያርሱ አገኙ፡፡

ቅዱስ ጴጥሮስም ሽማግሌውን ምግብ ለመናቸው፡፡ “በሮቼን ጠብቁ” ብላዋቸውም ሊያመጡላቸው ወደ ቤታቸው ሔዱ፡፡ ሽማግሌው እስኪመለሱ ቅዱስ ጴጥሮስ ሠላሳ ትልም ካረሰ በኋላ ቅዱስ ታዴዎስ በዚያ የነበረውን የሥንዴ ዘራበት፡፡ የተዘራውም ወዲያዉኑ በቅሎ፣ አድጎ፣ እሸት ኾነ፡፡ ሽማግሌው ምግብ ይዘው ከቤታቸው ሲመለሱም ሐዋርያት ያደረጉትን ተአምር አይተው ደነገጡ፡፡ ከእግራቸው ሥር ወድቀውም “እናንተ ከሰማይ የወረዳችሁ አማልክት ናችሁን?” አሏቸው፡፡ እነርሱም “እኛ የእግዚአብሔር ባሮች እንጂ አማልክት አይደለንም” አሉ፡፡ ሽማግሌውም ስላደረጋችሁልኝ በጎ ሥራ በምትሔዱበት ቦታ ኹሉ ልከተላችሁን? አሏቸው፡፡ እነርሱም “በሬዎቹን ለጌታቸው መልስና በቤትህ የምንበላውን ታዘጋጅልን ዘንድ ለባለቤትህ ንገራት ወደ ከተማዋ ገብተን እግዚአብሔር እስከሚጠራን ጊዜ ድረስ እንቆያለንና” አሉት፡፡

ሽማግሌውም የሥንዴው እሸት ይዘው፣ በሬዎቻቸውን እየነዱ ወደ ከተማ ሲሔዱ ሰዎች ወቅቱ የእርሻ እንጂ የእሸት ጊዜ ስላልነበረ እየተገረሙ “እሸቱን ከወዴት አገኘኸው?” አሏቸው፡፡ ሽማግሌው ግን መልስ አልሰጧቸውም፡፡ ሐዋርያት እንደዘዟቸው በሬዎቹን ለጌታቸው መልሰው ሚስታቸው ራት እንድታዘጋጅላቸው ነገሯት፡፡ የከተማው መኳንንት ስለ እሸቱ ሲሰሙ “በክፉ አሟሟት እንዳትሞት ከወዴት እንዳገኘኸው ንገረን” አሏቸው፡፡ ሽማግሌውም ሐዋርያት ያደረጉትን ሁሉና ወደ እርሳቸው ቤት ቢመጡ ሊያገኟቸው እንደሚችሉ ነገሯቸው፡፡ መኳንንቱም ሰይጣን ልቡናቸዉን አነሳስቶታልና ሐዋርያቱን ለመግደል ወሰኑ፡፡ ሌሎች ግን “አምላካቸው ኢየሱስ የሚሹትን ኹሉ ያደርግላቸዋልና ልንገድላቸው አንችልም፡፡ ይልቅ በከተማው በር አመንዝራ ሴት ርቃኗን ብናስቀምጥ ወደ ከተማችን አይገቡም” አሉ፡፡

እንደተባባሉትም አደረጉ፤ ሐዋርያቱ ግን በሰዎቹ ልብና በሴቲቱ ላይ ያደሩትን ርኩሳን መንፈስ አስወጥተው በማስተማር በሥላሴ ስም አጥምቀው አገልጋዮችን ሾመላቸው፡፡ ያቺንም ሴት ዲያቆናዪት አደርጎ ሾማት፡፡ ብዙ ድንቅና ተአምራትም አደረጉ፡፡ ሕዝቡም በእግዚአብሔር አመኑ፡፡ ከዚህ በኋላ አንድ ሰይጣን ያደረበትና ገንዘብ የሚወድ ጐልማሳ ባለጸጋም ታዴዎስን በበዙ ተፈታተነው እርሱም ጌታችን እንደተናገረ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ስትሾልክ አሳየው፡፡ ያ ባለጸጋም ከቅዱስ ታዴዎስ እግር ስር ወድቆ ይቅርታ ጠየቀ ገንዘቡንም ሁሉ ለድሆች አከፋፈለ፡፡ ተምሮና አምኖም ተጠመቀ፡፡ ቅዱስ ታዴዎስ በየአገሩ እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ ቆይቶ ከአይሁድና ከአረማውያን ዘንድ ብዙ መከራ ከደረሰበት በኋላ አገልግሎቱን ፈጽሞ ሐምሌ 2 ቀን ዐርፏል፡፡ በብዙ ስጋዊ መከራ ውስጥ የሚያልፉ ቅዱሳን ገዳማውያንም የሐዋርያትን ፈለግ ተከትለው ዓለምን ንቀዋል፡፡ በዓታቸውን እናጽና ገዳማቸውንም እንደግፍ፡፡


ገዳማዊያኑን በመደገፍ ለነፍሳችን ስንቅን እንያዝ።

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
10.05.202509:12
💥We have reached 101k

ማስታወቂያ ማስነገር ለምትፈልጉ
በዚህ ቦት 👉  @Addisnegermereja_bot ላይ አናግሩን ወይም ፃፉልን



እናመሰግናለን
© Addis neger mereja Admins
10.05.202505:43
የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወጥ ቀለም ሊቀቡ ነው

መንግሥት፣ በአዲስ አበባና ሌሎች ከተሞች የሕዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች እንደየአገልግሎታቸው ዓይነት “ወጥ ቀለም” እና መለያ ኮድ እንዲኖራቸው እቅድ መያዙን ተሰምቷል።

የተሽከርካሪዎች ቀለምና መለያ ኮድ ከከተማ ከተማ የተለያየ ይሆናል ተብሏል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሠጪ ተሽከርካሪዎች ሹፌሮችም፣ ወጥ የደንብ ልብስ እንዲለብሱ ለማድረግ እቅድ እንደተያዘ ተነግሯል።

የትራንስፖርት ሚንስትር ዓለሙ ስሜ፣ ያረጁ ተሽከርካሪዎችን ከሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ውጭ ለማድረግ እንደተወሰነ ሰሞኑን ባንድ ስብሰባ ላይ መናገራቸው መዘገቡ ይታወሳል።

Via : ዋዜማ

@Addis_News
@Addis_News
ስብሰባ‼️

የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ እና ሌሎች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄዎች እያነሱ ይገኛሉ።

ጥያቄያችን ካልተመለሰ ከአራት ቀን በኋላ የስራ ማቆም አድማ እንደሚጀምሩ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች እየተመለከትን ነው።
ከዚህ ጋር በተያያዘ የጎንደር አጠቃላይ ሆስፒታል በስሩ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን ለነገ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቷል።

@Addis_News
@Addis_News
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ተደረገ።

የ2017 ትምህርት ዘመን ኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ / የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚሰጥበት መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ይፋ ባደረገው መርሃ ግብር ፈተናው ከሰኔ 23/2017 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 8/2017 ዓ/ም የሚሰጥ ይሆናል።

በወረቀት የሚፈተኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 21 እና 22/2017 ዓ/ም እንዲሁም የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 29 እና 30/2017 ዓ/ም ወደሚፈተኑበት ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ይሆናል፡፡

በበይነ መረብ የሚፈተኑ ተፈታኞች ከመኖሪያ ቤታቸው በየቀኑ እየተመላለሱ በተመደቡበት መፈተኛ ማዕከል የሚፈተኑ ይሆናል።

የፈተናው ይዘት በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያተኮረ በመሆኑ እያንዳንዱ ተፈታኝ በትምህርት ቤቱ የተማረበትን የተማሪ መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ተገቢ የሆኑ አጋዥ መጽሐፍትን ለበለጠ እውቀትና መረዳት በመጠቀም እንዲዘጋጅ አገልግሎት ጥሪ አስተላልፏል።

መረጃው ከትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተገኘ ነው።

@Addis_News
@Addis_News
07.05.202510:33
ህንድ በፓኪስታን ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት አስር የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ሰዎች ተገደሉ

በፓኪስታን የሚገኘው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሸባሪነት የተፈረጀው ቡድን መሪ ማውላና ማሱድ አዝሃር ህንድ በፓኪስታን ባሃዋልፑር በሚገኘው ሱብሃን መስጂድ ላይ በፈጸመችዉ ጥቃት 10 የቤተሰቡ አባላት እና አራት የቅርብ አጋሮቹ መገደላቸውን አስታውቋል። አዝሃር የሚመራው ታጣቂ ቡድን ጄም  እሮብ እለት በሰጠው መግለጫ ሟቾቹ ታላቅ እህታቸው እና ባለቤቷ፣ የወንድሙ ልጅ እና ባለቤቱ፣ የእህት ልጅ እና አምስት ልጆች ከነቤተሰቦቻቸው ይገኙበታል።

ጄኤም በየካቲት 2019 በህንድ የምትተዳደር ካሽሚር ውስጥ 40 ወታደሮችን የገደለ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ የሚታወስ ሲሆን ጎረቤት ሀገራቱን ወደ ጦርነት አፋፍ መዳረጉ ይታወሳል፡፡ በጥቃቱ ሶስት የአዝሃር የቅርብ ረዳቶች እና የአንዱ ረዳቱ እናት መሞታቸውንም ቡድኑ ገልጿል።ህንድ በፓኪስታን እና በፓኪስታን በሚተዳደረው ካሽሚር በሚገኙ ዘጠኝ ቦታዎች ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈጽማለች። ፓኪስታን ስድስት ቦታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙን ገልጻ አምስት የህንድ ተዋጊ ጄቶች መምታቱን ተናግራለች።

የፓኪስታን የማስታወቂያ ሚኒስትር አታላህ ታራር የህንድ ጥቃት የእኛን ገደብ ያለፈ ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡የወታደራዊው ቃል አቀባዩ ስለ አጸፋዊ ጥቃቶች የተናገሩ ሲሆን"ይህ ጥቃት ተገቢ ያልሆነ እና ፍፁም ጭፍን ጥቃት ነው" ብለዋል። "በግልጽ የአጸፋ ምላሻችንን በመሬት  እና በአየር ላይ ጥቃት እንመልሳለን" ሲሉ ተደምጠዋል፡፡በድንበር አካባቢ በህንድ የአየር ጥቃት 26 ሰዎች ሲገደሉ 46 ቆስለዋል ስትል ፓኪስታን ተናገረች። ህንድ ፓኪስታን ውስጥ በሲቪሎች ላይ ስለደረሰ ጉዳት ምንም አይነት መረጃ አልሰጠችም፡፡

ህንድ እና ፓኪስታን ሁለቱም የኒውክሌር ኃይል የታጠቁ ሀገራት ሲሆኑ በህንድ የሚተዳደረው የካሽሚር ግዛት ውስጥ በፓሃልጋም ቱሪስቶች ላይ ባለፈው ወር የደረሰውን አስከፊ ጥቃት ተከትሎ በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት መሻከሩ ይታወሳል። የሕንድ ባለስልጣናት በአጥቂዎቹ እና በፓኪስታን መካከል ግንኙነት እንዳለ ማረጋገጡ አስታዉቋል፡፡ ኢስላማባድ ግን የኒዉ ዴሊን ክስ አጥብቃ ውድቅ አድርጋለች ። በጸጥታ ሃይሎች የማደን ዘመቻ አሁንም ቀጥሏል።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህንድ እና ፓኪስታን ድንበር መዝጋት እና የወንዝ ውሃ ስምምነትን ማገድን ጨምሮ አንዳቸው በሌላው ላይ የተለያዩ የበቀል እርምጃዎችን አውጀዋል። ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጡ ወታደሮች መጠነኛ የትጥቅ ግጭት ዉስጥ ገብተዋል፡፡

Via Dagu

@Addis_News
@Addis_News
10.05.202509:59
10.05.202508:20
ፈረንሳይ ዩራኒየምን ከኒጀር በኪሎ 0.80$ ብቻ እየገዛች በኪሎ ወደ 200 ዩሮ በመሸጥ ትልቅ ትርፍ ስታገኝ ቆይታለች።
ኒጀር እስካሁን በድህነት ያለች ሃገር ናት ይህ የኒጀር ዩራኒየም 70% የሚሆነውን የፈረንሳይ ኤሌክትሪክ በኒውክሌር ማብላያዋ ሲያመነጭ ቆይቷል ነገር ግን አብዛኛው ኒጄሪያውያን አስተማማኝ ኃይል ሳይኖራቸው በጨለማ  ይኖራሉ።

ለብዙ አሥርተ ዓመታት የፈረንሳይ ኩባንያዎች የኒዠርን የዩራኒየም ማዕድን ማውጫዎች ኢፍትሐዊ በሆነ ስምምነቶች ተቆጣጠረው በርካሽ ዋጋ ወደ ሃገራቸው ያግዙት ነበር

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር  በ2023፣ ጄኔራል ቺያኒ መፈንቅለ መንግስትን መራ ፕሬዝዳንት ባዙምን አስወገደ

እንደነዚህ አይነት ፍትኃዊነት የሌለው የሃብት  ብዝበዛ እንዲቆሙ ጠየቀ የፈረንሳይ ወታደሮችን አባረረ ኒጀር የራሷን ሃብት እንድትቆጣጠር አደረገ ይህንን ማድረግ ሲጀምር የምዕራቡ ዓለም ጄኔራል ቺያኒን ጨቋኝ መሪ ነው ብለው ፈረጁት

ፈረንሳይ በበላይነት የኒጀርን ሃብት በርካሽ ስትበዘብ  እና ስትጠቀም መሪዎች ዝም ሲሉ መሪዎቹ ችግር የለባቸውም ነገር ግን ይህ ኢፍትሀዊ  የሆነ የሃብት ብዝበዛ መቆም አለበት ብለው ለሃገራቸው ሲሟገቱ እንደጨቋኝ ይታያሉ ::
ይህን ነው በአፍሪካውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው

@Addis_News
@Addis_News
09.05.202518:47
በህንድ እና በፓኪስታን መካከል ስላለው የደህንነት ሁኔታ ወቅታዊ መረጃ


በፓኪስታን እና በፓኪስታን የሰለጠኑ የላሽካር ኢ-ታይባ አሸባሪዎች በህንድ ጃሙ እና ካሽሚር ውስጥ በፓሃልጋም በህንድ ቱሪስቶች ላይ  ጥቃት ፈጽመዋል። አንድ የኔፓል ዜጋን ጨምሮ 26 ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል፣ ይህ የሽብር ጥቃት ከ26ኛው ህዳር 2008 የሙምባይ ጥቃት በኋላ ከፍተኛውን የዜጎች ህይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል።

በፓሃልጋም የተፈፀመው ጥቃት እጅግ የከፋ አረመኔነት የተንጸባረቀበት ሲሆን ተጎጂዎቹ በአብዛኛው በቅርብ ርቀት እና በቤተሰቦቻቸው ፊት በተኩስ ተገድለዋል። የዚህ ጥቃት አፈፃፀም የቤተሰቡ አባላት ሆን ተብሎ በግድያው መንገድ እንዲጎዱ አድርጓል።

ጥቃቱ የተካሄደው በጥቅምት 2024 በተካሄደው ሰላማዊ ምርጫ ምክንያት የጃምሙ እና ካሽሚር መደበኛ ሁኔታ ለማዳከም ነው። በተለይ፣ በኢኮኖሚው ዋና መሰረት ላይ፣ ቱሪዝም ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ታስቦ ነበር፣ ባለፈው አመት 23 ሚሊዮን ቱሪስቶች ጃምሙ እና ካሽሚርን ጎብኝተዋል። ስሌቱ፣ የሚገመተው፣ በዩኒየን ግዛት ውስጥ ያለውን እድገትና ልማት መጉዳቱ ወደ ኋላ እንዲቀር እና ከፓኪስታን ለሚመጣው ቀጣይ ድንበር ዘለል ሽብርተኝነት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል የሚል ነበር።

ወቅታዊ መረጃ፡ በሜይ 6-7 ምሽት ህንድ ምላሽ የመስጠት እና የማስወገድ እንዲሁም ተጨማሪ የድንበር ተሻጋሪ ጥቃቶችን ለመከላከል መብቷን ተጠቅማለች። እነዚህ ድርጊቶች ተለክተዋል፣ ያልተጋነኑ እና ተመጣጣኝ ነበሩ።

የሽብር መሰረተ ልማትን በማፍረስ እና ወደ ህንድ ሊላኩ የሚችሉ አሸባሪዎችን በማሰናከል ላይ አተኩረው ነበር። የህንድ አላማ ጉዳዩን ለማባባስ ሳይሆን እ.ኤ.አ. ኤፕሪል 22 ቀን 2025 ለተከሰቱት የአሸባሪዎች ጥቃቶች በተነጣጠሩ ፣በትክክለኛ ፣በቁጥጥር እና በተመዘኑ ጥቃቶች ምላሽ ለመስጠት ነበር እና በፓኪስታን ወታደራዊ መሠረተ ልማት ላይ ምንም አይነት ጥቃት አልደረሰም። ከህንድ ምላሽ በኋላ በፓኪስታን የአሸባሪዎች የቀብር ሥነ ሥርዓት የተከናወነው በፓኪስታን ባንዲራዎች የታሸጉ ሣጥኖች እና የመንግሥት ክብር እንደተሰጣቸው እና ፓኪስታን አሸባሪዎችን ለመሠረተ ፣ ለመምራት ፣ ለማስተማር እና ለማሰልጠን ሃይማኖታዊ ቦታዎችን እንደ ሽፋን እየተጠቀመች መሆኑን መጥቀስ ተገቢ ነው ።

ነገር ግን፣ እ.ኤ.አ ሜይ 25፣ እ.ኤ.አ. በሜይ 7-8፣ ፓኪስታን ግጭቱን በማባባስ በሲክ ማህበረሰብ እና በጃሙ እና ካሽሚር ግዛት ውስጥ ባሉ ክርስቲያኖች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመሰንዘር ጉርድዋራ (የአምልኮ ማእከል) እና የሲክ ማህበረሰብ አባላትን ቤቶችን ብቻ ሳይሆን የክርስቶስ ትምህርት ቤት እና የክርስቲያን ገዳም ሁለት የኑስ ልጆችን በመምታት አጸፋዊ ጥቃት አድርሷል። በዚህ ጥቃት በድምሩ 16 ንፁሃን ዜጎች ሲሞቱ 59 ሌሎች ቆስለዋል።

ፓኪስታን የህንድን ድንበር ተሻጋሪ ሽብርተኝነትን በማህበረሰብ ማዕዘኑ ለመሳል እየሞከረች ነው፣ ይህም በፓሃልጋም ጥቃቶች አሸባሪዎች ያደረጉትን ሃይማኖታዊ መገለጫ ይታወሳል። በህንድ ብቻ ሳይሆን በአለም ዙሪያ ከሁሉም እምነት የተውጣጡ ሁሉም ሀይማኖቶች እነዚህን ጥቃቶች በማያሻማ መልኩ አውግዘዋል።

እ.ኤ.አ ግንቦት  8-9 ምሽት ፓኪስታን የሕንድን የአየር ጠፈር ጥሳለች እና ከጃሙ እና ካሽሚር እስከ ጉጃራት ባለው የህንድ ምዕራባዊ ድንበር ላይ ወታደራዊ እና ሲቪል መሠረተ ልማቶችን ኢላማ በማድረግ በሚሳኤል እና በድሮኖች የአየር ጥቃትን ቀጥላለች። እነዚህ ጥቃቶች በህንድ ኪነቲክ እና ኪነቲክ ያልሆኑ የመከላከያ እርምጃዎችን በመጠቀም በተሳካ ሁኔታ ወድቀዋል።

የፓኪስታን የተጠናከረ የከባድ መሳሪያ ጥይት እና የአሸባሪዎች ሰርጎ መግባት ሙከራ በህንድ ጦር ድንበር ላይ ውጤታማ በሆነ መንገድ ከሽፏል።

የእነዚህ የፓኪስታን ሰው አልባ አውሮፕላኖች ፍርስራሽ እንደ መጀመሪያው የቴክኒካል ምርመራ ዘገባ፣ የቱርክ ተወላጅ የሆኑት አሲስጋርድ ሶንጋር ድሮኖች ተለይተዋል።

ፓኪስታን የአየር ክልሉ ቢዘጋም የሲቪል አይሮፕላኑን ከህንድ ጋር በሚያዋስነው ድንበር ላይ ሲበር እንደ መሸፈኛ አየተጠቀመች፣ በዚህም የንፁሀን ሲቪል ተሳፋሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ ጥሏል። የሕንድ ኃይሎች በዚህ የሚበር አይሮፕላን ላይ ጠንከር ያለ ምላሽ ባለመስጠት የቁጥጥር እርምጃዎችን በመውሰድ በኃላፊነት ስሜት ተንቀሳቅሰዋል።

ለፓኪስታን ሌላ የመስፋፋት ሙከራ ምላሽ ህንድ በላሆር እና በሌሎች ቦታዎች፣በፓኪስታን የአየር መከላከያ ራዳሮች ላይ የተሳካ እና የተለካ ጥቃቶችን አድርጋለች። ሁኔታው አሁንም እየተሻሻለ ነው እናም በየጊዜው መደበኛ መረጃዎች ይቀርባሉ።

@Addis_News
@Addis_News
"የባህር ፖሊስ አደራጅቻለሁ" ፌደራል ፖሊስ

የህዳሴ ግድብ ሰው ሠራሽ ሐይቅ አገልግሎት መስጠት ሲጀምር ጥበቃ የሚያደርግ የ “ባህር ፖሊስ” መደራጀቱን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

የህዳሴ ግድብ የሚይዘው የውሃ መጠን 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን የሚሸፍነው የቦታ ስፋት ደግሞ አንድ ሺህ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሆኑ ይታወቃል።

ይህንን ረጅምና ስፋት ያለውን ሰው ሠራሽ ሀይቅ ለመጠበቅ እና በአካባቢው ሊፈጸሙ የሚችሉ ወንጀሎችን አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል የፖሊሲ ኃይል ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ በፌዴራል ፖሊስ የኢንስፔክሽንና ስታንዳርድ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር እስከዳር ብርሃን መግለጻቸውን የፕሬስ ድርጅት በዘገባው አመላክቷል።

ከዚህ መነሻነትም የ“ባሕር ፖሊስ” ወይም “ኮስታል ፖሊስ ጋርድ” መቋቋሙን ገልጸዋል ያለው ዘገባው የባሕር ላይ ውንብድናን መከላከል የሚችል ኃይልን ከትጥቅ ጋር የማደራጀት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል ብሏል።

ይህ “ኮስታል ፖሊስ ጋርድ” ወይም የ“ባሕር ፖሊስ” ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን የተደራጀ መሆኑን ገልጸው፤ በቀጣይ ከመንግሥት በሚሰጠው ተልዕኮ መሠረት ሥራውን በብቃት እንደሚወጣ ተናግረዋል።

ባሳለፍነው አመት 2016 ዓ.ም የፌደራል ፖሊስ ለህዳሴ ግድብ እና ሌሎች የሀገሪቱ ሀይቆች ጥበቃ የሚውሉ ጀልባዎችን ላሰራ ነው ሲል ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል፤ ጀልባዎቹን የሚሰራቸው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን መሆኑንም በወቅቱ ጠቁሟል።


@Addis_News
@Addis_News
👨‍💼 እቤትዎ ሆነው ስራ መስራት ይፈልጋሉ?👍


⌛🖥 የኦንላይን ስራዎች የሚሰሩበት እና እንዲሁም የስራ ማስታወቂያዎችን የሚያገኙበት አሪፍ አፕልኬሽን፤ ባሉበት ቦታ ሆነው በስልኮ በቀላሉ የሚሰሩበት እና በየወሩ ተከፋይ የሚሆኑበት አፕ እናስተዋውቅዎ❗️

💥🎮በቀላሉ ከታች ባለው ሊንክ አፑን ዳውንሎድ በማድረግ መስራት እና መጠቀም ትችላላችሁ።


📱📱 DOWNLOAD ለማድረግ 📱📱
                🔽🔽🔽🔽       
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.habeshanjobs.habeshanjobs



⚡️ @Habeshan_Jobs_Com
⚡️ @Habeshan_Jobs_Com
⏰የ Linkedln Account የ ኪራይ አገልግሎት

📌 Rent out your  LinkedIn account to help corporate marketing, expand global markets, and acquire customers accurately!

Requirements:
❗️ Account must be at least 6 months old
❗️Minimum 200 connections
❗️No more than 20 connections on the last 3 days
🛎For all Accounts Advanced Payment 4$ within 24hr of login
✅100_200 connection _32$ monthly
✅200_499 connection _40$ monthly
✅500-999 connection _60$ monthly
✅1000+connection _80$ monthly
✅3000+ connections _100 Monthly
💴Payment Weekly Based
📌USDT_BINANCE, OKX,BYBIT
📌 ETB_LOCAL BANKS ,TELEBIRR
CONTACT💬 :@Rental_servicee
दिखाया गया 1 - 24 का 1 038
अधिक कार्यक्षमता अनलॉक करने के लिए लॉगिन करें।