✨✨✨በ'ነሱ ቤት✨✨✨
✨✨✨ክፍል አርባ አምስት✨✨✨
ደህነት ክፉ መሆኑን የምታውቀው ሀብታሞች በተሰበሰቡበት ቦታ ስትገኝ ነው ፣ አንተ ለለት ጉርስህ ስንት ቦታ ረግጠህ ጠብ የሚል ነገር አጥተህ ፣ሳትጠግብ ስለነገህ አስቀርተህ ፣ ይሁን እስኪን ተለማምደህ ስትኖር ። ድንገት በተረፈው ሰው ቤት ተገኝተህ የሚባክነውን ሁሉ ስታይ ደህነትህ ይበልጥ ይከፋሃል ውስጥ ያዝናል አንዳች እርግማን እንዳለብህ ይሰማሃል ,,,,,,, አንዳንድ የሞላለት ሰው ይቻላል ሲልህ ውስጥህን ያነቃቃውና የመስራት የማግኘት ጉጉት ያድርብሃል እናም የነጋዴነት ችሎታው ሳይኖርህ ነጋዴ ለመሆን ትፍጨረጨራለህ ፣እንደተባለው ከትንሽ ተነስተህ ነው ትልቅ ቦታ የምትደርሰው እያልክ ለራስህ እየነገርክ መጣር ትጀምራለህ ትለፋለህ ትደክማለህ ነገርግን በትንሹ እንኳ በጀመርካት ንግድ ላይ ከላይ ታች አባራሪ ያዝብሃል ቀና እንዳትል የሚያደርግህ ቀበሌ ...ወረዳ...ክፍለ ከተማ.....ከስር ከስርህ እየተከተሉ ይገፈትሩሃል ምን ያክል ትቋቋማለህ ?እንጃ ጉሊት ነግደህ ንግድ ፍቃድ አውጣ ትባላለህ ...እሺ ብለህ ስታወጣ የምታገኘው ሌላ ግብሩ ሌላ .....እና ገፍተው ገፍተው ባፍጢምህ ይጥሉሃል ኪኪኪኪ,,,,
,,,,,የአብላካት እናት እዛ የሃብታም ቤት ውስጥ የሚከናወነውን ሁኔታ ሁሉ በትዝብት እያየች የራሷን ችግር እያስታወሰች አምላኳን ትሞግታለች ለለት ጉርሳቸው ሲሉ ከላይ ታች በየመንገዱ ጋሪ እየገፉ ከደንቦች ጋር እየተሯሯጡ ኑሯቸውን የሚገፉትን የስራ ባልደረቦቿን አስታወሰች ፣ የቤትክራይ መክፈል አቅቷቸው ሲጨነቁ ....የአስቤዛው ዋጋ ጣራ ነክቶ አንዱን ስለው አንዱ በሚል ሲወጠሩ .......
እዚ ደሞ ገንዘቤን ምን ላድርገው ባሉ አብታሞች ተከባ በውድ አልባሳት ባሸበረቁ ሴቶች እና ወንዶች መሃል ሆና ምግቡ መጠጡ ሲባክኑ በአይኗ እያየች ነው ፣ሕይወት እንዲ ናት እንግዲ,,,,,,,,,,,,,
፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"ሚጣ እባክሽ ለኔ የሚሆን ጊዜ አለሽ?"አላት ሰመረ አብላካትን ጠጋ ብሎ ።አብላካት ፊቷ በራ ይበልጥ አማረባት ዞር ብላ አይታው
"ሚጣ አይደለሁም ስንቴ ነው የምናገረው አቡሽ አብ ላካት ማለት ያን ያክል ይከብዳል ?"አለችው
"እሺ የኔ ውድ አንዴ ከግር ግሩ እንውጣ "አላት እጇን ያዝ አድርጎ ፣
"እሺ ምን ልታደርገኝ እንደሆን እናያለን "አለችው በፈገግታ ፣ሰመረ እጇን እንደያዘ ሲሄድ ፣አስተናጋጁ ሰሚር አይቶት ፈገግ አለለት ፣ሰመረም አስተናጋጁ ሰሚር ከአንዲ ጠይም ወጣት ጋር ሲያወራ ስለነበር አበጀህ በሚል ጠቀሰው ።
፨፨፨፨፨
አብላካትን ከግርግሩ ካራቃት በዋላ ፣እንዴት እንደሚያወራ ግራ ገብቶት ፈዞ ቀረ ፣አብላካት አይኖቹን በፍቅር አይን እያየችው እንዲያወራ ጠበቀችው ፣ሰመረ ግን አይኖቿን በስስት ማየቱን ቀጠለ ፣ አብላካት የተረዳችው ይመስል
"ሰሙ ይገባኛል ለኔ አሁንም ድረስ የሚሰማህ ስሜት አስፈርቶሃል ነገር ግን መጨናነቅ መፍትሔ አይሆንም በቃ የሚሆነው ነው የሚሆነው ንገረኝ ..."አለችው
"አይ አይ እኔ በቃ ከየት እንደምጀምር ግራ ስለገባኝ ነው ማለት አሁን ላይ አይሆንም ይሆናል በሚል አሳብ እራሴን የምጠምድበት ጊዜ አልፏል ፣ልቤንም በትክክል አዳምጬዋለው በቃ አንቺ የኔ ሰላም ነሽ ካጣውሽ እደክማለው ፣ የፈገግታዬ ምንጭ ሆነሻል ፣የሚጨንቀኝ ስሜቴን ላንቺ የምገልፅበት መንገድ በቂ ይሁን አይሁን አለማወቄ ነው ፣ምን ያክል ባወራ ውስጤን ላንቺ ያለኝን ፍቅር ይገልፀዋል የሚል ፍራቻ ብቻ ነው........."
"ሰሙ የኔ ፍቅር በጣም በጣም ነው የማፈቅርህ ከቃል በላይ አይኖችህና ድርጊትህ ለኔ ያለህን ፍቅር እና አክብሮት ይገልፅልኛል መቸገር የለብህም"አለችው ሁለቱንም እጆቹን ያዝ አድርጋ ።ሰመረ የተለየ ሙቀት በሰራ አከላቱ ሲዘዋወር ተሰማው ፣እናም የአብላካትን እንጆሪ የመሰለ ከንፈር በስሜት ታጅቦ ተጣበቀባቸው ፣ አብላካት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳመው ከንፈሯ ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍሯ አንዳች መልህክት አስተላለፈባት ከንፈሮቿ ተርበተበቱ .... ውስጧ በደስታ ጮቤ እረገጠ ፣ስለ ዓለም የሚሰማት አስቀያሚ ስሜት ሁሉ ከላይዋ ተገፎ የወረደ መሰላት ዓለም አብራት በስሜት በፍቅር በሰላም በደስታ የተወዘወዘች መሰላት መሰላት በፍቅር የተነሳ በፍቅር የተነሳ,*
*******,,,,,,,ተፈፀመ,,,,,,****************
✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19