tapswap community
tapswap community
Notcoin Community
Notcoin Community
Whale Chanel
Whale Chanel
tapswap community
tapswap community
Notcoin Community
Notcoin Community
Whale Chanel
Whale Chanel
Big Habesha Tech avatar
Big Habesha Tech
Big Habesha Tech avatar
Big Habesha Tech
Appleና Google የሶስተኛ ወገን መተግበሪያ ማከማቻዎችን (3rd Party app stores) እንዲፈቅዱ የሚያስገድድ ህግ ሊወጣ ነው።

App Store Freedom Act የተሰኘው ይህ ረቂቅ ህግ በአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አባል ካት ካምማክ የተቀረፀ ሲሆን The Verge ባወጣው ዘገባ መሰረት "በሞባይል መተግበሪያ የገበያ ቦታ ላይ የአፕሊኬሽን ተጠቃሚዎችና እና ደቨሎፐሮችን ለመጠበቅ እና ፍትሃዊ ውድድርን እንዲኖር ያለመ ህግ ነው ተብሏል።

እንደሚታወቀው Google ከተወሰኑ 3rd party አፕሊኬሽኖች (Amazon Appstore, Galaxy Store, F-Droid) በስተቀር ሌሎች አፕሊኬሽን ስቶሮችን Play store ላይ እንዲጫኑ አይፈቅድም።

Apple ደግሞ ምንም አይነት application store አፕስቶር ላይ እንዲኖር አይፈቅድም። ይህ አሰራርም ለዘመናት ተጠቃሚዎችና ዴቨሎፐሮች የPlay storeና App store ጥገኛ ሆነው ቆይተዋል።
ይህ አሰራር ፍትሃዊ የንግድ ውድድር አያመጣም በማለት ነው አሜሪካ ይህን ህግ እያረቀቀች ያለችው።

ይህ ህግ ከጸደቀ ማንኛውም ዴቨሎፐር የራሱን አፕሊኬችን ስቶር በመስራት play store ወይም app store ላይ መልቀቅ ይችላል።

Googleና Apple ይህን ህግ ተግባራዊ ካላደረጉ በሚጥሱት የህግ ብዛት እስከ 1ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል።

ተመሳሳይ ህግ በ2023 በአውሮፓ ህብረት እንደፀደቀ ይታወቃል። በአውሮፓ ህብረት የዲጂታል ማርኬት ህግ መሰረት Apple ተጠቃሚዎች የፈለጉትን የሶስተኛ ወገን መተግበሪያ ማከማቻዎችን እንዲጭኑና እንዲያወርዱ እንዲሁም default application store ማድረግ እንዲችሉ እንዲፈቅድ ግዴታ ተጥሎበት ነበር። ይህን ህግ በመከተል Google አውሮፓ ውስጥ ተጠቃሚዎች የፈለጉትን store እንዲጠቀሙ የሚያስመርጥ ምርጫ ይሰጣቸዋል።

@bighabesha_softwares
06.05.202521:23
እስኪ Champions league እያየ ያለ.....👌
እንኳን ለ84ኛው የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ!

🙏 ክብርና ምስጋና በዱር በገደል ወድቀው ውድ አገራችንን ላቆዩልን አርበኞች!

በዓሉን ምክንያት በማድረግ በአራቱም አቅጣጫ ስለ ኢትዮጵያውያን አርበኞች ገድል የሚተርከውን የሀበሻ ጀብዱ መፅሀፍ pdf ከታች አያይዘንላችኋል።

በዚህ link ገብታችሁ አውርዱት
https://t.me/big_habesha/291
የቴሌግራም አካውንታችንን እንዴት እስከ ወዲያኛው delete ማድረግ እንችላለን?

በመጀመሪያ ወደ https://my.telegram.org/auth እንሄዳለን ከዚያም delete ማድረግ የፈለግነውን አካውንት ስልክ ቁጥር ካስገባን ቡኋላ በቴሌግራም የሚላክልንን ኮድ እናስገባለን።
ከዚያም delete account የሚለውን መርጠን delete ማድረግ እንችላለን።

ማሳሰቢያ፦ አንዴ አካውንቱ ከጠፋ እንደ ፎቶዎች፣ቻናሎች፣ግሩፖች፣ቻቶች እና የመሳሰሉ መረጃዎች አብረው የሚጠፉ ይሆናል።

©bighabesha_softwares
Telegram_Update

ቴሌግራማችሁን update አድርጉት አዳዲስ ፊቸሮች ተጨምረዋል።

Group call
ከዘህ በፊት ከ2 በላይ Group call ለማድረግ የግድ Group create ማድረግ ግዴታ ነበር። አሁን ግን Group create ማድረግ አይጠበቅብንም። አንድ ለአንድ እያወራን ሌሎች ሰዎችን add ማድረግ እንችላለን።

How to start a group call
From an existing call. Just call anyone on Telegram, then tap the 'Add Person' button in the top right corner of your screen — and you're all set.
From the Calls Tab. Open your Calls Tab (you may need to enable it via Settings > Recent Calls), then tap New Call and select multiple people to call.
Using a link. In the Calls Tab, tap New Call, then select New Call Link.

Automated Business Accounts
Telegram premium ተጠቃሚዎች በTelegram business feature ላይ 3rd party chatbot በጨመር ይችላሉ።
እነዚህ ቦቶች message automatically መመለስ ይችላሉ፤ profile manage ማድረግ ይችላሉ፤ gift & star manage ማድረግ ይችላሉ፤ story manage ማድረግ ይችላሉ። ከ10 በላይ automated ተግባሮችን መፈጸም ይችላሉ።

Easily share
የቻናል post ላይ የshare ቀስቷን ጫን አድርጎ በመያዝ ለሰዎች ወይም ለራሳችን በቀላሉ share ማድረግ እንችላለን።

Frozen account
contact ላይ save ላላደረጋችሁት ሰዎች በተደጋጋሚ spam message የምትልኩ ከሆነ፤ ወይም በአካውንታችሁ scam የምታደርጉ ከሆነ አካውንታችሁ freeze ሊደረግ ይችላል። freeze ከተደረገ message መላክ አትችሉም፣ groupና ቻናል ላይ መፃፍ አትችሉም። Read-only mode ስለሚሆን ማንበብና ማየት እንጂ ምንም አይነት ሌሎች ተግባሮችን መፈጸም አትችሉም።
Appeal ማድረግ ግን ትችላላችሁ።

በመጨረሻም Telegram ይህን ብለዋል።
"We welcome security researchers to study the detailed documentation and open source code that powers the new group calls. For more than 10 years, Telegram has offered over $100,000 to anyone who could crack its encryption protocol — and no one has ever succeeded."😂😂
TikTok አዳዲስ አፕዴቶችን ለቋል።
⚫ እስከ 1 ሰአት የሚረዝም Video post ማድረግ ይቻላል።
⚫ Comment መስጫው ላይ ፎቶ ማካተት ተችሏል።
⚫ TikTok built-in video editor ላይ ብዙ ነገሮች ተካተዋል።
⚫ ማንኛውንም ፎቷችሁን ወይም ፕሮፋይላችሁ edit የምታደርጉበት የAI feature ተካቷል።
⚫ TikTok በኤርፎን እያያችሁ ኤርፎኑን ሳትነቅሉ ድምጹን በbackground ማጫወት ትችላላችሁ።
ይህን ለማድረግ
"የምታዩትን Video ጫን አድርጎ መያዝ ከዛ Background audio የሚለውን መምረጥ"
YouTube የአማርኛ Subtitle ጀምሯል።

Almost perfect ነው። ነገር ግን የሚሰራው ከ2 ወር በኋላ post በተደረጉ ቪዲዮዎች ላይ ነው። ከዛ በፊት ባሉ ቪዲዮዎች ላይ አይሰራም።

Check አድርጉት።
Openai እጅግ realistic የሆኑ ቪዲዬዎችን generate የሚያደርገውን Sora ለሙከራ ይፋ አድርጓል።

ነገር ግን መሞከር የሚችሉት chatGPT plus ተጠቃሚዎች ብቻ ናቸው።

መሞከር የሚቻለውም በድረገፅ chatgpt.com ላይ Sora የሚል የተካተተ ሲሆን ለMobile application ገና ይፋ አልተደረገም።

የተሰሩ አስገራሚ ቪዲዬዎችን ማየት ከፈለጋችሁ
https://sora.chatgpt.com/explore/videos
Telegram አካውንት የፈትንበትን ሲም እንዴት መቀየር እንችላለን?

ቴሌግራም አካውንታችን በድሮ አልያም በጠፋ ሲም ላይ ከሆነ የተከፈተው እና በተለያዩ ምክነያቶች ወደ ሌላ ቁጥር ማስተላለፍ ብንፈልግ በቀላሉ እነዚህ ሂደቶች በመከተል መቀየር እንችላለን።

በመጀመሪያ ወደ ቴሌግራም setting በመሄድ ከላይ ያሉትን ሶስት ሰረዞች ነክተን log out የሚለውን እንመርጣለን።

በመቀጠልም ከሚመጡልን ምርጫዎች መካከል change phone number የሚለውን እንመርጣለን።

በመጨረሻም መቀየር የምንፈልገውን አዲሱን ስልክ ቁጥር አስገብተን verify ማድረግ።
ነገር ግን አካውንቱን የምታስተላልፉለት ስልክ ቁጥር የቴሌግራም አካውንት ያልተከፈተበት መሆን አለበት። ቴሌግራም አካውንት ከተከፈተበት መጀመርያ delete ማድረግ ይኖርባችኋል።

©bighabesha_softwares
02.05.202512:33
Video editor እና graphics designer ከሆናችሁ እነዚህን ድረገፆች ጎብኟቸው። (part 1)

Font ለማውረድ
You got it — here’s a refined list of 100% free font download sites (no trials, no traps):
fonts.google.com
dafont.com
fontsquirrel.com
1001fonts.com
fontspace.com
fontesk.com
fontsarena.com
velvetyne.fr
collletttivo.it

የተለያዩ icons ለማውረድ
flaticon.com
icons8.com
material.io/resources/icons
iconmonstr.com
heroicons.com
bootstrapicons.com
remixicon.com
feathericons.com
css.gg
boxicons.com
eva.design/icons
tabler.io/icons እነዚህን ድረገፆች በመተጠቀም የተለያዩ animated የሆኑና ያልሆኑ icons በSVG እና በPNG format ማውረድ ትችላላችሁ።

©bighabesha_softwares
በ1 አመት ውስጥ Google Play ላይ የሚጫኑት አፕሊኬሽኖች በግማሽ መቀነሳቸው ተሰማ።

ከ2024 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ Goole play ላይ የተጫኑት አፖች ብዛት ከ3.4 ሚሊዮን ወደ 1.6 ሚሊዮን አፖች ዝቅ ማለታቸውን Google አስታውቋል። ከዚህ በፊት ከነበረው ቁጥር በ47% ቅናሽ አሳይቷል።

ይህ የሆነበት ምክንያትም Google ተግባራዊ ባደረገው ከፍተኛ ቁጥጥር ምክንያት እንደሆነ ተገልጿል። Spammy, Scammy እና ዝቅተኛ ጥራት ያላቸው አፖች እንዳይጫኑ ከልክሏል። ጥራት ያላቸው አፖችን ለሚሰሩ ዲቨሎፐሮች ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረም ታውቋል። ምክንያቱም አፖቻቸው በቀላሉ Google Play ላይ መታየት ስለሚችሉ።

ባለፉት አመታት Google Play መተግበሪያዎችን የሚገመግምበት መስፈርት ዝቅተኛ ስለነበር ገበያው ዝቅተኛ ጥራት ባላቸው መተግበሪያዎች እንዲጨናነቅ አድርጓል። በአንጻሩ Apple አፕስቶር ላይ የሚወጡ መተግበሪያዎች ጥብቅ የመተግበሪያ ግምገማ እርምጃዎችን ስለሚከተል ጥራት ያላቸው አፖችን በማውረድ ተጠቃሚዎች ከplaystore ይልቅ በapp store ደስተኞች ነበሩ።
በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የገበያ ብልጫ ተወስዶበት እንደነበር ይታወቃል። ለዚህ ነው ከብዛት ጥራት ይሻላል በማለት Google ይህን አሰራር የጀመረው።
የGoole አካውንታችሁ full ሆኖ Gmail መላክም መቀበልና ካልቻላችሁ
incognito mode

Incognito mode ብራውዘሮች የኛን እንደ History, site data እና cookies ያሉ መረጃዎችን save ሳያደርጉ ብራውዝ ማድረግ የሚያስችለን feature ነው።

Incognito mode ላይ የከፈትነው ማንኛውም ታብ አንዴ ከዘጋነው በኋላ የዛ ታብ መረጃ አብሮ የሚጠፋ ይሆናል። ይህም እኛ የከፈትነውን ድረገፅ ሌላ ሰው ሌላ ጊዜ ለመክፈት አይችልም።

Incognito mode privately browse ማድረግ ከማስቻሉም በላይ በርካታ ድረገፆች ላይ sign in አድርገን ተጠቅመን ስንጨርስ በራሱ sign out ያደርግልናል።

chrome browser ከሆነ የምትጠቀመት Incognito tab ለመክፈት በስልካችሁ ጥግ ጋር ያለውን ሶስት ነጥብጣብ ከነካችሁ በኋላ New Incognito tab የሚለውን መጫን። እንዲሁም በዴስክቶፕ ከሆነ የምትጠቀሙት በቀላሉ Ctrl + Shift + N (mac ተጠቃሚዎች በctlr ቦታ cmd ተጠቀሙ) በመንካት Incognito tab መክፈት ትችላላችሁ።

ነገር ግን Incognito tab ከፍታችሁ ድረገፅ በምትጠቀሙበት ጊዜ ድረገጾች፣ Internet Service providers እና የመሳሰሉት የናንተን መረጃ ሊመለከቱ ይችላሉ።

©bighabesha_softwares
#Skype

አንጋፋው የቪድዮ መደዋወያ ፕላትፎርም Skype ዛሬ ተዘጋ። ተጠቃሚዎችም ቻቶቻቸውን ወደ teams ወደተሰኘው ፕላትፎርም ማዘዋወር ይችላሉ ተብሏል።
የቻይና ግዙፉ የሀይል ማመንጫ Three Gorges dam የምድርን ሽክርክሪት እየቀነስ እንደሆነ ተነገረ።

የNASA ሳይንቲስቶች የቻይና ግዙፉ የሀይድሮ ኤልክትሪክ ሀይል ማመንጫ ግድብ (Three Gorges dam) የምድራችን አክሲስ በ2 ሴንቲ ሜትር ሽፍት እንዳደረገ አረጋግጠናል ብለዋል።

ይህም የቀኑን ርዝመት በ0.06 ማይክሮ ሰከንድ እንዲጨምር አድርጎታል።

ይህ ትልቅ የኃይል ማመንጫ በአመት 80 ሚሊዮን የሚጠጉ ቤቶችን ያለማቆራረጥ ሀይል የሚሰጥ ሲሆን ከአዲስ አበባ ባህርዳር የሚሆን ቦታ ይሸፈናል።
እኔ የምለው Guys ስለ Telegram username የማያቅ ሰው አለ እንዴ?
⚫ጥቅሙ ምን እንደሆነ?
⚫እንዴት set ማድረግ እንደምንችል
⚫እንዴት የሰው username ማየት እንደሚቻል።

⚫Username ሳታዩ ለምድን ነው ገንዘብ transfer የምታደርጉት?
⚫ሲቀጥል እኔ ማንንም ቢሆን ቀድሜ contact አላደርግም።
✔️የኔ username @bighabesha ብቻ ነው።

እራሳችሁ ተበልታችሁ መጥታችሁ እኔን አታዝጉኝ።
ስንት አይነት ሰው አለ በመድሐኒያለም🙈
29.04.202517:43
የmedicine ተማሪ ከሆናችሁ እንዚህ ድረገፆች ይጠቅማችኋል።

www.osmosis.org የተለያዩ ከትምህርቱ ጋር የተገናኙ animation ቪድዮዎች የምታገኙበት ሲሆን ስለምትማሯቸው ነገሮች በደንብ መረዳት ያስችላችኋል።

lecturio.com ከphysiology እስከ pharmacology cover የሚያደርጉ video lectures ታገኙበታላችሁ።

kenhub.com የmed ዕውቀታችሁን የሚጨምሩ ጥያቄዎች፣ አጫጭር ኖቶች እና Articles የምታገኙበት ደረገፅ ነው።

pubmed.ncbi.nlm.nih.gov/ የተለያዩ የmedical ጥናታዊ ፅሁፎች የሚቀርቡበት ሲሆን ይህም med ነክ ስለለሆኑ ነገረሮች የተብራራ መረጃ ማግኘት ያስችለናል።

medscape.com/ ስለ መድሀኒቶች እና ስለተለያዩ med ነክ የሆኑ መረጃዎች ዕውቀት የምትቀስሙበት ደረገፅ ነው።

©bighabesha_softwares
27.04.202505:24
Best telegram bots (part 3)

@ImajpgXD_Bot እስከ 100 mb ድረስ ያሉ ፋይሎችን ወደሊንክ የሚቀይርላችሁ bot ሲሆን ይህም አነሰዳንድ ነገሮችን በፍጥነትና በቀላሉ መላላክ ያስችላችኋል።

@aliexpress_discounts_robot ከaliexpress እቃ ስትገዙ ቅናሹን መፈለግ አድካሚ ስራ ነው ታዲያ ለዚህ የቴሌግራም bot የምትገዙትን ዕቃ ሊንክ ከላካችሁለት በኋላ ቅናሹን ተመሳሳይ ዕቃ ፈልጎ ሊንኩን ይልክላችኋል። ነገርግን እናንተም check አድርጉ!

@OCRFather_Robot ከቴሌግራም ሳትወጡ ፎቶላይ ያለን ፅሁፍ ወደ እውነተኛ ፅሁፍ የሚቀይር telegram bot ነው።

@StylishFontMakerBot አንድን ፅሁፍ ከ30 በላይ ወደሆኑ ፎንቶች መቀየር የሚያስችላችሁ bot ነው።

@flaguessbot የሀገራትን ባንዲራ እና ዋና ከተማዎችን የምትጠየቁበት bot ሲሆን ብቻችሁንም ሆነ ከጓደኛችሁ ጋር መጫወት ትችላላችሁ።

የትኛው ተመቻችሁ
©bighabesha_softwares
What a game!!!!!
⚫ተስፋ አለመቁረጥ
⚫እልህ
⚫ጀግንነት
⚫የግል ብቃት
⚫የቡድን ጥራት
ያየንበት ምርጥ ጨዋታ

እግር ኳስ ብዙ ነገር ያስተምረናል።

ደና እደሩ
16personalities.com

ይህ ድረገፅ የpersonality test ድረገፅ ሲሆን እኛን በርካታ መሰረታዊ ጥያቄዎችን ከጠየቀን በኋላ ስለኛ personality ተቀራራቢ የሆነ መረጃ ያቀርብልናል።

የሚጠይቀንም ጥያቄዎች ከስራ እና ከለትተለት ኑሯችን ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ሲሆን ስለኛ ስምም ሆነ ሌሎች መረጃዎች ጥያቄ አያነሳብንም።

የpersonality ውጤቱም እንደ አጠቃላይ የኛ personality ሁኔታ፣ ድክመቶቻችን፣ ጥንካሬዎቻችን፣ ከኛ ጋር ሊሄዱ የሚችሉ የስራ መስኮችን፣ ሊያነሳሱን የሚችሉ ነገሮች የመሳሰሉትን ይነግረናል።

Check አድርጋችሁ ውጤታችሁን በcomment አሳውቁን።
©bighabesha_softwares
እኔ የምላችሁ Guys ስልክ ሀገራችን ከመግባቱ በፊት ግን እንዴት ነበር ሰዎች ተቀጣጥረው የሚገናኙት?🤔

እኛ አብዛኛዎቻችን በጊዜው ህጻናት ስለነበርን የሰፈር ጓደኞቻንን ቤት ሄደን እንጠራለን። በዘመኑ ትልልቅ የነበሩ ሰዎች ግን እንዴት ነው የሚቀጣጠሩት? ዘመድ መጠየቅ ሲፈልጉ ምናምን እንዴት ነው ቀድመው የሚነግሯቸው? ወይስ ዝም ብለው ከች ብለው surprise ያደርጋቸዋል?

ሰው ሲሞት ወይ ልጅ ሲወለድ እንዴት ነው ሩቅ ሀገር ያለ ሰዉ የሚሰማው?

✍እስኪ በዚህ ዙሪያ የምታስታውሱት ትዝታ ካለ አካፍሉን።
እኔ በህፃንነቴ የማስታውሰው አንድ ጎረቤታችን ጦርነት የሄደ ልጃቸው (ethio-ertria) ደብዳቤ ላከ ተብሎ ድግስ ተደግሶ የሰፈሩ ሰዉ ተጠርቶ ሲበላ ትዝ ይለኛል።

አንድን ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ሳንጨርስ ሌላው እየመጣ ቴክኖሎጂ ምን ያክል ህይወታችንን እንዳቀለለው ራሱ እረስተነዋል።
http://info.cern.ch/

ይህ ድረገፅ በአለማችን የመጀመሪያው ድረገፅ ሲሆን በ1991 በወርሀ April ነበር የተፈጠረው።

ይህም ድረገፅ በውስጡ ስለ WWW (world wide web) አንዳንድ መረጃዎችን አካቷል። እስካሁንም ድረስ አገልግሎቱ አልተቋረጠም።

ከዚህ በፊት ታውቁት ነበር?
©bighabesha_softwares
Instagram የራሱን የቪድዮ ኢዲት ማድረጊያ መተግበሪያ አስተዋወቀ።

Instagram "Edits" ሲል የሰየመውን የediting መተግበሪያ ከቀናት በፊት አስተዋውቋል። ይህም ከቲክቶኩ የኢዲቲንግ መተግበሪያ Capcut ጋር በርካታ ተመሳሳይ features አሉት።

ይህ መተግበሪያ በAI የተደገፉ tools ስላሉት ለcontent creators ስራ አቅላይ ነውም ተብሏል።

አሁን ላይ ያን ያህል ከሌሎች የኢዲቲንግ መተግበሪያዎች ጋር መፎካከር የሚያስችለው features ባይኖሩትም ወደፊት ጥሩ features/አገልግሎቶች እንደሚያካትትም ተገልጿል።

መተግበሪያውን ከplay store ለማውረድ edits
©bighabesha_softwares
ስልካችሁን በመጠቀም መማር ከፈለጋችሁ ሊኖሯችሁ የሚገቡ መተግበሪያዎች።

Douligo እንደ እንግሊዝኛ፣ ፈረንሳይኛ ፣ አረብኛ ያሉ በርካታ ቋንቋዎችን ቀላል በሆነ መንገድ መማር ያስችለናል። እንዲሁም ብዙ የውደድር መድረክ ስላለው ይበልጥ አንድንማር ይገፋፋናል።

Brilliant የሒሳብ እና የሳይንስ ወዳጅ ከሆናችሁ ይህ መተግበሪያ በጣም ይጠቅማችኋል። (በተለይ ወደፊት ኢንጂነር መሆን የምትፈልጉ አውርዱት።)

sololearn coding ጀማሪ ከሆናችሁ እንደ Python,C++,Java ያሉ programming languages በቀላሉና ለጀማሪ በሚመጥን መንገድ መማር ትችላላችሁ።

Notion ምንም እንኳን የመማሪያ ፕላትፎርም ባይሆንም የትምህርት ፕሮግራማችንን እዚህ ላይ አሰናድተን የምንማራቸው ነገሮች ላዮ ይበልጥ ውጤታማ እንድንሆን ይረዳናል።

Quora የጥያቄ እና መልስ ፕላትፎርም ሲሆን እናንተም ማንኛውም የሰዎችን መልስ የሚሽ ጥያቄ መጠየቅ ትችላላችሁ። ከዚህ በፊት የተጠየቁትን ጥያቄወዎች በመመልከትም ዕውቀት መቅሰም ትችላላችሁ።

©bighabesha _softwares
दिखाया गया 1 - 24 का 109
अधिक कार्यक्षमता अनलॉक करने के लिए लॉगिन करें।