Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк

የ-ትብለጥ ግራኝ ሳቢር

TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateNov 11, 2022
Added to TGlist
Apr 27, 2025
Linked chat

Statistic of Telegram Channel የ-ትብለጥ ግራኝ ሳቢር

Subscribers

295

24 hours
1
0.3%Week
7
2.3%Month
24
8.9%

Citation index

0

Mentions0Shares on channels0Mentions on channels0

Average views per post

0

12 hours00%24 hours00%48 hours860%

Engagement rate (ER)

0%

Reposts0Comments0Reactions0

Engagement rate by reach (ERR)

0%

24 hours0%Week
0.28%
Month0%

Average views per ad post

0

1 hour00%1 – 4 hours00%4 - 24 hours00%
Connect our bot to the channel to find out the gender distribution of this channel's audience.
Total posts in 24 hours
0
Dynamic
-

Latest posts in group "የ-ትብለጥ ግራኝ ሳቢር"

ህፃናት ገና ት/ቤት ገብተው መማር ሲጀምሩ የመጀመሪያው ትምህርት ነጠብጣቦችን አገጣጥሞ ትክክለኛውን ፊደል ከዛ ከፍ ሲል ደግሞ ቃላትን መስራት ነው (ትሬስ ማድረግ)

እኔም እንደዛ አንዳንድ ጊዜ "ሀ" ብዬ - በህይወቴ ወደ ልጅነት ተመልሼ በእርምጃዎቼ መሀል ያሉትን ክፍተቶች ሞልቼ ጥርት ያለውን ምስሌን ልፈጥር ያምረኛል፡፡ በዛ መጠን ቀላል ቢሆንልኝ ኖሮ፡፡

ከእርምጃዎቼ መሀል....ላጠራ ያልቻልኩትን ያውቁልኝ ዘንድ እሄድ ነበር፡፡

"እሺ ትብለጥ እንዴት ነሽ?"
"ደህና ነኝ ዶክተር"
"ቆየሽ ከመጣሽ እንዴ ብዙ ቆየሽ?"
"አይ ብዙ አይደለም"

ስጋዬ አሁን ላይ ቢሆንም ሀሳቤ ትናንት ላይ ነበር፡፡ ማክሰኞ እና አርብ ከት/ቤት መልስ አባቴ ሰፈሮችን እያስጠናኝ፣ በየመሀሉ ፍዝዝ ስል መሪ ባልያዘ እጁ እየኮረኮረ እያሳቀኝ "ደስ ብሎሻል?" እያለ በተደጋጋሚ የሚጠይቀኝ ዶክተር ጋር ይወስደኝ ነበር፡፡

"ትብለጥዬ"
"......"(ሁሌም በማላውቃቸው ሰዎች ስጠራ አቤት አልልም)
"ይኼ ስንት ቁጥር ነው?"
"አምስት"
"ጎበዝ" (አይደንቀኝም ነበር)

(በአስር እና በሀያ ስምንት ዕድሜ ያለ የእኔ አንድ ዓይነት መሆን)

ለእኔ ቢሆንልኝ ኖሮ መደነቅ እነ መምህር "ደ" የክፍል ጓደኞቼን እንደሚስሟቸው ቢስሙኝ፣ እኔን ሲያዩ ቢስቁልኝ፣ በመኖሬ ባይማረሩ እንጂ እዚህ ዶክተር ጋር መመላለስ አልነበረም፡፡ የእሱ ፈገግታ ለደቂቃዎች ለማገኘው ሁኔታ እንጂ ወጥቼ ስለምጋፈጠው የመምህራኖቼ ሁኔታ ዋስትና አይሆነኝም ነበር፡፡ ለዛ ግን ጎበዝ ተማሪ ሆኜ ቀብድ መክፈል ነበረብኝ!!!

የሚወዷት ዓይነት ተማሪ አልነበርኩም፡፡ ቤት ደረጃ ላይ ቁጭ ብዬ ከመተከዝ ለመትረፍ ት/ቤት ልውደድ እንጂ ትምህርት አልወድም ነበር፡፡ መምህራኖቼም የዕለቱን ዕቅዳቸውን አሰርተው ከመውጣት እና ላልሰራሁት ከመውቀስ እና ከመምታት ውጪ አስበውኝ አያውቁም ነበር፡፡ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት ሳመጣ ትናንቴን እያጣቀሱ "ያኔ ዋንጫ ተሸላሚ እንዳልነበርሽ ዛሬ እንዲህ የማትረቢ ትሆኚ?" ከማለት ውጪ ምንም ያሰቡት ነገር አልነበራቸውም፡፡

"መቼ ነው ሰው የምትሆኚው?" የሚለውም ጥያቄያቸው ብቻዬን እጅ አውጥቼ ባልመረጡኝ ሰዓት ከሚሰማኝ "መቼ ነው የምወደድ ሰው የምሆነው?" ከሚለው ጥያቄዬ በላይ ዋጋ አልነበረውም

መልካምነት ላይ ከመድረስ በፊት መልካምም መጥፎም አለመሆን ይቻላል አይደል? እኔ ግን መለስ ብዬ ሳስብ ስለምጠላው ስሜም መልኬም ተጠያቂዎቹ መምህራኖቼ ነበሩ፡፡

"ትብለጥ...ምን አንቺ ትብለጥ ነሽ ትነስ ነሽ እንጂ" (ልጅነት ሞኙ አሜን ብሎ ይቀበላል)
"ግራኝ...አይሻልሽም ቀኝ" እያሉ በቃረሙት ሳቅ ለብዙ ዓመታት ከስሜ አፋቱኝ፡፡
"ነጫጩባ" እያሉ ለሰደቡት መልኬ ብዙ ዓመታትን ሰው ከማየት አሸማቀውኝ ነበር፡፡

ዛሬ ላይ ብድግ ብዬ ለራሴ ከንፈር እንዳልመጥ የሚያደርገኝ ምክንያት ደህና መሆኔ ነው፡ እናም እኔን የመታኝ ሁሉ ልጆቼን አለመንካቱ፡፡

የመጣልኝን እንዳልሳደብ፣ እንደመጣልኝ እንዳልረግጣቸው፣ እንደተሰማኝ ከክፍል ውጡልኝ የማልልበት በቂ ምክንያቴ ሰው መሆናቸው ነው፡፡ሲያጠፉም ሰዎች ናቸው፣ ዜሮም ሲያመጡ ሰዎች ናቸው፣ ሲደፍኑም ሰዎች ናቸው፣ ሲረሱም ሰዎች ናቸው፣ ሲያስታውሱም እንደዛው፡፡

ትንሽ ለሰሩት ስህተት ሀገር ያጠፉ ይመስል ይኼ ሁሉ ውርጅብኝ ማውረድ፣ የቤት ስራ አልሰራህም አልሰራሽም ብሎ በተማሪ ፊት ማሸማቀቅ፣ መግረፍ ቀርቶ መደብደብ፣ የኑሮን መከራ በልጆች መወጣት ክፉነት ነው፡፡

እንደ መምህርም፣ እንደወላጅም ዛሬ በምናወጣው አንድ ቃል እና ጉልበት የሰውን ህይወት ልናበላሽ እንደምንችል ልናውቅ ይገባናል፡፡

ምን ባደረጉ ይኼን ሁሉ ይቀበላሉ? ቤት የሚያሳልፉትን ማን አወቀላቸው? ሁሉም እኮ ተመችቷቸው አይኖሩም! ቢያንስ እንስማቸው፡፡ እንዲህ ስለነበር ነው እያሉ ስህተታችንን እያስተባበሉ የሚኖሩ ልጆች አንፍጠር፡፡
"አንቺ ግን መቼ ነው ሰው የምትሆኚው?" የሚል የመምህራኖቼ ጥያቄ ውስጤ ከነበረው "መቼ ነው የምወደድ ሰው የምሆነው?" ከሚለው ጥያቄ በላይ ዋጋ አልነበረውም፡፡

Records

13.05.202523:59
295Subscribers
24.04.202523:59
0Citation index
02.05.202519:09
48Average views per post
13.05.202516:16
0Average views per ad post
09.04.202519:09
8.33%ER
13.04.202502:10
17.71%ERR
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
27 APR '2504 MAY '2511 MAY '25

Popular posts የ-ትብለጥ ግራኝ ሳቢር

03.05.202504:48
ህፃናት ገና ት/ቤት ገብተው መማር ሲጀምሩ የመጀመሪያው ትምህርት ነጠብጣቦችን አገጣጥሞ ትክክለኛውን ፊደል ከዛ ከፍ ሲል ደግሞ ቃላትን መስራት ነው (ትሬስ ማድረግ)

እኔም እንደዛ አንዳንድ ጊዜ "ሀ" ብዬ - በህይወቴ ወደ ልጅነት ተመልሼ በእርምጃዎቼ መሀል ያሉትን ክፍተቶች ሞልቼ ጥርት ያለውን ምስሌን ልፈጥር ያምረኛል፡፡ በዛ መጠን ቀላል ቢሆንልኝ ኖሮ፡፡

ከእርምጃዎቼ መሀል....ላጠራ ያልቻልኩትን ያውቁልኝ ዘንድ እሄድ ነበር፡፡

"እሺ ትብለጥ እንዴት ነሽ?"
"ደህና ነኝ ዶክተር"
"ቆየሽ ከመጣሽ እንዴ ብዙ ቆየሽ?"
"አይ ብዙ አይደለም"

ስጋዬ አሁን ላይ ቢሆንም ሀሳቤ ትናንት ላይ ነበር፡፡ ማክሰኞ እና አርብ ከት/ቤት መልስ አባቴ ሰፈሮችን እያስጠናኝ፣ በየመሀሉ ፍዝዝ ስል መሪ ባልያዘ እጁ እየኮረኮረ እያሳቀኝ "ደስ ብሎሻል?" እያለ በተደጋጋሚ የሚጠይቀኝ ዶክተር ጋር ይወስደኝ ነበር፡፡

"ትብለጥዬ"
"......"(ሁሌም በማላውቃቸው ሰዎች ስጠራ አቤት አልልም)
"ይኼ ስንት ቁጥር ነው?"
"አምስት"
"ጎበዝ" (አይደንቀኝም ነበር)

(በአስር እና በሀያ ስምንት ዕድሜ ያለ የእኔ አንድ ዓይነት መሆን)

ለእኔ ቢሆንልኝ ኖሮ መደነቅ እነ መምህር "ደ" የክፍል ጓደኞቼን እንደሚስሟቸው ቢስሙኝ፣ እኔን ሲያዩ ቢስቁልኝ፣ በመኖሬ ባይማረሩ እንጂ እዚህ ዶክተር ጋር መመላለስ አልነበረም፡፡ የእሱ ፈገግታ ለደቂቃዎች ለማገኘው ሁኔታ እንጂ ወጥቼ ስለምጋፈጠው የመምህራኖቼ ሁኔታ ዋስትና አይሆነኝም ነበር፡፡ ለዛ ግን ጎበዝ ተማሪ ሆኜ ቀብድ መክፈል ነበረብኝ!!!

የሚወዷት ዓይነት ተማሪ አልነበርኩም፡፡ ቤት ደረጃ ላይ ቁጭ ብዬ ከመተከዝ ለመትረፍ ት/ቤት ልውደድ እንጂ ትምህርት አልወድም ነበር፡፡ መምህራኖቼም የዕለቱን ዕቅዳቸውን አሰርተው ከመውጣት እና ላልሰራሁት ከመውቀስ እና ከመምታት ውጪ አስበውኝ አያውቁም ነበር፡፡ ፈተና ዝቅተኛ ውጤት ሳመጣ ትናንቴን እያጣቀሱ "ያኔ ዋንጫ ተሸላሚ እንዳልነበርሽ ዛሬ እንዲህ የማትረቢ ትሆኚ?" ከማለት ውጪ ምንም ያሰቡት ነገር አልነበራቸውም፡፡

"መቼ ነው ሰው የምትሆኚው?" የሚለውም ጥያቄያቸው ብቻዬን እጅ አውጥቼ ባልመረጡኝ ሰዓት ከሚሰማኝ "መቼ ነው የምወደድ ሰው የምሆነው?" ከሚለው ጥያቄዬ በላይ ዋጋ አልነበረውም

መልካምነት ላይ ከመድረስ በፊት መልካምም መጥፎም አለመሆን ይቻላል አይደል? እኔ ግን መለስ ብዬ ሳስብ ስለምጠላው ስሜም መልኬም ተጠያቂዎቹ መምህራኖቼ ነበሩ፡፡

"ትብለጥ...ምን አንቺ ትብለጥ ነሽ ትነስ ነሽ እንጂ" (ልጅነት ሞኙ አሜን ብሎ ይቀበላል)
"ግራኝ...አይሻልሽም ቀኝ" እያሉ በቃረሙት ሳቅ ለብዙ ዓመታት ከስሜ አፋቱኝ፡፡
"ነጫጩባ" እያሉ ለሰደቡት መልኬ ብዙ ዓመታትን ሰው ከማየት አሸማቀውኝ ነበር፡፡

ዛሬ ላይ ብድግ ብዬ ለራሴ ከንፈር እንዳልመጥ የሚያደርገኝ ምክንያት ደህና መሆኔ ነው፡ እናም እኔን የመታኝ ሁሉ ልጆቼን አለመንካቱ፡፡

የመጣልኝን እንዳልሳደብ፣ እንደመጣልኝ እንዳልረግጣቸው፣ እንደተሰማኝ ከክፍል ውጡልኝ የማልልበት በቂ ምክንያቴ ሰው መሆናቸው ነው፡፡ሲያጠፉም ሰዎች ናቸው፣ ዜሮም ሲያመጡ ሰዎች ናቸው፣ ሲደፍኑም ሰዎች ናቸው፣ ሲረሱም ሰዎች ናቸው፣ ሲያስታውሱም እንደዛው፡፡

ትንሽ ለሰሩት ስህተት ሀገር ያጠፉ ይመስል ይኼ ሁሉ ውርጅብኝ ማውረድ፣ የቤት ስራ አልሰራህም አልሰራሽም ብሎ በተማሪ ፊት ማሸማቀቅ፣ መግረፍ ቀርቶ መደብደብ፣ የኑሮን መከራ በልጆች መወጣት ክፉነት ነው፡፡

እንደ መምህርም፣ እንደወላጅም ዛሬ በምናወጣው አንድ ቃል እና ጉልበት የሰውን ህይወት ልናበላሽ እንደምንችል ልናውቅ ይገባናል፡፡

ምን ባደረጉ ይኼን ሁሉ ይቀበላሉ? ቤት የሚያሳልፉትን ማን አወቀላቸው? ሁሉም እኮ ተመችቷቸው አይኖሩም! ቢያንስ እንስማቸው፡፡ እንዲህ ስለነበር ነው እያሉ ስህተታችንን እያስተባበሉ የሚኖሩ ልጆች አንፍጠር፡፡
"አንቺ ግን መቼ ነው ሰው የምትሆኚው?" የሚል የመምህራኖቼ ጥያቄ ውስጤ ከነበረው "መቼ ነው የምወደድ ሰው የምሆነው?" ከሚለው ጥያቄ በላይ ዋጋ አልነበረውም፡፡
08.05.202503:16
Log in to unlock more functionality.