Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ከእለታት....📖📚📖📚📖📚 avatar

ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

ለአስተያየታችሁ @Shedorka
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateMar 18, 2023
Added to TGlist
Aug 22, 2024
Linked chat

Latest posts in group "ከእለታት....📖📚📖📚📖📚"

ስላረፈድኩ አፍ የለኝም....በእንቅልፍ ልባችሁ እንድታነቡም አስተያየት እንድትሰጡም አትገደዱም(ማን ናት እድል ልትሉም ትችላላችሁ አሁን).....😁

ነገ ግን ጠብቃችኃለሁ.....😊

መልካም አዳር....
ለማንም ትንፍሽ አላልኩም......

ዝም እንዳልኩ የንሰሀ አባት ያዝኩ.....እየተሸማቀቅኩ ከሀ እስከ ፐ ያደረግኩትን እና ይዞብኝ የመጣውን ጣጣ ተናዘዝኩ.....በርከክ ብዬ " አታዋርደኝ" አልኩት አምላኬን......"አደራህን የባሏ ዘውድ አድርገኝ.....".....አልኩት......"ትናንት ሀይሎጋ ያሉኝ ፊት ከስሬ እንዳልመለስ" አልኩት......

በመጨረሻም "ጀበና ሙሉ ጠጥቼ ህይወት አልሆነኝም.....አቦል ይበቃኛል.....አተላ የተደፋበት ትናንቴን አፅዳ" አልኩት......

አፀዳልኝ።

አለቀ።....

✍ሸዊት

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
✨✨ፍቅር ቅብ✨✨

የመጨረሻው ክፍል✨

"አንድ አንዴ ይቅር የምንለው እንዲሁ ነው....እንዲሁ.....ለምን እንደተተውን ሳናውቅ.....ለምን እንደሄዱ ሳናውቅ.....ለምን እንዳስለቀሱን ሳናውቅ እንዲሁ".....ያለኝ መክብብ ነበር.....በነጋታው ካፌ ተገናኝተን ስለሆነው ሁሉ ሳጫውተው ነበር....እውነቱን ነው....አንድ አንዴ እንዲህ ነው....ሳናውቅ ይቅር ማለት ያለብን ይበዛል.....ሁሉን ካወቅንማ ይቅር አንልምም ይሆናል....

ቢሆንም ግን እናቴን ይቅር ማለት አልተቻለኝም....በየትም አቅጣጫ ባስብ ባወጣ ባወርድ ልቤ አልገራ አለ...አቃተኝ....ከራሴ ጋር ትግል መግጠሙን አልወደውም.....የትግሉ አሸናፊም ተሸናፊም እኔ ስለሆንኩ መታገሉን አልፈልገውም.....የማልደሰትበትን ድል ስለሚያቀዳጀኝ ከራሴ ጋር አልፋለምም...እናቴን ይቅር ለማለት አልታገልም.....ይቅር እንዳልላት አንቆ የያዘኝን ነገር ጊዜ እስኪያለዝበው ድረስ እጠብቃለሁ.....በትዕግስት እጠብቀዋለሁ.....እንኳን የሚመጣ ጊዜን የማትመጣ እሷን ስጠብቅ ኖሬ አይደል.....ጠብቃለሁ።

***

"ኧረ ኩሉን ማን ኩሏታል
ኩሉን ማን ኩሏታል....
ባትኳል እንኳን ያምርባታል
ኩሉን ማን ኩሏታል.......".........ይላሉ በርከት ያሉ የእናቴ እኩያ ሴቶች.....

"ኧረ እሱ አልፎበታል.....ሌላ ቀይሩ"......ትላለች ታናሽ እህቴ ሙሉ በሙሉ ያልደረቀ ጥፍር ቀለም የተቀባው ጣቷን አንጠልጥላ.....

"የኛ ዘበናይ ኡኡቴ......"......ትላታለች ከመሀላቸው አንዷ.....ይሳሳቃሉ....

"ውይ መዋረዳችን ነው ዛሬ....ኧረ ቶሎ ቶሎ በሉና ሙሽራዋን አዘጋጇት"....የምትለው የአባቴ እህት ነበረች.....አክስቴ።

"እታባ አታስቢ እኔ እህቷ አለሁ....."......ያለችው ሀኒ ናት......የሙሽራ ሜካፔ እንዳይበላሽ እና ለተጨማሪ ሶስት ሰአታት ተቀምጬ መሳል እንዳይፈረድብኝ እንባዬን ዋጥኩት እንጂ እንዲህ ስትል የተሰማኝን ደስታ ቃላቶች አይገልፁትም....እንኳን የምሯን ሆኖ አይደለም ልታስመስል ብትለው ራሱ ይሄ ቃል ለኔ ከባድ ነው.....ለአንድ ቀን ለማስመሰል መወሰን ለኔ ትልቅ ውለታ ነው....የምታፈቅረው ሰው ሰርግ ላይ ተገኝቶ ጥርስን ከፍቶ መዋል ትልቅ ህመም ነው.....

"ዋ እድል ዋ አንድ እምባ ካየሁ አለቀልሽ.....".....ተቆጣች ሀኒ....ዋጥኩት።

ማግባት እፈልግ ነበር....ሙሽራ መሆን ግን አልወድም.....አለ አይደል ነጭ ለብሶ እጅን ከግራ ወደቀኝ በስሱ እያውለበለቡ መዋል....ደግሞ እንደልብ የማያራምድ ቀሚስ አይሉት ድንኳን ውስጥ መዋሉ(ቆይ ሽንቴ ቢመጣስ እዛ ውስጥ ሆኜ)....መጥኖ መፈገግ.....መጥኖ መብላት.....መጥኖ መራመድ....ተቆጥቦ መዋል....ዳይሬክተር የሌለበት ፊልም ሲቀረፁ መዋል ይመስለኛል....እኔና ባለቤቴ 'ሄድን' ብለን ብቻ ወደ አዲሱ ጎጆአችን ብንሄድ ደስ ይለኝ ነበር.....አይቻልም እንጂ የኔ ተፈጥሮ እንዲህ ነበር.....'አዋጅ አዋጅ' ሳይሉ መጠቅለል....ምርቃት ተቀብሎ ብቻ ዝም እንዳሉ መሄድ.....እንዲያ ነበር የፈለግኩት.....አልሆነም እንጂ።

"ያንቺ ባለቤት ለመባል እበቃለሁ እድሏ.....አንቺስ ባለቤቴ ነው ለማለት አታፍሪም" ......አለኝ ወደ ጆሮዬ ተጠግቶ....መድረክ ላይ ነበርን.....

"አንዴ ብቻ አይደለም ሺ ግዜ.....አንድ ቀን ብቻ አይደለም ሺ አመት ባንተ ብጠራ....ባለቤቴ ብልህ....ንብረትህ ብሆን አይሰለቸኝም.....".....አልኩት እኔም ወደ ጆሮው ተጠግቼ እየተንሾካሾኩ....ከዚህ በላይ ብዙ ልለው ብፈልግም የትንፋሼን ሙቀት ፈራሁለት....."ሲቆም አያማክርም" ትለኝ ነበር ሀኒ.....እንደ እኔ ድንኳን ውስጥ ቢሆን እንኳን እሺ.....

ሀይሎጋው ደርቶ ዋለ.....ወዳጆቻችን ላባቸው ጠፍ እስኪል ዘለሉልን......አባቴ ከልቡ ሳቀ....ጓደኛዬ መክብብን እንደምታፈቅረው ረሳች.....ከልቧ አሞቀችልኝ.....ኮራሁባት....."የሚዜ ፈዛዛ የለውም ለዛ" የሚባሉ አይነት ሶስት ሚዜዎቼ ለቅሶ ቤት ያሉ ነበር የሚመስሉት.....የአክስት የአጎቶቼ ልጆች ናቸው.....በጎደለ ሙላ ብዬ ባመጣቸውም በማምጣቴ ተፀፀትኹ.....ደግነቱ ሀኒ ነበረች.....ብቻዋን አስር የሆነች ጓደኛዬ።

ሰአቱ ሲደርስ ከአባዬ ጋር ተላቀስን....ሀኒ ተጠምጥማብኝ ለእኔ ይሁን ለመክብብ ያለየሁትን እንባ አነባች.....እህቴ ደስታዋ ደፈረሰ.....የምሄድ አልመሰላትም ነበር መሰለኝ።

አዲሱ ጎጆዬ ገባሁ.....ሌላ የህይወት ምዕራፍ ገለጥኩ.....

የሰርጋችን ማታ ላይ መክብብ ያን ኮተት ከላዬ ሲጥልልኝ ትንሽ ተንፈስ አልኩ......ሁል ጊዜ እንደሚስመኝ ከንፈሬን በሁለትዮሽ ሳመ እና ጥሎኝ ሻወር ቤት ገባ.....ከሻወር ቤት እስኪወጣ ለዚህ ምሽት ያዘጋጀሁትን የለሊት ልብስ ከነላቦቴ ለብሼ ከነግራ መጋባቴ ጠበቅኩት.....

"እድሏ ታጥበሽ ብትለብሺው አይሻልም ነበር.....".....አለና ግንባሬን ስሞ ወደ ሻወር ቤት መራኝ...ሻወር ቤት ካስገባኝ በኃላ ሹልክ ብሎ ወጣ.....እንደነገሩ ታጥቤ ወጣሁ.....አቅፎ አዲሱ አልጋ ላይ በክብር አስተኛኝ....እንደ አባት እንክብክብ አርጎ መተኛዬን አመቻቸ....የቀኑ ድካም እቅፍቅፍ አርጎ አሰተኛን....."ሀይሎጋ" እያሉ አውለውን የራሳችንን ሀይሎጋ ሳንጨፍር ነጋ....

በነጋታው ጫጉላችንን አንድ ብለን ጀመርን.....እዚህ ጋር ነው ችግር የተፈጠረው.......ጠረኑ መጣ.....

"ተከፍቶ የኖረን ጊቢ ሁሉም ቆሻሻውን ያራግፍበታል...."....ስላት አስታውሳለሁ....እህቴን።

"ግን እኮ እህቴ ተዘግቶ የኖረን ደግሞ ድር ያደራበታል....."....ነበር ያለቺኝ አይደል።

"ድር እኮ መድሀኒትነት አለው....ቁስልን ለዘብ ያደርጋል....ላፅዳህ ብትዪውም በጄ ይልሻል.....የዘመናት ቆሻሻን ዘወር ብታደርጊው እንኳን ጠረኑ ከርቤም አይበቃውም....."....ከእህቴ ጋር የተነጋገርነው አንድ በአንድ መጣብኝ.....ጠረኑ መጣ.....አደባባይ ቤቴን ከፍቼ ያስገባሁት ቆሻሻ ክርፋቱ ለአፍንጫዬ ከበደኝ....

ከመክብብ ጋር ደስተኛ ልሆን አልቻልኩም....ከእለት እለት አልጋ ላይ የሚካሄደውን የጨዋ ጨዋታ ልወደው አልቻልኩም.....መክብብ ሰንፎ አይደለም.....እኔ ማየት የሌለብኝን ሳይ ኖሬ.... መንካት የሌለብኝ ስነካ ኖሬ ነው.....ሳግበሰብስ ኖሬ ምጥን አልበቃሽ ብሎኝ ነው.....ስፕሪስ ስጠጣ ኖሬ በብርቱካን አልረካ ብዬ ነው.....

ጠረኑ መጣ......

ያ ጠረን መጣ.....

ከርቤ የማያለዝበው ክፉ ጠረን ቤቴን ሊያፈርስ መጣ.....

በወር ሀያ ስምንቱን ቀን የተፈጥሮ ግዴታዬ ላይ ነኝ ማለት ጀመርኩኝ.....ሁለቷን ቀን ደግሞ ወይ ሰንበት ነው ወይ የአመቱ ገብርኤል ነው እያልኩ ማምለጥ ያዝኩ.....ለሰው አይነግሩት እዳ ሆነብኝ ....ተበደልኩ አልል ነገር የራሴው በለስ እዳ ሆነብኝ....ዮናስ እባብ ሆኖ ወደ አፌ የሰደደው በለስ.....የለመድኩት overdose ህይወቴን ሰደድ ውስጥ ጨመረው......
ትዝብት! የ90 ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ደሞዝ ለኔ የምትከፍለኝ ደሀዎ አፍሪካዊት ሀገር!

(ከስደት : Dr Abiyot Cheklaye, internist, gastroenterologist and transplant hepatologist)

ብዙ ባይመቸኝም አንዳንዴ የመንግስት ጡሩምባ ሚድያዎችን እሰማለሁ:: እናም ካድሬዎቹ ከአፍሪካ ግምባር ቀዴም ግዙፍ ኢኮኖሚ እያስመዘገብን ነው ይላሉ ።

የሚገርመው ነገር እኔ የምኖርባት የአፍሪካ ሀገር በአለም ላይ በጣም ድሀ ከሚባሉት ናት። ነገር ግን እኔ እዚህ በወር የማገኘው ደሞዝ ወዴ ETHIOPIA ብወስደው 90 ለሚሆኑ በእኔ የትምህርት ደረጃ ላሉ ስፔሽያሊስት ሀኪሞች የወር ደሞዝ መክፈል ይችላል። አሳፋሪ ነው::

እንደዚህ በጭንቀት የሚኖር የጤና ባለሙያ ጋር ሂዶ መታከም ራሱ ከባድ ነው:: አነሱ ሳይበሉ የሚያገለግሉት መላእክት አይደሉም:: በእርግጥ ያልታጠበ ቁርጥ ስጋ በየቀኑ እየበላ ለተቅማጥ በየጊዜው ባንኮክ ሪፈር አድርጉኝ እያለ አዛ ለሚያደርገው ካድሬ የህክምና ጥራት ምኑም አየይደለም::

ሳይቃጠል በቅጠል እንድሉ አስቸኳይ መፍትሄ ስጧቸው:: I advise all the health professionals to stand firm and united in any action; never fall back!

Dr Abiyot Cheklaye, internist, gastroenterologist and transplant hepatologist!
✨✨✨ፍቅር ቅብ ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀርቶታል....🥳

በትዕግስት ስላነበባችሁልኝ ምስጋናዬ በብርቱ ነው.......

እያቆራረጥኩ እንዳስመረርኳችሁ አውቃለሁ.....ታሪኩን የጀመርኩ ሰሞን የሚዘለል ቀን ካለ እየነገርኩ የሚለቀቅበትን ቀን ሳሳውቃችሁ  እንደነበር ይታወቃል.....በመሀል ግን የምዘለው ቀን የምፅፍበትን ቀን ማሳወቅ አሻፈረኝ አለ.....

በስራ ምክንያት መልክአ ምድሩ ለአይን እንጂ ለጤና የማይመች ቦታ ላይ የምኖር ላጤ እንደሆንኩ ልብ በሉሉልኝ.....በ'አለማየሁ ዋሴ እሸቴ' ሜትራልዮን በተሰኘ መፅሀፉ ላይ በአረንጓዴነቷ የተሽሞነሞነችው "ሚዛን ቴፒ" ውብ አይነ ግቡ ተፈጥሮ ያላት ብትሆንም የወባ መናሀሪያም ጭምር ናት......

"ላልተወሰነ ጊዜ ፍቅር ቅብ የለም" ብሎ ማለት አልቻልኩም.....እናንተ ስታነቡት ከምትደሰቱት በላይ እኔ ስፅፈው እደሰታለሁ.....እኔ ራሴ እንደዚህ ሳልፅፈው መቆየቱ ምቾት አይሰጠኝም..... "ዛሬማ መድሀኒቴን ቶሎ ወስጄ ተኝቼ ለሊት እፅፈዋለሁ" የምልበት እና ራሴን ጠዋት ስራ ለመሄድ ስንተፋተፍ የማገኝበት ቀን ከአንድ ጀምሮ ሶስት ቀን ቆጠረ....(አርብ እለት ማታ ማስታገሻ ወስጄ እየፃፍኩ ምን ሰአት እንቅልፍ እንደወሰደኝ ሳላውቅ ከለሊቱ ስምንት ሰአት ነቅቻለሁ.....)

ምን ያሀል እየጠበቃችሁኝ እንደሆነ ባውቅም ምን ቀን እንደምድን ሳላውቅ  በዚህ ቀን አደርሳለሁ ማለት አልቻልኩም.....በተጨማሪም እየታመምኩም ቢሆን ያለ እረፍት ለመስራት የተገደድኩት መደበኛ ስራዬ እና ለራሴ ራሴ ብቻ መኖሬ ከእቅድ ውጪ አደረገኝ.....(በጣም የተለመደ ስለሆነ ወባ ማንም አሰሪ ከቁምነገር ቆጥሮ እረፍት አይሰጥም....ጤነኛ መስሎ ከሚንቀሳቀሰው ህዝብ 75%ቱ የወባ ክኒን እየቃመ ነው.....)....

በተጨማሪም ለመፃፍ እጅ ብቻ ሳይሆን የተረጋጋ ጭንቅላትም አስፈላጊ ስለሆነ እስክረጋጋ መጠበቅ ነበረብኝ....በዚያ ስሜት ውስጥ ሆኜ ብፅፈው ራሱ ለአይናችሁ የሚመጥን ስራ እንደማይሆን ተሰማኝ....(የመጨረሻዎቹ ክፍላት አእምሮዬ ውስጥ እንጂ ወረቀት ላይ አልሰፈሩም ነበር....).....በመሀል የማደርሳችሁ አጫጭር ክፍላት የመጨረሻውን ክፍል በአንድ ከፍ አድርገውታል.....ስለዚህም ቀድሞ ባልኩት 20 ክፍል ሳይሆን በ21 ክፍል ለማጠናቀቅ ተገድጃለሁ...

እዮብን የሚያስንቅ ትዕግስት ለታገሳችሁኝ አንባብያን ከወገቤ ሸብረክ ከአንገቴ ጎንበስ ብያለሁ.....አመሰግናለሁ።

ነገ የመጨረሻው ክፍል አብባችሁ አስተያየታት መስጠታችሁን አትርሱ....እጠብቃችኃለሁ.....ቆዩልኝ💙
"ምንም አይነት ነገር ቢመጣ ከዚህ የሚከብድ አይመስለኝም....ከዛን ቀን በላይ ከባድ ምሽት የሚኖረኝ አይመስለኝም...እጃችሁን ይዤ እያለቀስኩኝ ነበር...በተኛችሁበት ይቅርታ እየጠየቅኳችሁ ነበር....በብርሀን አይናችሁን እያየሁ ማድረግ አልቻልኩም...."ጥያቹ ልሄድ ነው" ለሚል መርዶ የሚሆን ይቅርታ ይኖራል...?....."ካሁን በኃላ አይኔን ስለማታዩት ይቅር በሉኝ..."....ይባላል...?

ለረጅም ሰአት እያየኃችሁ ነበር ....ስትተኙ ደግሞ ይበልጥ ታሳሱ ነበር.....እንቅልፋችሁ ላይ እምነት ነበረ....ስትነቁ ሁሉም ነገር እንደሚቀጥል የሚነግራችሁ እምነት....

"ለምን እውነቱን አልነገርኳቸውም...?"....የምልበት ቀን አበዛዙን አታውቂም እድሏ.....የሆንኩትን አታውቂም እድሏ....ስንት ቀን እግሬን አንስቼ እንደመለስኩት አታውቂም ልጄ.....አንዴ አቅፌያችሁ ለመመለስ የፀለይኩትን ፀሎት አታውቂም ልጄ....ለልደታችሁ ሻማ እንደማበራ....ፎቶአችሁን በትልቁ እንደሰቀልኩ... የብቻ ቤቴ አድባር እናንተ እንደሆናችሁ አታውቂም የኔ ልጅ....

ከአመታት በኃላ ተመልሼ ልመጣ ሻንጣዬን ሸክፌ ነበር....እንዳትጎዱብኝ ብዬ ተውኩት እንጂ......ይቅር በሉኝ ልጆቼ....ይቅር በሉኝ....አልመጣም አትጠብቁኝ....እወዳችኃለሁ።".....ብሎ የሚዘጋ ደብዳቤ አንብቤ ለእህቴ ሰጠኃት....ስለ እናቷ የማወቅ መብቷን ከዚህ በላይ ልጋፋ አልፈለግኩም.....

'መምጣቴ ይጎዳችኃል' ነው ያለችው አይደል....! ...አሁን ማን ይሙት ለዘመናት ከእናት መለየት ቆዳ ተልጦ ጨው እንደተነሰነሰበት ሰውነት እንደሚለበልብ ጠፍቷት ነው....?...እንደዚህ ይደረጋል....?....አልመጣም ለማለት ይሄ ሁሉ ጊዜ ይጠበቃል.....

**

እውነቱ ግን ራስ ወዳድ መሆኗ ላይ ነው...የልጆቿን እምባ እና ድንጋጤ በአይኗ ማየት የሚፈጥርባትን ከባድ ስሜት ለማምለጥ ነው...ሁላችንም እንዲህ አይደል የምናደርገው....እኛ ሳናይ ስለሚወርዱት ዘላዎች ማሰብ አንፈልግም....ብቻ ማምለጥ....ብቻ መፈርጠጥ...

ብናምንም ባናምንም ሁላችንም ስለሚጎዳው ስሜታችን ስናስብ እንደደነበረ በሬ የሚያስፈረጥጥ ራስ ወዳድነት አለብን...

✍ሸዊት

የመጨረሻው ክፍል ነገ✨

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
✨✨ፍቅር ቅብ-20✨✨

ለቅፅበት ሀኒን ከአእምሮዬ የሚያስወጣልኝ ባገኝ ሳልደፋ 'እሺ' እንደምለው አውቃለሁ....

እጄ ላይ ያለውን ሹካ አስለቀቀና በሹካው ቦታ እጁ ተገኘ....የእጁን ልስላሴ ነግሬያችኃለሁ አይደል....እሱ ብቻ የሚሰጠኝ ምቾት ይሰማኝ ጀመር.....እጄ ከርዳዳ ስለሆነ ነው መሰለኝ የእጁ ልስላሴ ልቆ ይሰማኛል....

እጄ መከርደድ የጀመረው እናቴ እግሯ ከቤት ከወጣ ማግስት ከአባቴ ሻካራ ጃኬቶች ጋር መታገል ስጀምር ነው....የእናቴ እጅም ከርዳዳ ነበር.....ማታ ማታ ቀኝ እጄን ይዛ ትፀልይ ነበር....ምን እንደምትል ባላውቅም በጣም በቀስታ ታነበንብ ነበር.....እሷ ከሄደች በኃላ እኔም በከርዳዳ እጆቼ የታናሽ እህቴን ቀኝ እጅ ጨብጬ ሳነበንብ ራሴን አገኘሁት.....ያኔ ነው እናቴ ምን ብላ ትፀልይ እንደነበር ለመገመት የበቃሁት.....

ከከረደደ እጅ ጀርባ የከረደደ ትናንት የገገረ ልብ አለ.....ውሀ ቀጠነ ብሎ ባር ባር ከሚለው ሰው ጀርባ ሙሾ የሚያስወርድ ትናንት አለ.....በቀላሉ ማጅራቱ የሚጎብጥ ሰው ጀርባ ማጅራት ገትር የሚያሲዝ ትናንት ያልታወቀለት ቁስል አለ።

ሁላችንም የምንፈርደው የደረስንበት ላይ አይደል....የሌላውን ሸክም እንዳናቀል እኛም ሸክም የከበደን ነን....

የእጄ መጠጠር የጎረበጠው አይመስልም.....ተጠጋኝ.....ይሄ ዮናስ የሚጠጋኝ አይነት መጠጋት....'ዮናስ መክሮት ነው እንዴ' የሚያስብል አይነት መጠጋት.....እጁን ግን ወደሌላ ቦታ አልሰደደም.....ደስ አለኝ.....እጁን እንቁዬ ላይ ሳይጭን ልቤን ቀጥ ያደረጋት የመጀመሪያ ሰው.....መክብብ.....አይኔ ላይ በመቆየት ብቻ ላብ በላብ ያደረገኝ የመጀመሪያው ሰው.....መክብብ....."እወድሀለሁ.....በጣም እወድሀለሁ" አልኩት አይኑን ከአይኔ ሳይነቅል.....አስተያየቱን ፈራሁት.....ከማላብ አልፌ ማቃሰት ሳልጀምር እንኳን እንደምወደው ነገርኩት .....ያን ምትሀት ጥርሱን ገለጥ አረገው.....በጥርሱ ብቻ ብዙ ብዙ ማለት ይችላል.....በአይኑ ብቻ ስሜትን መበርበር ይችላል.....

ከቅድሙ ይበልጥ ተጠግቶኝ አይኖቼን ሳመ.....ወደ አይኖቼ ሲጠጋ ሊስመኝ እንደሆነ ገባኝና አይኖቼን ገርበብ አደረግኩለት....አይኖቼን ወደቦታቸው ሳልመልስ ከንፈሮቼን አንድ በአንድ ሳመ....

ልክ እንደጉንጭ ቀለል አድርጎ ነበር የሳመኝ....ከንፈር በክፍልፋይ እንደሚሳም ባላውቅም ዮናስ ጋር የሌለ የጨዋ አሳሳም ይሆናል ብዬ አለፍኩት....እሳት እንደነካ ሰው ከከንፈሮቼ በፍጥነት ሲላቀቅ ከንፈሮቼ እኔ የማላውቀው አንዳች መለኮታዊ ሀይል ይኖራቸው ይሆናል ብዬ ተውኩት....ከንፈሮቼ ላይ ባይቆይም አይኔ ላይ የቆየው መቆየት በልጦብኝ ልብ ላለማለት ወሰንኩ.....መሳም አቅቶት ሳይሆን ጊዜው ስላልመሰለው አላረዘመው ይሆናል ብዬ ዝም አልኩ.....የሚጠጣ ክትፎ አፍንጫዬ ላይ አስጠግቶ እንደነጠቀኝ አይነት ስሜት ቢሰማኝም መክብብ ስለሆነ ብቻ ዝም ጭጭ ረጭ አልኹ....

'የእራት ግብዣ መዝጊያ እራት መብላት ብቻ መሆን አለበት' ትለኝ ነበር ሀኒ በእራት ሰበብ ቁርስ አብልቶ ከሚሸኘኝ ዮናስ ስመለስ.....'እራት ላብላሽ ካለ መብላት የሚፈልገው ነገር አለ' ትለኝም ነበር...... ከምሽቱ ሶስት ሰአት ሲሆን መክብብ ሰአቱን አየት አረገና "ብንሄድ ይሻላል.....እየመሸ ነው....ቤተሰቦችሽም ይጨነቁ ይሆናል" አለኝና አስተናጋጁን ጠርቶ ሂሳብ አስተመነ.......

መኪናው ውስጥ ገባን....አልፎ አልፎ እያየኝ ያን ምትሀት ገለጥ ያደርግልኛል.....ለሀገር የሚበቃ ጥርስ ይዞ እዚ ምንድን ነው ሚሰራው እላለሁ....ግብፅ ስትተብትብን ምናል የመክብብን ጥርስ ይዘውት የግብፅ ጠቅላይ ሚንስትር ጋር ቢሄዱና ቢያደነዝዟቸው.... የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምን ነካው.....የዚን ጥርስ ባለቤት ግብ ጠባቂ ቢያደርጉት ምን አለ....አንዴ ፈገግ ካለ እንኳን ተቃራኒ ቡድን ይቅርና ሊገባ የሚንደረደረው ኳስ እግር አውጥቶ ወደኃላ ያፈገፍግ ነበር....አለማወቅ።

ቤቴ እንደደረስኩኝ ግንባሬን ሳመኝና ከመኪናው ወረድኩ.....ጊቢያችንን ማንኳኳት ስጀምር ሞተሩን አስነሳ.....መኪናው ከአይኔ ሲሰወር  ሀኒ ጭንቅላቴ ላይ ተንሰራፋች።

ቤት ስገባ እህቴ እያጠናች አባቴ ደግሞ ዜና ከሚዘግበው ጋዜጠኛ ፊት ለፊት ተቀምጦ እያንቀላፋ ነበር....

እራት በልተናል ቢሉም  'እድል ስፔሻል' የሚባለውን ምግቤን ሰርቼ ካልበላችሁ ብዬ አስጨነቅኳቸው.....በሉልኝ....."ዛሬ ጫን ያለው ነው ባክሽ....ምን ተገኘ" አለኝ አባቴ....."ደስ ብሎኝ ነው እንዲሁ.....እስቲ መርቀኝ.....".....አልኩትና ጉልበቱ ላይ ተደፋሁ.....

"እድሜ ይስጥሽ....ጤናሽን አይንሳሽ....ልብሽን ይጠብቅልሽ....እመቤቴ በፈረሰው ጎንሽ ትቁም.....".....አለኝና አይኑ ውስጥ የተጠራቀመውን እንባ በጋቢው አደራረቀ....."የፈረሰው ጎንሽ" ያለው ጋር እስኪደርስ ደህና ነበርኩ.....ካጎነበስኩበት ተነስቼ አቀፍኩት....ሳቅፈው ባሰበት....እሱም የሚመርቀው አጥቶ እንጂ የፈረሰበት ጎን እንዳለው ትዝ አለኝ....

እንደ እኔ እንደ እኔ ህይወት ሰፊ ካሬ ያላት መሬት ናት....የፈረሰ ጎናችንን ተወት አርገን ሌላ ማንነት ለመገንባት የሚያስችል ትርፍ ቦታ አላት.....የፈረሰው እስኪጠገን መጠበቅ ሞኝነት ነው.....እሱን የሚጠግነው ጊዜ የተባለ መሀንዲስ ነው.....ሌላው ካሬ ግን የእኛ ሀላፊነት ነው።

"ከትዳር ጋር የተያያዘ ምርቃት የለህም አባዬ.....".....አልኩት ከእቅፉ ሳልወጣ....አንድም ለመመረቅ ደግሞም መላቀሳችንን ረዝሞ ለእህቴ ጥያቄዎች አሳልፌ እንዳልሰጥ......

ከት ብሎ ሳቀና "ኧረ ሞልቶ".....አለና አዥጎደጎደው....ጉልበቱን ስሜ ተነሳሁ.....ቡና ካላፈላሁ ሞቼ እገኛለሁ ስለው 5 ሰአት እያለፈ ነበር......

"ውቃቢ እንዳለበት ሰው በጠራራ ለሊት....?".....አለ ከላዩ የወደቀውን የጋቢ ክፍል ወደቦታው እየመለሰ....

"መች ስድስት ሰአት ሆነ አባዬ ደሞ" ብዬ እንደማኩረፍ ስል እንዳፈላ ተፈቀደልኝ.....

"ፊትሽ ሁላ ፈካ....የሰጠሽን የሰጠሽ አምላክ ይመስገን.....".....አለኝ አቦል ቡናውን እየተጎነጨ።

**

አተኛኘቴ የሬሳ ነበር.....የእህቴ አቀሳቀስ ደግሞ ሬሳ የሚያስሮጥ ነበር....

የተጣጠፈ ወረቀት በእጄ ሰጠችኝ እና እያለከለከች ማውራት ጀመረች......"እድል የሆነች ተለቅ ያለች ሴትዮ ናት ለእህትሽ ስጫት ብላ የሰጠችኝ....ነጠላ ለብሳ ነበር....አጠር ያለች.....".....እንዳለችኝ ከአልጋዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁ.....አባታችን ቤት አልነበረም.....እጇን እየጎተትኩ ይዣት ወጣሁ....."በየት በኩል ነው የሄደችው ታስታውሻለሽ....እእእ" አልኳት በተጣደፈ ሰው ድምፅ....."ሰጥታኝ ታጠፈች....".....ባለችኝ መንገድ ታጠፍኩና ከአራት መንታ መንገድ ጋር ተፋጠጥኩ.....አንቺ በዚኛው ሂጂ እኔ ደግሞ በዚህ ብዬ ከአራት መንታው ሁለቱን መንገድ መረጥኩ.....በህይወቴ እንደዚህ የሮጥኩበትን ቀን አላስታውስም.....ልቤ ልትፈነዳ አንድ ሀሙስ እስኪቀራት ድረስ ሮጥኩ.....ከእንባ ጋር ሮጥኩ....ከትናንቴ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዤ ሮጥኩ.....
✨✨ፍቅር ቅብ-19✨✨

"ሰርፕራይዙን አበላሸሁት አይደል......".....አለቺኝ ስልኩን ከዘጋች በኃላ......

ግራ ገባኝ.....እሱን አግኝቼ እሷን ላጣት ነው....?...አንዱን አጥቶ ሌላ ማግኘት ህይወት ሊባል ይችላል....?.....ብሎልኝ ልቤን የሞላው ሰው ባሌ ከሆነ የሰርጌ እለት በግራ ባሌን አድርጌ በቀኝ የማደርጋት ስር ሚዜዬ ሀኒ ላትሆን ነው......?.....አጥንት የሚሰረስር ህመም ውስጥ ሆና ታጅበኝ ይሆን.....በሙሉ ልቧ "ይዟት በረረ....".....እያለች ትሸኘኝ ይሆን.....

ምን አለ እንዲህ ባታደርግ.....ምን አለ እንደመጀመሪያው ቀኗ ብትሆን.....ምን አለ ዛሬም እንደትናንቱ እንድታዘባት ብታደርግ.....በ"እድለኛ" ነሽ ፈንታ "መሰሪ ነሽ" ብትለኝ.....ምናል እንዲህ ባታደርግ.....አንገቷን ሰበር አድርጋ ባታለቅስ ምን አለበት.....ምናል እምባዋ እልህ ቢኖረው....ምናል አንድ ሁለት ስድብ ብትሰድበኝ...."ማን ስለሆንሽ ነው" ብትለኝስ.....

"አደራሽን ደግሞ እንዳላወቀ ሁኚ....ብዙም አትዘንጪ.....".....አለችኝ ስንሰነባበት.....ሳቅ ነገር ብትልልኝም ለፈገግታዋ መልስ አልሰጠሁም......ጭንቅላቴ ተወጥሯል....እያሰብኩ ነው.....ይሄ ነው የማልለው ከባድ ስሜት እየተጫወተብኝ ነው.....

"ስለ ባሌ የማወራው ለሀኒ እና ለንሰሀ አባቴ ብቻ ነው" የሚል መንግስት ያላፀደቀልኝ ህግ ነበረኝ....አሁን ስለመክብብ ምንድነው የምነግራት....ሌላው ቀርቶ የዛሬውን ቀን አብረን መፈንደቅ አልነበረብንም....ግማሽ ሳቅ ግማሽ ሳግ ይዤ ነው የፍቅር ጥያቄውን የምቀበለው....?

መታደልም አለመታደልም ነው ይሄ..... ዱባ እና ክትፎ ቀላቅሎ እንደመብላት ያለ ነው ይሄ....የፆም ቋንጣ እንደመስቀል ነው ይሄ.....ባንድ እግር ቤተስኪያን ቆሞ እንደማስቀደስ ባንዱ ደግሞ መሸታ ቤት ቡጊ ቡጊ እንደመጨፈር ግራ የገባው ነገር ነው.....በአንድ አይን የደስታ እምባ ባንዱ ደግሞ ዋይታ ነው ይሄ....

እሺም እምቢም ብለው ደስታ አለው....የቱ ደስታ ይበልጣል....?

***

አመሻሽ ላይ ስልኬ ጠራ.......መክብብ።

"ሄለው እድሏ......"......አለኝ ፍቅር ባለበት ድምፅ....... እድሏ ብሎኝ አያውቅም.....እድሏ  የምትለኝ እናቴ ብቻ ነበረች።

"አ....አቤት.....".....እንደእስከዛሬው ወዬ ማለት ሀኒን መክዳት መሰለኝ....

"የት ነሽ...."......አለኝ ወዬ አለማለቴን ከቁብ ሳይቆጥር......

"ቤት" አልኩት....ቤቴ ነበርኩ.....በቴሌቭጅን መስኮት ላይ በማያቸው በሚስቁ ሴቶች እየተደመምኩ....ይስቃሉ.....በጣም ይስቃሉ.....ይዝናናሉ.....ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ውስጥ ገብተው እንደ ንግስት ይስተናገዳሉ....'ለአንድ ቀን ኖሬው ብሞትም አይቆጨኝ' የሚያስብል ኑሮ ለአንድ ቀን ይኖራሉ።

"እራት እንብላ"....አለኝ....ድምፁ ላይ መሳቀቅ ነበር......እንዳልገባው ሆኜ "ብሉ" ልለው ነበር.....ውስጤን ደስ አላለውም.... እሱ ያጠፋው አንድም ጥፋት አለመኖሩን ለማሰብ ሞከርኩ.....ስመኘው የነበረው ነገር እንደነበር አስታወስኩ.....ሰውየው መክብብ እንደሆነ አስታወስኩ...."መክብብ የወራት ክስተት ነው.....ሀኒ ግን የዘመናት......".....አለኝ ስሙን የማላውቀው የጭንቅላቴ ክፍል.....

በደስታዬ መደሰት አለመቻሌ አብከነከነኝ.....

"እና ምን አልሽኝ.....".....ጥያቄውን አስታወሰኝ።

"እሺ".....አልኩትና ወደሚያናውዘኝ ጭንቅላቴ ተመለስኩ።

***

"ወድጄሻለሁ...."......አለኝና ኮፍያውን አውልቆ በራው ላይ ችፍ ያለውን ላብ በሶፍት አደራረቀ.....ፊት ለፊታችን ያስቀመጥነውን ምግብ ቆልለን.....ብዙ ዝባዝባዝንኬ እንደማልወድ የነገረችው ሀኒ መሆን አለባት....መግቢያም መንደርደሪያም የሌለው እንቅጭ ነው የነገረኝ....

የእጁን ርግብግቢት ያስተዋልኩት በእጁ የያዘው ሹካ አየር ላይ ሲውለበለብ ነበር....

"እድል" አለኝ ዝምታዬ ሲረዝምበት.....

"ወዬ".....አልኩትና አይኑ እንዳያገኘኝ ሳህኔ ላይ አፈጠጥኩ....

"ወድጄሻለሁ.....በጣም ወድጄሻለሁ....'ምን ታስቢያለሽ' ብዬ አልጠይቅሽም....ምንም ብታስቢ....ምንም ብትዪኝ እኔ ጋር የሚለወጥ ስሜት የለም....ድንገት እንደሆነብሽ እና እንዳስደነገጠሽ ይገባኛል....ምን አልባት ይሄን ለማለትም ፈጥኜ ይሆናል....ግን እድሏ ልቤ አላስቀምጥ አለኝ....መጀመሪያ ላይ እንዲሁ obsession መስሎኝ ነበር....ጭራሽ ጊዜ ሳይመርጥ ቀን እና ማታውን የማስበው ስላንቺ ሆኖ ሲያርፍ ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ....

ከልክ በላይ አሰብኩሽ....አንድ ሁለት ቀን ስለመስሪያ ቤት ሴቶች ለማሰብና አይኔ ላይ የምትጠገኚብኝን ነገር ለማደብዘዝ ሞከርኩ.....በውኔም በህልሜም በዚህ መንገድ አስቤያት ስለማላውቀው ሀኒ እራሱ ሳስብ ነበር.....ከማንም ላወዳድርሽ አልቻልኩም....አንቺን የማወቅ....አንቺን የመቅረብ ምኞቴ ከቀን ወደ ቀን እየጋለ ሄደ....".....አለኝና ፊት ለፊቱ ከተቀመጠው ውሀ አንድ ጉንጭ ጠጣለት።

"አይኔን የሳምከኝ እለት የሆንኩትን መሆን አስታውሳለሁ.... እረፍትም ፍርሀትም....ሳቅም ደስታም....ለቅፅበት የመኖር ፍላጎቴ ሲንር ይታወቀኝ ነበር....ላውቅህ እፈልጋለሁ.....በደንብ ላውቅህ....ሁልጊዜ እንባ ያቦዘዛቸውን አይኖቼን እንድትስም እፈልጋለሁ.....ባንተ መታቀፍ አለም ነው.....ስታዳምጠኝ ልብህን እስከ ጥግ ከፍተህ ነው....አንተን አለመውደድ አይቻልም"......ያለው ልቤ ነው......

ጎንበስ ብዬ ሳህኔ ላይ ያለችውን የሞተች ዶሮ ሬሳዋን በሹካ እየወጋሁ አላስተኛ እያልኳት ነው.....ላቤ ጀርባዬ ላይ ይንቆረቆራል....እንደ እሱ በራ ብሆን አናቴ ላይ ያለው ላብ ጎርፍ ሆኖ ይወስደው እና እኔም ከዚ አጣብቂኝ እገላገል ነበር......

"እድሏ......".....ጠራኝና 'መልስሽን እየጠበቅኩ' ነው አስተያየት አየኝ።

አላለቀም.....

✍ሸዊት

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
እሱ እና እሷ 2

እሱ

ለቀናት ፎቶው ላይ ሳፈጥ ከረምኩ.....አላይም ብዬ እተወውና መልሼ እራሴን ፎቶው ላይ ሳፈጥ አገኘዋለው ....ወስጤ ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ.....ከዛ በላይ ግን እረሳዋት ያለው ልቤ መልሶ በፍቅሯ ሲነድ ይታወቀኛል ።

ጥያቄዎቼን መልሼ መላልሼ ለራሴ እጠይቃለሁ ...አታፈቅረኝም ነበር ማለት ነው??? ያ ሁሉ ጊዜ ያ ሁሉ ነገር ውሸት ነበር ?? እንዴት ቻለችበት??? ምን አጎደልኩባት??? በአንድ ጊዜ ከሁለታችንም ጋር ነበረች ማለት ነው???? ካልሆነ እንዴት ???? ብዙ ብዙ ጥያቄዎች ውስጤን ያውከዋል ...መረጋጋት አቃተኝ ....ስለ ሌላ ነገር ማሰብ ከበደኝ.....ስራዬን ኑሮዬ ሁሉም ነገር ውሸት ሆነብኝ ......ከራሴ ጋር ብዙ ታግዬ ላገኛት ወሰንኩ ....እንዴት አገኛታለው ምንስ እላታለሁ አላውቅም ....ግን አግኝቻት ለጥያቄዎቼ መልስ ማግኘት አለብኝ ....

በጠዋት ተነስቼ ወደ ፎቶ ቤቱ ሄድኩኝ.....እንደገባው የደስደስ ያላት ቆንጅዬ ልጅ ተቀበለችኝ....ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ አድራሻዋን ለማግኘት የፈጠርኩትን ታሪክ ነገርኳት ...

"ወንድሟ ነኝ አልኳት (በስልኬ የሰርጓን ፎቶ እያሳየዋት) ስንት አመት ስፈልጋት ኖሬ ...የሰርግ ፎቶዋን facebook ላይ አየሁት ...ምናልባት አድራሻዋን ካወቃቹ ብዬ ነበር አመጣጤ እባክሽ ምትተባበሪኝ ነገር ካለ አግዢኝ" ብዬ አስተዛዝኜ ጠየኳት ....አመነችኝ አይኗ እንባ አቀረረ ...እኔም አብሬያት አለቀስኩ ...(ለምን አለቀስኩ እንጃ)

"እውነት በጣም ጥሩ ሰው ነክ..በዚህ ጊዜ እህት ይሁን ወንድም ማን ዞር ብሎ ያይካል ....እውነት የተባረክ ሰው ነክ....." አለቺኝ ባልሰራሁት ነገር በመሞገሴ ሀፍረት ቆነጠጠኝ....ቀጠለች "ከስልካቸው ይልቅ የሱን የመኖሪያ አድራሻ ብሰጥክ ይሻላል ...የሱ ቤት የፎቶ ኘሮግራም ስለነበረን አድራሻው ይኖረናል .ቆይ ልፈልግልክ "ብላ የሆነ ወረቀት ማገላበጥ ጀመረች .....ትንሽ እንዳገላበጠች ብጣቂ ወረቀት ላይ የሆነ ነገር መሞንጨር ጀመረች ...ከጨረሰች በዋላ ይኸው ብላ ከመልካም ምኞት ጋር ወረቀቱን ሰጠቺኝ ....አመስግኜ ተሰናብቼ ፎቶ ቤቱን ለቅቄ ወጣው።

በቀጥታ ወዳለችበት አድራሻ መሄድ ባላወኩት መንገድ ውስጤን ፍርሀት ለቀቀብኝ ...መሄዱን ለነገ አዘዋውሬ ወደ ቤት ተመለስኩ ። ለሊቱን ሙሉ ምን እንደምል እንዴት እንደማወራት እያሰብኩ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር አደርኩኝ ።

በጠዋት ተነስቼ ወደ ተባልኩት አድራሻ እራሴን አሳምኜ አቀናሁ ... "አካባቢው ከደረስክ ቤቱ አይጠፍክም" ብላኝ ነበር ልጅቷ ወረቀቱን ስትሰጠኝ....ደርሼ ሳየው እውነት መሆኑን አረጋገጥኩ ከብዙ ዘመናዊ ቤቶች መሀል ..ዙርያውን በግንብ እና በአደገኛ አጥር  ታጥሮ ..መግቢያው ላይ የመኖሪያ ቤት በማይመስል ግዙፉ በር ተከልሎ...ሥስት floor አከታትሎ ተጀንኖ የቆመ ትልቅ መኖርያ ቤት እንዴት ይጠፍል....ፈልጎ የመጣን ብቻ ሳይሆን በዛ ያለፈን ሰው ሁሉ ቀልብና ልብን የሚሰርቅ ውብ ቤት .....

ቤቱን ሳየው ለብር ብላ ይሆን ያገባችው ??? የሚል ጥያቄ ጭንቅላቴ ላይ አቃጨለብኝ....ስለቤተሰብም ሆነ ስለ ችግር ስታወራ ሰምቻት አላውቅም .....ስለ ምን ነበር ምናወራው እያልኩኝ ለራሴ መገረም ጀመርኩኝ.......እንዲሁ በሀሳብ እንደነጎድኩኝ የቤታቸው አጥር ስር እራሴን አገኘሁት ..... ከብዙ ማመንታት በዋላ የመጥሪያውን ደውል ተጫንኩት..አንዴ ስጫነው የልብ ልብ ተሰማኝ መሰለኝ ደጋግሜ ያለ እረፍት እጫነው ጀመረ

ከብዙ ጥሪ በዋላ የጊቢው በር ተከፈተ...እዳጠፍ ሰው አንዱን ጥግ ተለጥፌ ቆምኩኝ...ከፊት ለፊት ሰው ሲታጣ አንገትዋን አውጥታ ወደ ውጪ ልትመለከት ስትወጣ አይን ለአይን ተጋጨን ሁለታችንም በድንጋጤ. ተፍጠጥን. ያየችውን ማመን አቃታት መሰለኝ እራሷን ስታ መሬት ላይ ወደቀች

ይቀጥላል ....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
እሱ እና እሷ

እሱ

ስታጠፍ በቃላት ይቅርታ አትጠይቀኝም ሰውነቷ ነበር ይቅርታ የሚለኝ ...... አይኗ በስስት ያየኛል ...እጆቿ ሰውነቴ ላይ ይርመሰመሳሉ ...የቀረው የሰውነቷ ክፍል ሰውነቴን ሲነካኝ እግላለው...ፊቷን ወደ ፊቴ ስታስጠጋው ትንፍሿ ፊቴን ሲገርፈኝ ....ንዴቴን እረስቼ ሌላ ነገር ውስጥ እገባለሁ ...ታስገርመኛለች....ነገረ ስራዋ ሁሉ ይገርመኛል

መንገድ ላይ ስንሄድ አንዲት ወጣት ሴት በኔ አቅጣጫ ከመጣች ቦታ ትቀይረኛለች ...ለምን ብዬ ስጠይቃት ."በስተት አስመስላ ብትነካክስ" ትለኛለች ....ስቄ ዝም እላለሁ

አንዳንድ ጊዜ ደሞ እንዲሁ ከመሬት የሚነሳ ናፍቆት አለባት .... አንድ ቀን አብረን ውለን ማታ ላይ ተለያይተን ቤት እንደገባው በደቂቃ ልዩነት ደውላ በር ላይ ቆሜያለው ስትለኝ ምን ተፈጥሮ ነው ብዬ ተሯሩጬ ስሄድ ዘላ ተጠመጠመችብኝ ...ምን ተፈጠረ ብዬ ስጠይቃት "ናፈከኝ" አለችኝ ..ይውጣላት ብዬ እኔም ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት ...ለሰአታት እደተቃቀፍን ከቆየን በዋላ ...ከንፈሬን ስማኝ ቻው ብላኝ ሄደች

ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘዋት ቀንም አንዲህ ነበር ያደረገችው ...በማታ ጠርታኝ ከባለፈው ይበልጥ ጥብቅ አድርጋ ለብዙ ሰአት አቀፈቺኝ ..ስትሄድም ረዘም ላለ ጊዜ ነው ከንፈሬ ላይ የቆየችው ....በቃ ከዛን ቀን በዋላ አይቻት አላውቅም

ከተለያየን ከአመት በዋላ...ጓደኛዬ የላከልኝን ፎቶ ስመለከት ነዉ ማግባቷን ያወኩት ....ማየውን ማመን አልቻልኩም ...ከማግባቷ በላይ ያስገረመኝ ደሞ የሰርጓ ቀን ነው...ከፎቶው መጨረሻ ላይ በነጭ ቀለም በደማቅ ተፅፎበታል 12/08/14 ይላል ....ለመጨረሻ ያገኘዋት ቀን 11/08/14 ነበር ...ፎቶ ላይ እንደተፃፈው ከሆነ የተገናኘነው የሰርጓ ዋዜማ ነበር .....

ይቀጥላል .....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
Reposted from:
✍ዮ_ሚን avatar
✍ዮ_ሚን
ያልወለድነው እምቢ ብሎን ሊሆን ይችላል ... የተፋታነው ስላልተስማማን ነው... ያላገባነው ልባችን ስላልሞላ ይሆናል ...

ውጪ ያልሄድነው ፕሮሰሱ ፌል አደርጎ ነው፤ አልያም ተጓ'ቶ ነው ...
ከጎናችን ከማትጠፋው ልጅ ጋር፤ ከጎናችን ከማይጠፋው ልጅ ጋር ተለያይተን ነው።

ልጅ ያልደገምነው ወይ ኑሮ ከብዶን፥ ወይ እምቢ ብሎን፥ ወይ ተስማምተን ነው።
.
.
ገብስ ገብሱን ማውራት ልመዱ!

እንዳላየናችሁ መሄድ ሰልችቶናል። የቸኮልን የምንመስለው ሆን ብለን ነው ... ላጥ ላጥ ብለን ተራምደን ስናመልጣችሁ ደክሞን ቁጭ እንላለን ...

በናንተ ምክንያት ጉራ እና ውሸት ልንጀምር ነው። ...ስልጡን ሰው ኑሮ እና ህመም ውስጥ ሳያንኳኳ ሳያስፈቅድ ዘው አይልም...ግድ ካልሆነበት...

በርግጥ እነሱ አይሰሙም እንደው ልፉ ቢለን ነው 😀
© Adhanom Mitiku

https://t.me/yomin1_2

Records

16.05.202523:59
10.5KSubscribers
30.04.202523:59
750Citation index
13.05.202516:39
1.5KAverage views per post
13.05.202516:39
1.6KAverage views per ad post
29.03.202523:59
56.82%ER
10.09.202423:59
23.32%ERR
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
OCT '24JAN '25APR '25

Popular posts ከእለታት....📖📚📖📚📖📚

13.05.202518:41
✨✨✨ፍቅር ቅብ ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ብቻ ቀርቶታል....🥳

በትዕግስት ስላነበባችሁልኝ ምስጋናዬ በብርቱ ነው.......

እያቆራረጥኩ እንዳስመረርኳችሁ አውቃለሁ.....ታሪኩን የጀመርኩ ሰሞን የሚዘለል ቀን ካለ እየነገርኩ የሚለቀቅበትን ቀን ሳሳውቃችሁ  እንደነበር ይታወቃል.....በመሀል ግን የምዘለው ቀን የምፅፍበትን ቀን ማሳወቅ አሻፈረኝ አለ.....

በስራ ምክንያት መልክአ ምድሩ ለአይን እንጂ ለጤና የማይመች ቦታ ላይ የምኖር ላጤ እንደሆንኩ ልብ በሉሉልኝ.....በ'አለማየሁ ዋሴ እሸቴ' ሜትራልዮን በተሰኘ መፅሀፉ ላይ በአረንጓዴነቷ የተሽሞነሞነችው "ሚዛን ቴፒ" ውብ አይነ ግቡ ተፈጥሮ ያላት ብትሆንም የወባ መናሀሪያም ጭምር ናት......

"ላልተወሰነ ጊዜ ፍቅር ቅብ የለም" ብሎ ማለት አልቻልኩም.....እናንተ ስታነቡት ከምትደሰቱት በላይ እኔ ስፅፈው እደሰታለሁ.....እኔ ራሴ እንደዚህ ሳልፅፈው መቆየቱ ምቾት አይሰጠኝም..... "ዛሬማ መድሀኒቴን ቶሎ ወስጄ ተኝቼ ለሊት እፅፈዋለሁ" የምልበት እና ራሴን ጠዋት ስራ ለመሄድ ስንተፋተፍ የማገኝበት ቀን ከአንድ ጀምሮ ሶስት ቀን ቆጠረ....(አርብ እለት ማታ ማስታገሻ ወስጄ እየፃፍኩ ምን ሰአት እንቅልፍ እንደወሰደኝ ሳላውቅ ከለሊቱ ስምንት ሰአት ነቅቻለሁ.....)

ምን ያሀል እየጠበቃችሁኝ እንደሆነ ባውቅም ምን ቀን እንደምድን ሳላውቅ  በዚህ ቀን አደርሳለሁ ማለት አልቻልኩም.....በተጨማሪም እየታመምኩም ቢሆን ያለ እረፍት ለመስራት የተገደድኩት መደበኛ ስራዬ እና ለራሴ ራሴ ብቻ መኖሬ ከእቅድ ውጪ አደረገኝ.....(በጣም የተለመደ ስለሆነ ወባ ማንም አሰሪ ከቁምነገር ቆጥሮ እረፍት አይሰጥም....ጤነኛ መስሎ ከሚንቀሳቀሰው ህዝብ 75%ቱ የወባ ክኒን እየቃመ ነው.....)....

በተጨማሪም ለመፃፍ እጅ ብቻ ሳይሆን የተረጋጋ ጭንቅላትም አስፈላጊ ስለሆነ እስክረጋጋ መጠበቅ ነበረብኝ....በዚያ ስሜት ውስጥ ሆኜ ብፅፈው ራሱ ለአይናችሁ የሚመጥን ስራ እንደማይሆን ተሰማኝ....(የመጨረሻዎቹ ክፍላት አእምሮዬ ውስጥ እንጂ ወረቀት ላይ አልሰፈሩም ነበር....).....በመሀል የማደርሳችሁ አጫጭር ክፍላት የመጨረሻውን ክፍል በአንድ ከፍ አድርገውታል.....ስለዚህም ቀድሞ ባልኩት 20 ክፍል ሳይሆን በ21 ክፍል ለማጠናቀቅ ተገድጃለሁ...

እዮብን የሚያስንቅ ትዕግስት ለታገሳችሁኝ አንባብያን ከወገቤ ሸብረክ ከአንገቴ ጎንበስ ብያለሁ.....አመሰግናለሁ።

ነገ የመጨረሻው ክፍል አብባችሁ አስተያየታት መስጠታችሁን አትርሱ....እጠብቃችኃለሁ.....ቆዩልኝ💙
27.04.202517:44
✨✨ፍቅር ቅብ-9✨✨

እንደ ትናንት ትዝ ይለኛል ስምንተኛ ክፍል ነበረ....ከእስፖርት  ክፍለ ጊዜ መልስ ምሳቃዬ መማሪያ ጠረጴዛዬ ላይ በግላጭ ተቀምጧል....እየተንደረደርኩ ሄጄ ሳነሳው ገለባ ሆነብኝ.....ፈራ ተባ እያልኩ ስከፍተው በግዢ እንጀራ እና በአባቴ ምስር ያሸበረቀችው ምሳቃዬ ሌጣዋን ነች....ድንጋጤዬን ሳስታውሰው ምግብ የተበላብኝ ሳይሆን የአባቴን መርዶ የተረዳሁ ነበር የምመስለው።

ደንግጬ ብቻ ብተወውም መልካም ነበር...ጡጦውን እንደተቀማ ህፃን እሪሪሪሪ ብዬ አለቀስኩ.....ያኔ ነው ሀኒ ወደ ህይወቴ የገባችው.....

የበላብኝን ልጅ ፈልጋ ለማግኘት የፈጀባት ረፍት ሰአት ብቻ ነበረ.....ፊት ለፊቴ አምጥታ እንደ እባብ ስትቀጠቅጠው ፊቴ ላይ የነበረውን ደስታ አስታውሳለሁ...

ያን እለት ምሳቃዋን አጋርታኝ ጓደኝነታችንን ሀ ብለን ጀመርን.....'ጓደኛሞች እንሁን' ሳንባባል ጓደኛሞች ሆንን....እንዴት ብለን እንደተግባባን....ምን ሰአት ነብሶቻችን እንደተሳሰሩ ሁለታችንም አናውቅም።

*

ዛሬ ፊት ለፊቴ ተቀምጣ አፍ አፌን የምትለኝ ሴት ግርድፍድፍ ቃሌን አቃንታ የምታስተጋባልኝ....ገበና ከታቼ....ጓዳዬ....ጓ'ደኛዬ እንደሆነች ማሰብ ከበደኝ.....

"case አለ እንዴ" አለ ሸዋፈራሁ ደስአለኝ....ጉዳይ ቢኖራትስ ገና ፀጉር ይኑረው አይኑረው ላላወኩት ወንድ አናት አናቴን ማለት አለባት....ደግሞ እኔ የማላውቀው ጉዳይ ከመቼ ጀምሮ።

****

በአንድ ትሪ የቀረበልንን ቋንጣ ፍርፍር እና ዶሮ ቀና ሳልል መብላት ጀመርኩ....እኔ እና ሀኒ ስንበላ አንተያይም.....ምግብ እና ጓደኝነት ይለያያል ባይ ነን.....አንጎራረስም.....ይቺን ያዙልኝ አንጎራረስም።

"መኬ ግን ይሄ ወስፋታምነትህ መቼ ነው ሚለቅህ".....ካለች በኃላ እብድ የሚያህል ጉርሻ ወደ አፉ ሰደደች.....ሁለቱ ጉንጮቹ እንደፊኛ ተነፍተው ጥርሱ አልታዘዝ ያለው ይመስል ለሰከንዶች ከቆየ በኃላ ነው ተንፈስ ያለው....ጉርሻ ሳይሆን የግድያ ሙከራም ይመስል ነበር።

"ሀኒ በቃ ካላጎረስሽ አይሆንልሽማ...."....አለ ጉርሻውን በውሀ አለቃልቆ ከዋጠ በኃላ....ይሄን ጊዜ እኔ ጋር ያለችው ሀኒ እና እሱ ጋር ያለችው ሀኒ  የተለያዩ ሰዎች እንደሆኑ ተገለጠልኝ....

"ርቀትሽን ጠብቂ እድል...."....አልኩኝ በሆዴ።

'አይኗ ካንተ ላይ አይነቀልም....እንስፍስፍ ብላ ነው የምታይህ....አውቃለሁ ሰው ሲያፈቅር ምን እንደሚሆን....በተለይ ሴት ስታፈቅር....'....የሀኒ አሰተያየት እና አኳሀን አሌክስ አብርሀም መፅሀፍ ላይ ያነበብኳትን ፅሁፍ አስታወሰኝ....አይኗ ፍቅር አለበት....ድርጊቷ የተጠና ባይሆንም እንከን አልባ ለማድረግ እንደለፋችበት ያስታውቃል።

በየመሀሉ መታጠቢያ ቤት እየሄደች የምታረጥበው ከንፈሯ እና መላ ምትለው ፀጉሯ  ላይ ሳይቀር ፍቅር አለ....እኔ ሳውቃት እጇን አነባብራ ጥፍሯን የምታፍተለትለው አስተማሪ መልስ ሲጠይቃት ብቻ ነበር....ጭንቀት ከእግር እስከራሷ የሚወራት....ትንፋሽ የሚያጥራት ፕረዘንቴሽን ላይ ነበረ.... የተቆራረጠ ድምፅ ከተገለጠ ቅናት ጋር ያየሁት ዛሬ ነው....አሁን።

አስር አስር ፍቅረኞች ብንይዝ አይቀየርም ያልኳችሁን የአብሮነት ጊዜያችንን የጣሰው አንዱ መክብብ ነው....ከማውቃቸው የተፈቀደለት እርሱ ብቻ ነው....

"በህይወቴ የምጠላው ነገር ቢኖር በወንድ ምክንያት ከሴት ጓደኛ ጋር መናቆር ነው....ለምን ጥርግ አይልም ጓደኝነት ይበልጣል...."....ያለችኝ በቅርቡ ነበር....

"እድሌ ስለ ዮኒ አጫውችን እስኪ እንዴት ሆናችሁ...ብታይ መኬ እንዴት ደስ የሚሉ ጥንዶች መሰሉህ"....ስትል በንዴት አፍንጫዬ ራሱ ቀላ....በዮናስ ጉዳይ አይኔን ያስከፈተችኝ ሀኒ ናት ይቺ....?....እንዳልኳችሁ ይቺን ሀኒ አላውቃትም።

በጀርመንኛ 'ፍቅረኛ አላት አይንህን አንሳ' ማለቷ ነው....ሀኒ በወንድ ፊት pick me ጨዋታ ስትጫወት ሳያት ለመጀመሪያ ጊዜ ነው....ለድርጊቷ እንዴት ያለ ምላሽ እንደምሰጥም አላውቅም.....አኳሀኗ ያልሆነ እልህ ውስጥ እንዳይከተኝ እየፈራሁ በደፈናው "ደህና ነን" ብቻ አልኳት....

"ይሄ ቅዳሜን ጠብቆ ካላወጣሁሽ የሚለው ልጅ አለ.....?.....".....ስትለኝ ንዴቴ ፀጉሯን እንዳያስነጨኝ እየተጠነቀቅኩ ደረቅ ፈገግታ አሳየኃት.....'ምን ነካሽ ሀኒ' መሆኑ ነው.....በእርግጥ የሆነ ነገሬ 'የእሷን ጉድ ለምን አታፍረጠርጪውም' ሲለኝ ነበረ.....የሆነ ነገሬ ደግሞ 'እንዲያ ካደረግሽማ እሷኑ ሆነሽ አረፍሽው' ሲለኝ ተውኩት እንጂ።

"ወንድ ልጅ የተያዘች ሴትን መጠጋት ላይ እንብዛም ነው....ልቧ ሙጫ እንደሆነ ያውቃል....ድንግልናሽን የሚፈልገው ትግል አምሮት ብቻ አይምሰልሽ....አብዛኛዋ ሴት ልቧን  ከተኛችው ወንድ ጋር ታጣብቃለች....እዚም እዚያም ጋር የተበታተነ  ልብ ርጋፊው ከውስጥ አይገባም....አለ አይደል ብዙ እጅ የነካካው አበባ መአዛው እስከዚም ነው.....".....ያለቺኝ እሷ ነበረች.....

ከጅምሩ እኔ በመምጣቴ የተቆጨች ትመስላለች.....እውነቱን ለመናገር መክብብን ልቧ እንደከጀለው ለማወቅ ደይቃዎች አልፈጁብኝም....ቀድማ ብታሳውቀኝ እንደ ሎጥ ዘመን ዘር ሊጠፋ ሆኖ አንድ ያንጠለጠለ እርሱ ብቻ ቢቀር በእንጨት አልነካውም ነበር.... የተጠቀመችው ግን ተቃራኒውን ነበር....እኔን በእሱ ፊት እፍኝ ማሳከል.... በፊቱ ልታሳንሰኝ ስትሞክር ፍላጎቴ ናረ.... ውበቱ  ባሳነሰችኝ ቁጥር ጎላ.....መላጣ ይሁን በራ ያልታወቀ አናቱ ሚዶ የተሰካበት ጎፈሬ መስሎ ታየኝ።

አላለቀም....

✍ሸዊት

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
04.05.202507:43
ዛሬ በቀን ሁለቴ ነው🥳🥳🥳ለትናንቱ በጣም ይቅርታ🙏
13.05.202518:33
"ምንም አይነት ነገር ቢመጣ ከዚህ የሚከብድ አይመስለኝም....ከዛን ቀን በላይ ከባድ ምሽት የሚኖረኝ አይመስለኝም...እጃችሁን ይዤ እያለቀስኩኝ ነበር...በተኛችሁበት ይቅርታ እየጠየቅኳችሁ ነበር....በብርሀን አይናችሁን እያየሁ ማድረግ አልቻልኩም...."ጥያቹ ልሄድ ነው" ለሚል መርዶ የሚሆን ይቅርታ ይኖራል...?....."ካሁን በኃላ አይኔን ስለማታዩት ይቅር በሉኝ..."....ይባላል...?

ለረጅም ሰአት እያየኃችሁ ነበር ....ስትተኙ ደግሞ ይበልጥ ታሳሱ ነበር.....እንቅልፋችሁ ላይ እምነት ነበረ....ስትነቁ ሁሉም ነገር እንደሚቀጥል የሚነግራችሁ እምነት....

"ለምን እውነቱን አልነገርኳቸውም...?"....የምልበት ቀን አበዛዙን አታውቂም እድሏ.....የሆንኩትን አታውቂም እድሏ....ስንት ቀን እግሬን አንስቼ እንደመለስኩት አታውቂም ልጄ.....አንዴ አቅፌያችሁ ለመመለስ የፀለይኩትን ፀሎት አታውቂም ልጄ....ለልደታችሁ ሻማ እንደማበራ....ፎቶአችሁን በትልቁ እንደሰቀልኩ... የብቻ ቤቴ አድባር እናንተ እንደሆናችሁ አታውቂም የኔ ልጅ....

ከአመታት በኃላ ተመልሼ ልመጣ ሻንጣዬን ሸክፌ ነበር....እንዳትጎዱብኝ ብዬ ተውኩት እንጂ......ይቅር በሉኝ ልጆቼ....ይቅር በሉኝ....አልመጣም አትጠብቁኝ....እወዳችኃለሁ።".....ብሎ የሚዘጋ ደብዳቤ አንብቤ ለእህቴ ሰጠኃት....ስለ እናቷ የማወቅ መብቷን ከዚህ በላይ ልጋፋ አልፈለግኩም.....

'መምጣቴ ይጎዳችኃል' ነው ያለችው አይደል....! ...አሁን ማን ይሙት ለዘመናት ከእናት መለየት ቆዳ ተልጦ ጨው እንደተነሰነሰበት ሰውነት እንደሚለበልብ ጠፍቷት ነው....?...እንደዚህ ይደረጋል....?....አልመጣም ለማለት ይሄ ሁሉ ጊዜ ይጠበቃል.....

**

እውነቱ ግን ራስ ወዳድ መሆኗ ላይ ነው...የልጆቿን እምባ እና ድንጋጤ በአይኗ ማየት የሚፈጥርባትን ከባድ ስሜት ለማምለጥ ነው...ሁላችንም እንዲህ አይደል የምናደርገው....እኛ ሳናይ ስለሚወርዱት ዘላዎች ማሰብ አንፈልግም....ብቻ ማምለጥ....ብቻ መፈርጠጥ...

ብናምንም ባናምንም ሁላችንም ስለሚጎዳው ስሜታችን ስናስብ እንደደነበረ በሬ የሚያስፈረጥጥ ራስ ወዳድነት አለብን...

✍ሸዊት

የመጨረሻው ክፍል ነገ✨

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
Reposted from:
✍ዮ_ሚን avatar
✍ዮ_ሚን
09.05.202507:15
ያልወለድነው እምቢ ብሎን ሊሆን ይችላል ... የተፋታነው ስላልተስማማን ነው... ያላገባነው ልባችን ስላልሞላ ይሆናል ...

ውጪ ያልሄድነው ፕሮሰሱ ፌል አደርጎ ነው፤ አልያም ተጓ'ቶ ነው ...
ከጎናችን ከማትጠፋው ልጅ ጋር፤ ከጎናችን ከማይጠፋው ልጅ ጋር ተለያይተን ነው።

ልጅ ያልደገምነው ወይ ኑሮ ከብዶን፥ ወይ እምቢ ብሎን፥ ወይ ተስማምተን ነው።
.
.
ገብስ ገብሱን ማውራት ልመዱ!

እንዳላየናችሁ መሄድ ሰልችቶናል። የቸኮልን የምንመስለው ሆን ብለን ነው ... ላጥ ላጥ ብለን ተራምደን ስናመልጣችሁ ደክሞን ቁጭ እንላለን ...

በናንተ ምክንያት ጉራ እና ውሸት ልንጀምር ነው። ...ስልጡን ሰው ኑሮ እና ህመም ውስጥ ሳያንኳኳ ሳያስፈቅድ ዘው አይልም...ግድ ካልሆነበት...

በርግጥ እነሱ አይሰሙም እንደው ልፉ ቢለን ነው 😀
© Adhanom Mitiku

https://t.me/yomin1_2
20.04.202517:38
✨✨ፍቅር ቅብ...3✨✨

"በናትሽ ሀኒ አትቀልጂ...ጭንቅ ብሎኛል..."...ስላት የማያባራ የመሰለኝ ሳቋን ባንዴ ቁርጥ አደረገችውና ማውራት ጀመረች...

"ይኧውልሽ ዮናስ ትዳር በትክክል ምን ማለት እንደሆነ የሚያውቀው ነገር የለም...'ለምን ማግባት ፈለግክ' ተብሎ ሲጠየቅ ውስጡ ቢመልስ ኖሮ መልሱ 'የአልጋ ላይ ቡጊ ቡጊን የመሰለ ምን አለ...ያለ ገደብ እሱን ለማስነካት ነው' ነበር የሚሆነው..ግን የሚመልሰው አፉ ነው...'ስለምወድሽ ስለማፈቅርሽ...ማሬ ቅብርጥሴ' እያለ ይጠግርሻል....አይንሽን ክፈቺ...ከቃላቱ በላይ ድርጊቱን እይው...ላንቺም ቢሆን በባዶ ሆድ ነጋ ጠባ አልጋ ላይ መጨፈሩ ጥሩ አይደለም...u know energy የሚባል ነገር አለ...በባዶ ሆድ ስራ ካካካካካ...."...የተለመደው ሳቋን አስከተለች።

እኔ ውስጤ በጥያቄ መራወጥ ጀመረ...
ስራ ላይ የሌለ ትዕግስት ለኔ ከየት መጣ...ለሌላ ሰው የሌለው አክብሮት ለእኔ ከየት ተፈበረከ....የሚበላው አጥቶ እርሱን ለሚለምን ህፃን የሌለ ርህራሄ ለእኔ ከወዴት ተገኘ....?....በጥያቄ ታጨቅኩ....

****

ሶስት ቀን ከሞላው የልብ ካልሆነ ኩርፊያ በኃላ የሉሲ እኩያ የሚመስል ካፌ ቀጠረኝ...ዛሬ ስለዚህ ግንኙነት በግልፅ ላወራው ነበር ሀሳቤ....በአልጋ ላይ ትርኢት እና በውብ ቃላቶች ብቻ የታጀበው ግንኙነት እንዲያበቃ አልያም መስመር እንዲይዝ...

"እድሌ..."

"እድልክ አይደለሁም...እድል ካልከኝ ይበቃል...."...ከዚህ አጠራሩ በኃላ ምን እንደሚከተል ስለማውቅ እየተጠነቀቅኩ ነው...በኔ ቤት።

የፈራሁት አልቀረልኝም ተጠጋኝ...ከእርሱ ሌላ ማየት እስከማልችል ድረስ ቀረበኝ...ከዛም የምወድለትን አስተያየት አየኝ...እጄን አጥብቆ ይዞ ወደራሱ ሲያስጠጋኝ አር የነካው እንጨት እንደያዝከኩ ነገር መነጨቅኩት...'ጎበዝ እድል እንዲህ ነው መጀገን' ብዬ ራሴን አበረታታው...ቢያንስ እናውራ አይባልም...?...አኩርፌ ነበር እኮ...

"እድሌ ይገባኛል አጥፍቻለሁ...በጣም እያበሳጨሁሽ እንደሆነ ይገባኛል...ግን እመኚኝ እለወጣለሁ...በቅርቡ አንድ አሪፍ ስራ አግኝቻለሁ...እንደሚሳካ አልጠራጠርም...ከዛ እንጋባለን...."

"ኧረ ጉድጓድ ግባ"....በሆዴ ነው...በአፌ ምንም አልተነፈስኩም...ግን ምናለ ትንሽ ራቅ ብሎ ቢያወራ...የትንፋሹ ሙቀት እስኪሰማኝ ድረስ ተጠግቶኛል...ከአይኑ ግጭት እንዳልወድቅ እየተጠነቀቅኩ ነው....

"አፈቅርሻለሁ...አፈቅርሻለሁ...ሌላውን እርሺው..."...ካለኝ በኃላ ገፄን ገፁ ውስጥ አገኘሁት...አላስገደደኝም...ግን አስገድዶኛል...ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ነው...ግራ መጋባት አለው...መወሰንም አለመወሰንም...አዎ ከዚህ በኃላ በ'አፈቅርሻለሁ' ትርክት ላለመቀጠል መወሰኔን ላውጅ ነበር አመጣጤ...በነበር ቀረ እንጂ...

"ክክክ-ክክክ".....የሆነ አጠገባችን ያለ  ሰው ጉሮሮውን ሲጠራርግ ነው ከንፈሮቻችን ወደየ ቦታቸው የተመለሱት...

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ገና ስሙ ሲጠራ ያ ለግላጋው ቁመቱ አይታወሰኝም...ከዛ ይልቅ የሚጎላብኝ የአክሱሙ ርዝመት ነው...ዘናጩ ዮናስ አእምሮዬ ውስጥ የለም...ራቁቱን ቅልብጭ ይልብኛል...

ዮናስ ሲባል ሰው ሁሉ የሚደነግጥለት መልኩ እና ጆሮ ሚጠልፈው ድምፁ ጭራሽ አይታወሰኝም...ከጠራው ቆዳው በላይ በላብ የተጠመቀ ሰውነቱ ነው የሚመጣልኝ.....ከምወድለት ድምፁ በላይ አልጋ ላይ ስንጨፍር የሚያወራቸው ትርጉም የለሽ መዘላበዶች እና ቅስቻዎች ናቸው ትውስታዎቼ....

ገና "እድሌ" ከማለቱ ከስሜ በላይ ኩርፊያዬን የሚያስረሳ አለም ውስጥ እንደሚከተኝ በስውር ስለሚነግረኝ ነው ከራሴ ጋር ትግል ውስጥ የሚጨምረኝ....የሚያንቀለቅለኝ መጨረሻዬ ሁለት በሁለት የሆነች ጎጆ ውስጥ እንደሚሆን ስለማውቅ ነው....በራሱ ሜዳ... ራሱ ፈረስ ሆኖ...ራሱ ጋሪ ሆኖ... ራሱ ነጂ ሆኖ ነው የሚሾፍረኝ...

ከባነንኩ በኃላ ተበሳጨሁ...'ለዚህ ነበር ይሄ ሁሉ ፉከራ'...ጠየቅኩ ራሴን...በቃ በቅፅበት ለምረሳው ነው እንዲህ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ ደግሜ።

"ይቅርታ ከዚህ ካፌ ብዙም ሳትርቁ ፔንሲዮን አለ...."....አለ የቀሰቀሰን አስተናጋጅ...ጉሮሮ አጠራረጉ ግን ይቺን ለመናገር ብቻ አይመስልም ነበር...ነብሳቸውን ይማረውና የክቡር ዶክተር ጥላሁን ገሰሰ ጉሮሮ እንኳን ያን ሰረቅራቃ ድምፅ ጀባ ለማለት እንደዚህ የሚጠራረግ አይመስለኝም።

"እሺ እሺ ሂሳብ አምጣልን..."....እኔ የሆነ ቦታ ለመሄድ ስጣደፍ በማወጣው ድምፅ ከአስተናጋጁ ጋር ያወራል...እኔ ሽምቅቅ እንዳልኩ አለሁ...

"የኔ ጌታ ምንም አላዘዛችሁም እኮ...."....ከማለቱ ሳቄ አመለጠኝ...አስተናጋጁም ከእኔ ጋር ተደመረ...የዮናስ ግንባር ላይ ችፍ ያለው ላብ የሀፍረት ብቻ አይመስልም...አይኑም በመደፍረስ አገዘው...ከመርበትበቱ የተነሳ ላልተጠቀምነው ነገር ቲፕ ሰጠ...ባሁኑ አልሳቅኩም ጤንነቱን ጠረጠርኩ እንጂ.....

ከካፌው ወጣንና ከእኔና እሱ ውጪ ደንበኛ ከሌለው ቁርቁዝ ካለ  ፔንሲዮን ገባን...የተለመደው እርግጫ...የተለመደውን ጭፈራ ጨፈርን....ይሄን ጭፈራ ለሳምንት ቀጠልን...እንዳይደብረኝ ብሎ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ፖዝሽን መቀየር ብቻ ነው...ያኔ አንድ ጭፈራ የነበረው ወደ ብሄር ብሄረሰቦች ጭፈራ ይቀየራል...'በባዶ ሆድ ስራ' አለች ሀኒ...

***

✍ሸዊት

ይቀጥላል....react እያረጋችሁ

https://t.me/shewitdorka
05.05.202519:33
ረጅም ፀሎት ኖሮኝ አያውቅም.....ይሄ በህይወት ዘመኔ የፀለይኩት ሁለተኛ ፀሎቴ ነው.....አንደኛው "እናቴን ቤቷ መልስልኝ...."....ነበር.....

ውጤቴ እስኪደርስ ከዚህ በፊት ተሰምቶኝ የማያውቅ ዝብርቅርቅ ስሜት ተጫወተብኝ.....

የምፅአት ቀን እራሱ እንደዚህ የሚርቅ አይመስለኝም።

"እድል ሰጠኝ......".....ተጠራሁ።

አላለቀም.....

✍ሸዊት

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
30.04.202518:27
ከሁለት አመት በፊት ይመስለኛል...እኔና አንድ የጊቢ ጓደኛዬ ከጥናት ብሬክ እየወሰድን ነው....እኔ ያን ሰሞን ከፍተኛ የሆነ የእንቅልፍ አባዜ  ተጠናውቶኝ ስለነበር አባብላም ሽልማት አዘጋጅታም ነበር ላይብረሪ ያስመሸችኝ....(ሽልማቴ ምን መሰላችሁ የአስቱ ግጥም የተሰበሰበበት ፎልደር😊)

እንዲያም ሆኖ በየ ሰላሳ ደይቃው ወጣ ብለን ፊታችን እንታጠብ ብዬ እየተነዛነዝኩ ነው....ከዛንላችሁ በአንደኛው ጥያቄ መጠያየቅ ጀመርን.....

"ባልሽ ምን እንዲኖረው ትፈልጊያለሽ....?..."....አለችኝ።.....እኔም "አዳማጭ መሆን አለበት....በተለይ ፅሁፎቼን ሳነብለት....የምፅፈውን ነገር ወደደም ጠላም መስማት አለበት.....".....ሌሎችንም ለእናንተ የማይነገሩ ቅድመ ሁኔታዎቼን አሳወቅኳት(በሰአቱ መብሰል ይቀረኝ ነበር መሰለኝ ቅድመ ሁኔታዎቼ በዙ😁)

አሁን እዚህ እናንተ ጋር ስላመጣኝ ቅድመ ሁኔታ ልናገርና ልጨርስ።

"አፍንጫው ትልቅ መሆን አለበት....ግዴታ ነው አልኳት" ደንደን ብዬ....

"እንዴ ለምን ይሄን ያሀል...."

"look at my nose....".....ስላት ገባትና ፍርፍር ብላ ሳቀች።

"ልክ ነሽ ሸዊቴ በዚ አፍንጫሽ አፍንጫ የሌለው ካገባሽ የልጃችሁ አተነፋፈስ አደጋ ላይ ነው.....".....አለችኝ።

ይሄን ሁሉ ምዘበዝበው እኮ የአህያ ጉንፋን ይዞኝ ከዚችውም የአፍንጫ ቀዳዳ አንዱ ኤክስ አርጎ እየታገልኩ ፍቅር ቅብን ተረጋግቼ ታይፕ እና ኤዲት ማድረግ አልቻልኩም የሚለውን ለመናገር ነው....🥹

መቼስ እኔ ከአፍንጫዬ ጋር ስራ አትስራ እሰጣ ገባ ውስጥ ሆኜ ለእድል አታደሉም አይደል....አዎ😁።

ነገ እክሳለሁ ወገኖቼ....🙏

መልካም አዳር ተመኘሁላችሁ😊

ሸዊት ነበርኩ።
10.05.202508:06
እሱ እና እሷ

እሱ

ስታጠፍ በቃላት ይቅርታ አትጠይቀኝም ሰውነቷ ነበር ይቅርታ የሚለኝ ...... አይኗ በስስት ያየኛል ...እጆቿ ሰውነቴ ላይ ይርመሰመሳሉ ...የቀረው የሰውነቷ ክፍል ሰውነቴን ሲነካኝ እግላለው...ፊቷን ወደ ፊቴ ስታስጠጋው ትንፍሿ ፊቴን ሲገርፈኝ ....ንዴቴን እረስቼ ሌላ ነገር ውስጥ እገባለሁ ...ታስገርመኛለች....ነገረ ስራዋ ሁሉ ይገርመኛል

መንገድ ላይ ስንሄድ አንዲት ወጣት ሴት በኔ አቅጣጫ ከመጣች ቦታ ትቀይረኛለች ...ለምን ብዬ ስጠይቃት ."በስተት አስመስላ ብትነካክስ" ትለኛለች ....ስቄ ዝም እላለሁ

አንዳንድ ጊዜ ደሞ እንዲሁ ከመሬት የሚነሳ ናፍቆት አለባት .... አንድ ቀን አብረን ውለን ማታ ላይ ተለያይተን ቤት እንደገባው በደቂቃ ልዩነት ደውላ በር ላይ ቆሜያለው ስትለኝ ምን ተፈጥሮ ነው ብዬ ተሯሩጬ ስሄድ ዘላ ተጠመጠመችብኝ ...ምን ተፈጠረ ብዬ ስጠይቃት "ናፈከኝ" አለችኝ ..ይውጣላት ብዬ እኔም ጭምቅ አድርጌ አቀፍኳት ...ለሰአታት እደተቃቀፍን ከቆየን በዋላ ...ከንፈሬን ስማኝ ቻው ብላኝ ሄደች

ለመጨረሻ ጊዜ ያገኘዋት ቀንም አንዲህ ነበር ያደረገችው ...በማታ ጠርታኝ ከባለፈው ይበልጥ ጥብቅ አድርጋ ለብዙ ሰአት አቀፈቺኝ ..ስትሄድም ረዘም ላለ ጊዜ ነው ከንፈሬ ላይ የቆየችው ....በቃ ከዛን ቀን በዋላ አይቻት አላውቅም

ከተለያየን ከአመት በዋላ...ጓደኛዬ የላከልኝን ፎቶ ስመለከት ነዉ ማግባቷን ያወኩት ....ማየውን ማመን አልቻልኩም ...ከማግባቷ በላይ ያስገረመኝ ደሞ የሰርጓ ቀን ነው...ከፎቶው መጨረሻ ላይ በነጭ ቀለም በደማቅ ተፅፎበታል 12/08/14 ይላል ....ለመጨረሻ ያገኘዋት ቀን 11/08/14 ነበር ...ፎቶ ላይ እንደተፃፈው ከሆነ የተገናኘነው የሰርጓ ዋዜማ ነበር .....

ይቀጥላል .....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
11.05.202519:09
✨✨ፍቅር ቅብ-19✨✨

"ሰርፕራይዙን አበላሸሁት አይደል......".....አለቺኝ ስልኩን ከዘጋች በኃላ......

ግራ ገባኝ.....እሱን አግኝቼ እሷን ላጣት ነው....?...አንዱን አጥቶ ሌላ ማግኘት ህይወት ሊባል ይችላል....?.....ብሎልኝ ልቤን የሞላው ሰው ባሌ ከሆነ የሰርጌ እለት በግራ ባሌን አድርጌ በቀኝ የማደርጋት ስር ሚዜዬ ሀኒ ላትሆን ነው......?.....አጥንት የሚሰረስር ህመም ውስጥ ሆና ታጅበኝ ይሆን.....በሙሉ ልቧ "ይዟት በረረ....".....እያለች ትሸኘኝ ይሆን.....

ምን አለ እንዲህ ባታደርግ.....ምን አለ እንደመጀመሪያው ቀኗ ብትሆን.....ምን አለ ዛሬም እንደትናንቱ እንድታዘባት ብታደርግ.....በ"እድለኛ" ነሽ ፈንታ "መሰሪ ነሽ" ብትለኝ.....ምናል እንዲህ ባታደርግ.....አንገቷን ሰበር አድርጋ ባታለቅስ ምን አለበት.....ምናል እምባዋ እልህ ቢኖረው....ምናል አንድ ሁለት ስድብ ብትሰድበኝ...."ማን ስለሆንሽ ነው" ብትለኝስ.....

"አደራሽን ደግሞ እንዳላወቀ ሁኚ....ብዙም አትዘንጪ.....".....አለችኝ ስንሰነባበት.....ሳቅ ነገር ብትልልኝም ለፈገግታዋ መልስ አልሰጠሁም......ጭንቅላቴ ተወጥሯል....እያሰብኩ ነው.....ይሄ ነው የማልለው ከባድ ስሜት እየተጫወተብኝ ነው.....

"ስለ ባሌ የማወራው ለሀኒ እና ለንሰሀ አባቴ ብቻ ነው" የሚል መንግስት ያላፀደቀልኝ ህግ ነበረኝ....አሁን ስለመክብብ ምንድነው የምነግራት....ሌላው ቀርቶ የዛሬውን ቀን አብረን መፈንደቅ አልነበረብንም....ግማሽ ሳቅ ግማሽ ሳግ ይዤ ነው የፍቅር ጥያቄውን የምቀበለው....?

መታደልም አለመታደልም ነው ይሄ..... ዱባ እና ክትፎ ቀላቅሎ እንደመብላት ያለ ነው ይሄ....የፆም ቋንጣ እንደመስቀል ነው ይሄ.....ባንድ እግር ቤተስኪያን ቆሞ እንደማስቀደስ ባንዱ ደግሞ መሸታ ቤት ቡጊ ቡጊ እንደመጨፈር ግራ የገባው ነገር ነው.....በአንድ አይን የደስታ እምባ ባንዱ ደግሞ ዋይታ ነው ይሄ....

እሺም እምቢም ብለው ደስታ አለው....የቱ ደስታ ይበልጣል....?

***

አመሻሽ ላይ ስልኬ ጠራ.......መክብብ።

"ሄለው እድሏ......"......አለኝ ፍቅር ባለበት ድምፅ....... እድሏ ብሎኝ አያውቅም.....እድሏ  የምትለኝ እናቴ ብቻ ነበረች።

"አ....አቤት.....".....እንደእስከዛሬው ወዬ ማለት ሀኒን መክዳት መሰለኝ....

"የት ነሽ...."......አለኝ ወዬ አለማለቴን ከቁብ ሳይቆጥር......

"ቤት" አልኩት....ቤቴ ነበርኩ.....በቴሌቭጅን መስኮት ላይ በማያቸው በሚስቁ ሴቶች እየተደመምኩ....ይስቃሉ.....በጣም ይስቃሉ.....ይዝናናሉ.....ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ውስጥ ገብተው እንደ ንግስት ይስተናገዳሉ....'ለአንድ ቀን ኖሬው ብሞትም አይቆጨኝ' የሚያስብል ኑሮ ለአንድ ቀን ይኖራሉ።

"እራት እንብላ"....አለኝ....ድምፁ ላይ መሳቀቅ ነበር......እንዳልገባው ሆኜ "ብሉ" ልለው ነበር.....ውስጤን ደስ አላለውም.... እሱ ያጠፋው አንድም ጥፋት አለመኖሩን ለማሰብ ሞከርኩ.....ስመኘው የነበረው ነገር እንደነበር አስታወስኩ.....ሰውየው መክብብ እንደሆነ አስታወስኩ...."መክብብ የወራት ክስተት ነው.....ሀኒ ግን የዘመናት......".....አለኝ ስሙን የማላውቀው የጭንቅላቴ ክፍል.....

በደስታዬ መደሰት አለመቻሌ አብከነከነኝ.....

"እና ምን አልሽኝ.....".....ጥያቄውን አስታወሰኝ።

"እሺ".....አልኩትና ወደሚያናውዘኝ ጭንቅላቴ ተመለስኩ።

***

"ወድጄሻለሁ...."......አለኝና ኮፍያውን አውልቆ በራው ላይ ችፍ ያለውን ላብ በሶፍት አደራረቀ.....ፊት ለፊታችን ያስቀመጥነውን ምግብ ቆልለን.....ብዙ ዝባዝባዝንኬ እንደማልወድ የነገረችው ሀኒ መሆን አለባት....መግቢያም መንደርደሪያም የሌለው እንቅጭ ነው የነገረኝ....

የእጁን ርግብግቢት ያስተዋልኩት በእጁ የያዘው ሹካ አየር ላይ ሲውለበለብ ነበር....

"እድል" አለኝ ዝምታዬ ሲረዝምበት.....

"ወዬ".....አልኩትና አይኑ እንዳያገኘኝ ሳህኔ ላይ አፈጠጥኩ....

"ወድጄሻለሁ.....በጣም ወድጄሻለሁ....'ምን ታስቢያለሽ' ብዬ አልጠይቅሽም....ምንም ብታስቢ....ምንም ብትዪኝ እኔ ጋር የሚለወጥ ስሜት የለም....ድንገት እንደሆነብሽ እና እንዳስደነገጠሽ ይገባኛል....ምን አልባት ይሄን ለማለትም ፈጥኜ ይሆናል....ግን እድሏ ልቤ አላስቀምጥ አለኝ....መጀመሪያ ላይ እንዲሁ obsession መስሎኝ ነበር....ጭራሽ ጊዜ ሳይመርጥ ቀን እና ማታውን የማስበው ስላንቺ ሆኖ ሲያርፍ ቆም ብዬ ማሰብ ጀመርኩ....

ከልክ በላይ አሰብኩሽ....አንድ ሁለት ቀን ስለመስሪያ ቤት ሴቶች ለማሰብና አይኔ ላይ የምትጠገኚብኝን ነገር ለማደብዘዝ ሞከርኩ.....በውኔም በህልሜም በዚህ መንገድ አስቤያት ስለማላውቀው ሀኒ እራሱ ሳስብ ነበር.....ከማንም ላወዳድርሽ አልቻልኩም....አንቺን የማወቅ....አንቺን የመቅረብ ምኞቴ ከቀን ወደ ቀን እየጋለ ሄደ....".....አለኝና ፊት ለፊቱ ከተቀመጠው ውሀ አንድ ጉንጭ ጠጣለት።

"አይኔን የሳምከኝ እለት የሆንኩትን መሆን አስታውሳለሁ.... እረፍትም ፍርሀትም....ሳቅም ደስታም....ለቅፅበት የመኖር ፍላጎቴ ሲንር ይታወቀኝ ነበር....ላውቅህ እፈልጋለሁ.....በደንብ ላውቅህ....ሁልጊዜ እንባ ያቦዘዛቸውን አይኖቼን እንድትስም እፈልጋለሁ.....ባንተ መታቀፍ አለም ነው.....ስታዳምጠኝ ልብህን እስከ ጥግ ከፍተህ ነው....አንተን አለመውደድ አይቻልም"......ያለው ልቤ ነው......

ጎንበስ ብዬ ሳህኔ ላይ ያለችውን የሞተች ዶሮ ሬሳዋን በሹካ እየወጋሁ አላስተኛ እያልኳት ነው.....ላቤ ጀርባዬ ላይ ይንቆረቆራል....እንደ እሱ በራ ብሆን አናቴ ላይ ያለው ላብ ጎርፍ ሆኖ ይወስደው እና እኔም ከዚ አጣብቂኝ እገላገል ነበር......

"እድሏ......".....ጠራኝና 'መልስሽን እየጠበቅኩ' ነው አስተያየት አየኝ።

አላለቀም.....

✍ሸዊት

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
14.05.202520:00
ስላረፈድኩ አፍ የለኝም....በእንቅልፍ ልባችሁ እንድታነቡም አስተያየት እንድትሰጡም አትገደዱም(ማን ናት እድል ልትሉም ትችላላችሁ አሁን).....😁

ነገ ግን ጠብቃችኃለሁ.....😊

መልካም አዳር....
Reposted from:
✍ዮ_ሚን avatar
✍ዮ_ሚን
20.04.202509:15
ትንሳኤውን ለትንሳኤ ያድርግልን !

@yomin1_2
10.05.202520:03
እሱ እና እሷ 2

እሱ

ለቀናት ፎቶው ላይ ሳፈጥ ከረምኩ.....አላይም ብዬ እተወውና መልሼ እራሴን ፎቶው ላይ ሳፈጥ አገኘዋለው ....ወስጤ ብዙ ጥያቄዎች ነበሩኝ.....ከዛ በላይ ግን እረሳዋት ያለው ልቤ መልሶ በፍቅሯ ሲነድ ይታወቀኛል ።

ጥያቄዎቼን መልሼ መላልሼ ለራሴ እጠይቃለሁ ...አታፈቅረኝም ነበር ማለት ነው??? ያ ሁሉ ጊዜ ያ ሁሉ ነገር ውሸት ነበር ?? እንዴት ቻለችበት??? ምን አጎደልኩባት??? በአንድ ጊዜ ከሁለታችንም ጋር ነበረች ማለት ነው???? ካልሆነ እንዴት ???? ብዙ ብዙ ጥያቄዎች ውስጤን ያውከዋል ...መረጋጋት አቃተኝ ....ስለ ሌላ ነገር ማሰብ ከበደኝ.....ስራዬን ኑሮዬ ሁሉም ነገር ውሸት ሆነብኝ ......ከራሴ ጋር ብዙ ታግዬ ላገኛት ወሰንኩ ....እንዴት አገኛታለው ምንስ እላታለሁ አላውቅም ....ግን አግኝቻት ለጥያቄዎቼ መልስ ማግኘት አለብኝ ....

በጠዋት ተነስቼ ወደ ፎቶ ቤቱ ሄድኩኝ.....እንደገባው የደስደስ ያላት ቆንጅዬ ልጅ ተቀበለችኝ....ሰላምታ ከተለዋወጥን በኃላ አድራሻዋን ለማግኘት የፈጠርኩትን ታሪክ ነገርኳት ...

"ወንድሟ ነኝ አልኳት (በስልኬ የሰርጓን ፎቶ እያሳየዋት) ስንት አመት ስፈልጋት ኖሬ ...የሰርግ ፎቶዋን facebook ላይ አየሁት ...ምናልባት አድራሻዋን ካወቃቹ ብዬ ነበር አመጣጤ እባክሽ ምትተባበሪኝ ነገር ካለ አግዢኝ" ብዬ አስተዛዝኜ ጠየኳት ....አመነችኝ አይኗ እንባ አቀረረ ...እኔም አብሬያት አለቀስኩ ...(ለምን አለቀስኩ እንጃ)

"እውነት በጣም ጥሩ ሰው ነክ..በዚህ ጊዜ እህት ይሁን ወንድም ማን ዞር ብሎ ያይካል ....እውነት የተባረክ ሰው ነክ....." አለቺኝ ባልሰራሁት ነገር በመሞገሴ ሀፍረት ቆነጠጠኝ....ቀጠለች "ከስልካቸው ይልቅ የሱን የመኖሪያ አድራሻ ብሰጥክ ይሻላል ...የሱ ቤት የፎቶ ኘሮግራም ስለነበረን አድራሻው ይኖረናል .ቆይ ልፈልግልክ "ብላ የሆነ ወረቀት ማገላበጥ ጀመረች .....ትንሽ እንዳገላበጠች ብጣቂ ወረቀት ላይ የሆነ ነገር መሞንጨር ጀመረች ...ከጨረሰች በዋላ ይኸው ብላ ከመልካም ምኞት ጋር ወረቀቱን ሰጠቺኝ ....አመስግኜ ተሰናብቼ ፎቶ ቤቱን ለቅቄ ወጣው።

በቀጥታ ወዳለችበት አድራሻ መሄድ ባላወኩት መንገድ ውስጤን ፍርሀት ለቀቀብኝ ...መሄዱን ለነገ አዘዋውሬ ወደ ቤት ተመለስኩ ። ለሊቱን ሙሉ ምን እንደምል እንዴት እንደማወራት እያሰብኩ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር አደርኩኝ ።

በጠዋት ተነስቼ ወደ ተባልኩት አድራሻ እራሴን አሳምኜ አቀናሁ ... "አካባቢው ከደረስክ ቤቱ አይጠፍክም" ብላኝ ነበር ልጅቷ ወረቀቱን ስትሰጠኝ....ደርሼ ሳየው እውነት መሆኑን አረጋገጥኩ ከብዙ ዘመናዊ ቤቶች መሀል ..ዙርያውን በግንብ እና በአደገኛ አጥር  ታጥሮ ..መግቢያው ላይ የመኖሪያ ቤት በማይመስል ግዙፉ በር ተከልሎ...ሥስት floor አከታትሎ ተጀንኖ የቆመ ትልቅ መኖርያ ቤት እንዴት ይጠፍል....ፈልጎ የመጣን ብቻ ሳይሆን በዛ ያለፈን ሰው ሁሉ ቀልብና ልብን የሚሰርቅ ውብ ቤት .....

ቤቱን ሳየው ለብር ብላ ይሆን ያገባችው ??? የሚል ጥያቄ ጭንቅላቴ ላይ አቃጨለብኝ....ስለቤተሰብም ሆነ ስለ ችግር ስታወራ ሰምቻት አላውቅም .....ስለ ምን ነበር ምናወራው እያልኩኝ ለራሴ መገረም ጀመርኩኝ.......እንዲሁ በሀሳብ እንደነጎድኩኝ የቤታቸው አጥር ስር እራሴን አገኘሁት ..... ከብዙ ማመንታት በዋላ የመጥሪያውን ደውል ተጫንኩት..አንዴ ስጫነው የልብ ልብ ተሰማኝ መሰለኝ ደጋግሜ ያለ እረፍት እጫነው ጀመረ

ከብዙ ጥሪ በዋላ የጊቢው በር ተከፈተ...እዳጠፍ ሰው አንዱን ጥግ ተለጥፌ ቆምኩኝ...ከፊት ለፊት ሰው ሲታጣ አንገትዋን አውጥታ ወደ ውጪ ልትመለከት ስትወጣ አይን ለአይን ተጋጨን ሁለታችንም በድንጋጤ. ተፍጠጥን. ያየችውን ማመን አቃታት መሰለኝ እራሷን ስታ መሬት ላይ ወደቀች

ይቀጥላል ....

✍️kalkidan

https://t.me/storyweaver36
ትዝብት! የ90 ስፔሻሊስት ሀኪሞችን ደሞዝ ለኔ የምትከፍለኝ ደሀዎ አፍሪካዊት ሀገር!

(ከስደት : Dr Abiyot Cheklaye, internist, gastroenterologist and transplant hepatologist)

ብዙ ባይመቸኝም አንዳንዴ የመንግስት ጡሩምባ ሚድያዎችን እሰማለሁ:: እናም ካድሬዎቹ ከአፍሪካ ግምባር ቀዴም ግዙፍ ኢኮኖሚ እያስመዘገብን ነው ይላሉ ።

የሚገርመው ነገር እኔ የምኖርባት የአፍሪካ ሀገር በአለም ላይ በጣም ድሀ ከሚባሉት ናት። ነገር ግን እኔ እዚህ በወር የማገኘው ደሞዝ ወዴ ETHIOPIA ብወስደው 90 ለሚሆኑ በእኔ የትምህርት ደረጃ ላሉ ስፔሽያሊስት ሀኪሞች የወር ደሞዝ መክፈል ይችላል። አሳፋሪ ነው::

እንደዚህ በጭንቀት የሚኖር የጤና ባለሙያ ጋር ሂዶ መታከም ራሱ ከባድ ነው:: አነሱ ሳይበሉ የሚያገለግሉት መላእክት አይደሉም:: በእርግጥ ያልታጠበ ቁርጥ ስጋ በየቀኑ እየበላ ለተቅማጥ በየጊዜው ባንኮክ ሪፈር አድርጉኝ እያለ አዛ ለሚያደርገው ካድሬ የህክምና ጥራት ምኑም አየይደለም::

ሳይቃጠል በቅጠል እንድሉ አስቸኳይ መፍትሄ ስጧቸው:: I advise all the health professionals to stand firm and united in any action; never fall back!

Dr Abiyot Cheklaye, internist, gastroenterologist and transplant hepatologist!
04.05.202507:41
✨✨ፍቅር ቅብ-14✨✨

ከዮናስ ጋር ከተለያየን ስድስተኛ ወር አልፎ ሰባተኛውን ይዘናል...ጊዜው እንዴት ይሮጣል.....ፍቅር ቅብ የነበረው አብሮነታችን አንድ አመት ከመንፈቅ የቆየ ነበር....በዚ ሁሉ ጊዜ ውስጥ ዮናስ እንዲህ ነብስ ውጪ ነብስ ግቢ ሆኖ ያሳለፈበትን ቀን አላስታውስም።

"ምንድን ነው ንገረኝ እንጂ....".....አልኩት የተጋባብኝን ፍርሀት ለማባረር እየታገልኩ።

"እ....እ....".....አለና ተጨማሪ ሲንግል አዘዘ።

"ኧረ በፈጠረህ ዮናስ.....".....አልኩት ቆጣ ብዬ።

"አሞኛል.....".....አለኝ ያልጨረሰው ንግግር እንዳለ በሚያሳብቅ አስተያየት....በግንባሩ እያየኝ ነበር።

"ምንህን.....ሲቀጥል እኔ ምን ቤት ነኝ.....?.....".....ግራ ገባኝ።

"እ....አንቺም ሳያምሽ አይቀርም....."....አለና ትልቅ ሸክም ከላዩ እንዳራገፈ ነገር ተነፈሰ....

"ምንድን ነው የምትለው....ምንድን ነው በሽታዬ....ዝም ብሎ ታመሻል አለ እንዴ....."....አልኩት አይኔን በእንባ አቁሬ.....'እንዲህ ነው' ብሎ ባይናገረውም እያለ ያለው ነገር ገብቶኛል....ግን የገባኝ እንኳን ውሸት እንዲሆን በውስጤ እየፀለይኩ ነው....

"ቫይረሱ በደሜ ውስጥ አለ.....".....ሲለኝ ነብስና ስጋዬ ተላቀቀ....ሰውነቴ በደነብኝ.....ሁሉም ነገር ጭው አለብኝ....እያንዳንዱ ድምፅ "ፅፅፅፅፅፅፅ" ብቻ ሆኖ ይሰማኝ ደመር.....ጆሮዬ የሆነ ጩኧት እያወጣ ራሱን ብቻ መስማት ጀመረ....አንደበቴ ተሳሰረ...."እንዴት....መቼ....ለምን....."...... ሌላ የሚጠየቁም የማይጠየቁም ጥያቄዎች ቢመጡብኝም ራሴን አረጋግቼ መጠየቅ አልቻልኩም.....

ተነስቼ ስወጣ ተከተለኝ......

ብዙ ብዙ ነገር ይለፈልፋል....እኔ ግን አልሰማውም.....የሚሰማኝ የጭንቅላቴ ጭውታ ነው....."ፅፅፅፅፅፅፅ".....ይሄ ብቻ ነው የሚሰማኝ።

"ድር እኮ መድሀኒትነት አለው....ቁስልን ለዘብ ያደርጋል....ላፅዳህ ብትዪውም በጄ ይልሻል.....የዘመናት ቆሻሻን ዘወር ብታደርጊው እንኳን ጠረኑ ከርቤም አይበቃውም....."....ያልኳት እህቴ ትዝ አለቺኝ....አፌ ልክ ነበረ....ያልፀዳ ቆሻሻ.....ያልለቀቀ እድፍ ተሸክሜ አፌን እንዳሽሞነሞንኩ አታውቅም እሷ.....

የምናወራውን ብንኖር የት በደረስን....ውስጣችን ጠልሽቶ አፋችንን ማሽሞንሞናችን ምን ጥቅም...ከረፈደ ማስተዋል እንዴት ይቀፋል....ኪሳራ!

***

ፍጥነቴን በእጥፍ ጨምሬ ገሰገስኩ....."ዘወር በልልኝ አውሬ"  አልኩት አብሮኝ የሚሯሯጠውን ዮናስ....

"እኔም በቅርቡ ነው ያወቅኩት.....እመኚኝ እድሌ.....".....አለኝ እየተርበተበተ....

"እድሌ አትበለኝ....."....ብዬ አንዴ ሳንባርቅበት ባለበት ቆመ።

እንደሰከረ ሰው እየተንገዳገድኩ ቤቴ ደረስኩ....

አባዬ ቀዝቀዝ ብሎ ጠበቀኝ.....

"ፀጉርሽን ልትሰሪ አልነበር...."....ጠየቀኝ።

"መ....መብራት የለም...."....ብዬው ተስፈንጥሬ መኝታ ቤቴ ገባሁ....

"ምን ሆናለች ልጅቷ...."....አለና ተከተለኝ...."ንገሪኝ እስቲ ምንድን ነው....እኔ አባትሽም ጓደኛሽም ነኝ አይደል...."....አለኝ ትክ ብሎ እያየኝ.....

"ሞኝ ማለት አንድ ስህተትን ደግሞ ደጋግሞ የሚሰራ ነው....".....የሚል አባባል አቃጨለብኝ....ሞት ቢመጣ ለአባዬ አንድ ነገር አልነግረውም ያልኩበት አጋጣሚ ትዝ አለኝ....እንደ እናት መሆን እንዳለበት ሲሰማው የሆንኩትን ይጠይቀኛል.....የሳትኩትን ያለፍርሀት እንዳብራራ ይገፋፋኛል.....እኔም የልብ ልብ ተሰምቶኝ የሆዴን ከዘረገፍኩ በኃላ አባትነቱ ይመጣበታል.....

ነገሩ እንዲህ ነው....

አስራ ሁለተኛ ክፍል ነበርኩኝ....ኢንትራንስ ልንፈተን አካባቢ የነበረ እረፍት ነው....ፕሮቲን ለጭንቅላት ጥሩ ነው ያለው ማን እንደሆነ ባላውቅም አባዬ በጠዋት እየተነሳ በስጋ ፍርፍርና በእንቁላል ያጨናንቀኝ ጀመር.....አብልቶ መክሮ ወደ ላይብረሪ ይልከኛል....ታዲያ ስመለስ የሚጠብቀኝ መክሰስ ልዩ ነበር.... የሚሰራልኝን ምግብ እንዳይቀርብኝ ፈተናው እንዲራዘም እፀልይ ነበር....ለሊት ድንች ጠብሶ ሻይ አፍልቶ ይቀሰቅሰኛል.....እኔ ሳጠና እሱ ጋቢውን ለብሶ ፊት ለፊቴ ይቀመጥና ያንቀላፋል.....

ታዲያ በአንዱ ቀን ጠዋት ቁርሳችንን እየበላን ጨዋታ አነሳ....."እኔ አባትሽ እንዴት ያለሁ የድሮ አራዳ መሰልኩሽ.....".....ብሎ ጀምሮ ከእናቴ በፊት ስለጠበሳቸው አስራ ስድስት ሴቶች ነገረኝ....አብዛኞቹን በእኔ እድሜ እያለ እንዳበሰላቸው እና የዘር ፍሬውን በአግባቡ ቢጠቀምበት አንድ ቀበሌ የሚያህል ልጆች እንደሚኖሩት ነገረኝ.....

ከዚ በኃላ ነው " እንደ አባት እና ልጅ ሳይሆን እንደ ጓደኛ ንገሪኝ እስቲ እስካሁን ምንም የለም....?....".....ብሎ የጠየቀኝ።

"ኧረ የለም....".....አልኩት አንገቴን ቀብሬ።

"ኧረ ተይ ስድስት በመውለጃ እድሜሽ....".....ብሎኝ ሲስቅ  ተፍታታሁ....ቀጥዬም ስለ ሁለቱ ኤክሶቼና በሰአቱ ስለነበረው ፍቅረኛዬ የነገርኩት....

ከዛ በኃላ ነው አባትነቱ የመጣው....አንዴ በጥፊ ሲያዞርብኝ ለወራት ያጠናሁት ትምህርት ከአእምሮዬ ብን ብሎ ወጣ....(ለዛ ነው መሰለኝ ፈተናውን ያላለፍኩት)....ነገሩ በዚህ አላበቃም ውጤት ከወጣ እና መውደቄ ከተረጋገጠ በኃላ ነገሩ ባሰ......

"ለነገሩ ከማንም ጋር አሸሸ ገዳሜ እያልሽ ብታልፊ ነበር የሚገርመኝ ኪሳራ....."....."አቤት አቤት 'ፍቅር' አልቀረብሽም ኩክኒያም".....የሚሉ ስድቦችን ከቀበቶው ጋራ ስጠጣ ከረምኩ.....ከዛ በኃላ ነው ለእሱ መንገር እርም ያልኩት።

አሁን አጠገቤ ቁጭ ብሎ "እንደ ጓደኛ" ይለኛል.....የወጋ ቢረሳ ነው ነገሩ.....

****

ሀኒ በጣም አስፈለገችኝ.....እንዲህ ያለ ዱብዳ ወድቆብኝ ለማን አወራዋለሁ.....ባንድ በኩል ደግሞ መክብብ አለ....ሀኒ ለመክብብ ያላትን ስሜት ካነበብኩ በኃላ እሷ ላይ ነፃነቴ ጠፍቷል....

እንዲህ በራሴ ሀሳብ ሰክሬ ስልኬ ነዘረኝ....

"የምሳው ቀጠሮ እንዳለ ነው አይደል.....".....የሚል መልዕክት ነው።

አልመለስኩለትም።

አላለቀም.....

✍ሸዊት

https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
https://t.me/shewitdorka
Log in to unlock more functionality.