HAppy Mûslimah
አጫጭር ኢስላማዊ ታሪኮች ብቻ
ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️
Fôr Any Cømments👉 @NihalllAb
ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️
Fôr Any Cømments👉 @NihalllAb
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verifiedTrust
Not trustedLocationЕфіопія
LanguageOther
Channel creation dateMay 09, 2025
Added to TGlist
Mar 08, 2025Latest posts in group "HAppy Mûslimah"
13.05.202513:27
ቁርጥ እርሣቸዉን የምትመስል ቆንጆ ናት፣ ዉብ ዕድሜዋ ለጋብቻ ሲደርስ ብዙ ሰዎች ሊጠይቋት እርሣቸው ጋር መጡ፤ ብዙ የተከበሩና ትላልቅ ሰዎች …
አንዲት ዐሊን የምትወድ የአንሷር ሴት ዐሊ ዘንድ ሄዳ
“ፋጢማን ብዙ ሰው እንደጠየቃት ታውቃለህ ግን?” አለችው፡፡
“አዎን” አላት፡፡
“አንተሰ ለምን ሄደህ አትጠይቅም፤ ለምን ዳሩልኝ አትላቸዉም፣ ትወዳት የለ?” አለችው፡፡
አንገቱን አቀረቀረ
“ድሃ ነኝ ምን አለኝና? በምንድነው የማገባት?” አላት፣
“ዝምብለህ ሂድና ጠይቅ፤ መልካም ነገር ልትሰማ ትችላለህ አብሽር፡፡” ብላ አሳመነችው፡፡
ሄደ፡፡ ፈራቸው፤ እርሣቸው ፊት ተቀምጦ መናገር ከበደው፡፡ እናም ዝም አለ፡፡
“ምነው ዐሊ ምን ሆነህ ነው? ምንድነው ያመጣህ ጉዳይ?” አሉት፤ አከታትለው ጠየቁት፡፡
ዐሊ አሁንም ዝም አለ፡፡
“ምናልባት ፋጢማን እንድሰጥህ ለመጠየቅ መጥተህ እንዳይሆን፡፡” አሉት፡፡
አዎን በሚል ሀሳብ ራሱን ነቀነቀ፤
“ታዲያ ጥሎሽ ይኖርሃልን?” አሉት፡፡
“ምንም የለኝም” አላቸው፡፡
“የሆነ ጋሻ እንዳለህ አስታውሳለሁ፡፡” አሉት፡፡
“አዎን አለኝ፣ ግን እሱ ምን ያደርጋል፣ ምን ዋጋ ያወጣል?” አላቸው፡፡
“ይጠቅማል ሽጠዉና ...፡፡” አሉት፡፡
ቤት ገዙላቸው፤ ጋብቻው ተፈፀመ፡፡
ዐሊ እንዲህ ይላል
'ከዚያ በኋላ ፋጢማን እጅግ ወደድኳት፡፡ አንድም ቀን በስሟ ጠርቻት አላውቅም፤ “ የአላህ መልዕክተኛ ልጅ ሆይ” ነበር የምላት፡፡
ልክ እሷን ሳይ ሀሳብና ጭንቀቴ ሁሉ ይወገዳል፣ ልቤ እረፍት ይሰማዋል፣ አንድም ቀን አስቆጥቻት አላውቅም፣ አንድም ቀን አላስለቀስኳትም፣ አንድም ቀን አስቆጥታኝ፣ አንድም ቀን አስቸግራኝ አታውቅም፡፡ በአላህ አምላለለሁ አንድም ቀን ጀርባዬን ሰጥታችት አላውቅም፤ ሁሌም እጆቿን እንደሳምኳት …
ፋጢማ ከአባቷ ከአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) ህልፈት ከስድስት ወር በኋላ ተከተለቻቸው፡፡ በሞተችም ጊዜ ባለቤቷ ዐሊ አጠባት፣ ከፈናትም፣ ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎም
“ፋጢማዬ እኔ ዐሊ ነኝ፡፡” አላት፡፡
@heppymuslim29

27.04.202518:15
በሰርጓ ቀን አንዷ የMakeUp ባለሞያ እቤቷ አምጥታ በጥንቃቄ MakeUp ተሰራች። በጣም ለውበቷ በመጨነቅ በዝግጅቱም ላይ ልዩ ለመሆን ፈልጋ ነበር። ነገር ግን ከዛ ሁሉ የጥንቃቄ ሥራ በኋላ ልክ ቀጠሮው ሲደርስ አንድ ነገር ረስታ ነበር። MakeUp ከመሰራቷ በፊት ውዱእ ማድረግ። ውሃው ወደ ፊቷ እንዲደርስ MakeUpuን ማንሳት ነበረባት። የዝግጅቱ ግዜው ደረሰ፤ በአዲስ ድጋሚ ለመቀባባት ጊዜ አይበቃትም። አንዳንድ ከሷ ጋር የነበሩ ቤተሰቦቿና የ(MakeUp) ባለሞያዎች ‹‹አሁን አትስገጂ.. ዝግጅቱ ካለቀ በኋላ ቀዷእ ታደርጊያለሽ›› አሏት። ነገርግን እሷ አሏህን ስለምትፈራ እነሱን ትታ ፊቷ ላይ የነበረውን በሙሉ በውሃው አንስታ ውዱእ አደረገች። ሶላቷንም መስገድ ጀመረች፤ ነገርግን በጣም ቆየች... ቤተሰቦቿ እሷን መፈለግ ጀመሩ፤ ለካ እሷ ሱጁድ ላይ እያለች ሞታለች...!
አሏህን እንፍራ...ሶላትን አንተዉ....
@heppymuslim29
አሏህን እንፍራ...ሶላትን አንተዉ....
@heppymuslim29
25.04.202519:22
፡
:
ቁና ቁና እየተነፈስ የተናደደ ፊቱ ቀልቶ እግሩን እያማታ ቶሎ ቶሎ ይራመዳል ።
ልጄ የሚል ድምፅ የሰማ መስሎት ሲዞር ድቅቅ ያሉ ሽማግሌ በተለማማጭ አይነት ስሜት አይን አይኑን እያዩ እጃቸውን ዘረጉ፤
.....ምን ልስጦት አባባ ያው ባዶ ኪስ ነኝ ያለሁት ባዶ እያለ ኪሱን ገልብጦ አሳያቸው፤
..በሁኔታው ቅር አልተሰኙም."ልጄ አመስግን በአላህ እዝነት ተስፋ አይቆረጥም ባይገባህ ነው እንጂ አንተኮ ኪሱ ባዶ የሆነ ሱሪ አለህ ፡አንተ ያለህ የሌላቸው ብዙ አሉና ባለህ አልሀምዱሊላህ በል..ስታመሰግን የምታመሰግንበት ስታማርር ደግሞ ምታማርርበት ነው ሚሰጥህ "ብለው ማዝገማቸውን ቀጠሉ ።
... "ኪሱ ባዶ የሆነ ሱሪ አለህ.." የአዛውንቱ ንግግር ጆሮ ላይ አስተጋባ ። ""አልሀምዱሊላህ"ይቺ ቃል ልቡ ውስጥ ሲደጋገም ተሰማው።!
:
፡
" #ያለንን ብናውቅ የጎደለን የለም ነበር" ሚለው ንግግር እንዴት ትዝ አለኝ!

Reposted from:
ABX

20.04.202519:32
ዘዊጁና እና የእኔ ሁለት ትዳሮች
(ካማለላችሁ ብየ ነውንጂ...)
በ ሱለይ አደም
አንድ ሰሞን ብዙ መጽሐፍት በብዛት ታተሙ። በመሆኑም የቀን ንባብ ብቻ ሊገፋቸው የሚችሉ አልነበሩም። በሌሊት እንቅልፍን ተወት ድርጎ ማንበብ ጭምር የግድ ሆነ...
ጠረጴዛየን ተደግፌ እያነበብኩ አንድ የአክስቴ የልጅ ልጅ በImo ደወለች። "አንተ እያለህ እንዴት የእኔን ቤት የሚሰራልኝ ሰው ይጠፋል!?" አለችኝ። ሱሉልታ አካባቢ 200 ካሬ ቦታ ከገዛች ብዙ ወራት ቢቆጠሩም ለመስራት ግን ታምኖ ስራው የሚሰጠው ሰራተኛ አልተገኘም።
ግልጽ ለማድረግ ልጅቷ ስዑዲ ነው የምትኖረው። በዚህ ቅጽበት ወሬ ማስቀየስ ስለነበረብኝ "ያንቺ ቤት ይሰራል ቀላል ነው። መጀመርያ እኔን ዳሩኝ" አልኳት። እኔ ወሬ ማስቀየሴ ነበር እሷ ግን "ወላሂ በልስኪ!?" አለች። አሃ ወሬ ማስቀየስ ላይ ስለነበርኩ ከምሬ ሚስት እየፈለግኩ ኡእነበረም። ሆኖም እስኪ ዳሩኝ ብየ ወደ ጨዋታነት ለመቀየር ሞከርኩ። ተሳካልኝ ብየ እንዳስብ ስልኩ ጆሮየ ላይ ተዘጋ። ወደ ንባቤ ገባሁ።
ከአንድ ሰዓት በኋላ የአክስቴ የልጅ ልጅ ደወለች። ከታናሽ እህቴ ጋር አውርተው "ለጅቷ ተገኘችልህ!" አሉኝ። እየቀለድኩ እንደነበር ባውቅም ድንገት ጆሮየ ሁለ ነገሬ ቁምነገር ብሎ ማዳመጥ ጀመረ። "ሁሌ አንተን ሳስብህ ወላሂ ይቺ ልጅ ነች የምትመጣልኝ።" አለች። የትኛዋ ልጅ እንደሆነች ጠየቅኳት። እንደማላውቃት ነገረችኝ። ብቻ "ልጅቷ ግን እርግጠኛ ናችሁ ትሆነኛለች!?" አልኳቸው።
ሲያይዋት እኔ እንጂ በጭራሽ ሌላ ሰው እንደማይከሰትላቸው እየማሉ ነገሩኝ። ልቤ ወሬያቸውን ወደደው። ጆሮየ ቀጣዩን ወሬ ናፈቀ። መጽሐፎቼ ተዘጉ። እህ ብየ ማዳመጥ ጀመርኩ። "የሆነስ ሆነና የምትሏት ልጅ የት ነው ያለችው!?" ብየ ጠየቅኩ። ሳውዲ ጅዳ እንደሆነች ሲነግሩኝ ቀልዳችሁ አይጠገብም በሉ ተውት ስልኩን ዝጉት አልኩ። ዝም ብለህ ዱዓ አድርግ አሉኝ። አሃ ለካ ዱዓ አለና...
ቤተሰቦቿን አጣራሁ። ወደ አንድ የአጎቴ ልጅ ደውየ ስለቤተሰቦቿ ጠየቅኩት። ጥሩ ሰዎች ናቸው አለኝ። እሱን ትቼ ራሱ አጎቴ ላይ ደወልኩ። ለጋብቻ ይሆናሉ ተባልኩ። ከተቀመጥኩበት ተነስቼ ውዱ አደረግኩ ሁለት ረከዓ የጉዳይ ሰላቴን ሰግጄ ያ ረብ አልኩ። ለብዙ ዓመታት ያለ ቤተሰብም ኖሬያለሁና ከብቸኝነት ገላግለኝ። እህቶቼ እንዳሉት ልጅቷ ለእኔ የምትሆን ከሆነ አቅርብልኝ። ደግሞም የማትሆነኝ ከሆነ አርቅልኝ አልኩት። ልቤ ሌላ ስራ ጀምሮ አደረ...
አስገራሚው ነገር ይሄ ነው። ዱዓ ባደረግኩ በሶስተኛው ቀን ልጅቷ ጓዟን ይዛ አገሯ ገባች ተባለ። 100000000...0 ወንድ አቆብቁቦ የሚጠብቃት መሆኑን ሰማሁ። እህቶቼ ደወሉ። ለአላህ ምን ብለህ ነገርከው አሉኝ። የምትሆነኝ ከሆነች ኸይር ካላት አቅርብልኝ። ካልሆነችኝ ደግሞ አርቅልኝ ነው ያልኩት አልኳቸው። ተገረሙ። በል አገርህ ገብታለች አሉኝ። ደነገጥኩ። ሱቅ ደርሳ ስትመለስ ነው የጅዳ ፖሊስ የያዛት። በሶስተኛው ቀን ወደ አገሯ ያሳፈራት። እህቶቼ ይህን ያህል ጊዜ አረብ ሲያንገላታን ምነው እንዲህ ፈጣን ዱዓ ብታደርግልን አሉኝ። ክፈሉኝ ስል ተሳሳቅን...
በል ስልክ እንዳገኘን እንሰጥሃለን አሉኝ። ሐዋ ትባላለች። አዳም በሐዋ ነው ብቸኝነቱ የተገፈፈው። ሐዋ ሁሰይን። ሲም አውጥታ ስልክ እንደያዘች ተነገረኝ። ቁጥሯን ላኩልኝ። ወጉን ጀምረውታል።
ከሐር የለሰለሰ የሰላም ንፋስ ባቀፈው ድምጿ "ሔሎ!" አለችኝ። ከሰላምታ በኋላ ስሜን አስከተልኩ። ጭራሽ ሰከነች። ነግረውኛል አብሽር እንጫወታለን እናወራለን አለችኝ። ወደቤት ተመልሼ እቃ ማሟላች ጀመርኩ። ሲመቻት ጀወለች። አወራን ተገናኘን። አየኋት የአየችኝ። ወላሂ ልቤ ተከፈተ። ተስማምተን ቀጣይ ውይይት አደረግን። ስለ HIV ምርመራ ስለ ወርቆች መግዛት ወዘተረፈ
አገሯ በገባች 20 ቀን በኋላ ሰላማዊቷ፤ ቆንጂየይቷ ሐዋ ቤቴም ገባች። ወላሂ ሱመ ወላሂ እስከ ዛሬ በሐያቴ ካለፉ ዓመታት ከሐዊ ጋር ያሳለፍኳቸው ሁለት ዓመታት በእጅጉ የሚጥሙ፤ በጣም የተከበርኩባቸው፤ ሪዝቅም ያየሁባቸው ዓመታት ነበሩ።
ታውቃላችሁ ዛሬ የለችም። ሙታብኛለች። ልቤ በእግጉ ያዝናል። አላህ የፈቀደው ነውና ምንም ማለት አልችልም። አላህ ወደደ እኔ ተቀበልኩ። አላህ ያስመቻት። አላህ ከተላቁ ከተወደዱ ፊቱን የማየትን እጣ ከሚያገኙ የረሱሉን (ሰዐወ) ጉርብትና ከሚያገኙት ያድረረጋት፤ ከሐውድ እስከ ፍርዶስ የአላህ ውብ ስጦታዎች ይከታተሉባት። አላህ በወደደ ልንወድ ነውና ሐያቴን ልዩ ማዕዛ ቀብታው ነው ያለፈችው የኔዋ አበባ ሐዋ ሁሰይን።
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
በዑስታዝ ኑሩ ቱርኪ ጉዳይ አንድ የቀልድ ቃል ከምታወጡ ዝም ብትሉ ኸይር አለው። ትልቅን ቁምነገር ነው ያነሳው። በዚህ መንገድ የሚገናኙትን አላህ የሚዋደዱ ያድርጋቸው። ከሐራም ለመሰተር ትልቅ ሰበብ ነው የዑስታዝ ሙከራ። ይህን ሙከራ በቀላሉ አትዩት የዚና ኪታብ ሁለት ሙጀለድ የጻፈም ሰው አለ። ያስፈራል ያሳዝናል። ነገር ግን ዱዓ እናደርጋለን። አላህ ያግራራው።
https://t.me/MuhammedSeidAbx

13.04.202519:37
አንድ ሌባ በተደጋጋሚ በጨለማ ወደ አንድ ግቢ ይገባል። አንድ ቀን የግቢው ባለቤት ግቢው ውስጥ ከሚገኘው ዛፍ ላይ ወጥቶ ሌባውን ይከታተለዋል። ሌባው እሮጦ መጥቶ ዛፉ ስር ይቆምና ሰው መኖር አለ መኖሩን ቅኝት ይጀምራል። ወደ ፊት፣ወደ ኋላ፣ወደ ቀኝ እና ወደ ግራ እየተዟዟረ አየ። ይሄኔ የቤቱ ባለቤት ዛፉ ላይ ሆኖ አንዲት የዛፍ ፍሬ ወደ ታች ለቀቀበትና ፍሬዋም የሌባውን አናት ዳብሳ ወደቀች። ሌባው ቀና ብሎ ወደ ላይ ሲያይ ከቤቱ ባለቤት ጋር ተፋጠጠ። ባለ ቤቱም “ይህን ያደረግኩት ለምን እንደ ሆነ ታውቃለህ? ሁሌ ልትሰርቅ ባሰብክ ጊዜ ሰው እንዳያየኝ ብለህ ወደ ቀኝና ወደ ግራ ብቻ ሳይሆን ወደ 'ላይም ማዬት እንዳለብህ ላስታውስህ ፈልጌ ነው” አለው።
ሰው እንዳያየን ብለን ግራ እና ቀኝ ማየት ሳይሆን የፈጠረን አላህ ያየኛል ብለን ማሰብ አለብን። "የትም ብትሆን አላህን ፍራ" ማለት ይሄ ነው!!
@heppymuslim29
ሰው እንዳያየን ብለን ግራ እና ቀኝ ማየት ሳይሆን የፈጠረን አላህ ያየኛል ብለን ማሰብ አለብን። "የትም ብትሆን አላህን ፍራ" ማለት ይሄ ነው!!
@heppymuslim29
06.04.202507:05
ሰሞኑን በሪያድ ከተማ የተከሰተው የመኪና አደጋ
የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊቴ ተጋጭተው ነበር። አምቡላንስ አየሁ። ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ። አንድ ወጣት ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየሁ፡፡ ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል። አካላቱ ተቆራርጧል። እግሩም ጭምር ተቆርጧል። እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ።
ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል
"መሞት አልፈልግም። በጣም ፈርቻለሁ እሳት ነው 'ምገባው እኮ" ይለዋል። እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔ 'ኮ አልሰግድም ነበር። ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም። ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ። ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል።
ሰዎችም ተሰበሰቡ። እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ። በጣምም ፈርቻለሁ፡፡ በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል። የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ። ጩኸቱም ቀጠለ። ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ። ሊያድኑት ግን አልቻሉም።
አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሃዳ በል! ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል። ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም። ሱብሃነላህ በጣም ፈርቶ ነበር። ነገር ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ። ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን ሸሃዳን ምላሱ ለማለት እምቢ ማለቷ ነው። ዚያም አልተንቀሳቀሰም ሰውነቱም ደርቆ ቀረ።
ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ። ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት። ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም። ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም። ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት። ዘጋቢውም ይለናል " በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ። እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው። ሰላታችሁን ግን ጠብቁ። በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡ ዛሬውኑ መስገድ ጀምሩ። የመጨረሻ ቀናችን መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም። እኔም ከዚህ ክስተት በኋላ መተኛት አልቻልኩም። እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር። ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...”። እሰግዳለሁ፣ወላሂ ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ፣መሞት ግን አልፈልግም...ባለቀ ሰዓት ከንቱ ልፍለፋ ብቻ።”

29.03.202520:51
የሁሉን ዓመት ዒድ በደሰታ ስሜት ዉሰጥ ሆነህ አትደርስም መቸስ። አንዳንዱን በህመም፣ አንዳንዱን በገፍላ፣ አንዳንዱ በሐዘን፣ አንዳንዱን በችግር ዉስጥ ሆነህ... ልታሳልፈው ትችላለህ።
ሁሉ ዒዴ ዒድ ካለመሰለ አትበል። በሁሉም ሁኔታህ ዉስጥ አላህን አመስግን።
በሁሉም ሁኔታ ዉስጥ ላላችሁ ኡመተ ሙሐመድ እንኳን አደረሳችሁ።
ዒዱኩም ሰዒድ ወሙባረክ
عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
كل عم وأنتم بخير🤍

Deleted10.05.202505:26
28.03.202515:06
💫✨⭐️🌙💥✨⚡️🌙⭐️✨
#ለኢድ
ለወዳጅ ዘመዶ ምን አይነት ጥሩ ስጦታ ልስጥ ብለዉ አስበዉ ግራ ከተጋብ እንግዲያዉስ እኛ አለን #የሚሉን NYA #በመስገጃዎች እና #ቁርአን ላይ በወዳጅዎ ስም አልያም በፈለጉት መልዕክት በጥንቃቄ ሰርተን የልባችሁን እናደርሳለን ይሉናል👌
🔖ለዕራሶ
🔖ለቤተሰቦ
🔖ለጓደኛዎ አልያም
🔖ለስራ ባልደረባዎ
❤️ የማይረሳ እና ዉብ ስጦታ ከ-NYA
✨️በብዛት ሲያዙን ቅናሽ እንደምንሰጣቹ ልናበስራቹ እንወዳለን ✨️
🩵ስራዎቻችንን ለማየት
የTelegram group https://t.me/nya_rugs_group
👆ይሄን join ብለው ተቀላቅለው ቤተሰብ በመሆን የምንለቃቸውን አዳዲስ ስራዎቻችንን ይመልከቱ።
😊ሌሎች አካውንቶቻችንን ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ Link
📲0716675904
በቴሌግራም በውስጥ ለማናገር 📥@nya_rugs

26.03.202519:12
የሆነ አካል ዱአ አድርጉልኝ ብሎ
ሲለን እሺታችን ከአንገት ብቻ መሆን የለበትም። ይህን ሲለን ለእኛ ተራ ነገር መስሎ ሊታየን ይችላል ነገር ግን ለዛ ሰው ነጃ የመውጫ , የመፈረጃ ወይንም የኸይር መንስኤ ሊሆነው ይችላልና የሚሰጠንን አማና ችላ ባለማለትና የጠየቀንን ቀላል የሆነ ጥያቄ በመወጣት ሀላፊነታችንን እንወጣ ባይ ነኝ። እኔንም በዱዓቹ አትርሱኝ !!

24.03.202508:12
ወንጀል ሠርተህ ትፀፀታለህ፡፡ <ጌታዬ ሆይ ሁለተኛ አልመለሰበትም፡፡› ትላለህ፡፡ ተመልሰህ ያንኑ ወንጀል ትሠራለህ፡፡ ተፀፅተህ ጌታዬ ሆይ! አልመለስበትም፡፡ ትላለህ፡፡ ለሦስተኛ አራተኛ ጊዜም እንዲሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ተውባ ማድረጉ ይከብድሃል፡፡ ለምን ካልክ በራስህ ላይ እምነት ስላጣህ ነው፡፡ ዳግም ተመልሰህ ተውባ አድርጌያለሁ፡፡ ለማለት ታፍራለህ፡፡ አትፀናበትምና፡፡ በዚህ የተነሳ ባንተና በአላህ (ሱ.ወ) መካከል ትልቅ ክፍተት ይፈጠራል፡፡ መመለሱም ይከብድሃል፡፡ ዳግመኛ ተውባን እንዳታስብ የሚያደርግ ባንተና በአላህ መካከል ግርዶ እስከመከሰት ይደርሳል፡፡
ነገር ግን አላህ ይወድሃልና እንድትመለስ ይፈልጋል፡፡ ተውባ ታደርግ ዘንድ ይህ መሰናክል እንዴት ይወገድ ይሆን? አዎን ባልተለመደ ሁኔታ ይወገድልሃል፡፡ ባልታሰበ መልኩ ግዙፍ በሆነ ነገር መሰናከሉን ያነሳልሃል፡፡ ይህም ትልቅ ስጦታ ነው፡፡ በዚህም ስጦታ አላህ (ሱ.ወ) ወዳንተ ይወደዳል፡፡
ይህ ስጦታ ለይለቱል ቀድር ይባላል፡፡ ይህች ለሊት ይቅር የምትባልበት ሌሊት ናት፡፡ ያለፈ ወንጀልህ ሁሉ ይታበስልሃል፡፡ ስለሆነም ተውባ ለማድረግ ባትታደል እንኳ ይህን ስጦታ በመቀበል አዲስ ሕይወት ትጀምር ዘንድ በዚህች ሌሊት ወደሱ መምጣት ይኖርብሀል፡፡ በዒባዳ ወደሱ ትመጣለህ፡፡ በዚህ መልኩ አል-ዐፋው ወደ ተውባ ይመራሃል፡፡ ከዚያም በሌሊት አጋማሽ በራስህ ጊዜ እፍረት ይይዝህና በተውባ ወደ አላህ ለመመለስ ትወስናለህ፡፡ ባንተና በተውባ መካከል ያለው ግድግዳ ፈርሷልና፡፡ በዚህም የተነሳ ይህች ሌሊት ከተውባ ጋር አዲስ ጅማሮ ትሆንሃለች ማለት ነው።
ከቢስሚከ ነሕያ መጽሐፍ
ሙሐመድ ሰዒድ (ABX) እንደተረጎመው

20.03.202510:46
ከአጠገቤ የተቀመጠ ልጅ ነው። በግምት አስራ ሁለት / አስራ ሶስት አመት ይሆነዋል። የልጅ መዳፎቹን ዘርግቶ መለመን ይዞዋል። ጠበቅኩት። እንደ ልጅኛ ከማስበው በላይ ዱዐውን አርዝሞታል። ሲጨርስ ተጠግቼ ምን ብለህ ዱዐ አደረግክ? ብዬ ጠየቅኩት።
.
በልጅነት ጥርሶቹ ፈገግታውን እያካፈለኝ " ለኔ እና ለእናቴ የሚለፋን ሰው ጠብቀው።" እያልኩኝ ነበር አለኝ።
የልጁ አባት ይህንን ጊዜያዊ አለም ተሰናብተው ከሄዱ አመታት አልፈዋል። የቲም ነው።
ልጅ የህይወት ሽንቁራቸውን ለመሙላት ለሚጥር ሰው የዱዐ መዳፎቹን ዘርግቶ ይለምናል።
:
፡
በረመዳን ላይ የቲሞችን እናስታውስ። እንዘይር። ከተትረፈረፈው ምግብ እናካፍል። መስጠት ውስጥ ሰላምን መሰጠት አለ። የነፍስ እርካታ ይገኛል። የቲሞችን መንከባከብ የሀቢበላህን ጉርብትና የሚያስገኝ ተግባር ነው።

Records
07.03.202510:55
6.9KSubscribers28.02.202515:31
400Citation index28.03.202515:31
852Average views per post29.03.202523:59
852Average views per ad post06.04.202511:46
2.58%ER29.03.202523:59
12.42%ERRGrowth
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
Log in to unlock more functionality.