Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Nuru Turki Official ™ avatar
Nuru Turki Official ™
Nuru Turki Official ™ avatar
Nuru Turki Official ™
29.04.202517:21
👌በአላህ እምላለሁ!፡፡ አንድ ቀን ዉስጥህን የሚያስደስት፤ ከደስታ ብዛትም የሚያስፈነድቅሽ ነገር ይመጣል፤ ይህን ስልህ ወደፊት ስለሚሆነው ነገር ዕውቀት ኖሮኝ አይደለም፤ ግና በአላህ በርግጠኝነት ስለማምን እና ስለምተማመን ብቻ ነው፤ እሱ ለባሮቹ አዛኝ ነው፡፡  

🔎ወዳጆቼ!
ከሐዘን በኋላ ደስታ እንጂ ምን አለ!
ማጣትን ማግኘት እንጂ ሌላ ምን ይከተለዋል! ምሽቱስ እየነጋ አይደል የሚሄደው?? ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንጂ ምን ይመጣል፡፡ 

ኢንሻአላህ የጨለመው ይበራል ።
የጠፋዉም ይገኛል ።
29.04.202516:37
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
≈ በአላህ ስም…

"የአላህን መስጂድ የገነባ ሰው አላህ በጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል"


≈ ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው እኛ የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ በዋናው ግቢ (main campus) የሚገኘውን የመስጂዱን የቆርቆሮ አጥር በቡለኬት ለማጠር በእንቅስቃሴ ላይ ነን፡፡ይህን እንድናደርግ ካስገደደን ምክንያቶች ውስጥ የመስጅዱን ምንጣፍ እና የቆርቆሮ አጥሩን በየግዜው እየተዘረፍን ስለተቸገን መተካት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደረሰናል።ስለሆነም አጥሩን በዘላቂ ግንባታ ለመገንባት አቅደናል።አሁን ላይ ባለን በተማሪ በጀት መገንባት ስለማንችል 50 በ50 ወይም 2500 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው መሬት ላይ ለግንባታ የሚስፈልገን ወጪ ከአንድ ሚሊየን አምስት መቶ ሺ (1,500,000) ብር በላይ ስለሚያስፈልገን በያላችሁበት ሁናችሁ እንድታግዙን በአላህ ስም እንጠይቃለን፡፡

CBE:1000660517859

ወይም

CBO:1014100258727

Abdurezak Abdulkarim

And/or

Mohammed Umer

~ ለበለጠ መረጃ 0948184582 ወይም 0964588545 በዚህ ያግኙን።

የጋምቤላ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ጀምዓ


ሼር በማድርግ እንዲተባበሩን በአክብሮት እንጠይቀዎታለን።
~ጌታዬ  ሆይ! የቂያም ቀን ደርሶ ከማልቀሴ በፊት ዛሬ ባንተ ፍራቻ የምታለቅስ ዐይን ስጠኝ፤
• ያ ቀን ተከስቶ ከመቆጨቴ በፊት ዛሬ አስተዋይ ልቦና አውርሠኝ፤
• የቂያም ቀን እውን ሆኖ ከመባነኔ በፊት ዛሬ ተዘናግቼ ካለሁበት ሁኔታ ቀስቅሰኝ።

• አምላካችን ሆይ! ንፁሃንን ብቻ እንጂ የማትቀበል ከሆነ ለእኛስ ለቆሸሹት ማን አለልን!፤
• አሳማሪዎችን እንጂ የሚያበላሹትን የማትሰማ ከሆነ ለኛስ አጥፊዎቹስ ማን ይድረስልን!።
• ጌታችን ሆይ! ጥፋት ብንፈጽምም አንተን መታዘዝ እንወዳለን። 
• የተለያዩ በርካታ  ወንጀሎችን ብንፈጽምም ባንተ ማመፅን እንጠላለን።
• ወደ ጀነት ሊያስገባን የሚችል በቂ የሆነ መልካም ስራ ባይኖረንም ጀነትን ስጠን።
• እንደ ክፉ ሥራችን ብዛት የሚገባን ቦታ ጀሀነም ቢሆንም ከጀሀነም ጠብቀን፡ አርቀን።
Shown 1 - 10 of 10
Log in to unlock more functionality.