03.05.202521:35
የአንዳንድ ሠው መልኩ ከሠማይ ይገዝፋል
እርሱ በቆመበት የሚታይ ይጠፋል
የአንዳንድ ሠው ፀባይ ይገርማል ከመሬት
መሸከም ይችላል ሀሴት እና ምሬ'ት
እንደዚያ ነሽ አንች(2)
ፀባይሽ መሬት ነው ሠው መክዳት አያውቅም
መልክሽ አንዴ ካዩት ከሠው አይን አይለቅም
ትከሻሽ ለምዶታል የሁሉን ሠው ፀባይ የሁሉን ባህሪ
ታድያ ምን ያደርጋል...
በምናብ ነው እንጅ በምልዐት አትኖሪ
እንደ አንች አይነት ሴት በምድር ከተገኘ እንስልሻለን ብናራ ፈቅፍቀን
የአዳም ልጅ በሙሉ እንደ አንች አይነት ሴት ነው 'ምንፈልግ አጥብቀን
ሚተራሊዮን (ዓቢይ)

26.04.202520:06
ችርስ🥂 ለእኛ
ኑረት ነው ወይስ ተውኔት የሚያስብል አስማት ህይወት ለምንኖር
እንዲህም ይቻላል እንደ ለምናስብል
ኑረት ነው ወይስ ተውኔት የሚያስብል አስማት ህይወት ለምንኖር
እንዲህም ይቻላል እንደ ለምናስብል
13.04.202519:17
በአሽሟጣጭ ከናፈር ስሜን አስመጥጠሽ
ከፀሀይ ከነፋስ መንገድ አስቀምጠሽ
በመጠበቅ ድካም ነጣጥቼ እያየሽ
አንች ተኳኩለሽ...
ብትመጭም እንኳን ከመቅረት እኩል ነሽ
ዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
ከፀሀይ ከነፋስ መንገድ አስቀምጠሽ
በመጠበቅ ድካም ነጣጥቼ እያየሽ
አንች ተኳኩለሽ...
ብትመጭም እንኳን ከመቅረት እኩል ነሽ
ዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
12.04.202516:04
ቴሌግራም ፕሪይሜም ላይ በተፈጠረ ስህተት ዛሬ ልደቴ ለመሠላችሁና ለመልካም ምኞቶቻችሁ አመሰግናለሁ።
ባይሆን ስጦታ የምትገዙበት አንድ ወር ሰጠኋችሁ
ባይሆን ስጦታ የምትገዙበት አንድ ወር ሰጠኋችሁ
02.05.202508:36
መጀመሪያ የጀመርከውን ሳትጨርስ የምን አስሩን መያዝ ነው የሚሉ አስተያየቶች በውስጥ መስመር እንደ ጉድ ወረዱብኝ
ጥፋተኛ ነኝና አሜን ብዬ ተቀበልኩ
ጀምሬ የተውኩት የተኖረ የሚል ታሪክ አለ እርሱን ከመጀመሪያው ክፍል ጀምረህ ልቀቀው እያሉኝ ስለሆነ በአስተያየታቸው መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ታሪኩን ከክፍል አንድ ጀምረን እንለቃለን።
በተደጋጋሚ እንዳደረግነው ዛሬም ከወገብ ጎንበስ ከጉልበት ሸብረክ ብለን ከልብ በሆነ ተማፅኖ ይቅርታ እጠይቃለን።
እንደው እንደ ሀሳብ በቅርቡ የጀመርነው አንድ ስራ ነበረ
እፎይታ የማስታወቂያ ስራ ለተቋማት የማስታወቂያ ስራዎችን እየሰራን ነው
ስራዎችን ለማጋራት አድስ ግሩፕ እንክፈት ወይስ በዚሁ ይለቀቅ
መቼም ሀሳብ መስጠት አትወዱም እንደ ኢትዮጵያ ምርጫ ድምፀ ተሀቅቦ ይበዛዋል(ፖለቲካውን መንካት ፈልጌ አይደለም)
ብቻ ሀሳብ ስጡበት ብዙ ሰው አልፈልግም ቢያንስ 500 ሠው ሀሳብ ይስጥበት።
እናመሰግናለን
እንላለን
ጥርኝ ጥበቦች

26.04.202506:15
#አንዳንድ_ህይወት_ከሚኖሩት_በላይ_ሲናገሩት_ያደክማል
ሀቅ አላት ሲኖር የተቋቋመንው ስንናገረው መኖሩን እንደመድገም ያህል ያማል
ከመቁሰል በበለጠ ማመርቀዝ ይከፋል
ዓቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
..." ግን እኮ በጣም ደስተኞች ነበርን" አለችኝ የእምባ መባ በጉንጮቿ ላይ እያረገፈች ማልቀስ ሲያንሳት ነው የምርም በጣም ደስተኞች ነበሩ...
ምን ላውራ ብሎ አፉን ሰክቶ የሚውል የሠፈር ሠው በሙሉ ለአመታት ያህል "አቤት ፍቅር መፋቀርስ እንደእነሱ ፍቅር ስጋ ለብሶ የሚታይባቸው " ያለላቸው ሁላችንም ሠው የዚህን ጥጋት ድረስ ይተሳሰባል ብለን በመልካም ጎናቸው የጎሻሸምናቸው ነበሩ...
ለካ ነበሩ እንዲህ ቅርብ ነው ...ጉድ ካልንበት ፍቅር በገዘፈ ልኬት የመለያየታቸው ገድል ጉድ አስባለን መቼም ጉድ ስንወድ ለጉድ ነው... ከቻለች እንዲታወራ ፈቀድኩለት...
" የት ላይ እንደተላለፍን ባላውቅም የሆነ ቦታ ላይ ተለያዬን እያስመሰለ እንዳልነበረ እርግጠኛ ነኝ አብረን በነበርንበት ጊዜ በጣም ደስተኞች ነበርን የጉድ ቀን አጎደለችብኝ ...ምን እንዳሳጣሁት ምን እንደበደልኩት ሳላውቅ የት ላይ እንደተላለፍን ሳይገባኝ ተገፋሁ...ጀርባዬ ላይ የተሸከምኩት ፍቅር ቀረና ክህደት አጎባበጠኝ ከመሄዱ በላይ መሄዱን ለመቀበል የማደርገው ትግል አንገዳገደኝ ማጣቴን እንደት ልመን ፍቅራችንን ለመታደግ የገባነው ቃልኪዳን አንሶ ቀሎ ማየት አመመኝ የኖርኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ማወቅ ....ኡፍፍፍፍፍ ብቻ ያማል" አለችኝ ድጋሜ ላለማልቀስ በቆረጠ ስሜት አይኖቿን እየጠራረገች...
አዎ ያማል ቀላል ነው ብዬ ሸክምሽን ዋጋ ላሳጣው አልፈልግም አዎ አንዳንድ ህይወት ከተኖረው በላይ ሲነገር ያማል"
ሀቅ አላት ሲኖር የተቋቋመንው ስንናገረው መኖሩን እንደመድገም ያህል ያማል
ከመቁሰል በበለጠ ማመርቀዝ ይከፋል
ዓቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
18.04.202507:58
እኛ ያመጣናቸው እነርሱ በለጡን
እንኳን አደረሳችሁ
እየጎተንት ወደ ቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ይዘነው ገባን።የገዛንለትን ነጠላ ዘርግቶ ለመልበስ ግራ ሲጋባ ከሶስታችን መሀከል አንድኛው ተጠግቶ በአንገቱ ስል አመሳቅሎ አጣፋለትና
"እንዲህ አይሰገድም እሽ
እሽ
ምግብስ በልተሀል
ኧረ አልበላሁም
አዎ ምን ሆነሀላ ውሀ ራሱ ከጠጣህ ነገር ተበላሽቷል በቃ
አይ እንደዚያ አላደረኩም" ይቁነጠነጣል...በመሀል 1000 ሰግደን ለመውጣት የምንገፋፋው እኛ ቆመን ሳለ እርሱ ስድስት ሰባት ጊዜ ከፍ ዝቅ ብሎ ጉልበቱ እንደተብረከረከ ሰው በግንባሩ መሬቱን ተደግፎት ቀረ። እንግድህ ላለመነሳት ምክንያት እየፈጠረ መሆኑ ነው ቀና ማለት እንደከበደው ሰው ቁና ቁና ሲተነፍስ ይሰማናል።...
"ቃል እንደጓደኛ ይሄንን ልጅ ምንም መላ አናበጅለትም ማለት ነው"አለ ቢታንያ ወደ አንገቴ ተጠግቶ ... እኔ ደግሞ የአናንያን ህይወት እየሄደ ካለበት ቁልቁለት ለመመለስ መሞከር ውሀን ሽቅብ የማፍሰስ ያህል ድካሙ ብቻ ነው የሚታየኝ። ለጓደኛ በዚህ ልክ
መጠን ዝሎ መኖር ቢያሳፍርም... "ሱስ እኮ ነው እየበዛ በጣም ብሶበታል የት እናስጠምቀው በእናትህ" የየግል አስተያየታችንን ለጣጥፈን ስናበቃ ካጎነበሰበት በርከክ ብሎ አንገቱን ደፍቶ ነጠላውን አናቱ ላይ ጎዝጉዞ ተቀመጠ።
ለካ መቆም ቢያፍር ነው እንባ አርግዞ የወደቀው ድንገት ቀና ሲል ደንግጠን ተያየን በስጋው ላይ እንደተቆጣ የሚያሳብቁት የደም ስሮች ከወደግንባሩ እንድህ ተከታትለው ለመሰለፍ ምን አነቃቃቸው ከምኔው ፊቱ በእምባ ረጠበ አያስቀናም ልታፀድቁ በገሰፃችሁት ሰው ተሰብካችሁ እንደመሄድ ያለ ስብከት ወደየት ይገኛል።
የእኛ ፀፀት አርባአንድ ኪራላይሶን ብለን ከአይናችን ካልወረደ ለእርሱ በሰባት ዝቅ ማለት በዘነበለት እምባ እንዴት አይቀናም አምላኩ በልቡ አደባባይ በታተመለት ሰው ቁኑ ሀቁም ይሄው ነው።
በልምድ መመላለስ የፀና ሐዋርያም አንዳንድ ጊዜ ሊያፀድቅ ይዞ ከመጣው ወንበዴ ተምሮ ይሄዳል።...
ወዮ የሠው ስግደት ቆጥረን ለተመለስን 😢😢😢
ፀሀፊ ✍ ጌታሁን ደጉ
እንኳን አደረሳችሁ
13.04.202518:53
ችርስ
ከዝምታ ወርቅነት ላይ መዳብ መዳብ ለደረሰን
ያጠነክር 'ሚሉት ብሂል ከጥጋችን ላልደረሰን
ይልቁንስ እያሟሟ እንደ ውሀ ላፈሰስ
እናቴ ትሙት ችርስ...
ማን ጀግና አለ እንደኛ ከተረቱ ተረት ብቻ የቀረው
ይጠግናል ያሉት ዝምታ የሰበረው
ዝም ባለ አፍ ውስጥ በአርምሞ ከናፈር
ሲሉን ዝንብ አይገባም አምነናቸው ነበር
ውሸት ውሸት ነው ቅጥፈት ነገሩ
የዝንብስ ማረፊያ የሆኑት ዝም ያሉት ሠዎች ነበሩ
ችርስ ብቻ ለእኛ ማባረሪያ ጭራ ቅጠል ላልበጠስነው
ዝም ባለ ዝምታ ሁሉን ለታገስነው
ችርስ🥂
ዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
ከዝምታ ወርቅነት ላይ መዳብ መዳብ ለደረሰን
ያጠነክር 'ሚሉት ብሂል ከጥጋችን ላልደረሰን
ይልቁንስ እያሟሟ እንደ ውሀ ላፈሰስ
እናቴ ትሙት ችርስ...
ማን ጀግና አለ እንደኛ ከተረቱ ተረት ብቻ የቀረው
ይጠግናል ያሉት ዝምታ የሰበረው
ዝም ባለ አፍ ውስጥ በአርምሞ ከናፈር
ሲሉን ዝንብ አይገባም አምነናቸው ነበር
ውሸት ውሸት ነው ቅጥፈት ነገሩ
የዝንብስ ማረፊያ የሆኑት ዝም ያሉት ሠዎች ነበሩ
ችርስ ብቻ ለእኛ ማባረሪያ ጭራ ቅጠል ላልበጠስነው
ዝም ባለ ዝምታ ሁሉን ለታገስነው
ችርስ🥂
ዐቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
11.04.202519:00
ክፉ ላደረገ ክፉ መመለስ ሀጢአት ሆኖ ሳለ ቀላል
ደግ ላደረገ ደግ መመለስ ፅድቅና ባይሆንም መንገዱ ሆኖ ሳለ ከባድ ለምን ሆነ
ደግ ላደረገ ደግ መመለስ ፅድቅና ባይሆንም መንገዱ ሆኖ ሳለ ከባድ ለምን ሆነ
30.04.202516:07
ያልፋል እኮ እስከሚያልፍ ብዙ ፍርሀቶች አሉ ብናልፍስ አይደለም...
የምንወዳቸው የሚኖሩልን ለደስታችን የተዳፉ (እስከአሁን ያልተቃኑ)
ለእኛ ደስታ ብዙ የከፈሉ አሉ እነርሱን የማጣት ፍራቻ ነው ያከሳን እንጅማ ያልፋል...
ቀዳሚውን ባናውቅም ከሞታችን ሞታቸው ካለመኖራችን አለመኖራቸው ያስጨንቀናል
እንዲያልፍን ብለው ብዙ ጉድ ያለፉልንን ባናሳልፍላቸው እንኳን ባያልፍልን እንኳን አልፎ ቢያዩት ...
ሠሞኑን ደግሞ የሆነ dark story እያማረኝ ነው
በቅርቡ ደግሞ Horrible የሆነ ታሪክ ጠብቁ

23.04.202519:53
ወዳጅነት ውስጥ ያለዉ አመኔታ ከ ሁሉም ይልቃል. ወዳጅ አደለም በ ሰዉ ፊት በ እግዜርም ፊት አይከሰስም
.
.

16.04.202509:36
አንድ የእንባ ጠብታ አንዲት ዛላ ለቅሶ
የሚያንበረክከኝ ከደጅህ መልሶ
የሚያስታርቅ ከአንተ ቤትህ 'ሚመልሰኝ
ለንስሐ የሚሆን አንድ እንባ ለግሰኝ
አሜን
የሚያንበረክከኝ ከደጅህ መልሶ
የሚያስታርቅ ከአንተ ቤትህ 'ሚመልሰኝ
ለንስሐ የሚሆን አንድ እንባ ለግሰኝ
አሜን
13.04.202518:33
ሳላጣ ሳይጎድልኝ ሳይሟጠጥብኝ ከቤት ከሞሰቤ
ልሞት ነው መሠለኝ ሠዎች ሠው ተርቤ
የቀረበኝ ሁሉ እየተገፋፋ እየተራገጠ ለመሸሽ ከቤቴ
እንደምን ይለመድ አይ ብቸኝነቴ
የወደቀን እንጨት አያጣውም ምሳር
ከስለት ይከፋል ትቶ የመኬድ እግር
ዓቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
ሀሳብ
ከእይታ ብዕር የተወሰደ
ልሞት ነው መሠለኝ ሠዎች ሠው ተርቤ
የቀረበኝ ሁሉ እየተገፋፋ እየተራገጠ ለመሸሽ ከቤቴ
እንደምን ይለመድ አይ ብቸኝነቴ
የወደቀን እንጨት አያጣውም ምሳር
ከስለት ይከፋል ትቶ የመኬድ እግር
ዓቢይ አለሙ (ሚተራሊዮን)
ሀሳብ
ከእይታ ብዕር የተወሰደ
Reposted from:
እንማር

11.04.202512:56
የማንም ጓጆ በእውነት ብቻ አልተሰራም ። እውነት በመውደድ ፊት አቅም የለውም ። እውነት ላይ ክችች ያሉ ሰዎች ቤታቸው ሲፈርስ ፣ ከስራ ሲባረሩ ፣ ስራ ሲበላሽባቸው ነው ያየሁት ....
Undeniable truth !!
የሞቀ ቤት ያላቸው ብዙ ቤታቸውን ሊያቀዘቅዘው የሚችል ነገር ታግሰው ነው !! ሳድግ ያየሁት ጥበብ እሱን ነው ። መኖር ያሳየኝ እውነት ይሄ ነው ።
የሚያኖረው መለሳለሳችን ነው !!
ደረቅ እውነት አያሸንፍም። እውነት ብቻውን አያሻግርም ። እሚያኖረን ጥበባችን ነው ። የጎጆ መሰረት እውነት አይደለም መተላለፍ ነው።
ሁሉም የሞቀ ቤት ውስጥ የታለፈ ፣ይቅር የተባለ አደባባይ የማይነገር፣ ያልተነገረ ገበና አለ ።
እየተላለፍን ! ✋
© Adhanom Mitiku
⭐️@Enmare1988
⭐️@Enmare1988
30.04.202515:52
ሁሉም ሠው ሊያሳካው ያልቻለ ግግር ምኞት በልቡ አለ
19.04.202501:51
አዳም ለይሁዳ የፃፈው ደብዳቤ
ይሁዳ ልጄ ሆይ እንደምን አለህ እኔ የበደሌን ብዛት ሳይቆጥር የሀጥያቴን ግዝፈት ሳይመለከት በቸርነቱ ተመልክቶ ከዘመናት ነበልባል ከማይጠፋ እሳት ያወጣኝ እግዚአብሔር ስሙ ካከበራቸው ጋር የተመሰገነ ይሁን።
ልጄ ይሁዳ ሆይ ዛሬ ለእኔ ታላቅ ደስታ ነው ግን የአንተን ጉዳይ ሳስብ አባትህ ነኝና ውስጤ በሀዘን ይሞላል።
የኔ ልጅ እንዴት ከአባትህ ስህተት መማር አቃተህ ያንን ሁሉ አመት ስለእኔ የተነገረውን ሰምተህ የደረሰብኝን እየሰማህ አድገህ ስለምን አባትህ እንደበደለው በደልህ።
ዛሬ ፍጥረት ሁሉ ከሲዖል ሲወጣ በእኔ ጥፋት የሚቀጡት ስለተረፉ እየተደሰትኩ ሳለ አንድ ነገር ሰማሁ የቀረ ልጅ አለህ ዛሬ ወደ ሲዖል የመጣ ልጅ አለህ ተባልሁ።
እውነት ልጄ ከፋኝ ስለአንተ ብዙ አሰብኩና ልጠይቅህ ይህንን ደብዳቤ ፃፍኩልህ።
ሲዖል ለብቻህ እንዴት ነው የራስህን የሲቃ ድምፅ እየሰማህ መሰቃየት እንዴት ነው ውስጥህን መልስህን ሳስብ በሀዘን ተገረፍኩ።
ልጄ ሆይ አባትህን አይተህ ትድን ዘንድ ተስፋ ነበረኝ እኔ በበደልኩ ሰዓት ካለቀስኩት ጥቂቷን ብታለቅስ ጴጥሮስ ከተፀፀተው ጥቂቷን ብትፀፀት በዳንህ ነበር።
ልጄ ሆይ ንስሀን ያህል ትልቅ መንገድ መጠቀም ነበረብህ እነሆ ዛሬ ከነ አብርሃም እቅፍ ታርፍ ነበር።
" ስምህ ከመዝገብ የጠፋው ነበር የሆነው ታሪክህ
ጥቂት ፀፀት ስላጣህ በሀዘን ባለመንበርከክህ"
እኛስ ዘመናተ ይሁዳዎች የአባታችን አዳም ታሪክ አያስተምረንምን?
14.04.202502:41
የሰሙነ ሕማማት ሰኞ
መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡
በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦
ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

13.04.202513:06
ብዙዎች ዝም እንድንል ቢጠይቁን ምናልባትም ቢያስገድዱን
ገድለውን እንኳን ዝም ቢያሰኙን በባህሪው ምስጉን የሆነን እርሱ እግዚአብሔርን
የቢታንያ ድንጋዮች ያመሰግኑታል።
ሆሳዕና በአርያም
መልካም በዓል
ጥርኝ ጥበብ
ገድለውን እንኳን ዝም ቢያሰኙን በባህሪው ምስጉን የሆነን እርሱ እግዚአብሔርን
የቢታንያ ድንጋዮች ያመሰግኑታል።
ሆሳዕና በአርያም
መልካም በዓል
ጥርኝ ጥበብ
11.04.202502:21
አቤቱ የተወደደ የስስት ልጅህ ነቅቷልና ተመስገን
በተጨነቀ ከተማ ውስጥ የማያልቅ ቸርነትህን እንደተለመደው በፀጋ ለመቀበል የልቦናዬን ሰሌዳ ከፍቼ እግሮቼን አንስቼ ወደምትመራኝ ጎዳና ለመሄድ ተነሳሁ....ስምህ በሚከበርበት ቦታ አውለኝ።
የእናትህን የእናትነቷን ፍቅር አታሳጣኝ...
አሜን
በተጨነቀ ከተማ ውስጥ የማያልቅ ቸርነትህን እንደተለመደው በፀጋ ለመቀበል የልቦናዬን ሰሌዳ ከፍቼ እግሮቼን አንስቼ ወደምትመራኝ ጎዳና ለመሄድ ተነሳሁ....ስምህ በሚከበርበት ቦታ አውለኝ።
የእናትህን የእናትነቷን ፍቅር አታሳጣኝ...
አሜን
Shown 1 - 20 of 20
Log in to unlock more functionality.