Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Open reading 👐 avatar
Open reading 👐
Open reading 👐 avatar
Open reading 👐
07.05.202504:19
ባለጠጎች ጊዜን ይገዛሉ፤
ድሆች ቁስ ይሰበሰባሉ፤
ብልህ ሰዎች ችሎታን ይሸምታሉ፤
ሰነፍ ሰዎች ግን ሰበብን ይገዛሉ።


🙏 ይሔው ነው!

◆━━━ ✎ ✎ ━━━◆
➬ Open Reading
| Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1 
@open_reading1
06.05.202504:38
ፋኖስ ገፄን ተመልክተው፥
ሰዎች ለጉድ አደነቁ
ህጻናት እኔን መሆን ተመኝተው ፥
አዛውንት በደስታ ሳቁ
"ዘላለም ብራ "
ብለው መረቁ...
(የቀኑም አሉ በ'ውነቱ...)

እንስቶች አይናቸው ሞቀ ፥
ባ'ይኔ ፍም ተጥበረበሩ
{ አይተውኝ ግን ያልወደዱኝ
በቁጥር ስንት ነበሩ?}

( ቢሆንም...)

ልቤ ግን ደስ አላለውም፥
ለብቻ ስመረምረው
አንቺ አይተሽ ያልተሳብሽበት፥
ፀዳሉ ለ'ሱ ምኑ ነው?

*

@open_reading1
@open_reading1
30.04.202510:27
አንድ ጠበቃ የውሃ ጉድጓዱን ለመምህር ሸጠለት። ከሁለት ቀን በኋላ ጠበቃው ወደ መምህሩ መጥቶ እንዲህ አለው፡ "ጌታዬ፣ ጉድጓዱን ሸጥኩልህ እንጂ በውስጡ ያለውን ውሃ አልሸጥኩልህም! ውሃውን መጠቀም ከፈለግክ ተጨማሪ መክፈል አለብህ።"

መምህሩ ፈገግ አለና እንዲህ ሲል መለሰ፡ "አዎ፣ እኔም ወደ አንተ ልመጣ ነበር። ልልህ የነበረው ውሃህን ከእኔ ጉድጓድ ውስጥ እንድታወጣ ነው፣ አለበለዚያ ከነገ ጀምሮ ኪራይ መክፈል ትጀምራለህ።"

ይህን ሲሰማ ጠበቃው ተደናግጦ "ኦ! ዝም ብዬ እየቀለድኩ ነበር!" አለዉ።

መምህሩ እየሳቀ "እንደ አንተ ያሉ ሰዎች እኮ ከእኛ ዘንድ ተምረው ነው ጠበቃ የሚሆኑት!" አለው። ይባላል።


◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                   @open_reading1
                   @open_reading1
የንጉስ ሴት ልጅ የመፍትሄ አካል ህይወት አስቀጣይ፣ ከተማ ነፃ አውጪ ታዳጊ፣ የመልካምነት እና የርህራሄ መገለጫ ናት።

የፈርኦን ልጅ ባልተረዳችው እና ባልጠበቀችው መንገድ የእስራኤላውያን ባለውለታ ሆናለች። ርህራሄዋ አንድ ህፃን ከማዳን አልፎ ትውልድን ህዝብን ነፃ አስወጥቷል። ደግነትሽ እና ሩህሩህነትሽ በቅንነት የምታደርጊያቸው በጎ ነገሮች ትውልድን ጠቅመውናነፃ አውጥተው የሚያስቀሩ ይሆናሉና እንደንጉሱ ልጅ በሄድሽበት ቅንነትሽ እና ደግነትሽ ይቀጥል።

ዛሬም አንድን ሰው አንሺ ምከሪ አበረታች ከወደቀበት ከፍ አድርጊው ነገ የመፍትሄ ሰው ይሆንልሻልና።

|| ይድረስ የንጉስ ሴት ልጅ ለሆነው - ለዛች ሴት
👸👸


          ፌቨን ጋሻው እንደጻፈችው ....
◆━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━◆

                 @open_reading1
                 @open_reading1
መጻሕፍትን የሚሸከም ሁሉ በውስጡ ጥበብን አልያዘም። እውቀትም በወረቀት ክብደት አትመዘንም፤ ይልቅ በአመለካከት ከፍታ በማስተዋል ጥልቅነት ትፈተሻለች። ብዙዎች ጋዜጣ ይዘው ብንመለከት አንድ ነገር ከመጠቅለል ወይም ቂጥ ከመጠረግ ውጭ ሌላ አላማ የለውም።

ስልጣን ላይ መውጣት የመሪነትን አቅም አያሳይም፤ ከብትም ቤተመንግሥት ስለገባ ንጉስ አይሆንም፤ ይልቅ በአንጻሩ ቤተመንግስቱ በረት ይሆናል። አንባቢ ለመባል መፅሃፍት ይዘው የሚዞሩትን አየዋቸው፤ ከዛ በተሻለ ለደደብ ተስፋ አለው። ቢሆንም ግን ደደብ ብዙ ደደብ መጽሐፍቶችን ካነበበ በጣም የሚያበሳጭ እና አደገኛ ደደብ ይሆናል። ምክንያቱም በራሱ የሚተማመን ደደብ ይሆናል!።

አንድ መፅሃፍና እና የአንድ ሰው መፅሐፍ ካነበበ ሰው ተንቀቁ፤ ከዚህ ሁሉ በላይ ብዙ መፅሐፍት ካግበሰበሰ ሰው ጋር መከራከር ግንብን በጣት ለመብሳት የመታገል ያህል የልብ ቁስል ነው። እናም የምለው ይህንን ነው፡ አዋቂ ሰው የሚያነበውን ያውቃል፤ የሚያነበውን የሚያውቅ መርጦ ያነባል!


     ## ምንጭ - ከ "አርምሞ"

                    መልካም የመጽሐፍ ቀን!
◆━━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
20.04.202517:15
በሕይወት

ትልቁ መሰናክል— ፍርሃት

አስቀያሚው ስሜት— ጥላቻ

ትልቁ ስህተት— ተስፋ መቁረጥ

ምርጡ ስጦታ— ይቅርታ

ትልቁ ጥንካሬ— እምነት

በጣም ቆንጆው ነገር— ፍቅር

@open_reading1
@open_reading1
ይህ የአድኃኖም ምትኩ መልዕክት ነው🔥

ሰኞ ግንቦት 4 "በመኖር በኩል" እናስመርቃለን

እናንተን የማገኝበት የምጠራበት የምጽፍበት  ፌስቡኬ 180 ቀን ታገደ አለኝ .. ድግስ ደግሰን የፕሮግራሙ ሰዓት ላይ  አዳራሽ እንደተከለከልኩ አይነት ነው ያዘንኩት ...

ድግሱ ተሰናድቶ አልቋል ብቻዬን እንዳልሆን  እንደኔ ሆናቹ ጥሩልኝ አስተዋውቁልኝ ተብላችኋል፣ መልእክቱን ማጋራት አትዘንጉ!


◆━━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
“...... የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ምንጭ ነው። ከገንዘብ ይልቅ እውቀትን እና ጥበብን ለማሳደድ ብዙ ጥረት ብታደርግ የተሻለ ይሆናል። ጠቢቡ ሰሎሞንም ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ። ከፍ ከፍ አድርጋት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ብታቅፋትም ታከብርሃለች። ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፤ የተዋበ ዘውድንም ታበረክትሃለች ሲል ተናግሯል።

.
.
.
በነገራችን ላይ የአንድ ጎልማሳ ጤነኛ ሰው አዕምሮ በአማካኝ 2.5 ሚሊዮን ጌጋ ባይት ፋይል መያዝ የሚያስችል አቅም እንዳለው ጥናቶች ያሳያሉ። የሰው ልጅ ይህን አዕምሮውን ስርዓት ባለው ትምህርት በመታገዝ ተሸቀዳድሞ በመልካም እውቀትና ጥበብ ካልሞላ እንደ ተንኮል፣ ቅናት፣ ጥላቻ፣ ግድየለሽነት፣ ዘረኝነት፣ ምቀኝነት፣ ስግብግብነት፣ አድርባይነት በመሳሰሉ የሕይወት ቫይረሶች የመሞላት እድሉ ከፍተኛ ይሆናል።"


           በረደድ ገዳሙ ከፃፈው
◆━━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
29.04.202518:11
አለም ላይ እንደሚጠላኝ  ነፃነት የሚሰጠኝ የለም። ድል የሚናፍቀኝ ድል ለመቀናጀት እምታገለው  ለሚጠሉኝ ሰዎች ለማስደመም  አይደለም።

እሚጠላ ሰው ይቀናል እንጂ አይደመምም..!

አለም ላይ እንደሚጠላኝ ሰው እንደልቤ  የሚያደርገኝ ነፃነት የሚያጎናፅፈኝ ማንም የለም..

የጠራኝ ሰርግ ላይ በቁጣ እና በሲልፐር ልሄድ እችላለሁ ... ቀልዶ እንዳይከፋው ብዬ በውሸት አልስቅም ...ተባበረኝ ሲለኝ ካልቻልኩ ውሸት አልፈበርክም ....

ሎተሪ ደርሶት "ይደረሰዋ አይነት ፊት" ሳልሳቀቅ ማሳየት የሚያስችል ጉልበት እንዳንፀባርቅ መብት ይሰጠኛል.....

ድክመቴ የሚወዱኝ ሰዎች ናቸው ።

አሞኝ እንዳለመመኝ የማስመስለው..
አጥቼ አለኝ አይነት ወሬ የማወራው..
የተቀየሙኝ ከመሰሉኝ ደንግጬ የማብራራው..

ለሚወዱኝ ሰዎች ብቻ ነው !!

እምባዬን በፈገግታ የምሸፍነው ...
ተስፋ አጥቼ ተስፋን የማስሰው  ..
ሳዝን ሃዘኔ እንዳይጋባባቸው የምደበቀው ..
ከምችለው በላይ የምጥረው ..
እንዳይቀየሙኝ የምዋሸው ..

ለምወደው ሰው ብቻ ነው ... 

ችርስ የምንወዳቹ ሰዎች ❤🍻
           ©Adhanom Mitiku


- @open_reading1 -
ከምሞት ኑሮ ሳይመቸኝ መኖርን እመርጣለሁ።
ቢያንስ ባልደሰትም የሚደሰቱትን ሰዎች እያየሁ እኖራለሁ።
ምን አልባት ከሞትኩ አድራሻዬ ከጨለማው ሀገር ከሆነ የሚያለቅሱትን እንጂ የሚደሰቱትን የት አያቸዋለሁ?

..... ድከም ሲለኝ አማርራለሁ እንጂ የማመሰግንበት አልባ አድርጎ አልፈጠረኝም።  የተወለድኩባትን ምድር ለምን ልውቀስ?

ከሌላ ፕላኔት አልመጣሁ ነገር ...አዳም እንኳ ውኃ ሳይሆን ወተት፣ አሜከላ ሳይሆን ውብ ቅጠል፣ እንክርዳድ ሳይሆን የህይወት ፍሬ ከምታበቅለው መጠማት መታረዝ ከሌለባት ወርዶ እንደ ባሪያ  ጥሮ ግሮ አልፏል።

ያላየኋት ገነት ለምን ትናፍቀኛለች?
የኑሮ እንቆቅልሽ ባልደርስበትም የተከፈተው ሳይዘጋ አያድርም። መሞት ለምኔ በደሰሳ ጎጆ ውስጥ  ብኖርም የጥዋቱን  የወፎቹን ዝማሬ  እየሰማሁና በሽንቁር ዘልቃ የምትገባውን የፀሐይ ጮራ እየተመለከትኩ ተደስቸ እኖራለሁ።

.........የሐብት ሚስጥር ሳይገለፅላቸው በድህነት ከሚማቅቁ ሰዎች ይልቅ መሞትን የሚመኙ ሰዎች ያሳዝኑኛል።

ያልቀመሱት ነገር ጥፍጥናው የቱ ጋ ነው?
ሕይወት የበሰለች ምግብ ናት።
ተልጣ ፣ተቆራርጣ፣ በውኃ ተዘፍዝፋና በእሳት ተንተክትካ በስላ እንደወጣች ምግብ ።

ሕይወት ማስቀጠል የሚቻለው ውኃውንም እሳቱንም ቀምሶ ነው።
የመንታ እናት ተንጋላ ተኛች ሲባል ተመችቷት ሳይሆን ሁለቱንም ለመከታተል ላለማድላት ነው።
በሕይወትህ ተንጋለህ የምትተኛው የሰማዩን ርቀት ለማየት አይደለም ። ከድካም ጎንን ለማሳረፍ እንጂ።
እሳት እና ውኃ ሲሆኑ የዋሉትን ጎኖችህን ጣል ለማድረግ ።

◆━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━◆

                 @open_reading1
                 @open_reading1
|| ዛሬ ዓለምአቀፍ የመጽሐፍ ቀን ነው!

በዚህ ቀን መመስገን ካለባቸው ሰዎች አንዱን ላመስግን?

የደራሲ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር) የመጽሐፍ የብርሃን መንገድ!!

በዚህ ዘመን ካሉ የሥነጽሑፍ ሰዎች መካከል ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ (ዶ/ር ) "ከጥቁር ሰማይ ስር"፣ "በዓሉ ግርማ ሕይወቱና ስራዎቹ" መጻሕፍትን ጨምሮ እጅግ የተዋጣላቸው መጻህፍትን ለአንባቢያን ከማድረሱ በተጨማሪ የንባብ ባህል እንዲጎለብት፣የሀሳብ ውይይት እንዲዳብር እየሰራ የሚገኘው ስራ እጅግ አድናቆት የሚገባውና በብዙ መንገድ መበረታታት ያለበት ነው ብዬ አምናለሁ።

ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ በ"ዛጎል መጻሕፍት ባንክ"በኩል ሀገር እየገነባ ነው። የመጻህፍትን የብርሃን መንገድነት ለትውልዱ እያመላከተ ነው።

በኢትዮጵያ የተለየ ሀሳብ ይዘው ስራ ላይ ከሚገኙ ተቋማት መካከል አንደኛው የሆነው "ዛጎል መጻሕፍት ባንክ" ከ40ሺ በላይ መጻሕፍትን በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ለሚገኙ ት/ቤቶች ፣ ማረሚያ ቤቶች ፣ በገጠር ከተማ ለሚገኙ ቤተ-ንባቦች ማሰራጨቱን ያገኘሁት መረጃ ያመለክታል።

 ጋሽ
እንዳለጌታ ከበደ እንዱ ለሀገርም ፣ለትውልድም፣ ለሰው ልጆች ሁሉ ለምትሰራው ስራ እጅግ የላቀ አክብሮት አለኝ።

## ምንጭ - ኤቨንት አዲስ - (Natty manaye)

                    መልካም የመጽሐፍ ቀን!
◆━━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
| ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

-  @open_reading1 -
@open_reading1  -  @open_reading1
ምናልባት ላልሰማችሁ መጽሐፍ ወዳጆች
በድጋሚ ላስታውሳችሁ ...... !

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ የሚካሄደው የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይና ባዛር ዛሬ ተጀምሯል።

ምናልባት የጠፉ ወይም አዳዲስ የታተሙ የዩኒቨርሲቲ ፕረሱን መጽሐፍፎች እናገኝ ይሆናል፡

ሔዳችሁ ሸምቱ።
ለወዳጆቻችሁ ስጡ።
መጽሐፍ ተገባበዙ እስኪ
📚

◆━━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
02.05.202507:46
ደራሲ ማክዳ ሁሴን አርሺ በአሜሪካን ሃገር ትልቁን ዓለም አቀፍ የስነ-ፅሁፍ ውድድር አሸነፈች።
*
*

ነዋሪነቷን በአሜሪካን ሃገር ያደረገችውና በኦቲዝም ላይ ከፍተኛ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በመስራት የምትታወቀው ኢትዮጵያዊቷ ማክዳ ሁሴን በሃገረ አሜሪካ የተካሄደውን አለም አቀፍ የስነ-ፅሁፍ ሽልማት ተሸላሚ ሆናለች።

በAUTHORS READING በተዘጋጀው ስምንተኛው አለም አቀፍ የሰነ-ፅሁፍ ውድድር ላይ በማክዳ ሁሴን አርሺ የተፃፈው “THE WORLD NEEDS A UNIQUELY HAPPY YOU” መፅሃፍ የሽልማቱ አንድ ዘርፍ በሆነው “Children’s book concept“ ዘርፍ የPENCRAFT BOOKS AWARD ተሸላሚ ሆናለች። በዚህ ውድድር ከተለያዩ ሃገራት የመጡ ተወዳዳሪዎችም ተሳታፊ ነበሩ።

ይህ ማክዳ ተሸላሚ የሆነችበት Pencraft book award በ2009 እ.ኤ.አ በደራሲያን በተመሰረተው  “AUTHORS READING” የሚሰጥ ሽልማት ነው።

መፅሐፉ ከድርጅቱ ኤዲቶሪያል ዳይሬክተር ከሆኑትና ከ1990 እ.ኤ.አ ጀምሮ በስነ ፅሁፉ አለም በቆዩት ዴቢድ ሄርን ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።

ደራሲ ማክዳ አርሺ "Shining As I am" በሚል በእንግሊዝኛ ግጥም ተፅፎ በታገል ሰይፉ ወደ አማረኛ የተተረጎመው "እንዳለሁ አበራለሁ" የተሰኘና ለልጆች ኦቲዝም ምን እንደሆነ በቀላል ቋንቋ የሚያስረዳ እና በአንድ የኦቲዝም ተጠቂ ልጅ ላይ የሚያጠነጥን ታሪክ የያዘ መፅሃፍን ለንባብ አብቅታለች። በተጨማሪም "የአለም መብራቶች" የተሰኘ የልጆች መፅሃፍን በእንግሊዘኛም በአማርኛም ፅፋ በአማዞን ላይ እየተሸጠ ይገኛል።

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                   @open_reading1
                   @open_reading1
28.04.202519:43
አንዲት ሴት ፕሮፈሰር ስለ "አንድ ወንድ ብዙ ሚስቶችን ማግባት" በተሰኘ አርእስት በአንድ አካባቢ ለሚኖሩ ሴቶች እና ወንዶች ገለፃ እንድታደርግ ትጋበዛለች።

ፕሮፈሰሯ የተጠቀሰውን አርእስት ገለፃ ለማድረግ እራሷ ነበረ የመረጠችው።

ፕሮፈሰሯ አንድ ወንድ ብዙ ሴቶችን ሲያገባ ለሴት ልጅ ያለውን ጠቀሜታ በዝርዝር አስረዳች።

ሴቶችም ይህን የጋብቻ ልምድ ተቀብለው ቢፈፅሙት ያለውን ጠቀሜታ አስተማረች።

ጥቅሙ ለእራሷ ለሴቷ እንደሆነና መቃወም እንደሌለባት አዳራሽ ውስጥ ላሉት ታዳሚዎች አስረግጣ ገለፃ አደረገች።

በአዳራሹ የፕሮፈሰሯን ገለፃ ስትከታተል የነበረች አንዲት ሴት እጇን አውጥታ ለፕሮፈሰሯ  እንዲህ በማለት አስትያየት ትሰጣለች ።

"በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ እና ገለፃ ስላደረግሽልን አመሰገናለሁ!"

"ከባለቤትሽ ጋር አንቺ ሳታውቂ ፣ አብረሸው እያለሽ  ከተጋባን አሁን  አራት አመታችን ነው ፣ መንታ ልጆችም አለን አለቻት።"

ፕሮፌሰሯ ከሴትየዋ ይህንን ስትሰማ  በአዳራሹ ውስጥ እራሷን ስታ ወደቀች ፣ሆስፒታልም ተወሰደች።

ፕሮፌሰሯ ሆስፒታል ከአልጋ ላይ ሆና ስትነቃ ያቺ አዳራሽ ውስጥ አስተያየት የሰጣቻት ሴት ከአልጋዋ አጠገብ ሆና አየቻት ።

ሴትየዋ  ለፕሮፌሰሯ እንዲህ አለቻት:-

"ባለቤትሽን እንኳን ላገባው በአይኔም አይቼው አላውቅውም ይህን ያልኩት ልፈትንሽ ነበረ፤ ፈተናውን ወድቀሻል።"

"ለሌላ ግዜ ስለ አንድ አስተሳሰብ ተቀበሉና አድርጉት ብለሽ  ሌሎችን ስታስተምሪ ፣መጀመሪያ አንቺ ራስሽ አምነሽና ፣ ተቀብለሽ  መሆን አለበት" በማለት ለፕሮፈሰሯ ነገረቻት።

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                   @open_reading1
                   @open_reading1
"ፍቅር የህጎች ሁሉ የበላይ ነው የሚባልበት ምክንያት ነገሮችን በመቀየር አቅሙና በኃያልነቱ እንደሆነ በውጣ ውረድ ውስጥ አሳልፌ አይቼዋለሁ"

📚 ርዕስ፦ሉባር
✍️ ደራሲ፦በርደድ ገዳሙ

◆━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━◆

                 @open_reading1
                 @open_reading1
ሰው ማለት ሰው የጠፋ እለት ሰው ሆኖ መገኘት ነው‼️

ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙏 ለአራዳው ያሬድ

ዛሬ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሴት ታራሚዎችን 3 በሬ አርዶ ማእድ በማጋራት እንዲሁም በዘፈኑ ሲያዝናና እና ተስፋ እንዳይቆርጡ ምክር እኔ ወኔ ሰጥቷቸው ነው የዋለው!

    እስር ቤት ውስጥ አይደለም እንዲህ አይነት የመዝናኛ ነገሮች ይቅርና ጠያቂ እንኳን ሲመጣ እንዴት እስርህን እንደሚያቀልልህና ደስ እንደሚልህ የምታውቀው እስርን ስታውቀው ብቻ ነው!

      አስባችሁታል እስር ደግሞ ለሴት ልጅ ምን ያክል ከባድ እንደሚሆን

    በበዓል ወቅት እስረኛን ታማሚን እና አቅመ ደካሞችን መጠየቅ በጣም ትልቅ ነገር ነው🙌


◆━━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
18.04.202504:03
"ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ"

ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ ከወንዙ በወድያኛው ዳር
ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።

ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ። በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ
ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።

ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምመሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?" አለው።

ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?" በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።

✍ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም።
ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ የሰዎችን የህይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ህይወት አምጥተን ለመትግበር ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን፡፡


               -  @open_reading1 -
@open_reading1  -  @open_reading1
06.05.202514:09
ተጀመረ !

የመጻሕፍት ዐውደ ርዕይና ባዛር በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ  በስድስት ኪሎ ካምፓስ ዛሬ ተጀምሯል :: 

ጃዕፈር መጻሕፍትም ብዛትና አማራጭ ያላቸውን መጻሕፍት በቅናሽ ዋጋ ይዘን ቀርበናል ብሎናል::

እስከ ክረምት የሚበቃንን ያህል እንሸምት
📚

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
ሱፊዎች "ለጠቢብ ሰው እውነተኛ ገንዘቡና ሀብቱ 4 ነገሮች ናቸው ብለው ያምናሉ።አንደኛው ከአንድበቱ የሚወጣው ቃል እውነት ብቻ ሲሆን፤ሁለተኛው ንዴትና ቁጣውን መግዛት ሲችል፤ሶስተኛው ስለሚመገበው ምግብ እምብዛም ግድ ከሌለው፤አራተኛው በሁሉ ነገር የሚታመን ሲሆን በእርግጥም እርሱ ሀብታም ነው" ይላሉ።

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                   @open_reading1
                   @open_reading1
ካህሊል ጅብራን ነፍሴን ሰባት ጊዜ ታዘብኳት ይለናል  ......!

➬ መጀመሪያ  ~ ከፍታ ለመድረስ ስንትጠራራ

➬ ሁለተኛ ~ በአንካሳው ፊት እያነከሰች ስትሄድ

➬ ቀጥላ  ~  አስቸጋሪና ቀላል አማራጭ ቀርቦላት ቀላሉን የመረጠች ግዜ

➬ ደግሞ ቀጥላ  ~  "ስህተት ፈፅማ ሌሎችም ይሳሳታሉ "የሚል ውዳቂ ምክንያት ስታቀርብ

➬ ሌላ ጊዜ  ~  ለሽንፈት እጇን ከሰጠች በኋላ ታጋሽነቷን እንደ ጥንካሬ የተመለከተች ጊዜ

➬ ደሞ ሌላ ግዜ  ~  ከጭምብሎችዋ አንዱ መሆኑን ስታውቅ በአስቀያሚ ፊቷ ላይ  ስታላግጥ

➬ በመጨረሻም  ~  የምስጋና ዜማ ካሰማች በኋላ ውዳሴዋን እንደ ደግነት የቆጠረችው ግዜ  !!!

◆━━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━━━◆

                  @open_reading1
                  @open_reading1
|| በ 99 ዓመታቸው መጸሐፍ የሚጽፉ ጀግና አባት ስላሉን እንኳን አደረሶት ብንል የልጅ ወግ ነው።

           📷 Benju man

◆━━━━ ✎ ✦ ✎ ━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
እግዚአብሔር ታላቅ ነው!
ከ24 ዓመታት በፊት ተጋቡ፤
ከ14 ዓመታት በፊት ተፋቱ፤

ዛሬ ትንሳኤ ነው፤ ዛሬ ፋሲካ ነው።
በአራት ልጆቻቸው አርቲስት ገነት ንጋቱ እና ረዳት ፕሮፌሰር ሙሉጌታ ጀዋሬ  ዳግም ተሞሸሩ ፤ ዳግም ተጣመሩ...

ከፈንታሌ እስከ ኤርታአሌ ፕሮጀክት አንዱ
በሰቃ ሀይቅ ተንተርሶ በተሰራው ቬኑና ሪዞርት 18 ቤተሰቦች ብቻ በተገኙበት ተጣምረዋል።

እሰይ!
ደስ ይላል።

በነገራችን ላይ ...
ይህንን ቅዱስ ተግባር የፈጸሙት፤ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱት ሰው  የረገጡት መሬት አይክዳዎት።

ይህንን ትዕይንት እየተመለከትን፤ ( በዕንባ እና ሳቅ) እየታጀብን መርቀንዎታል። ...  ቀሪውን  ልብ ይመርቅ!


◆━━━━━━✎✦✎━━━━━━━◆
➬ Open Reading | Rҽαԃιɳɠ Lιϝҽ Sƚყʅҽ !!

@open_reading1  -  @open_reading1
@open_reading1  -  @open_reading1
17.04.202521:49
ሀዘን ሲሰማሽ እኔ እንዳለሁልሽ አስታዉሺ፣ ምናልባት በቂ ላልሆን እችላለዉ ግን ካጠገብሽ እሆናለሁ᎓᎓ ምክንያቱም እወድሻለሁ!

               -  @open_reading1 -
@open_reading1  -  @open_reading1
Shown 1 - 24 of 122
Log in to unlock more functionality.