Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ፍኖተ ሕይወት media avatar
ፍኖተ ሕይወት media
ፍኖተ ሕይወት media avatar
ፍኖተ ሕይወት media
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇

https://t.me/addlist/hEiOrEwr2MEwYTQ0
30.04.202516:18
ሰበር ዜና

ቋሚ ሲኖዶስ ልዩልዩ ውሳኔዎችን አስተላለፈ።

ሚያዝያ 22/2017 ዓ.ም አቤኔዘር ዘተዋሕዶ ገፅ

1. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል “ማርያም ቤዛዊተ ዓለም” አትባልም በማለት ከቤተ ክርስቲያናችን የነገረ ማርያም አስተምህሮ ውጪ የሰጡት ሕጸጽ ያለበት ትምህርት በሊቃውንት ጉባኤ በኩል በሚገባ ተመርምሮና ተጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር ለቋሚ ሲኖዶስ በአስቸኳይ እንዲቀርብ ብፁዕነታቸውም ጉዳዩ ተጣርቶ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ግቢ ውስጥ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በተአቅቦ እንዲቆዩ፣

2. ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት እና ብፁዕ አቡነ በርናባስ የደቡብ ካሊፎርኒያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፏቸው የስሕተት ትምህርቶችና በሌሎችም መምህራን የተላለፉ ነቀፋ ያለባቸው ትምህርቶች ካሉ የሊቃውንት ጉባኤ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ አንጻር በሚገባ መርምሮና አጣርቶ ከመፍትሔ ሐሳብ ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቋሚ ሲኖዶስ እንዲያቀርብ ተወስኗል።

መረጃው የ የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።


Share አድርጉት ለሁሉም ይድረስ ❗️❗️
https://t.me/silase
29.04.202520:01
የማንን መንፈሳዊ ትምህርት ይፈልጋሉ
ዕለተ
አርብ


ቅድስት ቤተክርስቲያን


https://t.me/Fnote_Hywet

https://t.me/Fnote_Hywet
https://t.me/Fnote_Hywet
24.04.202503:06
የመጥምቁ ዮሐንስ ልብስ ምን ነበረ❔
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ
የሁለተኛው ቀን ቶማስ

ፍኖተ ሕይወት media
https://t.me/fnote_hywet

አስተማሪ ከሆነ like and share
በማድረግ ለብዙ ሰው ይድረስ
03.05.202507:02
🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ?

   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤  ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
  🎤   ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ   🎤
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤    ዘማሪ አቤል መክብብ      🎤
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
🎤     ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ    🎤
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
   ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
  🎚       ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ      🎚
   ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
30.04.202513:44
እግዜአብሄር ሰውን ከምንድነው የፈጠረው ?
25.04.202511:04
🛑መንፈሳዊ ጥያቄ ተሳተፉ

“አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፤ አሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።”

ያለው ቅዱስ ማነው?
24.04.202502:58
እግዚአብሔር ሄዋንን ከአዳም ከየትኛው የሰውነት ክፍሉ ነው የፈጠራት ❔
01.05.202504:45
✞ጊዮርጊስ በዚያች ቀን✞

ጊዮርጊስ በዚያች ቀን ከፈተናው አንጻር
ስለ ሃይማኖቱ የታየው ምን ነበር

ያመነውን አምላክ አላውቀውም እንዲል
በሥልጣን በገንዘብ እርሱን ለመሸንገል
የዱድያኖስ ጭፍሮች ነበር ሲያሴሩበት
ልቡናው ምን አለ ሲቀርብ ለመስዋዕት
አዝ= = = = =
ስገድ ባሉት ጊዜ ሰው ለሰራው ምስል
ትዝ አለው ጊዮርጊስ የአምላኩ ሕያው  ቃል
ከሠለስቱ ደቂቅ ከዳንኤል ጋራ
በእሳት ነበልባል ውስጥ ተአምር ሲሰራ
አዝ= = = = =
ቂርቆስ ኢየሉጣን ከመቃጠል ዋጅቶ
ያቀዘቀዘውን ፍሉን ውኃ አጥፍቶ
አስታውሷል ጊዮርጊስ ያንን ኃያል ጌታ
መስቀል መሸከሙን በዚያች በዚያች ጎልጎታ
አዝ= = = = =
ጴጥሮስና ጳውሎስ አባቶቹን መስሎ
ሞትን አሸነፈ በእምነት ተጋድሎ
እንድንጸና በእምነት ይቺን ዓለም ንቀን
በሰማዕቱ ምልጃ አምላክ ይጠብቀን

መዝሙር
በማህበረ ቅዱሳን ዘማርያን


". . . .የእሳትን ኃይል አጠፉ. . . እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ . . . በእስራትና በወኅኒ ተፈተኑ በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፥ ተፈተኑ፥ በመጋዝ ተሰነጠቁ፥ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ . . . "
              ዕብ ፲፩፥፴፬-፴፯
╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
 @fnote_hywet
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧•  ══╯
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇

https://t.me/addlist/hEiOrEwr2MEwYTQ0
24.04.202520:24
ምናልባት
ወ ደ ፊ ት!
<strike>~</strike>~~~
እኔም ትልቅ ሆኜ
እሄ ትንሽ ልቤ አድጎ ከተገኘ
በ ትላልቅ ሀሳብ ቅኔ ከተቀኘ
~~~~
ዛሬ አሰባስቤ
ያስቀመጥኳቸውን የበደል ጥሪቶች በደሜ መዝግቤ
- - - ነገ በተራዬ
አስረክበዋለው ውስጤን ላቆሰለው ምስጋና ደርቤ

ለምን ቢባልማ

ክፉ ለቸረኝ ሰው ክፋት አላወርስም
ቂም በቀል አልይዝም
ምክንያቱም
- - - **እንኳን እኔ ፍጡሯ
ፈጣሪም ራሱ ምህረት ነው እንጅ ቅጣት አያውጅም!
             
𝕃𝕚𝕜𝕖❤️  𝑆ℎ𝑒𝑟💌  𝗝𝗼𝗶𝗻📥 🙏
     

         @AWDEKALAT_2112   🥇
20.04.202519:40
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ
#ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማክሰኞ
#ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ
#አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ
#አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ
#ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ
#ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ
#ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡

ፔጁን #Like_Sebscribe_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ።

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram 👇👇👇
https://t.me/Fnote_Hywet
https://t.me/Fnote_Hywet
ሰማዕተ እየሱስ
🥀ሚያዚያ 22 በዚህች ቀን ኢትዮዽያዊው ጻድቅና ሐዋርያ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከኢትዮዽያ ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዘው ከቅዱሳት መካናት ተባርከዋል::

ጻድቁ ምድረ እሥራኤል የገቡት በየመንገዱ መንፈሳዊ ዘርን እየዘሩ: እያስተማሩና እያሳመኑ ነበር:: የወቅቱ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሚካኤል ጋርም ተገናኝተው ቡራኬን ተሰጣጥተዋል::
+ዋናው ጉዳይ ግን ከዚህ በሁዋላ ነው::

ጻድቁ እመቤታችንና ጌታችን ከጽንሰታቸው እስከ ዕርገታቸው የረገጧቸውን ቦታዎች ሲመለከቱ በፍጹም ተደሞ እንባቸው ይፈስ ነበር:: ምክንያቱም እግዚአብሔር ስላበቃቸው ተክለ ሃይማኖት የሚያዩት ቦታውን አልነበረም:: በገሃድ:-
*በቤተ መቅደስ ብስራቱን
*በቤተ ልሔም ልደቱን
*በቤተ ዮሴፍ ግዝረቱን
*በፈለገ ዮርዳኖስ ጥምቀቱን
*በቤተ አልዓዛር ተአምራቱን ይመለከቱ ነበር::

የጉብኝታቸው የመጨረሻ ክፍል ወደ ሆነው ቀራንዮ ደርሰው ጌታቸውን እንደ ተሰቀለ ሆኖ ቢመለከቱት ከዓይናቸው ይፈስ የነበረው ቁጡ እንባ መልኩን ቀየረና ዓይናቸው ጠፋ::
በዚያች ቅጽበት ስም አጠራሯ የከበረ እመቤታችን ድንግል ማርያም ፈጥና ደርሳ ተክልየን ወደ ሰማይ አሳረገቻቸው::

+በዚያም:-
*የብርሃን ዐይን ተቀብለው
*6 ክንፍ አብቅለው
*የወርቅ ካባ ላንቃ ለብሰው
*ማዕጠንተ ወርቁን ይዘው
*ከ24ቱ ካህናተ ሰማይም ተደምረው
*ሥላሴን በአንድነቱና ሦስትነቱ ተመልክተው
*"ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ" ብለው መንበረ ጸባኦትን አጥነው ወደ መሬት ተመልሰዋል::

የተክለ ሃይማኖት አምላክ ከጻድቁ ትሩፋት: ጸጋና በረከት ይክፈለን::

የጻድቁ ወዳጆች ሼር 🌹 በማድረግ አዳልሱ 🙏🏻❤️

ምንጭ፡-ስክሳር ዘወርሐ ሚያዚያ 22
@fnote_hywet
24.04.202517:23
የጋብቻ ሕይወት እና የሩካቤ ሥርዓት – ክፍል ፩
የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ በፍቅርና በአንድነት መኖርን የሚሰብክ በመኾኑ ፍቺን አጥብቆ ይከለክላል፡፡ ከተጋቡ በኋላ የሕይወት መሰናክሎችን በመፍታት አብሮ መኖር እንጂ መለያየት ክርስቲያናዊ ሥርዓት አይደለምና፡፡ በመኾኑም ችግሮችን በውይይት በመፍታት፣ በመመካከርና በመፈቃቀር ተስማምቶ እስከ ሞት ድረስ መኖር ተገቢ ነው፡፡ ነገር ግን በትዳር ሕይወት እጅግ የከበደና መፍትሔ የሌለው ችግር ሊመጣ ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ ለጉዳዩ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ መወያየት፣ ከንስሓ አባት ጋር መመካከር፣ በጾም በጸሎት መትጋትና እግዚአብሔርን መማጸን ይገባል፡፡
ኾኖም በመካከላቸው በሃይማኖት ወይም ሊፈታ በማይችል ልዩ ልዩ ምክንያት ለጉዳትና ለሞት የሚያደርስ ግጭት በተደጋጋሚ ከተከሠተ፤ አንዳቸው ወይም ሁለቱም ከትዳር ውጪ ከሔዱ (ዝሙት ከፈጸሙ) እነዚህን ችግርች በምክክር መፍታት፣ በንስሓም ማጽዳት ካልተቻለ መፋታት ይፈቀዳል፡፡ ከዂሉም በላይ ከሁለቱ አንዱ በሞት ከተለየና በሕይወት የቀረው አካል ጋብቻ መመሥረት ከፈለገ ሁለተኛ ማግባት ይቻላል፡፡ ያም ኾኖ ግን በሕገ ቤተ ክርስቲያን ከተጠቀሰው ምክንያት በቀር መፋታት አይገባም (ፍትሐ ነገ. አን. ፳፬፣ ቍ. ፲፩-፲፯)፡፡


ለወዳጆ ያጋሩ 📲

        👇🏼👇🏼👇🏻👇🏼👇🏻👇🏼

🛐 https://t.me/Fnote_Hywet🛐
24.04.202506:20
የማንን መንፈሳዊ ታሪክ ይፈልጋሉ👇👇👇


┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የ አባ እንጦስ ታሪክ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የ ሰማእቷ ቅድስት አርሴማ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የ ንጉሥ ዳዊት
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የ ሙሴ ጸሊም
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የ አብነ ሺኖዳ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔የ ቅዱስ ኤፍሬም
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የ ቅድስት ፀበለ ማርያም
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔 የአማእቱ ቅዱስ ሚናስ
┗━━━━━━━━━━━━━━┛
┏━━━━━━━━━━━━━━┓
🔔የ ጻድቁ አባ ተክተክለሃይማኖት
┗━━━━━━━━━━━━━━┛

🔗የሁሉንም መምህራን ትምህርት ለማግኘት🔔
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
23.04.202515:07
🛑በ telegram ምን ማግኘት ይፈልጋል
20.04.202501:00
Shown 1 - 24 of 60
Log in to unlock more functionality.