Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት፪ avatar

ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት፪

TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateApr 03, 2025
Added to TGlist
Apr 03, 2025
Linked chat

Latest posts in group "ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት፪"

ገድለ ቅዱሳንን ማን ይጽፈዋል?
(ክፍል፩)
፩ኛ.በሕይወተ ሥጋ እያሉ ረድ ይሰጣቸዋል። ረድእ የሚሆን ጸዊረ ነገር የሚቻለው የአበውን የተጋድሎ ፈሊጥ የተረዳ ሰው ነው።
ያዩትን የሰሙትን በምሥጢር ያጫውቱታል ሲያርፉ ይጽፍላቸዋል።
፪ኛ.ፍጺማን አበው ለአበው እንደ ዕንጦንስ እና እንደ አባ ጳውሊ ሲገናኙ ያደረገላቸውን ይነጋገራሉ አንዱ ቀድሞ ያርፋል ውዳሴ ስለማይሆንበት ይነግርለታል ይጻፋል።
፫ኛ.ካረፉ በሁዋላ የሠሩትን ያገኙትን ጸጋ ክብር ከገዳሙ ላንዱ ለበቃው ጣዕም ለቀመሰው በአካለ ነፍስ መጥተው ያገኙትን ክብርና ኪዳን ይነግሩታል ይጻፋል።
፬ኛ.በሕይወት ዘመናቸው ማኅበሩ በየግሉ የተመለከታቸውን የተጋድሎ እውነቶች ያሰባስቡለታል ይጻፋል።
፭ኛ.አንዳንዶች በትዕዛዘ እግዚአብሔር ገና በሕይወት እያሉ በትእደዛዝ አጽፈው ይሰናበታሉ(አባ ኪሮስ ለአባ ባውሚን፣ብፁዓን ጻድቃነሰ ለአባ ዞሲማስ እንደ ነገሩት)።
፮ኛ.በሕይወተ ሥጋ እና በእረፍት ያደረጉት ተአምራት ይሰበሰባል የትሩፋተ-ጸጋ ብርሃናቸው እየጎላ ሲሄድ ይጻፋል።
፯ኛ.የትኛው ቅዱስ ግን ሳያርፍ ገድሉ አዘከርለትም።ቤተ ክርስቲያን ቅድስናውን ስትመሠክርለት በኋላ ነው ግን ገድሉ ተአምራቱ ሲነቡብ ይኖራል።
"እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።"ማቴ.፭፥፲፬
የተጠበቀ እውነት፦
እነዚህ ሦስት ነገሮች ተስማምተው ከተገኙ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል።
፩.ሰው ከእግዚአብሔር ጋራ ያለው ግንኙነት፣
እግዚአብሔር ወደሰው በረድኤት በጸጋ፣ሰው ወደ እግዚአብሔር፦በሕግ በአምልኮት።(ፍቅረ እግዚአብሔር ነው።)
፪.ሰው ከሰው ጋራ ያለው ግንኙነት።
(በፍቅረ ቢጽ)
፫.ሰው ከሥነ ፍጥረት ጋራ ያለው መስተጋብር።
(በመገቢነት)
እነዚህ በትክክል ተጠብቀው ከተገኙ ዓለም ትንሿ ገነት ትሆናለች።
ሁል ጊዜ በአጀብ እና በዘብ የሚወጣ የሚገባ አባት በምእመናን ላይ ችግር ያለ አይመስለውም።
መታጀቡ ክፉ ሁኖ አይደለም።ክብረ ቤተ ክርስቲያን ነው።
ዝናውን ችሎ ሥራ መሥራት ለማይችል አባት ግን ትልቅ መቅሰፊያ ነው።
ሁልጊዜ የሚታጀቡና የሚወደሱ ሰዎች ደግሞ ዝቅ ብሎ መሥራት ያቅታቸዋል።
https://t.me/mstaketsehay
በዚህ ገጽ ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ገጹን ለማሳደግ እባካችሁ ተባበሩን።
ጉባኤ ቤቱ ተደራሽ ሁኖ የጽሑፍ መልእክቶችን እንዲያደርስ ለምታውቁት ሰው ሊንኩን ጋብዙልን።
ተባበሩን።
ክርስቶስ በኩረ ትንሣኤ ነው።(ክፍል፪)
ትንሣኤ ማለት ተንሥአ ተነሳ ካለው የግዕዝ ቃል የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙ መነሣት፣መለወጥ፣መታደስ፣ከፍ ማለት፣መግነዝ ፍቱልኝ መቃብር ክፈቱልኝ ሳይሉ መነሣት ማለት ነው።ሰ፡-ሰው ፣ሣ፡-ትንሣኤ ነው።
ጥንቱን በተፈጥሮ ተንሣኢ ነበር።
ምሥጢረ ትንሣኤም አምላካችን እግዚአብሔር ትንሳኤም ሕይወትም እንደሆነ ማመን ነው።
ነፍስ ከሥጋ ከተለየች በኋላ በእግዚአብሔር አዋሐጂነት አንድ ወገን ሁነን እንነሣለን።
ከሞት ባሻገር ሕይወት እንዳለ በማመን እና በርሱ አዋሐጂነት መነሣት እንዳለ በማመን የሚገኘውን ተስፋ ስንጠባበቅ እንኖራለን።
    ትንሣኤ በሁለት ዋና ክፍል ይከፈላል፦
[  ] ፩ኛ ትንሳኤ ዘለሕይወት - የጻድቃን ትንሣኤ ነው፡፡[  ] ፪ኛ ትንሣኤ ዘለደይን -የክፉ ሰዎች ትንሳኤ ነው።
ወይም በላላም ገለጻ የትንሣኤ አይነቶች በአራት ሊነገሩ ይችላሉ፦
[  ] ፩. ትንኤ ልቦና (ኅሊና) በህሊናው ፍጹም ሃይማኖትን ይዞ በምግባር እየተገለጸ በተስፋ ሲጠባበቁ መኖር ነው።
[  ] ፪. ትንሳሣኤ አልአዛር፦ለጊዜው በሥጋ ተነሥተው ተመልሶ እስከ ትንሣኤ ዘጉባኤ ድረስ ማራፍ ነው።
[  ] ፫. ትንሣኤ ክርስቶስ፦በራሱ ፈቃድ የተከናወነ በኩር የሆነ ትንሣኤ ነው።
[  ] ፬.ትንሳኤ ሙታን ናቸው፤(ዘለ ክብር እና ዘለሀሳር) ይሄ በፍጻሜ ዓለም በእግዚአብሔር ትዕዛዝ የሚፈጸም ጉባኤያዊ ትንሣኤ ነው። የሰው ልጅ እናቶች ሦስት ናቸው፦
፩ኛ፦ እናት አባት፣
፪ኛ፦ዮርዳኖስ፣
፫ኛ፦መቃብር ናቸው፡፡
[  ]      ዋነኛው ትንሣኤ ልቡና ነው።
፩.  ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረውን  በሦስት አካል የተገለጠውን         አንድ አምላክ እግዚአብሔርን  ማመን  መታመን  እና መመሥከር፤መነሣሣት።
፪.  የአምላክን ሰው መሆን እና የሰውን ልጅ ድኅነት ማመን  መታመን  እና መመስከር፤መነሣሳት
፫.  ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሕብረት ሊነጥል የሚችል (ኅጢአት ፣ በደል) እና       የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኅብረት እንዳትቀጥል  ሊያደርግ ከሚችል ማንኛውም  ነገር (ፍልስፍና   ደርጅት) ጋር እንደ አመጣቱ ለመመለስ  የሚደረግ ተጋድሎ ትንሣኤ  የህሊና ትንሣኤ ይባላል፡፡
እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሰው ሁኖ ሊያድን እንደመጣ ፣ዳግመገኛም ለፍርድ እንደሚመጣ ማመን ትንሣኤ ነው።
ትንሣኤ ልቦና ያላቸው ሰዎች በአምላካችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ከኀጢአት ባርነት በሃይማኖት እና በንስሓ ነጻ የወጡ ናቸው፡፡ማለትም ኀጢአታቸውን  ለመምህረ ንስሓ ተናዘው ቀኖናቸውን ጨርሰው ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሚቀበሉ ሰዎች ትንሣኤ ልቡና የአላቸው ናቸው ማለት ነው።
በተቀደስች ሃይማኖት።፦ቀድምና ባላት ፣ተለዋዋጭ ባልሆነች፣ሰው ባልሠራት፣በተገለጠች፣በተቀበልናት፣በምናስረክባት ሃይማኖት  ሥርዓት እና ሕግ መሠረት መኖር ማለት ትንሣኤ ልቡና ነው፡፡
ክርስቶስ በኩረ ትንሣኤ ነው፦(ክፍል፩)
እግዚአብሔር በባሕርዩ ሕያው ነው።ለሕያውነቱ ምክንያትየለውም።ከሕያው እግዚአብሔር የተገኙ የተፈጠሩ መላእክትም ለሕይወት ተፈጥረዋልና የጸጋ ሕያዋን ናቸው።የባሕርይ መገለጫውን የሚሳተፉ ደቂቀ አዳምም የተፈጠሩት ለሕይወት ነው።እግዚአብሔር በባሕርዩ የሚገለጽበትን ሁሉ መላእክት እና ደቂቀ አዳም በጸጋ ይሳተፉታል።ለሰው ልጅ ሕይወት ጥንቱን የተፈጠርንለት ዓላማ ነው።ስለዚህ በተሀድሶ እየከበረ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት እንዲገባ የተፈጠረው የሰው ልጅ በነጻ ፈቃዱ የተሐድሶ እድሜውን አሳጥሮ ወደ ፍዳ ወረደ።ሕይወትን ሲያጣ የሞት ሞት በባሕርዩ ዘልቆ ገባ።በጸጋ ተዋሕዶ የከበረባትን ሕያውነትን አጣ።በነጻ ፈቃዱ እንደ ወደቀ ወደ ሕይወቱ የሚመልሰው፣ከሞት የሚያድነው የሚያድነው ይፈልግ ነበር።ፈታሒ በጽድቅ እግዚአብሔር ሞት ወደ አዳም ባሕርዩ ዘልቆ ቢገባም ሕይወትም ወደ አዳማዊ ባሕርዩ በተዋሕዶ ገባ።እስከ ጊዜው ድረስ የመጀመሪያው ሰው አዳም በበደሉ ምክንያት ከገነት ከወጣ በኋላ በዚህ ዓለም ቤት ሰርቶ ልጅ ወልዶ የሚኖር ሆነ።በዚህች የፍዳ ዓለም አዳም ልጆችን መውለድ ጀመረ።አዳምም ቃኤልንና አቤልን ወለደ፤ቃኤልም አቤልን ገደለው፤የአቤል ዘር በሞት ቀረ፣የቃኤል ዘር በኀጢአት ቀጠለ፣ነፍስ ከሥጋ የመለየት ሞት በአቤል ጀመረ።የሴት ዘር በልደተ ተስፋ የሚቀጥል ሆነ። የአዳም ፯ኛ ትውልድ ሄኖክ  ይባላል።ሄኖክም ይህ ዓለም ካልተውት አይተውም ብሎ እግዚአብሔርን ያመሰግን ነበረ ከዚህ ዓለምም ተሠወረ።በመጀመሪያው ልጅ በአቤል ሞት እንዳለ ነገረን።በሰባተኛው ልጅ በሄኖክ ደግሞ ትንሣኤ ዕርገት እንዳለ ነገሮናል።"በአቤል አፍርሆሙ ወበሄኖክ አንቅሆሙ-በአቤል አስፈራራቸው በሄኖክ አነቃቸው።"እንዲል ዮሐ. አፈ .ድር.ሞት እንዳለ በአቤል  አስፈራራን ትንሣኤ እንዳለ በሄኖክ ነገረን ማለት ይህ ነው።
ትኵረት የተነፈጋቸው አምዶች
❖ በአንድ ሥርዓተ መንግሥት ቅድሚያ የሚሰጣቸውና ለመጀመሪያ ትልቁ በጀት የሚበጀትላቸው ሁለት ናቸው እነዚህም
(አንደኛ) ትምህርት
(ሁለተኛ) ጦር ኃይል (ውትድርና)
ሀገር የምትጠበቀው በጦር ኃይልና በትምህርት ስለሆነ ።

❖ በቤተክርስቲያን ትኵረት የተነፈጋቸው ሁለቱ አምዶችም ጉባኤ ቤትና ገዳማት ናቸው ምክንያቱም ቤተክርስቲያን ተጠብቃ የምትኖር በእነዚህ ነውና እነዚህ ካልተጠበቁ ቤተክርሰቲያን በር አልባ ደጅ ናት
በር የሌለውን ደጅ ደግሞ ማንኛውም ገብቶ ይዘርፈዋል ለዚያም ነው አሁን ቤተክርስቲያንን ማንኛውም ገብቶ የፈለገውን መልዕክት ሲፈልጉ ሥጋዊ ፍላጎታቸውን ሲፈልጉ የምንፍቅና ኃሳባቸውን ዘው ብለው ገብተው የሚያስተላልፉባት ።

❖ [አንደኛ) ሚዲያ ወለድ ሊቃውንት ነን ባዮች
ላስታውሳችሁ ባለፈው በነየኔታ ገብረመድኅንና በእነ አባ ገብረኪዳን ስም ነገረ ክርስቶስ በሚል ስም የታተመው መጽሐፍ ላይ ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር አይባልም የሚል ቃል ተገኝቶ ይህ ስህተት ነው ክርስቶስ በሥጋው ፍጡር ይባላል ሲባል ሚዲያ ወለድ የሊቃውንት የቀለም ዘር የሌለላቸው ሊቃውንት ነን ባዮች በር አልባ አድርገዋት ገብተው ሲንጫጩብን የነበር ?

❖[ሁለተኛ] መታወቅ የቀደማቸው አላዋቂዎች
እንደ ግንቦትና እንደ ሰኔ ነጎድጎድና መብረቅ በባዶ ጩኸውብን ጩኸውብን ሚሊየነር ሁነው ትተውን የኮበለሉ ? የግንቦትና የሰኔ መብረቅና ነጎድጓድ ዝናም የለውም ነጉዶና በርቆ እልም ይላል እነዚህም  በጧፍ በከበሮ በሞንታርቦ በክራር .....ያለ አንዳች እውቀት በርቀውብንና ነጉደውብን እልም ድርግም አሉ ይህ ሁሉ ቤ/ያን በር አልባ ሆና አይደለምን ?

❖ ለቤተክርስቲያን ገዳማት የጦር ኃይሎቿ ናቸው ።
የገዳማውያን ፆም ጸሎት ትሩፋት መላው የቤተክርስቲያን ጦርና ጋሻ ናቸው በጾም በጸሎት ኤልያስ ሰማይን ዘግቷል ሰማይንም ከፍቷል እሳት አዝንሟል ፦ ኢያሱ በረድ አዝንሟል ፀሐይ አቁሟል ንጉሡ ካሌብ ጠላት አጥፍቷል ባህር ከፍሏል ።
እነዚህ ገዳማት በሲኖዶስ ትኵረት ሲነሳቸው
መናንያኑም ከገዳም ወደከተማ መነኑ አደለም ቤተክርስቲያንን ሊጠብቁ ቤተክርስቲያንን ወደመዝረፍ ገቡ አርአያ ምንኵስናን አስነቀፉ
ይህ ሁሉ ቤ/ያን በር አልባ ሆና አይደለምን ?

❖ ጉባኤ ቤቶች መምህራኗ ናቸው
በእውነት ሲኖዶስ ጉባኤ ቤቶች መኖራቸውን ስንኳን ለማወቁ እጠራጠራለሁ ቢያውቅማ ኖሮ በዚህ ባምስት በስድስት አመት ውስጥ ስንት ጉባኤ ቤቶች ናቸው የተዘጉ ? ስንት ደቀመዛሙርት ናቸው የተገደሉ? ስንት መምህራን ናቸው የታሰሩ ? ስንት ጉባኤ ቤቶች ናቸው የተቃጠሉ ?
የገንዘብ እጥረት እንዳይባል በፍጹም አደለም ምክንያቱም  በቢልዮን የሚቆጠር የቤተክርስቲያን ገንዘብ በባንክ ተከማችቶ ኢአማኒውና መናፍቁ ሊበራሉና ሴኩላሩ አደል ኢንፖርትና ኤክሰፖርት የሚያደርግበት ?
      [ለሁለቱ አምዶች (ምሰሶዎች) ትኩረት]
ያለነዚህ ግን ቤተክርሰቲያን በር አልባ ደጅ ናት።
የፍኖተ ኤማሁስ ደቀመዛሙርት እና ተርጓሚ መምህራቸው
 
✍️1..በፍኖተኤማሁስ ጉባኤ ቤት  ያሉ  መጠራጠር የጠፋላቸው ደቀመዛሙርት:-

✝️  ብልሆች ደቀ መዛሙርት  ናቸውና በመንገድ ቧልት ሳይሆን የመምህራቸውን  ታሪክና ትምህርት  ያወራሉ።    ሉቃ  24:14
✝️ በክርስቶስ አለባዊነት ለባዊያን(አስተዋዮች ) ደቀመዛሙርት ናቸውና የክርስቶስን መከራ እየተነጋገሩ ስለሚኖሩ  በጉባኤያቸው መካከል ሁሌ ክርስቶስ አለ:: ሉቃ 24:15
✝️. ጥቡዓን ናቸውና የመምህራቸውን መከራና ስቃይ ደፍረው ይናገራሉ ። ሉቃ 24: 18-21
✝️.  እውቀትን ይሻሉና ያጠራጠራቸውን ጠይቀው እውነቱን  ይረዳሉ ሉቃ 24:23-28
✝️. ፍቅር ያላቸው ናቸውና መምህራቸውን አብረኽን እደር አብረኽን እራት ብላ ይሉታል ። ሉቃ 24:29
✝️. ራሳቸውን ንጹሕ ያደረጉ እና በቃሉ ያመኑ ናቸውና ምሥጢር ከሚገልጠው ኅብስት (ቅዱስ ቁርባን) ይመገባሉ: በዚህም እውነተኛ ምሥጢርን የሚገልጥም  ክርስቶስ መሆኑን ያምናሉ::ሉቃ24:31
✝️.የሚወዱትን መምህራቸውን ድንገት ሲርቃቸው ከፍቅራቸው የተነሳ ይደነግጣሉ።ሉቃ 24:32
✝️. ንቁሐን ናቸው እና ያዩትን የሰሙትን የትንሣኤ ዜና ለሌላው ሁሌም ይሰብካሉ : እውነተኛ ምስክሮችንም(ቅዱሳንን) ያከብራሉ::ሉቃ 24:34

   በፍኖተ ኤማሁስ  ጉባኤ ቤት ያለ ሊቅም

✝️. ለደቀመዛሙርቱ ፍቅር ያለው ተርጓሚ መምህር ነውና  ሁሌም መንፈሱ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ነው : አብሯቸው እያዋለ እያደረ አለማመናቸውን ይገስጻቸዋል : ያሳምናቸዋል: ያተጋጋቸዋል : ያነቃቃቸዋል።  ሉቃ 24:25-28
✝️.በሥራና በቃል ብርቱ:ነቢይም ነውና ወደፊት የሚሆነውን ተንብዮ ለደቀመዛሙርቱ  ያስረዳል :ያስጠነቅቃልም።  ሉቃ 24:19
✝️. እውነተኛ ነውና መከራ ና ሞትን በድፍረት ይቀበላል :: ሉቃ 24:20
✝️. ጸጋ የበዛለት ተርጓሚ ሊቅ ነውና  በጸጋ መንፈስ ቅዱስ እየተማወቀ ሲተረጉም ደቀመዛሙርቱ ልባቸው እንደእሳት ይቃጠልባቸዋል : እነርሱም የመምህራቸው  አተረጓጎሙም  በልባቸው ውል ውል እያለ ትዝ ሲላቸው የፍቅር እንባ ይተናነቃቸዋል:: ሉቃ 24:32
✝️ . ንጽሕና እና ክህነት ያለው ነውና ደቀመዛሙርቱን ከትርጓሜው በተጨማሪ የምሥጢሩን ማዕድ ቀድሶ ይመግባቸዋል(ያቆርባቸዋል) :: ሉቃ 24:30
✝️ . ስለ ትንሣኤ ልቡና የሚሰብኩ ደቀመዛሙርቱንም ትጋታቸውን እያየ በመደሰት '' ሰላም ለእናንተ ይሁን '' እያለ ይጎበኛቸዋል።24:36
❌. ዓይነልቡናቸው የታወረባቸው ደቀመዛሙርት ግን መምህራቸውን ያለማወቅ  ማማትን ያዘወትራሉ : ይጠራጠራሉ ።ንስሐ ገብተው ከቅዱሱ ምሥጢር ካልተሳተፉ በቀር ምሥጢር አያፈልቁም ነገር አያደቁም። የምሥጢር ባለቤት መምህረ ዓለም  ክርስቶስ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች  ምሥጢሩን ይግለጽልን!
 
     '' ከእነርሱም፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡እንጀራውን፡አንሥቶ፡ባረከው፥ቈርሶም፡ሰጣቸው፤ ዐይናቸውም፡ተከፈተ፥ዐወቁትም፤እርሱም፡ከእነርሱ፡ተሰወረ። እርስ፡በርሳቸውም፦በመንገድ፡ሲናገረን፡መጻሕፍትንም፡ሲከፍትልን፡ልባችን፡ይቃጠልብን፡አልነበረምን፧ተባባሉ። ''  ሉቃ 24:30-33
https://t.me/mstaketsehay
" ኤሌክትሪክ አልባው ገመድ "
➽ አንድ የኤሌክትሪክ ገመድ ቆጣሪው ከተመለሰ በኋላ ምንም አገልግሎት አይሰጥም ቢጨብጡት አይዝም አምፖል ቢያንጠለጥሉበት አያበራም ግን ከትራንስፈርመሩ ተስቦ ገመዱ ተዘርግቶ ሲታይ የሚያገለግልና ፓዎር ያለው ይመስላል ።

➽ የእኛ የቤተክህነት መዋቅርም ይህንን ይመስለኛል የመዋቅር ዝርጋታው ግሩምና ይበል የሚያሰኝ ነው ዓለም በራሷ እንዲህ አይነት የአስተዳድር ዝርጋታ የላትም ቢኖራትም ስንኳን ከቤተክርስቲያን ወስዳ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ።
አስቡት እስኪ ? ▶ቅዱስ ሲኖዶስ ▶ፓትርያርክ ▶ ጠቅላይ ቤተክህነት ▶ ሀገረ ስብከት ▶ የሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ▶ ወረዳ ቤተክህነት ▶ የደብር አለቃ ▶ ሰበካ ጉባኤ ▶ የነፍስ አባት ▶ እንዲህ አይነት መዋቅር ወዴት አለ ? ግን ምንድን ይሆናል ይህ ሁሉ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ አደለምን ?

➽ በየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ በአመት የገንዘብ ኦዲት ይደረጋል ምዕመናንን ግን ማን ጠፋ ? ማን ንስሓ ገባ? ማን ሥጋውን ደሙን ተቀበለ ? ማን የነፍስ አባት አለው ብሎ ......... ብሎ ኦዲት የሚያደርግ መዋቅር አለ ?
ግን ምን ይሆናል ? ይህ ሁሉ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ የአበው ሊቃነ ጳጳሳት ግብርስ ተረስቶ የለምን ?
ቤተክርስቲያን ሲባርኩ ፦ ክህነት ሲሾሙ ፦ የሆነ ገዳም ሲጎበኙ ፦ ከሆነ ከተማ ሲገቡ ፦ ቀድሰው ሲያቆርቡ፦ ወደውጭ ሀገር ሲሄዱ ፦ መሠረተ ድንጋይ ሲያስቀምጡ፦
.....ሚዲያዎች በሰበር ዜና የሚያጥለቀልቁት ? አንድ አርሶ አደረ ገበሬ እንትና ዛሬ እርሻ አረሰ ተብሎ ይዘገባልን
ግን ምን ይሆናል ? ይህ ሁሉ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ ማንኛውም ግላዊም መንግሥታዊም መዋቅር በቤተክርስቲያን ላይ የፈለገውን አድርጎ በሽምግልናም በኮሚቴም ተማልዶ ጉዳዩ ሲፈጸም እንደገና እንደ አዲስ በደስታ የምንፈነጥዘው ለምንድን ነው ? ነገር ግን ይህ ሁሉ መዋቅሩ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ ጥቁር ልበሱ ተባልን ጥቁር ለበስን
እኛን ብቻ ስሙን የእኛንም ቃል ጠብቁ ተባልን እሺ አልን
እኛ ያልሾምነውን ማንኛውንም አትቀበሉ ተባልን እሺ አልን
በሻሸመኔ በጅማ በሐዋሳ በዲላ ......ምዕመናን እንደ በግ ታረዱ እንደጎመን ተቀረደዱ አጥንታቸው ተከሰከሰ ደማቸው እንደ ጎርፍ ፈሰሰ ነገር ግን ይህ ሁሉ ሳይታሰብ እኛ ተስማምተናል ተውትና ነጭ ልበሱ ተባልን ።
ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ ዝክረ ኒቅያ ተባለ ፦ በየሀገሩ ያሉ ሊቃውንት እንዲሰበሰቡ ትዕዛዝ ወጣ ነገር ግን ስንኳን ዝክረ ኒቅያ ሊሆን ዝክረ ቦሩ ሜዳም አልሆነ ። ምክንያቱም
(አንደኛ) በመላው ሀገሪቱ ያሉ ሊቃውንት አልተጠሩም
(ሁለተኛ) ጉባኤው የሚጋብዛቸው ሰዎች ታልፈዋል
(ሦስተኛ) ቀኑ በጣም አጥሯል በ፫ ቀን ምን ሊተገበር?
(አራተኛ) የተሰበሰቡት ስንኳን እንዲወሥኑ ሳይሆን መመሪያ ወስደው እንዲበተኑ ነው የተደረገው
(አምሥተኛ) የተወያዩበት ለምን ለሕዝብ ይፋ አልሆነም?
(ስድስተኛ) እያንዳንዱ ክርክር እየተከታተሉ መታወቅ ነበረበት ።
ይህ ሁሉ መዋቅሩ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?
"ኤሌክትሪክ አልባው ገመድ "
      ዝክረ ኒቅያ፦
ከሙሉ በክፍሉ ነገሩ ይሄው ነው።
(ከታች መምህሬ የኔታ ኃይለ ማርያም ገልጸውታል)
[  ] በመጀመሪያ አመራርጡ የቤቱ አሸርጋጆችን ማዕከል ያደረገ ነው።
[  ] ሁለተኛ ደረጃ ምንም ሴራው የማገቤባቸውን መሠረት ያደረገ ነው።
[  ] በሦስተኛ ደረጃ ትቂት ጉዳዩ የገባቸውን እጅ ሲያወጡ እንኳን እንዳይናገሩ አፍነው ነው የጨረሱት።
[  ] አራተኛ፦የተወያዩበትን ሳይሆን የሚፈልጉትን እንዲነገር የተደረገበት ነው።
[  ] አራተኛ በራሱ ጊዜ የጥፋት መልእክተኛ ሁኖ ከቅቡልነት የወረደውን አህጉረ ስብከት ስም መመለሻ ነው።
[  ] አምስተኛ፦የኒቅያ ጉባኤ ዓለም አቀፋዊ ነው ይሄ ግን ትግራይ ያሉ ሊቃውንትን እንኳን ያላካተተ ነው።
[  ] ስድስተኛ፦የቤተ ክርስቲያንን ህልውናዊ ጉዳይ የረሳ የጳጳሳቱ የክብር መጠበቂያ ጉባኤ ነው።
[  ] ሰባተኛ፦የጉባኤው ማሠሪያ የለውም።የጥፋት መሠረቱን ለመጠቀብ ቃል እንገባለን ተባብለው ነው የተበተኑት።
አንዳችም የቤተ ክርስቲያን ህልውናዊ ጉዳይ እንዳይነገር  ቂጭ ብለው ሲጠብቁት ሰነበቱ እንጂ በነጻነት ውይይት ማድረግ ያልቻለ ጉባኤ ነው።
በተጨማሪም በጥልቅ ጉዳዮች  ውይይት እንዳይደረግባቸው ጊዜው ያጠረ ነው።
በዚህ ማፋዘዣ ሥርዓቱም ድርሻ አለው ብየ አምናለሁ።በተጨማሪም በእኔ የሥራ አስከሀጅነት ዘመን ይሄ ተደረገ ለማለት የቀረበም ጭምር ነው።
[  ] ሊቃውንቱ ወስነው ተግብረው የተለያዩት ምንድን ነው? ምንም።
[  ] ብቻ ቤተ ክህነቱን ለመጠበቅ ቃል እንገባለን አስብለው አስምለዋቸዋል።
"ቀኖናው እንዳይሻር መጠበቅ አለባቸሁ?" ሲባል ነበር።ለመሆኑ ማን ነው የሻረው? ከማን ነው የሚጠበቀው?
፦የገዳማቱ ውድመት፣
፦የምእመናን እልቂት፣
፦የአብነተ ተማሪዎች ጅምላ መሞት፣
፦በየገዳማቱ የንዋየ ቅድሳቱ ስርቆት፣
፦የምእመናን ረሀብ እና ስደት፣
፦በመከፋፈላችን ምክንያት የደረሰው ችግር፣
፦የትግራይ አባቶች አንድነት ጉዳይ፣...ለምንድን ነው ያልተነሣው?
ሊቃውንቱ ይሄ ሁሉ አይመለከታቸውም? ...
ጎበዝ መረር ደፈር ብለን ካልመከርን ስለኔዎች በቁማችን እየቀበሩን ነው።
ሰላም ምንድን ነው?
፦ሰላም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣
፦ሰላም ማለት በባርነት ውስጥ ያለ ጸጥታ አይደለም፣
፦ሰላም በተሸናፊንተ ስነ ልቡና አርፎ መቀመጥ አይደለም፣
፦ሰላም ሞገድ የሌለው ባሕር ነው፣
፦ሰላም ማለት ከእግዚአብሔር ጋር በመኖር የምትገኝ ዕረፍት ናት፣
፦የሰላም ሰው ከራሱ ፣ ሰው ከሰው ፣ ሰው ከተፈጥሮ፣ ሰው ከእግዚአብሔር በሚያስበው ፣ በሚናገረው በሚተገብረው፣ በሚዋሐድበት እና በሚስማማበት ልክ እና መጠን የሚወሰን ነው፣
፦ሰላም ውስጣዊና አፍዊ ፤ልባዊ፣ ስሜታዊና ህውስታዊ (ኢማጅኔሽን) መስማማት ነው።
፦አውነታዊ የሆነ አእምሮ የሚያርፍበት ወደብ ነው፣
፦ሰው በሰላም ይኖር ዘንድ የሚገባው ፍጡር ነው፣
፦ሰላም ተፈጥሮአዊ መብት ነው፣
፦ሰላም የአግዚአብሔር ስጦታ ነው፣
፦ሰላም ትክክለኛ ፍትህ ነዎ፣
፦ሰላም አንጻራዊ አይደለም አንድ እውነት ነው፣
፦ሰላም የሚያድግ ጸጋ ነው፣
፦ሰላም የመንፈስ ቅዱሳዊ የጸጋ ተዋሕዶ ነው።

Records

10.04.202518:21
77.4KSubscribers
26.11.202423:59
0Citation index
17.04.202502:48
1.7KAverage views per post
03.04.202514:18
1.5KAverage views per ad post
02.04.202500:13
41.67%ER
04.04.202514:18
1.92%ERR
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
DEC '24JAN '25FEB '25MAR '25APR '25MAY '25

Popular posts ምሥራቀ ፀሐይ ጉባኤ ቤት፪

03.05.202511:59
      ዝክረ ኒቅያ፦
ከሙሉ በክፍሉ ነገሩ ይሄው ነው።
(ከታች መምህሬ የኔታ ኃይለ ማርያም ገልጸውታል)
[  ] በመጀመሪያ አመራርጡ የቤቱ አሸርጋጆችን ማዕከል ያደረገ ነው።
[  ] ሁለተኛ ደረጃ ምንም ሴራው የማገቤባቸውን መሠረት ያደረገ ነው።
[  ] በሦስተኛ ደረጃ ትቂት ጉዳዩ የገባቸውን እጅ ሲያወጡ እንኳን እንዳይናገሩ አፍነው ነው የጨረሱት።
[  ] አራተኛ፦የተወያዩበትን ሳይሆን የሚፈልጉትን እንዲነገር የተደረገበት ነው።
[  ] አራተኛ በራሱ ጊዜ የጥፋት መልእክተኛ ሁኖ ከቅቡልነት የወረደውን አህጉረ ስብከት ስም መመለሻ ነው።
[  ] አምስተኛ፦የኒቅያ ጉባኤ ዓለም አቀፋዊ ነው ይሄ ግን ትግራይ ያሉ ሊቃውንትን እንኳን ያላካተተ ነው።
[  ] ስድስተኛ፦የቤተ ክርስቲያንን ህልውናዊ ጉዳይ የረሳ የጳጳሳቱ የክብር መጠበቂያ ጉባኤ ነው።
[  ] ሰባተኛ፦የጉባኤው ማሠሪያ የለውም።የጥፋት መሠረቱን ለመጠቀብ ቃል እንገባለን ተባብለው ነው የተበተኑት።
አንዳችም የቤተ ክርስቲያን ህልውናዊ ጉዳይ እንዳይነገር  ቂጭ ብለው ሲጠብቁት ሰነበቱ እንጂ በነጻነት ውይይት ማድረግ ያልቻለ ጉባኤ ነው።
በተጨማሪም በጥልቅ ጉዳዮች  ውይይት እንዳይደረግባቸው ጊዜው ያጠረ ነው።
በዚህ ማፋዘዣ ሥርዓቱም ድርሻ አለው ብየ አምናለሁ።በተጨማሪም በእኔ የሥራ አስከሀጅነት ዘመን ይሄ ተደረገ ለማለት የቀረበም ጭምር ነው።
[  ] ሊቃውንቱ ወስነው ተግብረው የተለያዩት ምንድን ነው? ምንም።
[  ] ብቻ ቤተ ክህነቱን ለመጠበቅ ቃል እንገባለን አስብለው አስምለዋቸዋል።
"ቀኖናው እንዳይሻር መጠበቅ አለባቸሁ?" ሲባል ነበር።ለመሆኑ ማን ነው የሻረው? ከማን ነው የሚጠበቀው?
፦የገዳማቱ ውድመት፣
፦የምእመናን እልቂት፣
፦የአብነተ ተማሪዎች ጅምላ መሞት፣
፦በየገዳማቱ የንዋየ ቅድሳቱ ስርቆት፣
፦የምእመናን ረሀብ እና ስደት፣
፦በመከፋፈላችን ምክንያት የደረሰው ችግር፣
፦የትግራይ አባቶች አንድነት ጉዳይ፣...ለምንድን ነው ያልተነሣው?
ሊቃውንቱ ይሄ ሁሉ አይመለከታቸውም? ...
ጎበዝ መረር ደፈር ብለን ካልመከርን ስለኔዎች በቁማችን እየቀበሩን ነው።
29.04.202510:23
፦ዝክረ ኒቅያ ጉባኤ ፦
እንደ ተሳታፊ ከተሰብሳቢ አባቶች የተነሡ ጉዳዮች መልካም ናቸው።
የማጠቃለያ ሀሳብ የሰጡ አባቶች ግን ፍላጎታቸው ከተለመደው ማፋዘዣ ቃል ያለፈ አይመስልም።
የቤተ ክርስቲያን ክብርና ልዕልና እንዲጠበቅ፣ ሊቃውንቱ በተለዩ ጉዳዮች ቅብብሎሻዊ ውሳኔ እንዲያሳርፉ ሳይሆን የእኛን ጉዳይ አትዩብን።
በሚድያ ስለቀኖናም ሆነ ስለ ጥፋታችን አትጻፉብን፣
እኛ አንሳሳትም፣እመኑብን ተቀበሉ የሚል አይነት ማደማደሚያ ነው።
የትናንቱ ውሎ የሊቃውንቱ ድካም፣ያነሧቸው ጥያቄዎች፣ምክረ ሀሳቦች ይበል የሚያሰኙ ናቸው።
ጉባኤው ምንም አይነት የመፍትሄ ውሳኔ እንዳያመጣ ግን የተለመዱ አፋዛዦች ቁጭ ብለው ሲጠባበቁት መዋላቸው ከተለመደው፣በሰበካ ጠቅላላ ጉባኤ ከሚነሣው ውይይት ያለፈ አይሆንም።
በእኔ ግምት የጉባኤው ዋና ዓላማ በእኔ ዘመን ጉባኤ ሊቃውንት ተደረገ ለማለት ነው የሚል ሀሳብ አለኝ።
ስለ ጉባኤው የደከሙ አባቶችን ባንረሳም መፍትሄን እጅ እግሯን አሥረው የሚሸጧትን ግን መዘንጋት አያስፈልግም።
ሊቃውንቱ ተበድለዋል እያሉ
ብሶትን በማስተንፈስ እያሟሟቁ ማመንመን የእውነትኛ አባትነት መለኪያ አይደለም።
በመጨረሻም ያን ሁሉ የሊቃውንቱን ጥያቄና ውይይት አይነኬው ማብራራት ጀመሩ፦ መልስ ለመመለስ እና መመሪያ ለመስጠት ነው የተነሡ እንጂ የሊቃውንቱን ሀሳብ እንዳለ ለመውሰድ አይደለም።
አባቶች የሊቃውንት ጉባኤ ብለው መጡ እንጂ አባ እንተናን ለመጠየቅ አልነበረም።
የሊቃውንቱን የልብ ትርታ አዳምጦ በመመሪያ ዲሪቶ መሸኘት ተገቢ አይደለም።
፦መፍትሄው ሊቃውንቱ በተመረጡ ጉዳዮች ወስነው የሚሄዱበትን መንገድ መምከር አለባቸው።
፦በመመሪያ አጥር ሰበብ ውስጥ ታሥረው ከእውነቱ መውጣት የለባቸውም።
እውነቱን መጋፈጥ ግዴታችን ነው።
ጥያቄዎቼ፦
የቤተ ክርስቲያንን መከራ እጅ እግሯን አሥሮ ያስረዘመው ማን ነው?
ሐዋርያዊ ቀኖናን በመጣስ መርህ አልባነትን ያስፋፋው ማን ነው?
ምእመናን ከቤተ ክርስቲያን እንዲበተኑ ምክንያቱ ማን ነው?
ገዳማትን እና አብነት ትምህርት ቤትን በተዛዋሪ እጅ ያዳከመው ማን ነው?
ዕቅበተ እምነት እንዳይኖር ያደረገው ማን ነው?
ቤተ ክርስቲያን የተጠናከረ ሁለገብ ተቋም እንዳይኖራት በኋላ ቀር አሠራር ተብትቦ የያዘው ማን ነው?
ስለ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል በእምነቴ ብለው ለሚሠሩ አባቶች እንቅፋታቸው ማን ነው?
የስብከተ ወንጌል ዋናው ዕንቅፋቱ ማን ነው?
የዘረኝነት እና የሙስና ባለቤቱ ማን ነው?
...ሊቃውንቱ በእነዚህና በመሳሰሉ ጉዳዮች በደንብ መፈተሽ አለባቸው።
04.05.202504:00
የፍኖተ ኤማሁስ ደቀመዛሙርት እና ተርጓሚ መምህራቸው
 
✍️1..በፍኖተኤማሁስ ጉባኤ ቤት  ያሉ  መጠራጠር የጠፋላቸው ደቀመዛሙርት:-

✝️  ብልሆች ደቀ መዛሙርት  ናቸውና በመንገድ ቧልት ሳይሆን የመምህራቸውን  ታሪክና ትምህርት  ያወራሉ።    ሉቃ  24:14
✝️ በክርስቶስ አለባዊነት ለባዊያን(አስተዋዮች ) ደቀመዛሙርት ናቸውና የክርስቶስን መከራ እየተነጋገሩ ስለሚኖሩ  በጉባኤያቸው መካከል ሁሌ ክርስቶስ አለ:: ሉቃ 24:15
✝️. ጥቡዓን ናቸውና የመምህራቸውን መከራና ስቃይ ደፍረው ይናገራሉ ። ሉቃ 24: 18-21
✝️.  እውቀትን ይሻሉና ያጠራጠራቸውን ጠይቀው እውነቱን  ይረዳሉ ሉቃ 24:23-28
✝️. ፍቅር ያላቸው ናቸውና መምህራቸውን አብረኽን እደር አብረኽን እራት ብላ ይሉታል ። ሉቃ 24:29
✝️. ራሳቸውን ንጹሕ ያደረጉ እና በቃሉ ያመኑ ናቸውና ምሥጢር ከሚገልጠው ኅብስት (ቅዱስ ቁርባን) ይመገባሉ: በዚህም እውነተኛ ምሥጢርን የሚገልጥም  ክርስቶስ መሆኑን ያምናሉ::ሉቃ24:31
✝️.የሚወዱትን መምህራቸውን ድንገት ሲርቃቸው ከፍቅራቸው የተነሳ ይደነግጣሉ።ሉቃ 24:32
✝️. ንቁሐን ናቸው እና ያዩትን የሰሙትን የትንሣኤ ዜና ለሌላው ሁሌም ይሰብካሉ : እውነተኛ ምስክሮችንም(ቅዱሳንን) ያከብራሉ::ሉቃ 24:34

   በፍኖተ ኤማሁስ  ጉባኤ ቤት ያለ ሊቅም

✝️. ለደቀመዛሙርቱ ፍቅር ያለው ተርጓሚ መምህር ነውና  ሁሌም መንፈሱ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ነው : አብሯቸው እያዋለ እያደረ አለማመናቸውን ይገስጻቸዋል : ያሳምናቸዋል: ያተጋጋቸዋል : ያነቃቃቸዋል።  ሉቃ 24:25-28
✝️.በሥራና በቃል ብርቱ:ነቢይም ነውና ወደፊት የሚሆነውን ተንብዮ ለደቀመዛሙርቱ  ያስረዳል :ያስጠነቅቃልም።  ሉቃ 24:19
✝️. እውነተኛ ነውና መከራ ና ሞትን በድፍረት ይቀበላል :: ሉቃ 24:20
✝️. ጸጋ የበዛለት ተርጓሚ ሊቅ ነውና  በጸጋ መንፈስ ቅዱስ እየተማወቀ ሲተረጉም ደቀመዛሙርቱ ልባቸው እንደእሳት ይቃጠልባቸዋል : እነርሱም የመምህራቸው  አተረጓጎሙም  በልባቸው ውል ውል እያለ ትዝ ሲላቸው የፍቅር እንባ ይተናነቃቸዋል:: ሉቃ 24:32
✝️ . ንጽሕና እና ክህነት ያለው ነውና ደቀመዛሙርቱን ከትርጓሜው በተጨማሪ የምሥጢሩን ማዕድ ቀድሶ ይመግባቸዋል(ያቆርባቸዋል) :: ሉቃ 24:30
✝️ . ስለ ትንሣኤ ልቡና የሚሰብኩ ደቀመዛሙርቱንም ትጋታቸውን እያየ በመደሰት '' ሰላም ለእናንተ ይሁን '' እያለ ይጎበኛቸዋል።24:36
❌. ዓይነልቡናቸው የታወረባቸው ደቀመዛሙርት ግን መምህራቸውን ያለማወቅ  ማማትን ያዘወትራሉ : ይጠራጠራሉ ።ንስሐ ገብተው ከቅዱሱ ምሥጢር ካልተሳተፉ በቀር ምሥጢር አያፈልቁም ነገር አያደቁም። የምሥጢር ባለቤት መምህረ ዓለም  ክርስቶስ እንደ ኤማሁስ መንገደኞች  ምሥጢሩን ይግለጽልን!
 
     '' ከእነርሱም፡ጋራ፡በማእዱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡እንጀራውን፡አንሥቶ፡ባረከው፥ቈርሶም፡ሰጣቸው፤ ዐይናቸውም፡ተከፈተ፥ዐወቁትም፤እርሱም፡ከእነርሱ፡ተሰወረ። እርስ፡በርሳቸውም፦በመንገድ፡ሲናገረን፡መጻሕፍትንም፡ሲከፍትልን፡ልባችን፡ይቃጠልብን፡አልነበረምን፧ተባባሉ። ''  ሉቃ 24:30-33
30.04.202511:32
የተነቃነቀ ጥርስ፦
አንድ ዓመት የጠቅላላ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳትፌያለሁ።
ከሁሉም አህጉረ ስብከቶች በሚባል ደረጃ ችግሮች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎች ጥያቄና ጥቆማ ይቀርብባቸውና በመጨረሻም አባታዊ መመሪያ ተሰጥቷቸው ይታለፋሉ።
ጉባኤው በየዓመቱ እንዲህ እያለ በልማዳዊ ጥፋት ነው የሚቀጥለው።
ለመፍትሄ የተነሣሣውን ትውልድ፦በቅድሚያ ስሜቱን ይኮረኩሩታል፣ቀጥሎ አናግሮ ማፋዘዝ፣አሳልፎ መስጠት፣በማይተገበር መመሪያ ማጠር ነው።
የሚሠሩ ሩቅ አሳቢ ሰዎችን መመሪያው ይይዛቸዋል፤የሚያጠፉ አውርቶ አደር ሰዎችን መመሪያው ያጸድቅላቸዋል።
በዚህ የአዙሪት መንገድ ቤታችን በመመሪያ የታጠረ፣ምእመናን ግድ የማይሉት፣ ሐዋርያዊ ቀኖና የለሽ.. የአደገኛ ቦዘኔዎች መሰባሰቢያ እየሆነ ከመጣ ሰንበትበት ብሏል።
በየስብሰባዎች መጨረሻ የቤተ ክርስቲያን ዋናው የተልዕኮ ዓላማ ይረሳና በባዶ ልፈፋ የተሞላ ሽኝት ይደረጋል።
ብዙውን ጊዜ የተከበረውን የታፈረውን ኦርቶዶክሳዊ ሀብት በተለያየ የማፌዘዣ ስልት ይነቀንቁታል።
"የተነቃነቀ ጥርስ ደግሞ ቢመሉበት አያደቅ ቢስቁበት አያደምቅ"ይሆንና በክብረ-ልዕልና የማይደምቅ፤በስልታዊ-አፈጻጽም የማያደቅ ይሆናል።
ስለ ነገው እያሰቡ መረር ጠበቅ እያሉ ስለ እውነት ማውራት እና መሥራት ካልተቻለ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በምሥራቅ አፍሪካ ታሪክ ብቻ እንጂ ህልውናዋ የተመናመነ መሆኗ አይቀሬ ነው።
ታሪኳንም ከውሸተኛ ትርክት ለይቶ የሚያወራላት ከተገኘ ብቻ ነው።
በብዛት ይሄ ሁሉ ዕዳ የሚመጣው ግን ክብር፣ዝና፣ሥልጣን፣ በማይበቃቸው ገደብ የለሽ የሥርዓቱ አቡኖች ነው።
05.05.202512:46
የተጠበቀ እውነት፦
እነዚህ ሦስት ነገሮች ተስማምተው ከተገኙ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል።
፩.ሰው ከእግዚአብሔር ጋራ ያለው ግንኙነት፣
እግዚአብሔር ወደሰው በረድኤት በጸጋ፣ሰው ወደ እግዚአብሔር፦በሕግ በአምልኮት።(ፍቅረ እግዚአብሔር ነው።)
፪.ሰው ከሰው ጋራ ያለው ግንኙነት።
(በፍቅረ ቢጽ)
፫.ሰው ከሥነ ፍጥረት ጋራ ያለው መስተጋብር።
(በመገቢነት)
እነዚህ በትክክል ተጠብቀው ከተገኙ ዓለም ትንሿ ገነት ትሆናለች።
01.05.202518:41
እንዴት ተረሳ?
፦የገዳማቱ ውድመት፣
፦የምእመናን እልቂት፣
፦የአብነተ ተማሪዎች ሞት፣
፦የንዋየ ቅድሳቱ ስርቆት፣
፦የምእመናን ረሀብ፣
፦በመከፋፈላችን ምክንያት የደረሰው ችግር፣
.....እንዴት ይረሳል???
30.04.202517:30
በመንበረ  ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት በሊቃውንት ጉባኤ አዘጋጅነት ለሦስት ተከታታይ ቀናት በዘርፈ ብዙ የቤተክርስቲያን ጉዳዮች ላይ ሲመክር  የቆየው  የሊቃውንት  የምክክር ጉባኤ ባለ 14 አንቀጽ የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት  ተጠናቋል። የመግለጫው ሙሉ ሐሳብ   እንደሚከተለው ይነበባል።
============================
ሚያዚያ 22 ቀን 2017ዓ.ም አዲስአበባ 

እኛ ሊቃውንት እንደምንረዳው ጉባኤ ኒቅያ በምንልበት ጊዜ በቤተ ክርስቲያን አነጋገር  ጉባኤ ተደረገ ሲባል ሰዎች ተሰብስበው ይህን ማመን አለብን ያንን መተው አለብን ብለው በድምጽ ብልጫ ተስማምተው የጋራ መግለጫ አወጡ ማለት ሳይሆን ሰፊ እርሻ /ሁዳድ/ ያለው ገበሬ በአዝመራው መሐል እህሉን መስሎ አዝመራውን የሚጎዳ የሚያበላሽ አረም ሲበቅልበት ከእህሉ መካከል አረሙን በጥንቃቄ ነቅሎ እንደሚጥል ሁሉ ቤተ ክርስቲያንም ክርስቶስን በዓይኗ ዓይታ ትምህርቱን በጆሮዋ ሰምታ በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያን በአባቶቻችን በሐዋርያት አማካይነት የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ዓይታ በምታውቀውና በምታምነው እውነተኛ ሃይማኖት መሐል የራሷን እምነት ሳይሆን ተመሳስሎ የሚጎዳትን የመናፍቃን የአስተሳሰብ አረም ነቅላ ለመጣል አረሙን ነቅላ ትምህርት አዝመራዋን ትከላከላለች፡፡በኒቅያ ጉባኤም የተደረገው ይኸው ነው አረም አርዮስ ተነቀሎ የክርስቶስ አምላክነት በምላት በስፋት ተነገረ የሃይማኖት መግለጫ የሆነው ጸሎተ ሃይማኖት ጸደቀ ፡፡ እኛም የሠለስቱ ምዕት የልጅ ልጆች የኢትዮጵያ ሊቃውንት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የበቀለውንና እየበቀለ ያለውን አረም በትምህርት የአረም ማጥፊያ መድኀኒትነት ለመንቀል ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ለመጠበቅ ምእመናንን ለማጽናት በዚህ በመንበረ ፓትርያርክ ቅጽረ ግቢ ተሰብስበን መክረን ተወያይተን-
1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጉባኤው መክፈቻ የሰጡትን ቃለ ምእዳን አባታዊ መመሪያና ቡራኬን በመቀበል የሰጡትን አባታዊ መመሪያ በየመጣንበት ጉባኤ ቤት ሥራ ላይ ለማዋል ቃል እንገባለን፡፡
2. ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤የባሕር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በጉባኤው መክፈቻና በየመርሐ ግብሩ መካከል ያስተላለፉትን የሥራ መመሪያ ወቅቱ በሚጠይቀው ቤተ ክርስቲያን በምትፈልገው ምእመናን ለሚጠይቁት ጥያቄ ሁሉ ምላሽ ለመስጠት በየጉባኤ ቤታችን ከማስተማር ከማገልገል ባሻገር እንደአባቶቻችን ለሃይማኖታችን አለኝታና ጠበቃ ሆነን ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡
3. ጥንታዊት ሐዋርያዊት የሆነችውን የኢትዮጵያ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረጅም ታሪኳ ውስጥ ባሳለፈቻቸው አጋጣሚዎች ሁሉ ያካበተችውን የእቅበተ እምነት (ሃይማኖት) ልምድ ከመጀመሪያው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ያሉትን የዐቃብያነ ሃይማኖት ተጋድሎዎች በመረዳት ቅብብሎሹን ለማስቀጠል ቃል እንገባለን፡፡
4. አሁን ባለንበት ክፍለ ዘመን ከሚከሠቱት አሉታዊ ግድፈቶችና ሥርዋጾች መካከል በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በገድላት፣በድርሳናትና በታአምራት የቤተ ክርስቲያን አዋልድ መጻሕፍት በመከለስ በመሸቀጥና በመበረዝ መንፈሳዊነታቸውን ለቀው የተዛባ ሐሳብ እንዲኖራቸው ከእግዚአብሔር ፈቃድና ሐሳብ እንዲወጡ የሚደረገው ሴራ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ስለሆነም ጥንታውያን በቀኖና መጻሕፍት የተሠፈሩና የተመዘኑ መጻሕፍቶቻችን ባሉበት ሁኔታ ተጠብቀው ይቀጥሉ ዘንድ እኛ የጉባኤ መምህራን የመጻሕፍቱ ጠበቃ በመሆን  በሊቃውንት ጉባኤ በኩል ያላለፉ በትንሣኤ ማሳተሚያ ድርጅት አሳታሚነት ያልታተሙ መጻሕፍት ባለመጠቀም ደቀ መዛሙርትና ምእመናን እንዳይገለገሉባቸው ለማስተማር ቃል እንገባለን፡፡
5. የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥዕላት፣መስቀል፣ሥነ ሕንፃና ኪነ ጥበብ ይዘትና ቅርጽ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተለካ ሃይማኖታዊ ምሳሌነታቸው እንደ መጻሕፍት የሚነበብ እንደሰው የሚናገሩ እንደ መምህራን የሚያስተምሩ ንዋያት ናቸው፤ስለሆነም እነዚህን ንዋያተ ቅድሳት በየዘመኑ የሚነሱ የውስጥና የውጭ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የተለያየ ስሜት እንዲፈጥሩ የሚሰጡት ትርጉም እንዲዛባ ለማድረግ የሚያደርጉት ሙከራ እጅግ ብዙ ነው አባቶቻችን በብዙ ውጣ ውረድ ያቆዩልንን የስገኙልንን  እነዚህን ንዋያተ ሃይማኖት ጠብቀን በማስጠበቅ ጥቅማቸውን በማስተማር ባሉበት ሁኔታ ለትውልድ ለማስተላለፍ ምትክ የሌለውን ድርሻችንን ለመወጣት ቃል እንገባለን፡፡
6. አጽራረ ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱን የውስጥ ሁኔታ በማጤን ራሳቸው በሚሰጡን አጀንዳ በሚፈጠር  የተዛባ የፖለቲካ አመለካከት የመሪዎችን አቋምና ትከሻ በመለካት በሚገኝ አጋጣሚ ሁሉ በመጠቀም ሠርጎ በመግባት ኑፋቄን በመዝራት በቀኖና፣በታሪክና በትውፊት በምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ በቅዳሴ በትርጓሜ በበዓላት አከባበር ላይ ሁሉ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆኑ እንግዳ ነገሮችን ሊያሸክሙን እንደሞከሩና አንዳንዶቹም አዳዲስ ትርክት እንደጫኑብን ታሪክ እንደቀየሩብን በማኅበረሰቡ ውስጥ ቅራኔ እንደፈጠሩብን ከቀረቡት ጥንታዊ ጽሑፎች ተረድተናል፡፡ስለሆነም የደረሱብን ችግር የቀኖና የትውፊት የታሪክ ተፋልሶ ስህተቶችን በማኅብረሰቡ ውስጥ ሠርጎ የገባ የትርክት አረሙን ከስንዴው በጥንቃቄ በመለየት ወደ ጥንታዊ ማንነታችን ለመመለስ የሚጠበቅብንን ሁሉ ረድኤተ እግዚአብሔርን አጋዥ በማድረግ ለመሥራት ቃል እንገባለን፡፡
7. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተች ጀምሮ መከፋፈል ያልገጠማት    የተማከለ የአስተዳደር መርሕ ስለምትከተልና ወጥ በሆነ የአሰራር መዋቅር ስለምትመራ መሆኑ የታወቀ ነው፤ስለሆነም ከቤተ ክርስቲያናችን ኣንጻር የተማከለ ኣሰራር የተሻለ ውጤት እንዳለው ለቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖትና ሥርዐት መጠበቅ ጠቃሚ መሆኑን ስለተገነዘብን  ማእከላዊ መዋቅራችንን ለመጠበቅና ለማስጠበቅ የበኩላችንን ድርሻ ለመወጣት ተስማምተናል፡፡

8. በአምስት ሊቃውንት ቅዱሳን ስም በቡድን ተከፋፍሎ በየርእሱ የተደረገው ውይይትና  የመፍትሔ ሐሳብ ቀርቧል፡፡ቡድኑ የተወያየበት ሠነድ የዚህ ቃለ ጉባኤ አካል በማድረግ ጥቅል ሠነዱ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዲቀርብ የሚድረግ ሆኖ ለማሳያ ያህል በክብዙ በጥቂቱ በአቋም መግለጫ እንዲወጣበት አድርገናል፡፡በዚህም መሠረት
ሀ. በነገረ ማርያምንና በነገረ ክርስቶስን ዙሪያ በጉባኤው ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በዚህ ዙሪያ ውይይት ያደረገው ቡድን ለሚነሱ ጥያቄዎች ሰፊ ምላሽ የሚሰጡ ከቅዱሳት ማጻሕፍት በማጣቀስ የውይይቱን ውጤት አቅርቧል በዚህም መሠረት፡- እመቤታችን በተመለከተ ጊዜውን ተደራሽ ያደረጉ ጥያቄዎች ጥንተ አብሶን፣ ቤዛዊተ ዓለም፣ አማላጅነት፣የጌታችን ወንድሞችና የእመቤታችን ትንሣኤና ተያያዝ ጥያቄዎች በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ሰፊ ውይይትና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ስለሆነም ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት በማድረግ አባቶቻችን ነቢያት፣ አባቶቻችን ሐዋርያት ቀደምት ሊቃውንት ያቆዩልንን የነገረ ማርያም ትምህርት ዛይበረዝ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጠንክረን እናስተምራለን፡፡
03.05.202518:36
" ኤሌክትሪክ አልባው ገመድ "
➽ አንድ የኤሌክትሪክ ገመድ ቆጣሪው ከተመለሰ በኋላ ምንም አገልግሎት አይሰጥም ቢጨብጡት አይዝም አምፖል ቢያንጠለጥሉበት አያበራም ግን ከትራንስፈርመሩ ተስቦ ገመዱ ተዘርግቶ ሲታይ የሚያገለግልና ፓዎር ያለው ይመስላል ።

➽ የእኛ የቤተክህነት መዋቅርም ይህንን ይመስለኛል የመዋቅር ዝርጋታው ግሩምና ይበል የሚያሰኝ ነው ዓለም በራሷ እንዲህ አይነት የአስተዳድር ዝርጋታ የላትም ቢኖራትም ስንኳን ከቤተክርስቲያን ወስዳ ነው ብንል ማጋነን አይሆንም ።
አስቡት እስኪ ? ▶ቅዱስ ሲኖዶስ ▶ፓትርያርክ ▶ ጠቅላይ ቤተክህነት ▶ ሀገረ ስብከት ▶ የሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ▶ ወረዳ ቤተክህነት ▶ የደብር አለቃ ▶ ሰበካ ጉባኤ ▶ የነፍስ አባት ▶ እንዲህ አይነት መዋቅር ወዴት አለ ? ግን ምንድን ይሆናል ይህ ሁሉ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ አደለምን ?

➽ በየአጥቢያ ቤተክርስቲያኑ በአመት የገንዘብ ኦዲት ይደረጋል ምዕመናንን ግን ማን ጠፋ ? ማን ንስሓ ገባ? ማን ሥጋውን ደሙን ተቀበለ ? ማን የነፍስ አባት አለው ብሎ ......... ብሎ ኦዲት የሚያደርግ መዋቅር አለ ?
ግን ምን ይሆናል ? ይህ ሁሉ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ የአበው ሊቃነ ጳጳሳት ግብርስ ተረስቶ የለምን ?
ቤተክርስቲያን ሲባርኩ ፦ ክህነት ሲሾሙ ፦ የሆነ ገዳም ሲጎበኙ ፦ ከሆነ ከተማ ሲገቡ ፦ ቀድሰው ሲያቆርቡ፦ ወደውጭ ሀገር ሲሄዱ ፦ መሠረተ ድንጋይ ሲያስቀምጡ፦
.....ሚዲያዎች በሰበር ዜና የሚያጥለቀልቁት ? አንድ አርሶ አደረ ገበሬ እንትና ዛሬ እርሻ አረሰ ተብሎ ይዘገባልን
ግን ምን ይሆናል ? ይህ ሁሉ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ ማንኛውም ግላዊም መንግሥታዊም መዋቅር በቤተክርስቲያን ላይ የፈለገውን አድርጎ በሽምግልናም በኮሚቴም ተማልዶ ጉዳዩ ሲፈጸም እንደገና እንደ አዲስ በደስታ የምንፈነጥዘው ለምንድን ነው ? ነገር ግን ይህ ሁሉ መዋቅሩ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ ጥቁር ልበሱ ተባልን ጥቁር ለበስን
እኛን ብቻ ስሙን የእኛንም ቃል ጠብቁ ተባልን እሺ አልን
እኛ ያልሾምነውን ማንኛውንም አትቀበሉ ተባልን እሺ አልን
በሻሸመኔ በጅማ በሐዋሳ በዲላ ......ምዕመናን እንደ በግ ታረዱ እንደጎመን ተቀረደዱ አጥንታቸው ተከሰከሰ ደማቸው እንደ ጎርፍ ፈሰሰ ነገር ግን ይህ ሁሉ ሳይታሰብ እኛ ተስማምተናል ተውትና ነጭ ልበሱ ተባልን ።
ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?

➽ ዝክረ ኒቅያ ተባለ ፦ በየሀገሩ ያሉ ሊቃውንት እንዲሰበሰቡ ትዕዛዝ ወጣ ነገር ግን ስንኳን ዝክረ ኒቅያ ሊሆን ዝክረ ቦሩ ሜዳም አልሆነ ። ምክንያቱም
(አንደኛ) በመላው ሀገሪቱ ያሉ ሊቃውንት አልተጠሩም
(ሁለተኛ) ጉባኤው የሚጋብዛቸው ሰዎች ታልፈዋል
(ሦስተኛ) ቀኑ በጣም አጥሯል በ፫ ቀን ምን ሊተገበር?
(አራተኛ) የተሰበሰቡት ስንኳን እንዲወሥኑ ሳይሆን መመሪያ ወስደው እንዲበተኑ ነው የተደረገው
(አምሥተኛ) የተወያዩበት ለምን ለሕዝብ ይፋ አልሆነም?
(ስድስተኛ) እያንዳንዱ ክርክር እየተከታተሉ መታወቅ ነበረበት ።
ይህ ሁሉ መዋቅሩ ኤሌክትሪክ አልባ ገመድ ሆኖ አይደለምን ?
"ኤሌክትሪክ አልባው ገመድ "
ሰማዕታት ሁሉንም ናቸው።
፩.መናኝ ናቸው፦ባልመነኑት ዓለም ሰማዕትነትን አዮቀበሉም።
፪.መምህራን ናቸው፦ወንግልን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር የሰበኩ ናው።
፫.ንጹሓን ናቸው፦ሰውነታቸውን በደመ መለኮት የተጣቡ ፍጹማን ናቸው።
፬.ባህታውያን ናቸው፦ዘመን የወለደውን ሹም የወደደውን ሳይሉ ብቻቸውን መከራ የተቀበሉ ናቸው።
መድኅን ክርስቶስ በመስቀል ተሰቅሎ ደሙን አፍስሶ ሲዋሐዳቸው አይተው መከራ መስቀሉን ተሸክመው ደማቸውን አፍስሰው ተዋሐዱት።
የክርስትና ሕይወት የመስቀል እና የሰማዕትነት ሕይወት ናት።
"ሰማዕታት የዚህችን ዓለም ጣዕም ናቁ፣መራራ ሞትንም ታገሡ"
አሁን በክብር ተገልጸው ከጨረቃ ደምቀው ከፀሐይ አሸብርቀው ይታያሉ።
06.05.202516:38
ገድለ ቅዱሳንን ማን ይጽፈዋል?
(ክፍል፩)
፩ኛ.በሕይወተ ሥጋ እያሉ ረድ ይሰጣቸዋል። ረድእ የሚሆን ጸዊረ ነገር የሚቻለው የአበውን የተጋድሎ ፈሊጥ የተረዳ ሰው ነው።
ያዩትን የሰሙትን በምሥጢር ያጫውቱታል ሲያርፉ ይጽፍላቸዋል።
፪ኛ.ፍጺማን አበው ለአበው እንደ ዕንጦንስ እና እንደ አባ ጳውሊ ሲገናኙ ያደረገላቸውን ይነጋገራሉ አንዱ ቀድሞ ያርፋል ውዳሴ ስለማይሆንበት ይነግርለታል ይጻፋል።
፫ኛ.ካረፉ በሁዋላ የሠሩትን ያገኙትን ጸጋ ክብር ከገዳሙ ላንዱ ለበቃው ጣዕም ለቀመሰው በአካለ ነፍስ መጥተው ያገኙትን ክብርና ኪዳን ይነግሩታል ይጻፋል።
፬ኛ.በሕይወት ዘመናቸው ማኅበሩ በየግሉ የተመለከታቸውን የተጋድሎ እውነቶች ያሰባስቡለታል ይጻፋል።
፭ኛ.አንዳንዶች በትዕዛዘ እግዚአብሔር ገና በሕይወት እያሉ በትእደዛዝ አጽፈው ይሰናበታሉ(አባ ኪሮስ ለአባ ባውሚን፣ብፁዓን ጻድቃነሰ ለአባ ዞሲማስ እንደ ነገሩት)።
፮ኛ.በሕይወተ ሥጋ እና በእረፍት ያደረጉት ተአምራት ይሰበሰባል የትሩፋተ-ጸጋ ብርሃናቸው እየጎላ ሲሄድ ይጻፋል።
፯ኛ.የትኛው ቅዱስ ግን ሳያርፍ ገድሉ አዘከርለትም።ቤተ ክርስቲያን ቅድስናውን ስትመሠክርለት በኋላ ነው ግን ገድሉ ተአምራቱ ሲነቡብ ይኖራል።
"እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ። በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሰወር አይቻላትም።"ማቴ.፭፥፲፬
30.04.202515:39
          "ኮሚቴ ይቋቋም"
ቤታችን 100% በሚባል ደረጃ ለተፈጠሩ ችግሮች የሚሰጠው ውሳኔ ኮሚቴ ይቋቋም የሚል ነው።
ኮሚቴውን ደግም በጊዜና በውስጥ ትውውቅ እንደ አባ ለትጹን ነፍስ ያሻሹታል።
ችግሩ መፍትሄ እንዳያገኝ በኮሚቴ ይቋቋም ሰበብ ያሳልፉታል።
ከዚያ እኛም ሊታይልን ነው ብለን ስንጠብቅ ስንጠብቅ እንሰነብት እና እንረሳዋለን።
የተቋቋመው እና ምንም ሳይሠራ የፈረሰው የኮሚቴ ብዛትኮ በድንቃድንቅ መዝገብ ያስመዘግበን ነበር።
ደግሞ ኮሚቴ ሲቋቋም ተፈላልገው የሚላላሱ ሰዎች ይሆናሉ።
የማንን ችግር ማን አጥንቶ ማን ይናገረዋል? ነግህ በእኔ ነዋ!
"ምእመናን ተቆጥተዋል ጨርሶ እንዳይከፋቸው ብቻ ኮሚቴ ይቋቋም።"በቃ።
ቤተ ክርስቲያን እንዲህ መሳለቂያ እንደሆነች፣እኛም እንዲህ እንደ ተቃጠልነ እንኖራለን።
22.04.202503:50
ኖላዊ ሆይ ! ባይጠብቁ አያስክዱ !?!?
➠ እመቤታችን ቤዛ አትባልም እንዲሉ ያስገደደዎት ምንድን ነው ? አውቀው ነው ? ወይስ ሳያውቁ ነው ?
ለማደናገር ነው ? ለማስካድ ነው ? ለማሰናከል ነው ?

➠ እመቤታችን ቤዛ እንዳይደለች ያነበቡት መጽሐፍ አለ?
ወይስ የጠየቁት  መምህር አለ ? ነው የተገለጠልዎት መገለጥ አለ ? ወይስ ያዩት ራዕይ አለ? ነው የነገረዎት መልአክ አለ ? ይህንንስ ተናግረው የሚመልሱት መናፍቅ በትምህርትዎት የሚያጸኑት ምዕመን አለ ? ነው የሚያስጨብጡት መሠረታዊ ዕውቀት አለ ከሌለ ይህን እንዲናገሩና እንዲያስተምሩ ምን አስገደደዎት ?

➠ በእርግጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ጵጵስና ? ካገኙ የማያጧት ከገቡ የማይወጡባት ከወረሷት የማትነጠቅ መንግሥተ ሰማያት
ከሆነ ውሎ አድሯል ። አንድ ሰው የጵጵስና ቆብ ከጫነ በኋላ የፈለገውን የሚናገርበት ያሰበውን የሚተነፍስበት ዓውደምህረት ይፈጥራል ከዚያ በኋላ ለተናገረው ስሑት ነገር ቀኖና ሳይገባ ወይ ተድበስብሶ ይታለፋል ያለዚያም በይቅርታ ይተዋል ግን ለምን ይሆን ?

➠ ቤዛ ማለት ምንድን ማለት ነው ?
ይህ ኃሳብ በእርግጥ የጳሱ ሳይሆን የፕሮቴስታንት ኃሳብ ነው ፕሮቴስታንት ቤዛ መድኃኒት መባል ለጌታ ብቻ እንጅ ለሌላ አይገባም ቤዛነትን ለሌላ አካል መስጠት የጌታን አዳኝነት መካድና ሌሎቹን ከጌታ ጋራ ማስተካከል ነው ይላሉ ስለዚህ ብፁዕነትዎ እንዲህ እንዲሉ ከጀርባዎት ማን ነው ያለ ?

⏩ ቤዛነት በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ምንድን ማለት
  ነው ?  ቤዛ ማለት ሁለት ትርጕሞችን የያዘ ነው
፩ , ተቤዘወ አዳነ ካለው የወጣ  የግዕዝ ግሳዊ ቃል ሲሆን ትርጕሙ መድኃኒት አዳኝ ማለት ነው ።
ዮም ተወልደ ቤዛ ኵሉ ዓለም  ፦ ዛሬ የዓለም ሁሉ መድኃኒት ተወለደ እን ቅ ያሬ
፪, ስለ፣ ፈንታ ማለት ነው ዐይን ቤዛ ዐይን ወስን ቤዛ ስን ስለዐይ ፈንታ ዐይን ይጥፋ ስለ ጥርስ ፈንታ ጥርስ ይርገፍ እን ዘጸ ማቴ ፭ ÷  ስለዚህ እመቤታችንን ቤዛ ሲላት ምን ማለት ነው ኅፀፅስ አለው ወይ ?

⏩  ስለእመቤታችን ቤዛነት ከመናገሬ በፊት ትንሽ ነገር ልናገር  እወዳለሁ ለአንድ ግስ ሦሰት ነገሮች አሉት
፩, ንባብ
፪, ትርጕም
፫, ምሥጢር ፦ እነዚህን ጠንቅቆ አለመረዳት ፍጹም ወደሆነ የስህተት ጕድጓድ መውደቅ ነው ።
ማንኛውም ነገር በንባብ ይገናኛል በትርጕምም ይገናኛል በምሥጢር ግን ይለያያል ።

⏩ ይህም ማለት እግዚአብሔር ቅዱስ ይባላል መላዕክት ቅዱሳን ይባላሉ ሰዎችም ቅዱሳን ይባላሉ ፍጥረታትም ቅዱሳን ይባላሉ ።
ቅዱስ ማለት ልዩ ንጹህ ክቡር ማለት ነው ስለዚህ እግዚአብሔርን ቅዱስ ስንለው የባህርዩ ነው መላእክትን ቅዱሳን ስንላቸው የጸጋ ነው አንድ ጊዜ ተሰጥቷቸዋል እያደጉ ይሄዳሉ እንጂ መመለስ መውደቅ የሌለበት ነው (ከዲያብሎስ ውጭ) ሰዎችን ቅዱሳን ስንላቸው በተፈጥሮ ይሰጣየዋል በልጅነት ይታደላየዋል ኋላ በኃጢአት ነሳቸዋል በምግባር በትሩፋት በንስሃ ይመለስላቸዋል ፍጥረታትን ቅዱሳን ስንላቸው የተፈጥሮ ነው ማለት እግዚአብሔር ሲፈጥር አንድ ጊዜ ንፁህ አድርጎ ፈጥሯቸዋልና ፤
ስለዚህ ቅዱስ ባለው ንባብ ይገናኛሉ ልዩ ባለው ትርጕምም ይገናኛሉ በምሥጢር ይለያሉ ማለት የእግዚአብሔር ቅድስና ከመላዕክት የመላዕክት ቅድስና ከሰዎች የሰዎች ቅድስና ከሥነፍጥረት ቅድስና ፈጽሞ የተለየ ነው

⏩ እግዚአብሔር ረቂቅ ነው መላዕክትም ረቂቃን ናቸው
ነፋስም ረቂቅ ነው ውሃ በእጅ የማይጨበጥ በዓይን የማይታይ በእቃ የሚያዝ ረቃቅ ነው እሳት በዓይን የሚታይ በእጅ የማይጨበጥ ረቂቅ ነው ሰይጣን ረቂቅ ነው እሊህ ሁሉ ግን ንባብ ትርጕም ቢያገናኛቸው የርቀት ምሥጢር ይለያየዋልና የአንዱ ርቀት ከአንዱ ርቀት ፈጽሞ የተለነ ነው

🕎 መጽሐፍ እመቤታችንን ቤዛ ሲላት ከጌታ ቤዛነት ጋራ
ንባብና ትርጕም አገናኛት እንጅ ምሥጢር አያጋናኛትም
የእርሷ ቤዛነት ( ፈንታነት ) ስለሔዋን ነው ይህ ማለት ሔዋን ትዕዛዘ እግዚአብሔርን እንቢ በማለት ሞትን አመጣች ቤዛ ሔዋን እመቤታችን እንደቃለህ ይሁንለኝ ብላ ትዕዛዘ እግዚአብሔርን በመቀበል ሕይወትን አመጣች ።

🕎 ሔዋን ባለመታመን በጥርጥር በዓለም ላይ የሞት አዋጅን አሳወጀች ቤዛ ሔዋን እመቤታችን በፍጹም እምነት በፍጹም አለመጠራጠር በዓለም ላይ የሕይወት አዋጅን አሳወጀች ሔዋን ቃለ ሰይጣንን ሰምታ ሰምታ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስን አመጣችብን ቤዛ ሔዋን እመቤታችን ቃለ መልአክን ሰምታ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስን አመጣችልን ቤዛነት ማለት ይህ አይደለምን ?

🕎  ሔዋን ምክንያተ ሞት መሠረተ ሞት ቃኤልን ወለደች
ቤዛ ሔዋን እመቤታችን ምክንያተ ሕይወት መሠረተ ሕይወት ክርስቶስን ወለደች ።
ነገር ግን ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምንያት የሚሆን ቃኤልን ወለደች ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች ሃይ አበ ፷፯ ÷ ፬

🕎  ገነት በሔዋን ምክንያት እነደተዘጋች በቤዛ ሔዋን በእመቤታችን ምክንያት ተከፍታለች ሔዋን ለዓለም ድቀት ምክንያት ከሆነች ቤዛ ሔዋን እሠቤታችን ለዓለም መነሳት ምክንያት ሆነች ቢባል ምንድን ነው ጥፋቱ ?

🕎 ክርስቶስ ግን ቤዛ ሲባል በመጥወተ ርዕስ (ራሱን ሠሥዋዕት አድርጎ) በመስጠት ሥጋውን በመቁረስ ደሙን በማፍሰስባህርያዊ መሥዋዕት በማቅረብ ነው ።
እርሱ የመሥዋዕት በግ ነው እርሱም መሥዋዕት አቅራቢ ሊቀ ካህናት ነው እርሱ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ሕይወቱ ከመንፈስቅዱስ ጋራ መሥዋዕት ተቀባይ ነው
              ሃይ አበ  ፴፮ ÷ ፳፮
ስለዚህ ብፁዕነትዎ ቤተክርስቲያን እመቤታችንን ቤዛ ስትል የጌታን ቤዛነት ሰጥታ እመቤታችን ሥጋዋን ቆርሳ ደሟን አፍስሳ ቤዛ ሆነችን እያለች አደለም ።
ስንዱዋ እመቤት ቤተክርስቲያን ይህንን ያህል ዘመን እመቤታችንን ቤዛ ስትል በረቀቀ ዐይን ተመልክታ አየረ አየራትን ወጥታ እመቀ እመቃትን ወርዳ እንጅ በገዘፈ ዐይን እንዳይመስልዎት ?!?!
ስለዚህ ይህ ኃሳብ ለዘመናት ሲነገር የኖረ የፕሮቴስታንት ኃሳብ እንጅ የእርስዎት ኃሳብ አደለም ።
ወይ ተገልጠው ይምጡ ወይ አጥፍቻለሁ ብለው ቀኖና ገብተው ይመለሱ በጀርባዎት የሌላ ኃሳብ ተሸክመው አያወናብዱን !?!?
           ( ኖላዊ ሆይ! ባይጠብቁ አያስክዱ!?!?)
      የሰማዕትነት መጨረሻው።
በ፸ ነገሥታት መካከል "እኔ ክርስቲያን ነኝ"ብሎ በመመሥከር የክርስቶስን መስቀል ለሰባት ዓመታት የተሸከመው መክብበ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው።
ስለ ክርስቶስ ፍቅር ሲል ሁሉንም መከራ በሁሉም አይነት ትዕግሥት ተቀብሎ በፍጹም የሃይማኖት ልቡና በሰባተኛው ዓመት በሰማዕትነት ፍጻሜ ሰባት ፍጹማውያን አክሊላትን ተቀዳጅቷል።
የልዳ ፀሐይ የፋርስ ኮከብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣትነት  መስቀልን ከመሸከም አልከለከለችውም።
ዛሬ ግን የሁላችንም የኪዳን አባታችን ሆኗል።
የሰማዕትነት የክብር መገሐጫ መጨረሻው ይሄ ኪዳን ነው።
21.04.202517:29
#እመቤታችን_ቤዛዊተ_ኩሉ_ዓለም_ናት!!!

በማኅበራዊ ሚድያ ሲዘዋወር አንድ አባት የተናገሩት ቢድዮ አየሁት፡፡ጥቂት ነገር ልበል፡፡
ቤዛ ምንድን ነው???
#ቤዛ፣ቤዛነት ማለት ስለ አንድ ነገር ምትክ መሆን ነው፡፡እመቤታችን ቤዛ ናት ማለት እግዚአብሔር ቃል ሰው እንዲሆን ከሰው ልጅ የሚጠበቅ ነገር አለ ይህም መርገመ አዳም ወሄዋን ያልወደቀበት ንጹሕ ዘርእ ነው፡፡
እመቤታችን ቤዛ የሆነችው ደቂቀ አዳም ይጠብቁት የነበረውን ንጽሕና ይዞ መገኘት ነው፡፡ስለዚህ እመቤታችን ቤዛ ናት ማለት የደቂቀ አዳምን ግብር ወክላ የተገኘች ስለደቂቀ አዳም ፋንታ በንጽሕና በቅድስና ቤዛ ሆነች ማለት ነው፡፡
#ቤዜነቷም፦
የንጽህና የቅድስና ቤዛነት
የድንግልና ቤዛነት
የመጽነስ ቤዛነት
የመውለድ ቤዛነት
የማሳደግ ቤዛነት
የመሰደድ ቤዛነት
የርሀብ የጽምእ ቤዛነት
የሕማም የመከራ ቤዛነት
የአቂበ ህግ ቤዛነት ከፍላለች፡፡
ቤዛ አበው ነቢያት
ቤዛ ጻድቃን ነገሥት
ቤዛ ንጹሃን ደናግል
ቤዛ ፍንዋን ሐዋርያት
ቤዛ ግፉዓን ጽድቃን
ቤዛ ከዓውያነ ደም ሰማዕት
ቤዛ ስዱዳን ባሕታውያን
ቤዛ ተላውያን ፸ አርድእት ናት፡፡
እኒህ ሁሉ አበው በእመቤታችን ቤዛነት የዳኑ ናቸው እንጂ በእነርሱ ሥራ አይደለም የእነርሱ መከራ ሰውነታቸውን እንደ ወርቅ ቢያጸራውም አምላክን ለመወሰን አለበቁም የእመቤታችን የንጽሕና ቤዛ ግን በማሕፀኑዋ እንድትወስነው አድርጉዋታል፡፡

"እውነት እላችኋለሁ፥ብዙዎች ነቢያትና ጻድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም፥ የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም።
ማቴ13:17::
"ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ትን.ኢሳ.64:6
ነቢያት ሁሉ የአዳም መርገም ወድቆባቸው ሥራቸው ሁሉ ለጽድቅ አላበቃቸው ብሎ ኑረዋል፡፡ እመቤታችን ግን የአበውን ሁሉ ጩኸት የፈጸመች የጩኸታቸው ቤዛ ሆነችላቸው ማለት ነው፡፡
እመቤታችን ቤዛዊተ ዓለም ማለት ከዓለም የሚያስፈልገውን ሥራ ይዞ መገኘት ነው፡፡
ይህን ቤዛነት አለመረዳት እጅግ አደጋ ነው፡፡

"ንትፌሣሕ ኩልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም ወበደመ ዮሐንስ መአድም ቅድስት ማርያም ቤዛዊተኩሉ ዓለም" ቅዱስ ያሬድ
"ኢትኅፈር ልደቶ እም ብእሲት እስመ ይእቲ ኮነተነ ምክንያተ ሕይወት አስተጋበአተነ ቅድስት ማርያም ዘይእቲ ንዋየ ድንግልና ዘአልቦ ሙስና ወይእቲ ዘዳግም አዳም ገነት እንተ መንፈስ ወይእቲ ጽምርተ ህላዌ ወይእቲ በዓለ መድኃኒት እንተ ተቤዘወነ ጽርኅ ንጽሕት እንተ ባቲ ተመርዐወ ቃል"
ተረ ቄር 18፡5
"ዮም ፍሥሓ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም እምሐና ወኢያቄም ከመ ተቤዙ ነቢያተ ወጸድቃነ አማን ተወልደት እመ ብርሃን"
ቅዱስ ያሬድ
"መጽአ ዐቃቤ ሥራይ እም ኀበ አብ እምጽርሐ አርያም መድኃኒት ተረክበት በሀገረ ዳዊት እንተ ስማ ጽዮን ወተፈጸመ ዘተብህለ መኑ ይሁብ መድኃኒተ እም ጽዮን"
መጽ ምሥ 20፡11:
#ቅዱስ ያሬድ፣አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ፤ቅዱስ ቄርሎስ ቤዛዊተ ዓለም ካሏት እነዚህ አባት ቤዛዊተ ዓለም የማይሎት ከማን ወገን ሆነው ነው??
መልሱ ከንስጥሮስ ወገን መሆናቸው ነው፡፡

#እመቤታችን ለዓለም ሁሉ ብቸኛ ንጽሕት ዘርዕ ሆና ከጥፋት በመታደግ ለሁሉም ቤዛ ሆናለች፡፡
ጠቅለል ሲል እመቤታችን ንጹሕ አካሏን ለዓለም ቤዛ አድርጋ ለእግዚአብሔር አቅርባለች ነው፡፡
"የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንነ እንደ ገሞራም በመሰልነ ነበር::
ትን. ኢሳ. 1:9::
#እሰግድ ለንጽሕናኪ ወአስተበርክ ለድንግልናኪ ማርያም ድንግል ቤዛዊተ ነፍስየ ዘኮንኪ!!!

❖እናመልከው ዘንድ ለፈጠረን እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው እንላለን!!!
             ❖አ.ዘ.ያዕቆብ፡፡
©ጌዴዎን ዘለዓለም::
    
ለሲኖዶስ ግባት ተብለው ሊቃውንቱ ያነሧቸው ሀሳቦች መቀበል እንጂ አዲስ ውሳኔ አያስፈልጋቸውም።
ለምሳሌ፦
[  ] ነገ ሥጋዌ ውሳኔ አያስፈልገውም።
[  ] ነገረ ማርያም ውሳኔ አያስፈልገውም።
[  ] ሐዋርያዊ ነገረ ቀኖና ውሳኔ አያስፈልገውም።
[  ] ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ውሳኔ አያስፈልገውም።...
እነዚህን የመሰሉ ሀሳቦች እንዳለ የምንቀበላቸው የምንጠብቃቸው እና ለሚመጣው ትውልድ የምናስረክባቸው ናቸው እንጂ እንደ ሐዲስ ውሳኔ የሚሰጥባቸው አይደሉም።
ሊቃውንቱ ከአባቶቻቸው የተቀበሏቸውን አስተምህሮዎች እንዳለ ጠብቀው ሃይማኖታቸውን በጉባኤ ገልጠው "እንዲህ እናምናለን"ብለው አስረድተው ከመሄድ ውጪ አሁን ባለው ሲኖዶስ የሚጸድቅ ዶግማ የላቸውም።
ውሳኔ የሚያስፈልገው አሁናዊ አሠራርን መሠረት ባደረገ ዕሳቤ ላይ ነው።
ለምሳሌ፦ማንም ተነሥቶ "ድንግል ታማልዳለች? ወይስ አታማልድም? ወስናችሁ ንገሩኝ?" አይችልም።
ሊቃውንቱ የተሰበሰቡት ስለ ድንግል ማርያም አማላጅነት እንዲመሠክሩ እንጂ እንዲወስኑ አይደለም። አማላጅነቷማ በአካል ሳትኖር በነቢያ፤ በግብር በሐዋርያት የተነገረ ነው።
Log in to unlock more functionality.