Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Инсайдер UA
Инсайдер UA
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Инсайдер UA
Инсайдер UA
በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ avatar

በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

➲የበእውቀቱ ስዩም ፈገግታም እውቀትም የሚሰጡ ወጎች ፣ ግጥምች እና የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡
@bewketuseyoum19
Creator - @abela1987 📨
For your comment,feedback and promotion @Bewketuseyoum2bot
Thank you!
TGlist rating
0
0
TypePublic
Verification
Not verified
Trust
Not trusted
Location
LanguageOther
Channel creation dateMay 14, 2025
Added to TGlist
Sep 23, 2024
Linked chat

Latest posts in group "በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ"

ተማሪ ነህ/ሽ
ስንት አመትህ/ሽ ነው ❓
Deleted22.05.202514:07
🌐 ሰበር ዜና 🌐

✅ ቴሌ ነፃ ኢንተርኔት 🎉 ለ 7 ቀን  የሚቆይ ስጦታ መስጠት ጀምሯል፡፡😍❤️😍
👇ከታች #JOIN ብላቹ ሴቲንጎቹን በማስተካከል መጠቀም ትችላቹ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Deleted22.05.202514:07
የሚፈልጉትን መፅሀፍ መርጠው ያንብቡ
እኛ...

እንደ ቀላይ ስፋት
እንደ ዓባይ እርዝመት
ሄዶ ሄዶ ሄዶ፣
ዳርቻ እንደሌለው
እንደ ምድሩ ነፋስ፣
ሰርክ እንደሚነጉደው

በኮርቻ ፈረስ ፣ ሀሳብ ሲያባክነን
ለበዛው ሽንቁሩ ፣ አለም ሲያስጨንቀን
የምንኖር እንጂ ፣ የምንሞት አይመስለን።

እዝጎ😌

(ታደሰ ደምሴ)

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Deleted22.05.202511:49
ፍቅር እስከ መቃብር

ዴርቶ ጋዳ

ዣንቶዣራ

ዝጓራ አንዲሁም የተለያዩ  pdfochen ይፈልጋሉ እንግዲያዉስ የፈለጉትን አማርጠዉ ያንብቡ📝📝📝📝📝

https://t.me/addlist/vsvVhFrjbHxiNzk0
.
ደስታ ያልነው : እድሜ የለው
ገንዘብ ያልነው : ጤና አይገዛ፣
.
አለኝ ብለን : ብዙ ሳይቆይ
እልም ይላል : እንደ ጤዛ።

#ኤዶምገነት
@Edom_ge

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
Deleted22.05.202506:04
🔴 ሰበር ዜና ዛሬ ትምህርት ሚኒሰትር ያወጣው አዲስ ያልተጠበቀ መግለጫ   ‼️

ሙሉ መግለጫውን ለማንበብ ከስር open ሚለውን ይጫኑ 👇👇
Deleted22.05.202506:04
ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ
Deleted21.05.202521:38
ጎልልልልልልልልል ብሩኖኖኖኖኖኖኖ

ብሩን ፈርናንዴዝ ለማን ዩናይትድ ያስቆጠራትን ድንቅ ጎል ለመመልከት 👇👇👇

https://t.me/+zVTrm-b4SMRkMDc8
Deleted21.05.202521:38
የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 5 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️
✨✨✨ባለ ጭንብሉ✨✨✨
✨✨✨ክፍል አስራ አራት✨✨✨

ሲፈን ቤቷ ገብታ ፡ከመቀመጧ ስልኳ ጮኽ፡አነሳችው፡አዳም ነበረ፡ምን ፈልጎነው፡ደሞ አለች አሳቡን ከመስማቷ በፊት፡ንጭንጭ እያረጋት፡"ሄሎ?!"
"አዳም ነኝ"
"አውቃለው መናገር አይጠበቅብህም!"
"እሺ ድምፅሽ ግን ይስተካከልልኝ፡ትንሽ ውበት ስጪው!"
"ለማን ለምን ብዬ?!"
"እንዴ ስቀልድሽ ነው፡ምነው ተቆጣሽ ችግር አለ?"
"ቀልድ አላማረኝም ለጊዜው፡"
"እሺ ወንድሜ እንዴት ነበር ተመቸሽ?"አለ አዳም
"አቤት !ምን ለማለት ፈልገህ ነው!?"ሲፈን ንድድ አላት
"ኧረባክሽ ምርር ምርር አትበይ! ያው ሊሸኝሽ ስለወጣ ፡ ብዬነው፡ "
"አመሰግናለው ፡ስለምቾቴ ስላሰብክ ፡ግን ይሄን ለመጠየቅ ነው የደወልከው፡?"ሲፈን በንዴት መንፈስ ጠየቀች
"አይ እኔ እንኳ እንደ ጨዋታ መግቢያ አደረኩት እንጂ ፡ስለአባትሽ ፡ማለት ቅድም ስለነገርሺኝ፡ነገረ ግልፅ እንድታደርጊልኝ ነበር፡"አለ አዳም፡
"ኦኬ የአባቴ ጉዳይ ላንተ እንደጫወታ መቆጠሩ ነው! በጣም ልታስገርመኝ ነው ፡የሌባ አይነደረቅ ሆንክብኝ፡እኮ፡"አለች ሲፈን ተቆጥታ
"ይሄ ሌባ ምናምን የምትይውን ነገር ተይው!"
"ኧረ ልተወው ግን እውነታው እሱ ነዋ፡እኔም የማውቅህ ጭምር!አሁን ይኽውልህ፡እራስህን እንድትጠብቅ ነግሬሃለው፡በአባቴ ጀርባ ሆኜ ለማይገባው ሰው፡እርዳታ እያደረኩ መሆኔ ቢሰማኝም፡ነገርግን፡በሌላ መልኩ፡እንዳንተ አይነቱን፡ደነዝ፡አንድ ነገር አድርጎ ወንጀለኛ፡ቢሆን ፡ዞሮዞሮ ተጎጂ ነኝ፡ስለዚ፡ከአባቴ እይታ እራቅ፡በቃ!!"አለች ሲፈን ኮስተር ብላ
"ሄሄ አትሳደቢ ደሞ ያሙሰኛ አባትሽ፡በሕዝብ ገንዘብ ነው እየተንደላቀቀ የሚያንደላቅቅሽ፡ሰማሽ፡እያንዳንዷ ንብረቱላይ ፡ዕምባ አለበት፡እራስሽን እንደ የጨዋልጅ አትቁጠሪ!"
"ሀሀ!ሀሀ እሺ የኛ ዕምባ ጠባቂ ፡በለሊት የመጣኽው ከአባቴ ወስደህ የንብረት ክፍፍል ልታደርግ ነበር !!እሺ እኔንስ ?አንተ እመን ባለጌ ነህ በቃ፡አየ እኔ ነኝ የማይገባህን ቦታ የሰጠውህ፡ ነገሮች ሁሉ የሆኑት በጊዜያው ምኞት በመነሳሳት ይሆናል ብዬ፡ነበር፡አንተ ግን አስበህና አቅደህ ነው ያደረከው፡እና ከአሁን በዋላ ይህንን ስልክ እርሳው፡ወንድምህን ሰላም በልልኝ፡ገደል ግባ!!"ብላ ሲፈን ስልኩን ጆሮውላይ ዘጋችው፡እና ሶፋው ላይ ውርውር አረገችው፡ የማይረባ፡ወይኔ ሲፈን ይሄልጅ፡በዚው ከቀጠለ ያሳብደኛል፡ከሱ መራቅ አለብኝ፡እባክህን፡ልቤ ተወኝ ተወኝ ......
,,,,,,,ባለጭንብሉ,,,,,
አብዲ በቁጣ እንደጦፈ አዳምን፡ያዳምጠዋል፡ወሬውን ሲጨርስ፡ዘሎ ሊከመርበትም ያሰበ ይመስላል ፡ይቁነጠነጣል፡አዳም፡አብዲን፡ለማስረዳት፡መከራውን አየ ቀላቶች ሁሉ አልበቃ አሉት ፡ጓደኛውን በፍፁም ማጣት አልፈለገም፡ለአብዲ ለማሳመን፡እንባ ቀረሽ፡ነው የሆነው፡አብዲ የአቶ ይርጋ፡ወሬ ፡አይምሮው ውስጥ እየተመላለሰ የቱን ማመን እንዳለበት፡ግራ አጋባው፡እሳቸው የነገሩት፡እውነት የሚመስል፡ነገር ይበዛዋል፡አዳም ደሞ ሌላ እውነታ ይዞ መጥቷል፡ከማናቸው፡ይሁን ..."አብዲ እመነኝ ጓደኛዬ በርግጥ የመጀመሪያ መነሻ የሆነኝ አሳብ ካንተጋር ስናወራ፡ስለ አቶይፍሩ አብት ሁኔታ፡በጣም ነበር፡የምናደድ የነበረው እና አይገባቸውም ብዬም አስብ ነበር፡ግን በዚመልኩ ለዘረፋ እነሳለው የሚልም አሳብ አልነበረኝም፡ይህ ነገር የመጣልኝ፡ታዲዮስ አንድ ሽጉጥ፡የተገኘነው፡ከጓደኞቼ፡እና እስከሚሸጥ ድረስ ደብቅልኝ ብሎ ሲያመጣው፡በቃ እኔም፡ታውቃለህ፡ተመርቄ፡ስራ ባፈላልግ፡አጥቼ ቁጭ ያልኩ ሰው ነኝ፡ብዙ ነገር መሞከሬንም ታውቃለህ፡ያው እንደምታየው ጡረተኛ ነኝ፡እና ሳስበው፡ለኛ ስራ ፈትነት ምክንያት፡እንደ አቶ ይፍሩ ያሉ ሰዎች፡ናቸው፡ስለዚ እሳቸው ጋር ያለ ንብረት ለኔም፡ይገባኛል ብዬ አጥራቸው፡ደፈርኩ ግን ባጋጣሚ አልተሳካልኝም ይቅርታ መነሻዬ ያንተ አሳብ በመሆኑ፡"አለ አዳም፡እየተለማመጠ
"አይ አይ፡ስትልከሰከስ ነው የተያዝከው፡ሲፈን ላይ አንተ ....ይዘገንናል!"
"አደለም !አደለም!ውሸት ነው ሲፈንን ምንም አላደረኳትም፡በርግጥ ሞክሬ አለው፡ግን ዝም እንድትል፡ለማስፈራራት እንጂ፡ለሌላአልነበረም፡ያ ይርጋ የምትለው ሰው ምን እንደሚፈልግ ባላውቅም፡ግን ውሸት ነው የነገረ፡በጣም ብዙ ውሸት፡እመነኝ ጓደኛዬ እንደውም እሱን ሰውዬ መጠርጠር ጀምሬ አለው፡እባክህ፡ተረጋግተን እናስብና፡የአባት ገዳይ፡ላይ፡ተረዳድተን፡እንድረስበት!"አለ አዳም
"አትዋሸኝ አዳም፡ጓደኛዬ ነበርክ የማምን ሰው፡ነበርክ፡ !"አለ አብዲ ቀጭ ብሎ፡ጭንቅላቱን እያወዛወዘ ከቅድሙ ግን ተረጋግቷል፡
"አብዲ አሁንም ጓደኛዬ ነህ ሁሌም፡ችግር ነው የማይደፈረውን እንድዳፈር ያረገኝ፡እመነኝ ጓደኛዬ ከማንም ጋር አልተባበርኩም፡ ፅግዬ ትሙት፡እናቴን ያሳጣኝ፡በጭራሽ፡ለአባትህ ሞት ከማንም ጋር አልተባበርኩም፡በጭራሽ ያሁሉ ድብደባ እንኳ ሲወርድብኝ፡እነሱን ከመሳደብ ውጪ የማንንም ስም አልጠራውም እመነኝ!!!"አለ አዳም በጭንቀት ጓደኛውን እየተለማመጠ፡አብዲ በመጨረሻ ለስለስ እያለ መጣ፡ከዛም ማውራት ጀመሩ ማነው አባቴላይ እጁን ያነሳው፡ለምን ፖሊሶቹስ፡አንድ ነገር ላይ አይደርሱም ፡ለምን .....
,,,,,,,ባለ ጭንብሉ,,,,,,
"ኤዶ ምነው ፍዝዝ አልክብኝ አለሜ?!"አሎ እትዬ ፅጌ
"እ እእ አይ እኔ እሙ አረሰላም ነኝ የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር፡!"አለ ኤዶም
"ስለምን አለሜ ፡ምነው ስራ ቦታ ነው።ያልተስማማህ ነገር አለ?"
"ኧረ እማ አትጨነቂ ሰው እኮ ማሰብ አለበት ለተወሰነ ሰሃት፡አልያ ከእንስሳ በምን ይለያል፡ሲያስብ ነው ነገሮችን መቀየር የሚችለው !"አለ ኤዶም ከእናቱ ጥያቄ ለማምለጥ
"አይ ከዚ በፊት እንዲ ሆነህ አይቼ አላውቅም ለዛ ነው!"አሉ ፅጌ
"አሃ እስኪ ተይው ፅግዬ መልሱን ሰጠሽ አደል፡ምን እንዳይሆን ነው፡ያስብ እኛም አስበን ነው ከዚ የደረስነው፡የሚያስቡ ልጆችም ያመጣነው ሀሀሀሀ አስብ ልጄ ተዋት እሷን መጨነቅ ነው ስራዋ!"አሉ አቶ አይሉ ጣልቃ ገብተው፡በዚ መሃል አዳም ገባ ፡ትንሽ የቀማመሰ ይመስላል እንደ መንገዳገድ ብሎ፡ሶፋው ላይ ዘጭ አለ፡አባት ፡ገልመጥ አደረጉት፡ኤዶም፡"ሰላም አመሻቹ አይባልም ቢያንስ! ዝም ብለህ ትቀላቀላለህ?!"አለው
"እእ ሼ ሼባው ልትወጥሪኝ ነው፡እኔ አልኩ አላልኩ ማምሸትህ አይቀር፡!"አለ አዳም ኮልተፍ እያለ
"ችግር የለም አለሞቼ ዋናው በጊዜ መሰብሰባቹ ነው፡ግን አዳም ይሄን መጠጥ ተወው እባክህ፡!"
"ውይ እማ ሦስት ብቻ እኮነው ግን የኔ ነገር ያው አልችልም ለዛ ነው!"አለ አዳም ለመዋሸት እየሞከረ
"ሲነጋ እናወራለን ፡"አሉ አቶ አይል ኮስተር ብለው
ኤዶም ተነስቶ ሊወጣ ተዘጋጀ ፡እናት ወደኤዶም እያዩ"ወዴት ነው ኤዶ መሽቷል እኮ ፡ወንድምህ ሲገባ!.."አሉ
"ኧረ እማዬ ግቢውስጥ ነኝ የትም አልሄድም"
"ኧረ አንተ አይደብርህም ፡እኔን ስታይ መደንገጥ ጀምረሃል፡ችግር አለ ?!"አለ አዳም እንደመቆም እያለ
"የምን ችግር ምን ያስደነግጠኛል?!"አለ ኤዶም ፊት ለፊት እያየው
"ብቻ እኔ ያሰብኩት ነገር እንዳይሆንና እንዳንጨራረስ ፍራ፡ ዋ...."አለ አዳም ሲፈንን አስቦ
"ምንድነው የምታስበው"
"ነገርኩህ አዳታረገው !"
ሲፈን፡የኤዶም እናት ወይ አዳም ቢመጡስ የሚል ድንገተኛ ስሜት ተሰምቷት እንደመነሳት ብላ ተቀመጠች፡ኤዶም ፡አብሯት ቁጭ ለማለት ሞከረ፡ግን እመም ስለተሰማው አቃስቶ ተመልሶ ተኛ፡ሲፈን ስቅ አለች እጁን ያዝ አደረገችው፡በጭንቀት ፡ከወደበሩ የአዳም ድምፅ ተሰማ፡ ሲፈን ድንግጥ ብላ ዞረች፡አዳም አያት ተያዩ.......
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,

✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19
አዳም ድንግጥ አለ በዚ ሁኔታ ማንም ባያገኘው ፡ደስ ይለዋል፡ኤዶም፡ማንን ነው፡ብሎ ዞረ፡ሲፈን፡ናት፡ቤቱን፡ባለፈው ከለቅሶ ቤት፡ሆኖ አዳም አሳይቷት ነበር፡ስልኩ፡ባይነሳላት ጊዜ ቀጥታ መምጣቷ ነው፡ብዙ አልተቸገረችም፡ኤዶም፡ልቡ ለሁለት የተከፈለ እስኪመስለው፡ትርክክ አለ፡ፍዝዝ እንዳለ ፡ቆመ፡አዳም፡ቀጥታ በመሄድ፡ሲፈንን፡ግቢ ብሎ አስገባት፡ሲፈን ገብታ መሃላይ ስትቆም ፡እናት ተቀመጪ ፡ቡና ይፈላ ሻይ ይሻልሽ፡ይሆን፡አሉ፡ጭንቅ፡እያላቸው፡እነ አዳም ቤት ውስጥ ሴት አምጥተው አያውቁም፡ለትዬ ፅጌ አዲስ ነገር ነው፡ሽርጉድ አሉላት፡አዳም አጠገቧ ሄዶ ተቀመጠ"እእ ስሚኝ ሲፈን፡"አለ ቀስ ብሎ ድምፁ እንዳይሰማ እየተጠነቀቀ፡"ሁሉንም አስታውሻለው፡አንድም ሳይቀር፡አባትሽ፡ካጠፋውት በላይ ነው የቀጡኝ፡እና፡ክፍያ መጠየቄ አይቀርም፡!"አለ ኮስተር፡ብሎ፡
"በእውነት ሁሉንም ክንዴንም፡?!"
"አዎ ሲፈን በጣም ነው የተጫወቱብኝ ፡!"
"እኔንስ ያደረከኝ ነገረ!?"ብላ ቆጣ አለች
"አንቺ ምን አደረኩሽ፡እራስሽ ነሽ፡እንደዛ እንድሆን ያረግሺኝ !"
"ነው በጣም፡የምትገርም እራስ ወዳድ ሰው ነህ!"ብላ ተነሳች ሲፈን"እዚ የመጣውት፡እንድትጠነቀቅ ልነግርህ ነው፡ካላስታወስክ፡ልትጎዳ ትችላለህ ብዬ፡የአባቴ ሰዎች ሊያተኩሩብህ ይችላሉ በተረፈ እንኳን ደሳለህ ሊሂድ"አለች ሲፈን ጥግ ላይ ወደ ተቀመጠው ኤዶም እያየች፡አንተም የሱ ቢጤ ትሆን ይሆናል ያልታደሉ እናት ምስኪን አለች ወደ ትዬ ፀጌ በማየት "እንዴ ቡና ላፈላልሽ ነው ሳትቀመጪ ምነው፡አስቀየመሽ፡እሱ እንደው፡ሰው መያዝ አይችልበት፡አንተ ምን ዝም ትላለህ፡አስቀምጣት እንጂ?!"አሉ እናት፡አዳም ከተቀመጠበት ሳይነሳ ጭራሽ ተጠንቀቅ ፡ከነሱም ብሶ ይላል አዎ በርግጥ፡የሰው አጥር፡ተዳፍሬ አለው፡ግን ያሁሉ ዱላ ይገባኝ ነበር፡ሞቼ ነበር እኮ፡አዳም ፡ከሱ ጥፋት ይልቅ የነሱ ነው ጎልቶ የታየው፡፡ሲፈን"አይ እማማ ልሂድ፡!"አለች፡
"እሺ መቼስ በባዶ ይሁና በል ተነስተህ ሸኛት "አሉ እናት፡ኤዶም በድፍረት"አይ ተይው እሱን ዛሬ ጠንነት ፡አልተሰማውም መሰለኝ እና እኔ እሸኛታለው !"አለ፡አዳም፡በመገረም ወንድሙን እያየ ተስማማ፡ሲፈን፡አልደበራትም፡እሺ አለች
ተሰናብታቸው ከኤዶም ጋር ወጣች፡እናም፡የአዳምና የኤዶም፡ልዩነት፡እስኪገርማት፡ሆነች፡ፈራተባ እያለነው፡የሚያወራት፡ትህትናው፡አክብሮቱ ፡ቁጥብነቱ ተዳምረው፡የአዳም ተቃራኒ አደረጉባት፡በተለይ፡ዛሬ አዳም፡ፍፁም፡ወደ ቀድሞ አውሬነቱ ተመልሷል አለች በውስጧ፡
"እእ መኪና ይይዘሻል እእንዴ ?"
"አዎ ያቻት ወደውስጥ ይዣት ከምገባ ብዬ ነው በዋላ ለመዞር አይመቸኝም፡ብዬ፡ተመለስ በቃ፡ደርሻለው፡"
"አይ ችግር የለም፡እእ አብሬሽ ብሄድ ሁላ ቅር አይለኝም"ብሎ ፈገግ አስባላት
"እውነት፡ከሆነ ደስ ይለኛል፡"አለች በዛውም፡አዳምንም ለማበሳጨት፡አስባ
"ከምር ፈቀድሺልኝ፡እእ ባንዳፍ፡ቀጥለሽ አንቺም፡የምትፈልጊውን፡ትጠይቂኛለሽ፡ታያለሽ እምቢ አልልሽም፡!"ብሎ ደግሞ አሳቃት
"ክክክክክ አንተ ተጫዋች ነህ ለካ ዝም ያልክ መስለህ!"
"ላንቺ ሲሆን ነው መሰለኝ"አላት ሳቅ ብሎ፡ሲፈን፡ቀለል አላት፡መኪናዋን፡ከፍታ አስገባችው፡"አሃ የወንዱን ስራ"አላት ኤዶም
"በራስህ መኪና ሲሆን ነዋ ግባ ግዴለም፡"ብላ አስገባችው፡እሺ አለ ሳያመነታ፡የሚሄድበት፡ምክንያት ባይኖረውም፡ከሲፈን ጋረር መሆን ግን፡ፈልጓል፡ወንድሜስ፡ከልቡ ወዷት ቢሆንስ፡በአንድ ጊዚ ሁለታችንም ለአንዲት ሴት ስሜት ሊኖረን ነው እንዴ.......ከዚ በፊት እንዲ አይነት ስሜት፡ተሰምቶኝ አያውቅም፡እና ምን ላድርግ......ለቅሶ ላይ ካየዋት ጀምሮ አስባታለው፡ እና ምን ልሁን ዛሬ ጭራሽ ቤት መጣች፡ኧረ ኧረ በወንድሜ ላይ ለመቀኝ ነው እንዴ ኧረፈጣሪዬ ምን እየተካሄደነው፡.....አለኤዶም ጭንቅ፡ጥብብ እያለው .....
,,,,,,,ባለጭንብሉ,,,,,,,

🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,

✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19
✨✨✨ባለ ጭንብሉ✨✨✨
✨✨✨ክፍል አስራ ሶስት✨✨✨

እንግዲ ቀን አለፈ፡አቶየሱፍም ከሞቱ አስራምስት፡ቀን አለፋቸው፡አብዲም ነገሮች ሁሉ ግራ እንዳጋቡት፡እንደተምታቱበት፡ቀጥሎዋል፡በተለይ በተለይ ያቶ ይርጋ፡ ፡በቀልድ እያዋዙ፡አንዳንድ፡ቃላቶች መሰንዘር፡ግራ እያጋባውና፡ጥርጣሬውን፡ይበልጥ እየጨመረለት፡መጥቷል፡የበለጠ ደሞ ስለ አዳም፡አንዳንድ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች ይናገሩና ፡ትኩረት ሰቶ ሊያዳምጣቸው፡ሲል ፡ስቀልድህ ነው፡ጥሩ ልጅ ይመስላል እያሉ ያምታቱታል፡በልቡ እኚ ሰውዬ፡ምንድነው፡አሳባቸው፡ይላል፡ደሞ ለምንድነው፡ሱቅ የሚመላለሱት፡ለምን፡ያዘኑ ይመስላሉ፡እኔ እንደው፡እስካሁንም፡ታዝቤአቸዋለው፡እንዴ፡ለአባባ፡አንዲት፡ዘለላ እንባ እንኳ ጠብ አላላቸውም፡እና አሁን፡እየመጡ፡እኔን የሚያደርቁኝ፡ለምንድነው፡እንደ አቶ ይፍሩ ፡አንደኛቸውን፡አጠገቤ ዝር፡ባይሉ ደስታዬ ነው፡
"እኔ የምልህ ግን አብዲ፡ስለ አዳም የምታውቀው ነገር አለ?"አሉ አቶ ይርጋ
"አአልገባኝም፡ይሄን ጥያቄ በተደጋጋሚ ጠይቀውኛል፡ባለፈውም፡ምንድነው፡ፋዘር፡ስለሱ፡ሊነግሩኝ፡የፈለጉት፡ነገር ካለ፡ግልፁን ይንገሩኝ!!"አለ አብዲ ተሰላችቶ፡እንዴ ፡አዳም አዳም፡
"አይ፡እእ እኔ የማውቀው፡የለሊት ዘራፊ መሆኑን ነው፡ማለት፡ሰው ቤት አጥር ዘሎ፡እንደገባ አውቃለው፡አንተ ስለሱ፡ምንም፡እንደማታውቅ ግን ከሁኔታህ ተረድቻለው፡ለዚነው፡ስለሱ ያለህን፡ነገር ለማወቅ ፡ስፈትሽ፡የነበረው፡አትበሳጭብኝ፡ልጄ፡ለመጠንቀቅ ፡ብዬ ነው፡በተለይ፡አባትህ፡ከሞተ፡በዋላ፡ከቤትም ስመጣ፡እዚም እሱቅ ድረስ፡እየመጣ፡ሲጠጋጋህ፡እኔ፡ከማውቀው፡ማንነቱ ጋር፡በጭራሽ፡አልጣመኝም፡አንተንም፡ማጣት አንፈልግም፡ልጄ፡ያባትህ፡ይበቃል!!"አሉ አቶ ይርጋ፡ያሰቡ በመምሰል፡የአብዲን፡ጭንቅላት፡ለመበረዝ፡አየሞከሩ፡አብዲ፡በመገረምና፡በመደናገጥ፡ፍጥጥ ብሎ፡ቀረ፡ምንድነው፡የሚሉት? በሚል አስተያየት፡እያያቸው"እእ፡አልገባኝም፡የምን ዘረፋ፡የምን፡ማጣት?! ከአዳምገር ምን ያገናኘዋል፡ደሞ፡አዳምን፡የት ያቁትና ነው ፡ጓደኛዬ፡በጣም ስርሃት፡ያለው፡ልጅ ነው፡ከአይለኝነቱ በስተቀር፡ሌባ አይደለም፡ስለማያውቁት፡ነገር፡እንዲ በድፍረት፡እንዴት፡ያወራሉ!!"አብዲ፡እራሱን መቆጣጠር፡አቃተው፡አቶይርጋ፡ተረጋግተው ካስጨረሱት በዋላ፡ቀስ፡ብለው፡ስለ አዳም፡የሚያውቁትን ፡ማውራት ጀመሩ፡ጭንብል፡በማድረግ፡ማንነቱን ሳያሳውቅ፡በለሊት፡የአቶ ይፍሩ ቤት፡መግባቱን፡ከዛም፡ከአቶ ይፍሩ፡ገንዘብ መጠየቁን እና ሲፈንን እንደደፈረ፡በዋላ፡ዘበኛቸው፡ድንገት፡ነቅቶ፡በዱላ ሳያስበው፡መቶ፡እንደጣለው፡አቶይፍሩም፡ከዘበኛው ጋር፡ተጋግዘው፡አቶ ይፍሩ ጊቢ በሚገኘው፡ትንሽዬ መጋዘን ውስጥ፡አስረው፡ሲደበድቡት፡እንደነበር፡በዋላ ማነው፡የላከህ፡ብለው፡በማስገደድ፡ቢጠይቁት፡አቶ የሱፍ፡መሆናቸውን፡እንዳመነ ከዛ፡መልሰው፡የተጎዳ ሰውነቱ እንዲያገግም አኪም ቤት እንዳስተኙት፡ጤንነቱ ሲመለስ፡ይኽው፡ወደቤቱ ተመለሰ ብለው ጨረሱ፡ከትንሽ እውነት ጋር፡ብዙ ውሸት፡ቀላቅለው፡አብዲን፡በአቶ፡ይፍሩና በአዳም ላይ ለማስነሳት፡እያሴሩ፡፡አብዲ፡የሰማውን ማመን አቃተው፡የምን ተረተረት ፡ነው፡የሚያወሩልኝ፡ከየት ወዴት፡ነው፡እኚ ሰውዬ ሊያሳብዱኝ ነው እንዴ
"ምን አይነት፡ሰው ነዎት፡በፍፁም፡እውነት፡አይደለም፡እንዴ፡ባባቴ ሞት፡ተጠያቂ አቶይፍሩና አዳም፡እጃቸው፡አለበት፡እንደማለት፡እኮ ነው፡የሚናገሩትን ያውቁታል!?"ጮኽ አብዲ
"እኔ የሱፍን፡እነሱ አጠቁት እያልኩ አደለም፡ግን፡ይፍሩ፡ከአዳም፡የሰማው፡ሊዘርፍ፡ሊመየቻለበት ምክንያት፡በየሱፍ ትህዛዝ እንደሆነ ነግሮታል፡ይሄን ነው የማውቀው፡እንግዲ ፡የሱፍ፡ምን ያጣው ነገር አለና፡ወደሱ ይልከዋል፡አዳም፡ለማምለጥ ብሎ የተጠቀመበት፡ሳይሆን አይቀርም፡ያው ያንተ ጓደኛ ስለሆነ፡ምን አለባት፡በጓደኝነት መንፈስ ተነሳስተህ ስለኛ፡ብዙ ሳታወራው፡አልቀረህም፡እሱን፡ነው፡የተጠቀመበት፡ሲመስለኝ፡እኔ ግን አሁን ያልገባኝ፡እንዴት፡የሱፍ፡ሲሞት፡እሱ መጣ፡መጠርጠር ጀምሬ አለው፡ነግ በኔ ነውና፡ይፍሩ የያዘውን፡ሌባ፡ጓደኛችን በሞተ ማግስት ለቀቀው እንዴት?!"ብለው፡የባስ ዘባረቁበት፡አብዲ ጩጩህ አለው፡ነገሮች፡ተመሳሰሉበት፡አዳም፡ስለ ሁሉም ያውቃል፡ብዙ ነገር፡አውርቶታል፡እንደሚሲጢረኛ ጓደኛው፡እና ፡ምን ጓደኛዬ፡አላምንም አላምንም ፡አዳም፡ጭንብል ለብሶ፡በለሊት፡የሰው አጥር ደፈረ እንዴት ....እንዴት....
♥ባለጭንብሉ♥
አዳም ሰውነቱ ይንቀጠቀጣል ፡ነገሮች፡በጣም ቀውስ አድርጎታል፡ትላንት አብዲ ተናግሮት ከሄደ በዋላ ሲረባበሽ ነበር፡ያደረው፡በሰሃቱ ሲምል ሲገዘት፡ነበር፡ኤዶምም ጭምር ተከላክሎለታል ወንድሜ ከትህቢቱ በስተቀር ሌላ ምንም አመል የለበትም፡እንዴት፡እንዲ ትናገረዋለህ፡ብሎ አብዲን፡ተቆጥቶ ፡አሰወጥቶታል፡ብዙ ነገር ተፈጥሮ ነበር፡እውነት፡ሲፈን ያለችው፡ትክክል ይሆን እንዴ ብሎ እራሱን ሲጠይቅ ነበር ፡እንዎ ዛሬ እውነቱ ተገልፆለታል፡እያንዳንዱን ነገር ፡አስታውሶታል፡በጣም ተደናግጧል፡የበለጠ እንዲያስታውስ የሆነበት ምክንያት ደሞ፡ታዲዮስ የተባለ ጓደኛው፡መጥቶ፡ወደቤት መመለሱ እንዳስደሰተው፡ተናግሮ፡እንዴት ነው፡ነገርዬው፡እጅህ፡ላይ ነው፡አሁን፡እባክህ መልስልኝ፡ጓደኛዬ ሊፖሽረው፡ነው በድብቅ የሚገዛን፡ሰው አለ፡ሲለው ግራ በመጋባት፡ምኑን ቢለው፡ሽጉጡን፡የት አደረከው ምኑን ትላለህ እንዴ ብሎ ሲያፈጥጠው፡በድንገተኛ ድንጋጤ ተሞላ ፡ተነሳ ወዲያ ወዲ አለ ወጭንቀት፡ትንሽ ቆይቶ እያንዳንዱ ምስል አይምሮውስጥ ተመላለሰበት፡የክንዴ ድምፅ፡ሽጉጡን ከየት ነው የተዋስሺው፡ጭንብሌ፡ማነው የሰጠሽ፡እሱንም ሰርቀሺው፡ነው ፡ምን አገባህ፡አይለኛ የክንዴ ዱላ ፡አዳም፡ትውስታው፡አሳቀቀው፡ክንዴ ደጋግሞ ሲመታው፡ስቃዩ መጣ፡ጭንቅላቱን ይዞ ቁጭ አለ፡ታዲዮስ "ምንድነው ጀለስ፡ጥለሺው ነው!?"አለው መልሶ"እሺ ኧረ ምንድንሼ!የታለ ሽጉጤ ኧረ አዴ !"አለው፡አዳም ተነስቶ በቁጣ ጮኸበት
"ውጣ ጥፋ ከፊቴ፡!!"አለው እየገፈተረው
"ኧረ እሺ አዴ እንዳትመታኝ ይኬዳል፡እንኳን ሽጉጥ ሰውም ይቀራል፡ተረጋጋ ጓደኛዬ!"አለ ታዲዮስ አዳምን ይፈራዋል እንኳን ሰንዝሮበት፡እናም፡ቶሎ ብሎ አመለጠው፡አዳም ወዲያ ወዲ እያለ፡በብስጭት፡ተወራጨ ክንዴ አቶ ይፍሩ የሲፈን፡አባት፡ወይኔ ተጫውተውብኛል፡ወይኔ ምን አይነት፡የማልረባ ሰው ነኝ፡ወይኔ አዳም፡አብዲ እንዳለው፡አቶየሱፍ በኔ ምክንያት ከሞቱ ፡አለቃቸውም፡አቶይፍሩን፡ላደረጉት ነገር ይከፍሏታል፡ብሎ ፎከረ፡አዳም፡ሲወዛወዝ፡ኤዶም ገብቶ መቆሙን እንኳ ልብ አላለውም ነበር፡
"እሺ ምንድነው አሁን ደሞ?"አለው ኤዶም ተገርሞ
"አይ እእ ዝምብዬ ነው!"
"አዳም እእ ልክ አትመስለኝም፡ቁጭ በልና እናውራ!"አለው
"ይኽውልህ ኤዶም እኔን መጨቅጨቅህን ካላቆምክ፡መልሼ እጠፋልሃለው፡ዝም በለኝ!"አለው በቁጣ፡ፊትለፊት፡እያየው ለመቆጣተሸ ሲዘጋጅ፡ከውጪ እናት ገቡና ገላገሏቸው፡እናታቸውን ሲያዩ ሁለቱም ተረጋጉ፡"እናንተ ምንድነው፡ትግል ሊገጥም የተዘጋጀሰው መስላቹ የቆማችሁት፡ክክክክ ውይ ልጆቼ፡ግቢ ግቢ እናቴ ሁለቱም አሉ፡ግቢ !"አሉ
Subscribers
Citation index
Avg views per post
Avg views per ad post
ER
ERR
OCT '24JAN '25APR '25

Popular posts በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ሆናዋለች ቤዛ

በአምላኳ ተመርጣ ፤ ያውም ለናትነት
ባሪያው ነኝ እያለች ፤ የምታዘዝለት
በሄዋን ትእቢት ፤ የተዘጋው ገነት
ዳግም ተከፈተ ፤ በማርያም ቅንነት።
እንግዳ የሆነን ፤ የሥጋዌ ሚስጥር
አምና ተቀብላ ፤ በሄዋን ጥርጥር
ዳቢሎስ ካስገባን ፤ የገሀነምወህኒ
ማርያም አሶጣችን ፤ ብላ ይኩነኒ።
ዳግሚት ሰማዩ ፤ ዙፋኑ ለመሆን
የተገባች ሆና ፤ ልጁ ልጇ እንዲሆን
ሄዋን ያጣችውን ፤ ቅድስና ይዛ
ማርያም ለዓለሙ ፤ ሆናዋለች ቤዛ።

✍ አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
06.05.202508:34
--------💕አትጥፊ ከቤቴ💕--------
እኔ አቅም አልባ ሀጥያት ያደከመኝ፣
መፈጠር ትርጉሙ ጠፍቶኝ ያባዘነኝ፣
የዓለም ብልጭልጯ ስቦ ያባከነኝ።

ሞትን ያላሰበው ይህ ሞኝ ልቤ፣
ዛሬ አቅም አጥቶ ወድቋል ከአንዱ ግርጌ።
ልጥራሽ ድንግል ብዬ ስሚኝ እመቤቴ፣
ሀጥያት ባቆሸሸው ባደፈው እኔነቴ፣
ድረሺልኝ ድንግል ሳጠፋ ህይወቴ።

የሰውነት እድፍ ይለቃል በውሃ ፣
የልብስም እድፍ ይነፃል በውሃ ፣
ነፍሴ ቆሽሻለች ልትቀር ነው በረሀ፣
ድንግል ጥሪኝና ልንፃ በንስሀ።

ከአምላክ የተሰጠሽ ልዩ ስጦታዬ፣
ከጭንቀት ገላጋይ ሀጥያትን ማብቂያዬ።
ለልቤ ሠላሟ ፈውስ ነሽ ለህይወቴ፣
ወላዲተ አምላክ አትጥፊ ከቤቴ።


                   በሳምሪ የዝኑ ልጅ
                    
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
28.04.202514:27
ሞትን የማቀው በእናቴ ነበር ። አሟት ..አሟት.. ትንሽ በርታ ስትል እየመከረቺኝ ቃል እያስገባቺኝ ቁርጥ ቀን ሲመጣ አይን አይኔን እያየቺኝ በዙርያ ያገኘችውን ሰው አደራ አደራችሁን ... የቤቢን ነገር አደራ እያለች እየተማፀነች አምላኳን ቃል እያስገባች ሄደች.... አካሄዷ የመጨረሻ አልመሰለኝም ነበር ...

ነብሷ ሲወጣ አጠገቧ ነበርኩ ። የቃተተቺው መቃተት ያየቺኝ አስተያየት ። ብዙ ቀን አይኔ ላይ እየመጣ ያቃዠኝ፣ ያባንነኝ ነበር ።
የሞተችብኝ ክረምት ላይ ነበር እኔ የአምስተኛ ክፍል ልጅ ነበርኩ...

እናቴ ስትቀበር ቀብር ሄድኩ .. ሲቀብሯት አየሁ ...አይኔ እያየ ጉድጓድ ውስጥ ሲከቷት እየተንከባለልኩ እናቴ አልኩኝ ....ቀብረናት የተመለስን ማታ ዝናብ ዘነበ እናቴን ዝናቡ መታት እያልኩ ጮሁክ።

ሲርባት ማን ያበላታል? ዝናቡ ይደበድባታል እያልኩ በሰሌን ብቻ ለምን ቀበራችኋት እያልኩ አነባው

ግዜ ትኩስ እምባዬን አደረቀው እድሜ ሞት የሁሉም የሰው ልጅ እጣ ፈንታ ነው ብሎ አብራራልኝ. ።
ሁሌ ድል ባገኘሁ ቁጥር እናቴ ይሄን ብታይ እያልኩ ሊገኝ በማይችል እድል እየቆዘመኩ አልም ነበር ።

በድላችን ወቅት የምንወደው ሰው አለመኖር የሚያክል ቀፉፊ ነገር አለ ? ?

ቀን ሄደ ።

እየኖርኩ ሳለ
ሞት ደግሞ በወንድሜ በኩል መጣ ....አየሁት ... ትልቅ ሰው ሆኜ ስለነበር ። ያዘንኩበትን ነገር ለልቤ እያስረዳው ብዙ አዘንኩ ። በህይወት እያለ መንከላወሱን እያብራራው አዘንኩ ። እውቀት ትካዜን ታበዛለች እንዲል ቃሉ ።

እናቴን እንኳን ይሄን አላየሽ እያልኩ ...አንቺ ብቶሪልኝ ኖሮ እያልኩ ወንድሜ መከታዬ እያልኩ አዘንኩ ።

ወንድሜንም ሳጣ እናቴን አጥቼ ያዘንኩት ሃዘን ተቀሰቀሰ ።
ሃዘን አይረሳም ልብ ውስጥ ይቀበራል እንጂ !!

ሞትን ማስመለጥ የማይችል የሰው ልጅ ስልጣኔ ምንድን ነው ?? የሰው ልጅ የሚያህል ፍጡር ሞትን እለት እለት እያየው እለት እለት እንዴት ተዘነጋው ??

አሁንም ግዜ ሄደ

የማላቀው አይነት ጥበብ ዳግም ሞትን እስረሳኝ ።

ድንገት ....በእግረኛ መንገድ እየሄድኩ ፍሬኑ የተበላሸበት መኪና መሰለኝ ....እኔን ስቶኝ አጠገቤ ትንሽ ራቅ ብሎ የተቀመጠን ብላቴና ሊስትሮ ገጨው..... አገጫጩ ሰቅጣጭ ነበር እሚተርፍም አይመስለኝም .....

የተገጨውን ብላቴና ለማየት ፣ ለማትረፍ ሲረባረቡ ደንዝዤ ነበር ። ትንሽ ራቅ ብዬ ውሃ ልኩ ጋር ተዘርፍጬ ሰማይ ሰማይ እያየሁ እንባዬ ወረደ ....

በቅፅበት እንደወጣው ልቀር ስለነበር መሰለኝ !
የሚወዱኝ ሰዎች ድንገታዊ ሞቴን ሲሰሙ የሚያዝኑትን ሳስብ ይሆን ??
ምድር የፈለገ ብትመር ምሬቷ ከመሞት እንደማይበልጥ ገብቶኝ ይሆን ብቻ እንባዬ ፈሰሰ !!

ሊሰራ የወጣው ብላቴና አደጋ ዘግንኖኝ ይሆን ?
የሰው እግር ስር ሆኖ ኑሮን ሲታገል...
ምን አልባት ለነገ ብሎ ምሳውን ዘሎ ይሆን ?
ምን አልባት ኗሪ ነኝ ብሎ ሰው በድሎ ይሆን ?
ምን አልባት ኗሪ ነኝ ብሎ ለእናቱ ሊልክ የነበረውን ያንሳታል ጠርቀም ይበልላት ብሎ ይሆን ....??

የሰው ልጅ ግን አያሳዝንም ?!
© Adhanom Mitiku

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
17.05.202505:27
ሰሞንኛ
(በእውቀቱ ስዩም)

ስሙኝማ፤ ሻሩክ የተባለ የህንድ ፊልም ተዋናይ ትዝ ይላችሁዋል?፤ በልጅነታችን ደብረማርቆስ ውስጥ ፊልም ቤት ገብተን፤ ደምበጃን በሚመስል ቲቪ ፥ ሻሩክ አርባ ደቂቃ ዘፍኖ አምሳ ደቂቃ የሚደባደብበት ፊልም እናይ ነበር፤ በጊዜው መሄጃ ስላልነበረን ,ከድህነት እና ከኩርኩም የተረፈው ልጅነታችን የቦሊውድ መጫወቻ ነበር፤

ይሄ የቢሊውድ አውራ ሰሞኑን በኒውዮርክ እንግድነት ተጋብዞ ሂዶ ነበር፤ እና አንዱ ድምባዣም ጋዜጠኛው ሲያየው “ ደሞ አንተ ማነኝ አልህ?” የሚል ጥያቄ ሰነዘረበት፤
ሻሩክ “ ለካ እኔን የሚያውቁኝ ያገሬ ልጆች እና አጎራባች ቺስታ ህዝቦች ናቸው ፤ እኔን ብሎ ዝነኛ “ ሳይል አልቀረም፤

ባጋጠመው ነገር ልቡ ተሰብሮ ፥ በማግስቱ፥ በፓኪስታን አዳሪው አውሮፕላን ተሳፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ፤

አንድ ቲክቶክ ፉገራ ሰርተህ ፥ የብረት ምጣድ ቂጥ የሚመስል የሰለብሪቲ መነጽር ገድግደህ ፥ ልዝብ ሰላምታ ሰጥቶ የሚያልፈውን መንገደኛ ሁሉ “አላውቅኸኝም እንዴ “ እያልህ የምታፋጥጥ ሰውየ፥ ክፍለከተማው ካውቀህ ይበቃል፤ እንኳን አንተ ሻሩክም ተዘንግቷል፤

የሻሩክ ግን እንድ ሀገር ክብር ይነካል፤

እኔ የህንድ የባህል ሚኒስተር ብሆን ኖሮ የማረገውን አውቅ ነበር፤

ምን አረጋለሁ?

በህንድ መንግስት ስም ቶምክሩዝን ወደ ቦሊውድ እጋብዘዋለሁ ፤ ከዚያ እልል ያለ እደግስና የሀንድ አክተሮች በቀይ ምንጣፍ ሲያልፉ ቶምክሩዝ በነጠላ ጫማ ትኩስ ሬንጅ በለበሰ አስፋልት ላይ እንዲያልፍ አደርገዋከሁ፤

ከዚያ አንድ አልባሌ ጋዜጠኛ እልክና “Who a fuck are you ? “ አንተ ደሞ የማን አባህ ነህ ? “ብሎ እንዲጠይቀው አደርግ ነበር፤


በዚህ ሳምንት ካንገብባቢ ሀገራዊ ጉዳዮች በላይ የሶሺያል ሚድያ አጀንዳ ሆኖ የነበረው የአስጌ ነገር ነው፤

አስጌ “በፍቅር ያበደች ሴት ካሳየኸኝ የማይሞት ሰው አሳይሀለሁ “ ይላል፤

ዠለስ! በፍቅር ያበደች ሴት አላጋጠመችህም ማለት የለችም ማለት እኮ አይደለም፤ አንተና እኔ ሴቶችን በፍቅር የሚያሳብድ ፊታውራሪ አልታደልንም ፤

በርግጥ የተናገርከው ሙሉ በሙሉ ሀሰት ነው ለማለት ይከብዳል፤

የዚህ ዘመን ብዙ ሴቶች ኑሮ ስላሳበዳቸው በፍቅር ሊያብዱ የሚችሉበት ሁኔታ አጠራጣሪ ነው፤ የተሰጣቸውን የእብደት እድል አንዴ ጨርሰው ተጠቅመውበታል፤

ወይዛዝርት ሆይ! የመልስ ምቴ ከተመቻችሁ በልዩ ጥቅም ባርኩኝ 🙂 ካናድድኳችሁ ደግሞ ምኝታቤቴ ድረስ መጥታችሁ እሰሩኝ!


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
19.05.202518:34
✨✨✨ባለ ጭንብሉ✨✨✨
✨✨✨ክፍል አስራ ሁለት✨✨✨

አዳም እና አብዲ አጠገብ ለአጠገብ ተቀምጠዋል፡ከነሱ ፊት ለፊት ፡ሲፈን ከነ እህቶቿ ተቀምጣለች ፡ኤዶም ከወዲያ ወዲ እያለ ለቆስተኛውን ያስተናግዳል፡ንፍሮ ያሲዛል፡ብሩክ የተባለው ጓደኛቸውም፡አብሮት ውሃ እየሰጠ፡ያግዘዋል፡ይህን የሚያደርጉት ፡ተረኛ ፡የሆኑ የእድሩ አባል ጋር ነው፡እነሱም ትብብራቸውን ወደውታል፡ይህ ኢትዮጲያዊ ስሜት ነው መጤ ያልሆነ ከማንም ያልተቀበልነው፡የፈለገ ብን ጎነታተል፡የፈለገ ፡ቅሬታ ቢኖረን፡በአዘን በችግር ጊዜ ፡ለማፅናናት የሚደረግ፡የአለውልህ፡ስሜት፡ነው ፡በቃ ፡የትም የማንሸሸው፡መቼም ፡የማንክደው፡የተሰራንበት፡የማንነታችን፡መለያ ነው፡አበሻዊ፡ስሜት፡ ደስ ይላል ከልብ ካዳመጥነው፡ የኔነው ብለን፡ከያዝነው፡ከሌሎች ጋር የምናወዳድረው ጉዳይ አደለም፡ እኛ ፡በራሳችን ፡ማንነት ውስጥ ፡ይዘን የመጣነው፡ወግና ስርሃት፡ያለን እዝቦችነን፡ በቃ እኛ ለኛ ......
"አብዲ እእ ፖሊሶቹ ምን አሉ ?"አለ አዳም
"ያው ሊጠየቅ የሚችል ጥያቄ ነው ፡ከዚ በፊት ፀበኛ ነበራቸው ወይ?እቤት ውስጥ አብዝቶ የሚመጣሰው አለወይ፡ ጠዋት ሲወጡ የተናገሩት ነገር ነበር ወይ በስራ የሚገናኙአቸውን ሰዎች፡ታውቃቸዋለህ ወይ........ምናምን!በቃ እንጃ እኔ ግን ያባቴን ገዳይ ካላወኩ አርፌ አልተኛም!"አለ አብዲ በቁጭት
"በርግጥ የተለመደ የፖሊስ ጥያቄ ነው ፡ግን እያንዳንዷ መረጃ ስለሚጠቅማቸው፡የምታስታውሰውን፡አብራቹ ያወራችሁት ነገር ካለ ፡ንገራቸው፡ !"አለ አዳም፡
"እሺ ታውቃለህ አይምሮዬ፡ ሊረጋጋልኝ አልቻለም፡ስለዚ፡ ማሰብ አለሸቻልኩም!"አለ አብዲ፡በዚመሃል ኤዶም መጥቶ "ንፍሮ ያዙ አዳም፡እእ አብዲ ያዙ እዚው ላስቀምጠው!?"አላቸው፡
"አይ እሱ ነገር ይቅርብኝ ፡ታውቅ የለ ሆዴን ፡ያናግረዋል !!"ብሎ አዳም ሳቅ አለ
"እእ ትንሽ በቃ ውሰደው ውሃ ብቻ አምጣልኝ "አለ አብዲ:፡ኤዶም ወንድሙ ሲስቅ ስላየው ደስ አለው፡
"እሺ አብዲሽ ፡ብሩክ ያመጣልሃል፡"አለ ኤዶም
"እኔ የምልህ፡እዛ ገር ከተቀመጡት ሴቶች መሃል የምታቃት አለች?ከትላንት ጀምሮ ነው፡እያየቺኝ ስትደነግጥ የነበረው ከአራት አንዱን ተመልከት፡የቷን ነው የምታቃት?!"አለ ኤዶም ወንድሙን ቀስብሎ እንዲያያቸው ምልክት እየሰጠ
"እህ፡ምን አስጨነቀ ደስ ብለሃት ይሆናል፡ማለቴ ብለሃቸው!"አለ አዳም ፈገግ ለማለት እየሞከረ
"አአይ እንደዛ አደለም፡የቺ ከአራቱ በጣም የምትቆነጀው፡ በፈጣሪ ሁሉም የየራሳቸው ቁንጅና አላቸው!"አለ ኤዶም
"ኧረ ኧረ ኪኪኪኪኪኪ!ወንድሜ ሴት ማድነቅ ጀመረ!" አለ አዳም እየሳቀ፡ኤዶም እንዲ፡አይነት ቃል ወጥቶት አያውቅም፡በጣም ፈሪ ነበር፡ለጥቂት ቀን ዞር ስልለት ጀግና ሆነልኝ፡አለ
"አይ እንግዲ ይሄ ማሽካካትህ ሊጀምርህ ነው ፡እኔ የጠየኩህን መልስልኝ እንጂ!ያቺን ልጅ በርግጠኝነት ታውቃታለህ ግን የት፡?!"
"አሃ ምን አስጨነቀ፡ደስ ካለህ ግባበት!ኪኪኪኪኪ"አለ አዳም
"አፈር ያስገባህ እሺ ደሞ መጣ፡አፉን ሊከፍት!"አለ ከልቡ ባልሆነ ስሜት
"ቆይ ቆይ የዚህን ያህል፡ካሳሰበህ፡እኔ እነግርሃለው ኤዶም፡ያቺልጅ ሲፈን ትባላለች፡የአባቴ ጓደኛ የአቶ ይፍሩ ልጅ ናት፡አጠገቧ ያሉት እህቶቿ ናቸው፡"አለው አብዲ ጣልቃ ገብቶ ፡የወንድማማቾቹ የውሸት ፀብ ከበፊትም ያዝናናዋል
"አዎ እንግዲ ወንድሜ አብዲ እንደነገረህ ነው፡ከአንዷ በስተቀር መርጠህ ግባ ማለቴ ይቅርታ ከሁለቱ በስተቀር ኪኪኪኪኪ!"አለ አዳም እየሳቀበት
"አንተ እኔ መቼ ስለሌላ ነገር አወራው፡ደሞ ሆኖስ ከሆነ ምንማለተሸ ነው ከሁለቱ በስተቀር!?"አለ ኤዶም በመገረም እያየው
"እእ እኔም አልገባኝም!ከምር ታውቃቸዋለህ እንዴ?"አለ አብዲ
"አይ አይ እንደዛ ማለቴ ሳይሆን ፡አንዳን፡ለራሴ አስቤአታለው ፡ማለት ቅድም ሲፈን ብለህ የጠራሃትን ሁለተኛዋ ደሞ፡ያው ልጅ ናት ያስታውቃል ቲን ኤጅ መሆኗ፡ለቅሶ እራሱ ለመድረስ ገናናት፡እእ ከሁለቱ መምረጥ ትችላለህ በቃ፡እስኪ የኔ ደፋር!"አለ አዳም
"እውነቱን ልንገርህ፡ ሲፈን ያልካትንልጅ ታውቃታለህ !"
"ኧረ አብዲ ውሃ ይፈልጋል !"አለ አዳም፡ወንድሙ ሲወጥረው ቆጣ ብሎ፡ኤዶም ደረቅ ብሎት ሄደ፡
አብዲ የሚሰናበቱትን ሰዎች ጎንበስ እያለ ያሰናብታል፡ በዚ መሃል አቶ ይርጋ መጡ፡እና አብዲን "በል አብዲ መፅናናቱን ይስጣቹ ፡መቼም፡ከሞት አይቀር ለኛም ትልቅ ጓደኛችንን ነው ያጣነው፡ተፅናና!"አሉት፡አብዲ እናቱ የተናገሩትን አስታውሶ ፡በጥርጣሬ አያቸው፡ያን ያክል ያዘኑም ፡መስሎ አልታየውም፡እስቸውን ተከትለው አቶ ይፍሩ መጡ፡ሲፈሩ ሲቸሩ ፡ቀረብ አሉት ፡አዳምም እንዳያተኩርባቸው ፀለዩ፡ አዳም ቀጥታ የሚያየው፡ወደሲፈን ነበር፡ዋው፡በጣም ልዩ ናት፡ለትንሽ ደቂቃ ባወራት ደስ ይለኝ ነበር፡ግን ለምን አይሆንም፡ባወራትስ ፡ምንችግር፡አለ፡ብሎ ከራሱ ጋር ተማከረ፡፡ድንገት አንድ የሚከብድ ወፈር ያለ ድምፅ ሲሰማ እንደመድንገጥ አለ፡የትነው ይህን ድምፅ የማውቀው፡ብሎ አብዲን ከሚያፅናኑት፡ሰው ላይ አይኖቹ አረፉ፡እንዴ፡አውቃቸዋለው፡ግን የት፡በጣም አተኮረ፡እሳቸው፡ከአይኖቹ ሊሸሹ ሞከሩ፡በዚ መሃል፡ሲፈን፡መጥታ ትኩረቱን፡ወደራሷ ፡ወሰደችው
"ይቅርታ አዳም፡አንዴ ላውራህ?"ደስ በሚል፡ለስለስ ባለ ድምፅ
"እእ እሺ ፡ቁጭ በይ!"አለ እነደመነሳት እያለ ሊያስቀምጣት
"አይ ወጣ ማለት እንችላለን!"አለች ሲፈን፡
"እሺ "ብሎ ተነስቶ ተከተላት፡እናም ከድንኳኑ ወጥተው እራቅብለው ቆም አሉ ፡አዳም፡በሆዱ ምንድነው፡ይሄ ሁሉ ፡ሲፈን፡የነገረችኝ፡ታሪክ የምር ነው፡ማለት ነው፡እንግዲያው፡ለምን፡ያን ሁሉ ነገረ ያደረገኝ አባቷ፡ይፍሩ ከሆነ ለምን፡ሲያየኝ አልገረመውም፡ከትላንት ጀምሮ አይቶኛል፡ግን አንዳችም፡የስሜት ለውጥ፡ባቶ ይፍሩ ላይ አላየውም፡እንዴት፡ነው፡ነገሩ፡እኔ እራሱ በምን፡እና እንዴት፡አድርጌ ነው፡የአብዲ አባት ጓደኛ ቤት ድረስ በመሄድ፡ያን ሁሉ ታምር፡የፈጠርኩት፡የተፈጠረብኝ!፡አልገባኝም የሲፈን ሚስጢር፡ምንድነው?
"አቤት ሲሲፈን ስለምን ድነው?"
"አዳም፡እኔ ነገሮች ሁሉ አሁንም ድረስ እየተምታቱብኝ ነው፡አንተ በየትእንዴት አድርገህ እኛቤት እንደመጣህ ሳስበው፡ባጋጣሚ ነው ብዬ ለማሰብ፡ይከብደኛል፡!"
"እና ምነሸ እንዴት ሆነ ልትይ ነው!"አለ ግራ በመጋባት
"እንጃ ትውስታህ ሙሉ በመሉ ቢመለስ፡ጥሩ ነበር፡ሁሉንም ነገር መፍታት ይቻላል፡ሆኖም ግን፡አሁንም፡የነገሮች ሂደት ለኔ እንደሚያመላክቱት፡አንተና አብዲ ትተዋወቃላቹህ፡ስለዚ አንተ እኛቤት ስለመምጣትህ አብዲ ሊያውቅ ይችላል፡እላለው!"
"እእ አብዲ ኧረ እንዴት እያወቀ እንዲ ሊረጋጋ ይችላል አይ አይመስለኝም፡ሲቀጥል ደሞ እኔ አንቺ ስለነገርሺኝ፡ታሪኬ ገና ለማመን፡አልበቃውም፡"አለ አዳም ፡
"እኔ አንዳችም ውሸት አለሸነገርኩህም፡ድንኳን አባባ ሲያወራ በትኩረት ስትከታተለው ነበር፡የሆነ ነገር እንደተሰማህ ገምቼ ነበር እንውጣ ያልኩህ፡!"
"እንጃ ድምፃቸውነሸ ከዚ በፊት የሰማው ስለመሰለኝ ነው፡ ግንአንቺ በነገርሺኝ መልኩ እንዳይሆን እፀልያለው!"አለ አዳም፡፡ሲፈን ከዛ በዋላ መናገር አልፈለገችም፡አዳም፡እንዳይጎዳ መጠበቅ ፈልጋለች፡ግን እንዴት፡አባቷን ከመቼውም ይበልጥ ፈርታቸዋለች፡መፍራት ብቻ አደለም መጠረጠርም ጀምራለች፡አንድን ሰባዊ ፍጡር አስረው አሰቃይተው፡እስከመግደል የሚያበቃ ድብደባ ፡እንዳደረሱ ከየች በዋላ ለአባቷ ያላት ክብር ውርድ ብሎባታል፡እና ስለዚ፡አዳምን፡ከአባቷ፡መጠበቅ ፈለሸጋለች፡
"አዳም፡ሁሉም ይቅር፡በቃ ስታስታውስ ታስታውሳለህ፡ነገርግን፡አብሬህ፡ልሁን ማማለቴ፡ቶሎቶሎ እንገናኝ ምን አልባት ለሁለታችንም ጥሩ ይሆንልናል እእ!?"አለችው ሲፈን በልምምጥ

🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,
30.04.202516:31
ታክሲ ውስጥ ነኝ ጠዋት ነው

ከጎኗ ነኝ ድንገት የሆነ ነገር ክፍት አለ
ስዞር እያዛጋች ነው ......በነፃነት ነው እስከ መጨረሻ የከፈተቺው እጇን አፏ ላይ ጭና ማዛጋት አልፈለገችም ....

በርግጥ እንዳከፋፈቷ ምኗንም ብትጭንበት የምትሸፍነው አይመስለኝም

ገልመጥ አድርጊያት ዞርኩ ....

አራት ደቂቃ አልሆነኝም

ደግማ አዛጋች ይሄኛው ድምፅ አለው....
ልትበላኝ ነው እንዴ የሚያስብል ማዛጋት ነው

"ቡና ነው ?
ቁርስ ነው ?
እንቅልፍ ነው ወይ?" አልኳት ?

ዝም አለቺኝ

እጇን አፏ ላይ ለማድረግ የደከማት ልጅ ምን ብላ ከኔ ጋ ወግ ትገጥማለች እያልኩ በልቤ

ሌላ ወሬ ልወረውር ወደሷ ስዞር

እሷ ወደ እኔ ዞራ ስታዛጋ ተገጣጠምን ....

ግማሽ ፊቴ አፏ ውስጥ የገባ አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ

ጨንቅላቴን ወዷሃላ ስቤ ረዳት ረዳት

ወራጅ ወራጅ ወራጅ ...አልኩ

ይሄው
ቀኑን ሙሉ ላንቃዋ ጎሮሮዋ መንጋጋዋ እንጥሏ አይኔ ላይ ዋለ😃
@adhanom Mitiku

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
03.05.202505:16
እንደምትወዳት ንገራት,

(በእውቀቱ ስዩም)
ሕይወት የብድር በሬ፥መቼ ሁሌ ይጠመዳል
ለጊዜው ብቻ የመጣ፥ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፥ ደሞ ካንተ ይወሰዳል::

ቀለበት፥ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ ሁልጊዜ የሉም
-ቀናት ሳምንታት ወራት
ዛሬውኑ ፥አሁኑኑ፥ እንደምትወዳት ንገራት::

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያጸድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፥ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ ፥እንደምትወዳት ንገራት፤

ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደማትቀባው አመድ
ወደማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንትም አንደበት ሳለህ፥ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
13.05.202518:30
✨✨✨ባለ ጭንብሉ✨✨✨
✨✨✨ክፍል ሁለት✨✨✨

እየቀረባት ሲመጣ የልብ ምቱም አብሮጨመረ ፡እጆቹን በቀስታ ወደ ተራቆተው ጡቷ ሰደድ አደረገው መልሶ በፍጥነት እሳት እንደነካ አይነት ሰበሰበው እንደገና በፊቷ ላይ የተነሰነሰውን ፀጉር ወደጎን ወደጎን እያደረገ አስተካከለው ፡ይህን ሲያደርግ ውበቷ የበለጠ ቁልጭ ብሎ ታየው ፡ከንፈሮቿን መሳም ፈለገ እናም ቀረብ አላት ፡ሲፈን በሆነ ታምር ያወቀች ይመስል ተገላበጠች ፡ባለጭንብሉ በድንጋጤ ወደዋላው አፈገፈገ ፡እንቅስቃሴው ፡የረበሻት ይመስል ፡ከእንቅልፏ ተቀሰቀሰች ፡አይኖቿ ተከፈቱ ፡ፊትለፊት ባለ ጭንብሉን ከለላሲፈልግ አየችው፡ሲፈን ከመቅስበት አልጋው ላይ ያለውን አንሶላ ወደራሷ በመሰብሰብ ቁጭ አለች ፡ሰውነቷ በድንጋጤ ደረቀ፡ባለጭንብሉ ፡ቀጥሎ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ስለገባው ፡እራሱን አረጋጋ ፡ቀረብ አላትና ፡ልትጮህ ያሰናዳችውን አፋን በሰፊ መዳፉ በማፈን ፀጥ አደረጋት "ስሚ አንዳች እረብሻ አስነሳለው ብትዪ ሁሉንም ቤተሰብ ችግር ውስጥ ነው የምትከቺው !ገባሽ! ተመልከች እዚች ሽጉጥ ውስጥ አምስት ቀልሃ አለ ለአምስቱ ቤተሰቦችሽ በቂ ነው፡ዝም ብትዪ ላንቺ ነው የሚጠቅመው!!!"አላት በጭንብሉ ቀዳዳ የፈጠጡ አይኖቿ ውስጥ እየተመለከታት፡ሰውነቷን ብርድ ብርድ አላት መንቀጥቀጥ ጀመረች፡'ማነው !ይህ ሰው ምን ፈልጎነው?እህቶቼ ደና ይሆኑ ?እማሚ እና አባቢስ ?ውሾቹ እንዴት ከስገቡት ?ዘበኛውስ ? በሩስ እንዴት ተከፈተለት?በምን በየት በኩል...?!!'የጭንቀት ጥያቄዎች በተራበተራ አይምሮዋ ውስጥ ተመላለሱ፡ፍርሃቷ ወደር አጣ፡ባለጭንብሉን አፋን እንዳፈናት አልጋዋላይ ፈርከክ ብሎ ዝም እንድትል ሲያስጠነቅቃት እያየችው ነው ጥቁሩ የሹራብ ጭንብል ይበልጥ አስፈራራት ፡ትዝ አላት ፊልም ላይ ያየቻቸው የመደፈር አደጋዎች፡በርቀት ትሰማቸው የነበረ የሴቶች ጥቃት ፡እያንዳንዱ ፡ሲታወሷት፡ዛሬ በሷላይ ፡ለዛውም በገዛ አልጋዋላይ ፡ምን አይነት የቀን ጎዶሎ ነው እዚ ሴጣን ላይ የጣለኝ አለች ስቅቅ ብል፡፡ባለጭንብሉ ዝም እንዳለች ለመፈተሽ ይመስል ቀስ ብሎ ለቀቅ ፡ሲያደርጋት ፡በተከፈቱት እግሮቹ መሃል ጉልበቷን በማስገባት፡እንትኑን ክፉኛ አገኘችው፡እንደማቃሰት ብሎ ለቋት ወደዋላው በመሸሽ ፡አጉተመተመ ፡ለጥቂት ሰከንድ፡ አፉን ከፍቶ ተሰቃየ ፡ሲፈን እንደምንም እራሷን አበርትታ ከክፍሏ ለመውጣተሸ ወደበሩ ተንቀሳቀሰች ፡ባለጭንብሉ "ቁሚ የማትረቢ ጨዋታውን አበላሸሺው እንቀሳቀሳለው ብትዪ እተኩሳለው !ተመለሽ አፍሽን ዝጊና ከነበርሽበት ተመለሽ!!"አለ ሽጉጡን ደቅኖ ፡ሲፈን ወደነበረችበት ተመለሰች፡ይበልጥ እየተንቀጠቀጠች፡ለመነች ፡ባለጭንብሉ ፡የለበሰውን ካፖርት አወለቀው ካወለቀው በዋላ ኪሱ ውስጥ በመግባት ብላስተር አወጣ ብላስተሩን በመፍታት ባጭሩ ቆረጠው፡
"እባክህን ምንድነው የምትፈልገው ፡አንተማነህ ተው እኔ ምንም አልጮህም ተወው ፕላስተሩን.."አለች ሲፈን በልመና
"አሃ ካንቺጋር የምስማማበት ምንም ምክንያት የለም ፡የምፈልገውን ላንቺ መንገርም አይጠበቅብኝም !!"አለ በቁጣ እናም የሱሪውን ዚፕ ፈታው ሱሪውን ወደታች ዝቅ በማድረግ ወደሲፈን በመጠጋት"ማንን እንዳስቆጣሽ አየሽ! ተመልከች !ተመልከች! ይህ እራስሽ የፈጠርሺው ግርግር ነው እና ስለዚ እራስሽ ታስተካክይዋለሽ!እይው እይው!"አለ ባለ ጭንብሉ በማስገደድ ፡ሲፈን ፡አለቀሰች ፡እንደመሸሽ እየለች ከአልጋው ኮርነር ተጣበቀች ፡ባለጭንብሉ እይ ምን እነደሰራሽ እያለ ተከተላት ፡አናም እግሯቿን ጎትቶ በመክፈት ወደራሱ አስጠጋት፡ፊቷን በተሸፋፈነው ፊቱ መተሻሸት ጀመረ ለማን ለምን ነካሽብኝ እንደዛ ማድረግ አነበረብሽም አለደጋግሞ ቁረጥ ቁርጥ በማል ድምፅ ፡ሲፈን ከእግሮቿ መሃል የገባውን ሰውነቱን ለመሸሽ ተንፈራፈረች እጆቿን ለመከላከል ወደፊቷ የቀረበውን ጨንቅላቱን ለማራቅ ስትጠቀምባቸው ድንገት ጨንብሉን ከፊቱ ላይ አወለቀችው፡ባለጭንብሉ ካሰበው ቅጣት ሳይደርስ በድንጋጤ ፡ተስፈንጥሮ ተነሳ ፡ሲፈን እግሮቿን በፍጥነት ሰብስባ ፡የባለ ጭንብሉን የተጋለፀ ፊት ላይ አፈጠጠች፡እሱም እንደዛው፡ በጣም ተናደደ ፡ፊቱን ስላየችው፡ እንደሚገድላት ዛተ በቃ፡በዝች የማትረባ ከምጋለፀ ፀጥ አድር ጌያት፡ ወደዋናው አላማይ መጓዝ አለብኝ ፡ብሎ ሽጉጡን በማንሳት፡ፊት ለፊቷ አቀባበለባት፡ሲፈን አለቀሰች መጮህ አማራት፡መልሳ እህቶቿን እንደምታጣ እንዲሁም ወላጆቿን የነገራትን አስታውሳ ድምፀጿን ቀንሳ እያለቀሰች ተማፀነችው፡
"እባክህ አትግደለኝ እባክህ የምትፈልገውን ሁሉ ውሰድ እኔ እረዳሃለው እባክህ!!"
"አይ ፊቴን ማየት አልነበረብሽም ፡ብተውሽ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም፡አንቺ በሕይወት እድትኖሪ መፍቀድ በራሴላይ ታናዳፊ እባብ የመጠምጠም ያህል አደጋ አለው !ይቅርታ አድርጊልኝ! "አለና ትራስ ይዞ ተጠጋት የመሳሪያውን ድምፅ ለማፈን እንዲ ጠቅመው ፡ሲፈን እንደ እፃን ልጅ እጇን ዘረጋች "በናትህ እኔ መሞት አልፈልግም እህት የለህም ..በበናት ትህ እእእእ መሞት አአአልፈ ፈልግምም እእእእ እፈራለው መሞ ት እእእእ በፈጣሪ ይ"ቁጭ ብድግ እያለች ለመነች ፡የባለጭንብሉን ቆንጆ እና ጠይም ምንም ወንጀለኛ የማይመስል ፊት፡ እያየች፡ "አይ ነገረኩሽ ባታይኝ ጥሩ ነበር ፡"ብሎ በመጠጋት ትራሱን ወደፊቷ አቅጣጫ አደረገው፡
ምትለው ግራ ገባት በሕይወት ለመትረፍ፡ምን አይነት የመለመኛ ቃላት እንደምትጠቀም ጠፋት ከሞት ጋር ፊት ለፊት ተጋፍጣ ተንዘፈዘፈች፡ በዛ በለሊት፡ ምን አይነት ሴጣን ነው፡ እሷን ብቻ መርጦ ሕይወቷን ሊነጥቃት የመጣው፡ ካሁኑ ቤተሰቦቿ ናፈቋት የእንስፍስፍ እናቷ ፍቅር የአባቷ ኮራ ያለ ትእዛዝ የእህቶቿ ውበት ከነሳቃቸው ከነጨዋታቸው እንባዋ የባስ ዱብ ዱብ አለ
"ወንድሜ እባክህ እኔ እኔ.......እእእእ
ከደጅ የእግር ኮቴ ተሰማ ባለጭንብሉ ትራሱን አልጋው ላይ ወርውሮ ወደበሩ በመሄድ በሩን ከውስጥ ቀስብሎ ዘጋው ፡እናም ኮቴው እየቀረበ መጣ " እናም ከሲፈን አጠገብ ያለው በር ሲጢጢ ብሎ ተከፈተ ትነሽ ቆይቶ ተመልሶ የመዘጋት ድምፅ አሰማ ቀጥሎ ሌላኛው ክፍል ተከፈተ መልሶም ተዘጋ ፡ቀጥሎ የሲፈን ክፍል ተገፋ ባለጭንብሉ መውጫ ቀዳዳ አማተረ ምንም መደበቂያ አጣ ፡ኮስተር ብሎ ወደሲፈን በማየት አስጠነቀቃት ጠጋብሎም"አፍሽን ብትከፍቺ እንጨራረሳለን !"አላተ ቀስ ብሎ "እማዬ ናት ሁሌም ለሊት ላይ ለሽንት ስትነሳ ታየናለች ለዛ ነው በር የማንዘጋው፡የኔበር ሲዘጋ አዲስ ስለሚሆንባት መረበሿ አይቀርም"
"እና ምን ይሁን ነው የምትይው?!"
"ቀስ ብለህ ክፍት አድርገውና ጥግ ላይ ተደበቅ!"
እሺ ብሎ ሊከፍት ሲጠጋ በሩ መንኳኳት ጀመረ ለስለስብሎ ኳኳኳኳኳ ቀጠለ የሮዛ እናት ፡የሲፈን በልተለመደሁኔታ በር መዝጋት ደስ አላሰኛቸውሙ ከሮዛ ጀምረው ሁሌም እንደሚያደርጉት ልጆቻቸውን በተራ ተራ አይተው ብርድልብሱን ለበስ አድርገው ነው ወደቀረቻቸው ሲፈን የመጡት በሯ ተዘግቷል እንዴት............?ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳጨመረማንኳኳቱ ኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳኳ

🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,

✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19
21.05.202519:41
✨✨✨ባለ ጭንብሉ✨✨✨
✨✨✨ክፍል አስራ አራት✨✨✨

ሲፈን ቤቷ ገብታ ፡ከመቀመጧ ስልኳ ጮኽ፡አነሳችው፡አዳም ነበረ፡ምን ፈልጎነው፡ደሞ አለች አሳቡን ከመስማቷ በፊት፡ንጭንጭ እያረጋት፡"ሄሎ?!"
"አዳም ነኝ"
"አውቃለው መናገር አይጠበቅብህም!"
"እሺ ድምፅሽ ግን ይስተካከልልኝ፡ትንሽ ውበት ስጪው!"
"ለማን ለምን ብዬ?!"
"እንዴ ስቀልድሽ ነው፡ምነው ተቆጣሽ ችግር አለ?"
"ቀልድ አላማረኝም ለጊዜው፡"
"እሺ ወንድሜ እንዴት ነበር ተመቸሽ?"አለ አዳም
"አቤት !ምን ለማለት ፈልገህ ነው!?"ሲፈን ንድድ አላት
"ኧረባክሽ ምርር ምርር አትበይ! ያው ሊሸኝሽ ስለወጣ ፡ ብዬነው፡ "
"አመሰግናለው ፡ስለምቾቴ ስላሰብክ ፡ግን ይሄን ለመጠየቅ ነው የደወልከው፡?"ሲፈን በንዴት መንፈስ ጠየቀች
"አይ እኔ እንኳ እንደ ጨዋታ መግቢያ አደረኩት እንጂ ፡ስለአባትሽ ፡ማለት ቅድም ስለነገርሺኝ፡ነገረ ግልፅ እንድታደርጊልኝ ነበር፡"አለ አዳም፡
"ኦኬ የአባቴ ጉዳይ ላንተ እንደጫወታ መቆጠሩ ነው! በጣም ልታስገርመኝ ነው ፡የሌባ አይነደረቅ ሆንክብኝ፡እኮ፡"አለች ሲፈን ተቆጥታ
"ይሄ ሌባ ምናምን የምትይውን ነገር ተይው!"
"ኧረ ልተወው ግን እውነታው እሱ ነዋ፡እኔም የማውቅህ ጭምር!አሁን ይኽውልህ፡እራስህን እንድትጠብቅ ነግሬሃለው፡በአባቴ ጀርባ ሆኜ ለማይገባው ሰው፡እርዳታ እያደረኩ መሆኔ ቢሰማኝም፡ነገርግን፡በሌላ መልኩ፡እንዳንተ አይነቱን፡ደነዝ፡አንድ ነገር አድርጎ ወንጀለኛ፡ቢሆን ፡ዞሮዞሮ ተጎጂ ነኝ፡ስለዚ፡ከአባቴ እይታ እራቅ፡በቃ!!"አለች ሲፈን ኮስተር ብላ
"ሄሄ አትሳደቢ ደሞ ያሙሰኛ አባትሽ፡በሕዝብ ገንዘብ ነው እየተንደላቀቀ የሚያንደላቅቅሽ፡ሰማሽ፡እያንዳንዷ ንብረቱላይ ፡ዕምባ አለበት፡እራስሽን እንደ የጨዋልጅ አትቁጠሪ!"
"ሀሀ!ሀሀ እሺ የኛ ዕምባ ጠባቂ ፡በለሊት የመጣኽው ከአባቴ ወስደህ የንብረት ክፍፍል ልታደርግ ነበር !!እሺ እኔንስ ?አንተ እመን ባለጌ ነህ በቃ፡አየ እኔ ነኝ የማይገባህን ቦታ የሰጠውህ፡ ነገሮች ሁሉ የሆኑት በጊዜያው ምኞት በመነሳሳት ይሆናል ብዬ፡ነበር፡አንተ ግን አስበህና አቅደህ ነው ያደረከው፡እና ከአሁን በዋላ ይህንን ስልክ እርሳው፡ወንድምህን ሰላም በልልኝ፡ገደል ግባ!!"ብላ ሲፈን ስልኩን ጆሮውላይ ዘጋችው፡እና ሶፋው ላይ ውርውር አረገችው፡ የማይረባ፡ወይኔ ሲፈን ይሄልጅ፡በዚው ከቀጠለ ያሳብደኛል፡ከሱ መራቅ አለብኝ፡እባክህን፡ልቤ ተወኝ ተወኝ ......
,,,,,,,ባለጭንብሉ,,,,,
አብዲ በቁጣ እንደጦፈ አዳምን፡ያዳምጠዋል፡ወሬውን ሲጨርስ፡ዘሎ ሊከመርበትም ያሰበ ይመስላል ፡ይቁነጠነጣል፡አዳም፡አብዲን፡ለማስረዳት፡መከራውን አየ ቀላቶች ሁሉ አልበቃ አሉት ፡ጓደኛውን በፍፁም ማጣት አልፈለገም፡ለአብዲ ለማሳመን፡እንባ ቀረሽ፡ነው የሆነው፡አብዲ የአቶ ይርጋ፡ወሬ ፡አይምሮው ውስጥ እየተመላለሰ የቱን ማመን እንዳለበት፡ግራ አጋባው፡እሳቸው የነገሩት፡እውነት የሚመስል፡ነገር ይበዛዋል፡አዳም ደሞ ሌላ እውነታ ይዞ መጥቷል፡ከማናቸው፡ይሁን ..."አብዲ እመነኝ ጓደኛዬ በርግጥ የመጀመሪያ መነሻ የሆነኝ አሳብ ካንተጋር ስናወራ፡ስለ አቶይፍሩ አብት ሁኔታ፡በጣም ነበር፡የምናደድ የነበረው እና አይገባቸውም ብዬም አስብ ነበር፡ግን በዚመልኩ ለዘረፋ እነሳለው የሚልም አሳብ አልነበረኝም፡ይህ ነገር የመጣልኝ፡ታዲዮስ አንድ ሽጉጥ፡የተገኘነው፡ከጓደኞቼ፡እና እስከሚሸጥ ድረስ ደብቅልኝ ብሎ ሲያመጣው፡በቃ እኔም፡ታውቃለህ፡ተመርቄ፡ስራ ባፈላልግ፡አጥቼ ቁጭ ያልኩ ሰው ነኝ፡ብዙ ነገር መሞከሬንም ታውቃለህ፡ያው እንደምታየው ጡረተኛ ነኝ፡እና ሳስበው፡ለኛ ስራ ፈትነት ምክንያት፡እንደ አቶ ይፍሩ ያሉ ሰዎች፡ናቸው፡ስለዚ እሳቸው ጋር ያለ ንብረት ለኔም፡ይገባኛል ብዬ አጥራቸው፡ደፈርኩ ግን ባጋጣሚ አልተሳካልኝም ይቅርታ መነሻዬ ያንተ አሳብ በመሆኑ፡"አለ አዳም፡እየተለማመጠ
"አይ አይ፡ስትልከሰከስ ነው የተያዝከው፡ሲፈን ላይ አንተ ....ይዘገንናል!"
"አደለም !አደለም!ውሸት ነው ሲፈንን ምንም አላደረኳትም፡በርግጥ ሞክሬ አለው፡ግን ዝም እንድትል፡ለማስፈራራት እንጂ፡ለሌላአልነበረም፡ያ ይርጋ የምትለው ሰው ምን እንደሚፈልግ ባላውቅም፡ግን ውሸት ነው የነገረ፡በጣም ብዙ ውሸት፡እመነኝ ጓደኛዬ እንደውም እሱን ሰውዬ መጠርጠር ጀምሬ አለው፡እባክህ፡ተረጋግተን እናስብና፡የአባት ገዳይ፡ላይ፡ተረዳድተን፡እንድረስበት!"አለ አዳም
"አትዋሸኝ አዳም፡ጓደኛዬ ነበርክ የማምን ሰው፡ነበርክ፡ !"አለ አብዲ ቀጭ ብሎ፡ጭንቅላቱን እያወዛወዘ ከቅድሙ ግን ተረጋግቷል፡
"አብዲ አሁንም ጓደኛዬ ነህ ሁሌም፡ችግር ነው የማይደፈረውን እንድዳፈር ያረገኝ፡እመነኝ ጓደኛዬ ከማንም ጋር አልተባበርኩም፡ ፅግዬ ትሙት፡እናቴን ያሳጣኝ፡በጭራሽ፡ለአባትህ ሞት ከማንም ጋር አልተባበርኩም፡በጭራሽ ያሁሉ ድብደባ እንኳ ሲወርድብኝ፡እነሱን ከመሳደብ ውጪ የማንንም ስም አልጠራውም እመነኝ!!!"አለ አዳም በጭንቀት ጓደኛውን እየተለማመጠ፡አብዲ በመጨረሻ ለስለስ እያለ መጣ፡ከዛም ማውራት ጀመሩ ማነው አባቴላይ እጁን ያነሳው፡ለምን ፖሊሶቹስ፡አንድ ነገር ላይ አይደርሱም ፡ለምን .....
,,,,,,,ባለ ጭንብሉ,,,,,,
"ኤዶ ምነው ፍዝዝ አልክብኝ አለሜ?!"አሎ እትዬ ፅጌ
"እ እእ አይ እኔ እሙ አረሰላም ነኝ የሆነ ነገር እያሰብኩ ነበር፡!"አለ ኤዶም
"ስለምን አለሜ ፡ምነው ስራ ቦታ ነው።ያልተስማማህ ነገር አለ?"
"ኧረ እማ አትጨነቂ ሰው እኮ ማሰብ አለበት ለተወሰነ ሰሃት፡አልያ ከእንስሳ በምን ይለያል፡ሲያስብ ነው ነገሮችን መቀየር የሚችለው !"አለ ኤዶም ከእናቱ ጥያቄ ለማምለጥ
"አይ ከዚ በፊት እንዲ ሆነህ አይቼ አላውቅም ለዛ ነው!"አሉ ፅጌ
"አሃ እስኪ ተይው ፅግዬ መልሱን ሰጠሽ አደል፡ምን እንዳይሆን ነው፡ያስብ እኛም አስበን ነው ከዚ የደረስነው፡የሚያስቡ ልጆችም ያመጣነው ሀሀሀሀ አስብ ልጄ ተዋት እሷን መጨነቅ ነው ስራዋ!"አሉ አቶ አይሉ ጣልቃ ገብተው፡በዚ መሃል አዳም ገባ ፡ትንሽ የቀማመሰ ይመስላል እንደ መንገዳገድ ብሎ፡ሶፋው ላይ ዘጭ አለ፡አባት ፡ገልመጥ አደረጉት፡ኤዶም፡"ሰላም አመሻቹ አይባልም ቢያንስ! ዝም ብለህ ትቀላቀላለህ?!"አለው
"እእ ሼ ሼባው ልትወጥሪኝ ነው፡እኔ አልኩ አላልኩ ማምሸትህ አይቀር፡!"አለ አዳም ኮልተፍ እያለ
"ችግር የለም አለሞቼ ዋናው በጊዜ መሰብሰባቹ ነው፡ግን አዳም ይሄን መጠጥ ተወው እባክህ፡!"
"ውይ እማ ሦስት ብቻ እኮነው ግን የኔ ነገር ያው አልችልም ለዛ ነው!"አለ አዳም ለመዋሸት እየሞከረ
"ሲነጋ እናወራለን ፡"አሉ አቶ አይል ኮስተር ብለው
ኤዶም ተነስቶ ሊወጣ ተዘጋጀ ፡እናት ወደኤዶም እያዩ"ወዴት ነው ኤዶ መሽቷል እኮ ፡ወንድምህ ሲገባ!.."አሉ
"ኧረ እማዬ ግቢውስጥ ነኝ የትም አልሄድም"
"ኧረ አንተ አይደብርህም ፡እኔን ስታይ መደንገጥ ጀምረሃል፡ችግር አለ ?!"አለ አዳም እንደመቆም እያለ
"የምን ችግር ምን ያስደነግጠኛል?!"አለ ኤዶም ፊት ለፊት እያየው
"ብቻ እኔ ያሰብኩት ነገር እንዳይሆንና እንዳንጨራረስ ፍራ፡ ዋ...."አለ አዳም ሲፈንን አስቦ
"ምንድነው የምታስበው"
"ነገርኩህ አዳታረገው !"
ሲፈን፡የኤዶም እናት ወይ አዳም ቢመጡስ የሚል ድንገተኛ ስሜት ተሰምቷት እንደመነሳት ብላ ተቀመጠች፡ኤዶም ፡አብሯት ቁጭ ለማለት ሞከረ፡ግን እመም ስለተሰማው አቃስቶ ተመልሶ ተኛ፡ሲፈን ስቅ አለች እጁን ያዝ አደረገችው፡በጭንቀት ፡ከወደበሩ የአዳም ድምፅ ተሰማ፡ ሲፈን ድንግጥ ብላ ዞረች፡አዳም አያት ተያዩ.......
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,

✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19
ልዩ ምሥክር ናት

እንደ ከዚህ ቀደም ፤ አብሳሪው መልአክ
ለሌሎች እንዳለው ፤ ከአርያም ሲላክ
ሠምቶሻል እግዚአብሔር ፤ የልብሽ መሻቱን
አላለም ለድንግል ፤ ሲጀምር ብሥራቱን ።

ምክንያቱም እሷ ፤
ለምና አታውቅም ፤ ሥለትም ተስላ
የፈጣሪ እናት ፤ እኔ ልሁን ብላ ።

ምክንያቱም እሷ ፤
እንደ ደናግላን ፤ ድንገት አሁን ካሁን 
ጠብቃ አታውቅም ፤ ለመውለድ መሲሁን ።

ምክንያቱም እሷ ፤
እንደነ ኤልሳቤጥ ፤ ወይም እንደ ሐና
ልጅ እንኳን ለማግኘት ፤ አታውቅም ተማፅና ።

ምክንያቱም እሷ ፤
መሆኑ አልገባት ፤ እንድትሆን እልፍኙ
ገና በልጅነት ፤ ያረጋት መናኙ ።

ምክንያቱም እሷ ፤
በልቧ ጸንሳው ፤ መኖርን ነው እንጂ
መባል አታስብም ፤ አምላክን ውለጂ ።

ምክንያቱም እሷ  ፤
ምረጠኝ ሳትለው ፤ ወዶ የመረጣት
አንዳችም ሳትሻ ፤ ሁሉ የተሰጣት
የእርሱ ድንቅ ሥራ ፤ ልዩ ምሥክር ናት ።

✍ አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
02.05.202512:51
ክፉ ቀን ነበር በመንገዴ የመጣችው ...ጠይም ናት ሰውነቷ የተሞናደለ ነው ...ስትጠራኝ አጠራሯ እሷ ጋ ብቻ የማቀው ቃና አለው ....

ማንም እሷ ወዳኝ እየተንከራተተች መሆኑን አያምንም እሷም ጭምር ...

ላግኝሽ ሰላት እየከተፈች ያለውን ሽንኩርት ትታ ትመጣለች ....

መሞናደሏ አይን ይይዛል ከፊት ያያት ከኋላ ለማየት ይዞራል ...ካልዞረ ሚስቱ ካጠገቡ ነች ማለት ነው

. .. ቤቴ ትመጣለች ስለጓደኛዋ ስለ አባቷ ፣እናቷ ሳታልፍ ስለመከረቻት ፣ስለሚሰማት ታወራልኛለች ... ክርክር ትገጥመኛለች አብራራለሁ እያብራራሁ እንደምትወጂው ንገሪው ንገሪው ልቧ ይላታል መሰለኝ .....ጉንጬን በስስት ትስመኛለች
.

ወክ እናደርጋለን በትንሽ ነገር ታኮርፋለች .... በዙርያዬ ያሉ ሴቶችን አትወዳቸውም አጠገቧ ሆኜ ሲደውሉልኝ ደስ አይላትም
.
ልታወራኝ ያለቺው ወሬ ይጠፋባታል ፊቷ ቅይር ይላል እስቃለሁ አንተ ሳቅ እያቃጠልከኝ ትላለች መቅናቷን አትደብቅም

እኔ በበቄ ቀንቼ አውቃለሁ? እላታለሁ ትስቃለች ...በኛ አያቴ በሚያክሉ ሰውዬ ልትቀና ትፈልግ ነበር ?

እኔ ሼባ ነው የምፈራው ወጣቱ እኮ ትቷል እላታለሁ ....ትስቅልኛለች ...

እናቷን እንዴት እንዳጣቻት የነገረቺኝ ቀን እንዴት እንዳዘንኩላት ??

ታውቅ ይሆን የነገረቺኝ ሁሉ ሆዴ ውስጥ ገብቶ እንዳባባኝ ? ..ግን የፃፍኩላትን ግጥም ለምን አላነበብኩላትም ?

ለመጀመርያ ግዜ በጣም የፈራሺው መቼ ነው አልኳት ?

ይመስለኛል ....ማደጌ የታወቀኝ እለት

እንደዚ ግብድዬ እንደሆንሽ የታወቀሽ ቀን ማለት ነው ?

ሂድ... አይደለም ...

በሳቅ ውስጥ ሃዘን ሳይ...እየሳሙኝ የአሳሳማቸውን ግለት ስለካ ....
እያደነቁኝ ድምፃቸውን እና አይናቸውን ፍላጎታቸውን ሲገባኝ ....

ያኔ ፈራው ....!

ትንሽ እያለሁ ....
ሰፈራችን ሽንኩርት፤ ቲማቲሚ ድንች ጉሊቱ ጋ የሚሸጡ እኔ ዝናብ አጉረመረመ ብዬ ስሮጥ ፀሃይ ነው ብዬ እየተማረርኩ ሳልፍ
እነሱን ዝናቡም ፀሃዩም ጉሊታቸውን ለምን እንደማያስለቅቃቸው ማየት ስችል

ማደግ የሚታየውን ሲገልጥልኝ ፍርሃት ነው የተሰማኝ ....

የሆነ ከትራፊክ ጋር አትቅጣኝ እያለ እሚለምን ሹፌር ሳይ ምን አለማመጠው እያልኩ ሳብራራ .... ልመናው የልጄን ምሳ አትቅጣኝ መሆኑ ሲገባኝ ....

ባላድግ እና ዝም ብዬ በትሽ በትልቁ በሳኩኝ አልኩኝ ....

አንተስ ?

እ እኔ ...እኔጃ መፍራት ሂወቴ ነው መቼ ለመጀመርያ ግዜ እንደፈራሁ አላስታውስም መሰለኝ "

እቤቴ ስትመጣ ቤቴ ይሞቃል ሄለን በርሄን ከፍታ እኩል እያንጎራጎረች ቤቱን እያፀዳች ብርሃን ታደርገዋለች... እኔ አልጋዬ ላይ ተጋድሜ መፅሃፍ አነባለሁ ....በየግዜው የሰበሰብኩትን ፌስታል በስታይል ታጣጥፋቸዋለች ....ወጥ ትሰራለች እንበላለን .....

እቤቷ ደውላ አንዶን ጓደኛ ሃኪም ቤት ገባች ወይ ሌላ ቀለል ያለ መዓት ነገራቸው እኔ ጋ ታድራለች ....

ሽጉጥ ብላብኝ ታድራለች ... ንጉስ ነህ ታሰማኛለች...አወዳደዷ መሞትን እንድፈራው ያደርገኛል .....

ድንገት ስነቃ በሀርማዶ ሄዳለች ...
ለምን እዛ ቤት አብረን እንድንኖር አልሞከርኩም.... ለምን ስትሄድ ሸኘኋት? ለምን ቆንጆ ልጆች አልፈለፈልንም ?

ለምን ጭዋ እንደሆንኩ በማስረጃ አላሳየኋትም? ለምን አበባ እየሰጠው ለምን ግጥም እየፃፍኩ ትዝታ ልቧ ላይ አላኖርኩም?

እኔ ትዝ እንደምትለኝ ትዝ እላት ይሆን?
እንጃ እኔ ምን አውቃለሁ ?

ማንስ ያውቃል? ' ከፍለጋ የያዙትን ማግኘት እንደሚከብድ' ..

©Adhanom Mitiku

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
05.05.202510:14
ዕለት ዕለት፤
ቀን እና ሌት፤

በሃሳቤና ግብሬ፤
በከንቱ ምግባሬ፤
ጌታዬን ቸንክሬ፤

በሚስማር ወጋሁት፤
ዳግመኛ ሰቀልኩት፤
በመስቀል አዋልኩት፤

ልክ እንደ ፃዲቅ ሰዉ፤
ራሴን ቆጥሬ፤
ሌላዉን ስኮንን ፤
ቃሉን ተዳፍሬ፤

ያደፈዉ መንፈሴን፤
በነጭ ነጠላ ፤
በአልባስ ሸሽጌ፤
ይምረኝ እንደሆን፤
እጠብቀዋለዉ፤
እርሱን......
ተስፋ አድርጌ፤


ዔደን ታደሰ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19
15.05.202517:54
✨✨✨ባለ ጭንብሉ✨✨✨
✨✨✨ክፍል አምስት✨✨✨

አቶ ይፍሩ ኮራ ብለው ከጓደኞቻቸው ጋር እየተገባበዙ ፡ከአንድ ግሮሰሪ ተቀምጠዋል፡ወሬያቸው ሁሉ ስለ ባለ ጭንብሉ ወጣት ነበር ሁለቱም ጓደኞቻቸው፡ከሳቸው ጋር በሚስጥር የተሳሰሩ ናቸው፡ነገርግን ለመጀመሪያ ጊዜ ፡በባለጭንብሉ ምክንያት፡አቶይፍሩ፡ጥርጣሬ ገብቷቸዋል፡'ማነው ከሁለት አንዱ የከዳኝ፡ወይስ ያልጅ ተራ ሌባ ነው! ግን እንዴት ሙሰኛ አጭበርባሪ፡ሊለኝ ቻለ፡ እያሉ በጨዋታቸው መሃል ፡ግራ በመጋባት፡ያይዋቸዋል፡ከግንባራቸው ይነበብ ይመስል፡አቶ ይርጋ ሜታ ቢራቸውን ጎንጨት ብለው"አና ይፍሩ ልጁን ከቤትህ አስረህ ማቆየትህ ተገቢ ነው!"አሉ
"አሃ ማንነቱን ሳታውቅ ልቀቀው ነው የምትለኝ?"አሉ ቆጣ ብለው አቶይፍሩ
"ማለቴ የዘንድሮ ልጆች ደረቆች ናቸው፡ለምን፡ጠንካራ መሆን እንዳለባቸው እንኳ ጠንቅቀው አያውቁትም ፡ዋላ ሰበብ እንዳይሆንብህ!"አሉ ይርጋ የጓደኛቸውን አይበገሬነት ቢያውቁትም፡እንደው ለማለት ያህል፡የሁለቱንም ንግግር ሲሰሙ ቆይተው፡አቶ የሱፍ የአይላንድ ውሃቸውን፡ጥጥት አደረጉና ፡"እንደኔ እንደኔ ይህ ልጅ ኩርኩም ብቻ ነበር የሚያስፈልገው እንደው ልምድም ያለው ሌባ አይመስለኝም፡እንደው ስራ አልሆን ሲለው፡አሳቡን ቀይሮ በዚ ካለፈልኝ ብሎ ይመስለኛል፡!" አሉ
"እሱ ግን አሁን እናንተ እንደምትሉት አይደለም ሁኔታው፡!"አሉ አቶይፍሩ ፡አሳስቧቸዋል፡ እንዴት አድርገው ነው የሚያውጣጡት በምን መልኩ ይህን ልጅ አንድ ነገር ቢያረጉት የላከው ሰው ኖሮ የበለጠ ጉዳዩ ቢከርስ፡ከየት ነው የመጣብኝ ?...
......ባለጭንብሉ......
ሲፈን ቤት ውስጥ ከናቷ ጋር ተቀምጣ ታወራለች፡ሰሞኑን ሁሉ ባለጭንብሉን ካየችበት ቀን ጀምሮ ተረብሻለች፡ያሊደፍራት የታገላትን፡ሁኔታ ሁሉ ላለማስታወስ ጥራለች ፡ከዛ የበለጠ ግን እያሳሰባት ያለው፡ አባቷ ልጁን በትክክል እንዳሉት ለቀውት ይሆን ወይ የሚለው ነው፡አባባ የዛን ያክል ተናዶ እንዴት ነው እንደተራ ነገር በቃ አንተ ባለጌ ወደቤትህ ሂድ፡እንደማለት አይነት የሚሸኙት፡ምንም አልተዋጠላትም፡ እናትም በዚ ጉዳይ እርግጠኛ አደሉም ግን ክፉ ነገር እሰከሚያደርሱበት ሳይሆን የሚገባውን ቅጣት ሰጥተው እንደሚለቁት ነው የተሰማቸው
"እማ ይመስልሻል፡አባባ እንዲ በቀላሉ የሚተወው ?
"የኔ ቆንጆ አባትሽን ክፉኛ መጠርጠርሽ ተገቢ አይደለም !ምን ያደርገዋል ብለሽ ነው፡እኔ አባትሽ ሲገባ አይቼዋለው ከመናደዱ በስተቀር የተለየ ነገር እንዳረገ ሰው አልነበረም፡ሲፈኔ ተይ፡በቃ እርሺ ስለዚ ነገር!"
"እማ አዎልጁ ችኩል ቢጤ ነበር እሱ አይካድም ፡ግን እስከሞት የሚያደርስ ቅጣት ይገባዋል፡ብሎ ውስጤ በፍፁም ሊነግረኝ አልቻለም፡እማዬ እኔ ጭንብሉን ሳወልቅበት ያየውት ፊት እንደው በድፍረት፡ተነሳስቶ እንጂ፡ልምድም ያለው አይመስለኝም!" አለች ሲፈን
"እንዴ አባትሽ ነብሰ ገዳይ መስሎ ታየሽ እንዴ!?ደሞ ሊደፍርሽ ለነበረ አንድ ዱርዬ የምን መራራት ነው ፡ምንድነው ነገርሽ ከዚ በፊት እንደሚያውቀው ሁሉ የምትሆኚው ምን አገባሽ!"የሮዛ እናት ቱግ አሉ
"እማዬ እኔ ስለማውቀው ስለማላውቀው አደለም፡ እሱ እንደ ደፋሪም አይደለም እኔነኝ በመታገሌ ለፀብ ያነሳሳውት !"አለች ሲፈን ግራ በገባው እኔታ
"እሰይ አሁን ገና ጉድ መጣ!አጥር ዘሎ ውሾች ገሎ ቤትሽ ድረስ ገብቶ በላይሽ ሊሰፍር የነበረው ለፍቅር ነበር እንዴ ሆሆሆ ምን እያልሽ ነው?"
"እማዬ እኔ በርግጥ ጥፋተኛ አይደለም እያልኩሽ አይደለም፡ልጁ ግን አጋጣሚ ሆኖ እነጂ ለኔ ብሎ አይደለም የመጣው ፡ለዘረፋ ነው በቃ!"
"እንግዲ ዘረፋው አንቺንም ያካተተ ነበር አፍኖ በርሽን ዘግቶት ነበር!"
"አዎ እማዬ አሁን ስለተፈጠረው ነገር አይደለም ፡ስለ ባለጭንብሉ ልጅ ነው በሕይወት ነው ወይ የተለቀቀው እሱን ማወቅ እፈልጋለው!"አለች ሲፈን ቁርጥ ባለ ቃል
"እሺ ይፍሩ ገድሎታል ነው አሳብሽ፡ምንድነው አንቺ ልጅ?!"ቆጣ ብለው
"እሱን አላልኩሽም፡ግን ትክክል የሆነ ነገር እየሸተተኝ አይደለም !"አለች ሲፈን ፊቷን ቅጭም አድርጋ
"እንግዲያው ይሄን ሽታ የፈጠረብሽ ያ በሽተኛ ልጅ ነውና እንፍ ብለሽ አስወግጂው፡አባትሽንም ያለ አግባብ መጠርጠርሽንም አቁሚ !"
"ምክንያት አለኝ !"
"ደሞ ምንድነው ምክንያትሽ ?"ተናደዱም ደነገጡም
"ክንዴ ከዛን ለት ጀምሮ በጭራሽ አላየውትም ፡ድንገት ስራውን ለቀቀ ተባለ ፡መቶ እንኳ አልተሰናበተንም ሲሄድም አላየነው ፡ወዲያው ወደማታ ሌላ ዘበኛ ተቀጠረ !እንደገና የዛን ለት ማታ ልብ አላልሽ እንደው እንጂ አባባ ልብሱ ደም ነበረበት እጁ እስካሁን ቆስሏል በመጠኑም ቢሆን እኔ ስገምት ልጁ አንዳች ነገር ሆኗል ክንዴ ደሞ ያውቃል ስለዚ የሱ እዚ መኖር አስፈላጊ አይደለም ለምን አይታይሽም እማ፡አባባ ልክ አይደለም ችግር ውስጥ ነው!!"አለች ሲፈን ውስጧያለውን እየተነፈሰች
"አንቺ ልጅ እንግዲያው ምንም ቢፈጠር አይመለከተንም፡ ማንም ሰው የሰው ቤት በውድቅት ሊት ሰብሮ ሲገባ የማባበል ግዴታም የለብንም ፡ይሄ ድፍረት ነው፡የተከበረ ቤት ነው መሪ ያለው ፡ይፍሩን የመሰለ አባወራ ያለው ምነካት ልጅቷ አጉል ሚዛናዊነትሽ አልተዋጠልኝም !"
"ኧረ እማዬ፡ይህ ልጅ እንደኛ ወላጅ ይኖረዋል
"ምን ዋጋ አለው ወላጅ ሁሉ ወላጅ ነው እንዴ ?
"እማ ከመቼጀምሮ ነው ጨካኝ የሆንሺው?"
ሮዛ፡ወደውስጥ ድንገት ገባች"እእ ማሚን ጨካኝ ሲፍ ማሚን?ይሄኔ ለፍራንክ ብለሽ እኮ ነው!?"አለቻት ሲፈን ደንገጥ ብላ ወሬዋን አቋረጠች፡ቀስ እያለም ቤቱ በቆነጃጂቶች ደመቀ አራቱም እህታማቾች እየተቀላለዱ ማሽካካት ጀመሩ ካካካካካካካኪኪኪኪሁሁሁሁሁሁሁሂሂሂሂሂ
....... ባለ ጭንብሉ.......
ክንዴ የመረረው ይመስላል ይህን ልጅ ሲጠብቅ ሳምንት አለፈው አቶ ይፍሩ ለማየት የቀፈፋቸው ይመስል፡ወደዚም ድርሽ አይሉ ብቻ አሳባቸውን በስልክ ማስተላለፍ ብቻ ትንሽ ምግብ ስጠው ውሃ ስጠው ጎሸም እያደረክ ማን እንደላከው አውጣጣው ፡እምቢ ካለ እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገህ ግረፈው 'እንዴ እኔ ደከመኝ አሁንስ እኔ እራሱ እየተደበደብኩ መሰለኝ ኧረ ክንዴ እሱ በዱላ ያደገ ይመስል ፡አይሰማው፡ደነዝ፡ ኧረ ሰለቸኝ !'ይላል ክንዴ እጁን እያሻሸ
"ስማ ጭንብሌ እኔ የምለው ሰው ነህ እንዴ?እንደው ምን አለበት ማን እንደላከህ ተናግረህ፡አቶ ይፍሩም ሌላ ተደብዳቢ ፡ቢያመጡ፡አንተም ከዚ በዋላ በዱላ ብዛት መልክህ ከሚጠፋ ባይጠፋ!እኔም ፡ሌላ ተደብዳቢ እስኪመጣ እረፍት እንድወስድ ብትረዳኝ፡ኧረባክህ ባክህ!!"አለ ክንዴ እንደማሾፍ እንደመናደድም ብሎ ወጣቱ ያባበጠ ፊቱ የሸፈነበትን አይኑን በስቃይ እያቁለጨለጨ "ማንም አላከኝም አልኩ እኮ እእ ግግን አአንተ ከጌታህ የየበለጠ መጥፎ ሰው ነህ የማይገባህ እራሴ ነኘ የየራሴ አዛዥ አልኩ እኮ አንተ ባባሪያ ለለፍርፋሪ ብብለህ ነነብሴን ልልታወጣኝ ነው ከከውሾቹ ጋጋር በበገደልኩህ ሰሰው መስለኽ......"ባለጭንብሉ ተናግሮ ሳይጨርስ ክንዴ ተነስቶ በፍጥነት አቶ ይፍሩ በመቱት ብረት አናቱ ላይ ሰነዘረበት !ባለጭንብሉ ከዱላው አይለኝነት የተነሳ ከመሬቱጋር ተጋጨ ፡አይኖቹ ብዥዥዥ .....ጭልምልም መሞቴ ነው እንዴ አለ በሰመመን ውስጥ እናቱ ወይዘሮ ፅጌ ታዩት ወፍራም ቀይ ፊታቸው ሲፀይም እማማ እማማ ይቅርታ እእእአባዬ አባዬ ይይይ ዳመና የጋረደው መሰለው ፀጥጥጥ ጥቁርቁር ........
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,

✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19
13.05.202518:00
✨✨✨ባለ ጭንብሉ✨✨✨
✨✨✨ክፍል አንድ✨✨✨

ፀጥታ በወረሰው በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ፡አንድ ሰው የሆነ ቦታ ለመድረስ ይጣደፋል ፡የሆነ አላማ ያለው ይመስላል ፡አንዳንዴ እንደ መደናቀፍ ይላል ፡ኮሮኮንቻማው የውስጥለውስጥ መንገድ በጣም አስቸግሮታል ፡ትህግስት የለሽ ቢጤ ነው ቶሎቶሎ ይናደዳል አጠገቡ ማንም ባይኖርም አልፎ አልፎ ይራገማል ፡ይሳደባል ፡እንዲ እንዲ እየተቻኮለ ተጉዞ ያን አስቀያሚ ጨለማ ሰፈር ጨርሶ ሲወጣ ድምፅ አውጥቶ"የማይረባ አገር ሁሉን ነገር ማጨለም ቲ!"አለ እናም ቀኝ እግሩን ከመሬቱጋር አጋጨው ፡"መብራት የለም፡ ውሃ የለም፡.....ችግር ቲ ፡አሁን እኛ ጠግበን ሳንበላ ጤፍ ጤፍ እንኳ በአቅሙ ለውጭ ይሸጣል ፡መብራት መብራት በስርሃት ሳናበራ ፡ለውጭ ይሸጣል ቲ! ኧረ ስንቱን ስንቱን ትሸጣለች..... !ነጋዴ አገር! ግን ያላተረፈች ! ቲሽ፡ ባዶ ባዶ ፡ሰርተህ ባዶ ፡ነግደህ ባዶ ፡ሰርቀህ ባዶ ....ኪኪኪኪኪ ...ነገሩ የሚሰረቀውን ሰው ጠንቅቆ ያለማወቅ እራሱ ባዶነት ነው ኪኪኪኪኪ....ስንት ሙሰኛ በተንጣለለ ጊቢ ውሻና ዘበኛ ሰብስቦ የሚኖረውን ትቶ እነማዘር በመከራ ያገኟትን ሳንቲም ከነቦርሳው መንትፎ መሮጥ መስረቅ ነው እንዴ ኪኪኪኪኪ .....ኧረረረ ከሰረቁ አይቀር እንደኛ የጀግና ተልእኮ ማካሄድ ነው ኪኪኪኪኪ!!" እያለ ለብቻው እየለፈለፈ እየሳቀ በብርሃን ወደ ተሞላው ግን ፀጥ እረጭ ካለው ፕሮግራሙ ውስጥ ከከተተው ሰፈር ደረሰ ፡ቆም ብሎም አካባቢውን በጥሞና ማስተዋል ጀመረ ፡እናም ሰሞኑን ጊዜ ወስዶ ሲያጠናው ወደሰነበተው ፡አንድ ትልቅ ነጭ በጥቁር የተቀባ ብረት በር ላይ አተኮረ "፡አንድ ዘበኛ፡ ሁለት ውሻ አንድ እማወራ ፡አንድ አባወራ ፡አራት ሴት ልጆች ፡ኪኪኪኪኪኪ..ይሄ ሌባ አባወራ ቲ አራት በሙሉ ሴት ይወልዳል የማይረባ ፡በደንብ አይሰራም ነበር ኪኪኪኪ ይሄኔ ሙስናውን ቢሆን በደንብ ይሰራው ነበር ፡ልክ የአንዱን ነብረት ለአንዱ እየሰጠ እንደሚያስተላልፈው ሁሉ ፡ሁለቱን ሴቶች ፡ከኛቤት አባወሮች ጋር ፡እኔን በመሰለ ጀግናና በዛ ጅል መንትያ ወንድሜ በቀየረ ነበር ኪኪኪኪኪ ..."እያለ ብቻውን ገለፈጠ ፡መልሶ አፉን እንደመያዝ አድርጎ እራሱ በራሱ ላይ አለመጠ ፡ለሱ ይሄ ጉዳይ ምንም አይነት መረበሽን ባያስከትልበትም ፡ፀጥታው ግን የሞት ያህል ያስፈራል ፡ቀስ እያለ የግቢውን ዙሪያ ዞር ዞር ካለው በዋላ ከለበሰው ጥቁር እረዥም ካፖርቱ ውስጥ የፊት መሸፈኛ የሹራብ ጭንብል አውጥቶ አጠለቀ ለአይኖቹ ብቻ የሚታዩትን ቀዳዳዎች በትክክል ካደረጋቸው በዋላ፡ አንዲት አነስተኛ ሽጉጥ በማውጣት በሁለት እጁ እያቀያየረ አሻሻት ፡እናም ፈገግ አለ ፡እናም ከሌላኛው ኪሱ ውስጥ በላስቲክ የተጠቀለለውን በመርዝ ያበደ ስጋ አወጣ ፡በጊቢውስጥ ዘበኛው ልክ ከለሊቱ 6:00ሰሃት ላይ የሚፈታቸው ውሾች እንደሚንቀሳቀሱ ያውቃል ፡ዘበኛውም በዚ ሰሃት አሳቡን ለውሾቹ ጥሎ ለሽ እንደሚልም ያውቃል ፡ስለዚ የስጋዎቹን ቁርጥራጮች ይወረውረው ጀመር ወደጊቢው ፡ድምፆች ተሰሙት፡ባሰበውልክ ሁኔታዎች እየሄዱ መሆኑንም ተገነዘበ ፡ለራሱ 'አዎ እንደሱ!'አለ እናም ለጥቂት ጊዜ ወደዛ ወደዚ እያለ ጠበቀ ፡አዎ በዚያ አስፈሪ ለሊት ከጨረቃና ጭል ጭል ከሚሉት ክዋከብት በስተቀር አንዳች ታዛቢ በሌለበት ብቻውን ፡በድፍረት ከዛቤት ለመግባት ቆርጧል ፡ እናም ውሾቹ ዝም ማለታቸውን ሲያረጋግጥ እንደጦጣ እየተንጠላጠለ ቀልጠፍ ብሎ ወደ ጊቢው ገባ ዘበኛው እንደተኛ ነው ውሾቹ ተራርቀው በድካም ተንጋለዋል መርዙ ስራውን እንደሰራ አወቀ ፡ 'እንግዲ መሆን ስላለበት እንጂ ፀቤ ከናንተ አይደለም'ብሎ ውሾቹን አልፎ ወደ ሚያምረው ቬላ ተጠጋ እናም ብዙም በማትከብደዋ አነስተኛ መስኮት እጁን ሰደድ በማድረግ ፈተሻት እንደገመተው ነበርና ያለችግረ ከፈታት ፡እናም በቀስታ ወደውስጥ ዘለቀ ፡እናም በመጀመሪያ እነዛ ልህልት ወደመሰሉት እህትማማቾች ክፍል ነው መሄድ ኪኪኪኪ እያንዳንዳቸውን ነው መጎብኘት ኪኪኪኪ መቼም እንግዳ አቀባበሉ አይጠፋቸውም እንዴ ሳኩ እንዴ ምን አባቴ ነው የምሰራው ፡ አለ ለራሱ እናም እንዳለው በመጀመሪያ የቤቱ ታላቅ ወደሆነችው ሮዛ መኝታ ክፍል ዘው አለ በፀጥታ እግሮቿን አጣጥፋ ተኝታለች ፡'ስታምር 'አለ እናም ትቷት ወጣ ቀጥሎ ከሮዛ ጎን ወዳለው ክፍል ቀስ ብሎ ገባ ፡በአልጋው ላይ ሊያና ራሔል ጎን ለጎን ተኝተዋል ብዙጊዜ ራሔል የቤቱ ሁለተኛ ልጅ ብትሆንም ብቻዋን መተኛት ከመፍራቷ የተነሳ የቤቱ መጨረሻ ከሆነችው ሊያጋር ነው የምታድረው ፡ባለጭንብሉ ፡ለብቻ ለብቻ ነበር መተኛት የነበረባቹ ቲ 'ግን ይህ የማይረባ እንዴት ነው ዘሩ እንዲ የሚያምረው 'አለ እናም ዞር ዞር እያለ ውበታቸውን አደነቀ ፡በመጨረሻም፡ የሊያ ታላቅ የቤቱ ሦስተኛ ልጅ ወደሆነችው ሲፈን ክፍል ገባ ፡እንደገባ ለራሱም ያስገረመው ድንጋጤ ተሰማው፡ሲፈን በጀርባዋ ተንጋላ ነው የተኛችው የለበሰችው ሰፊ ቢጃማ በከፊል ተገልፆ እርቃኗ ይታያል እረዥም ፀጉሯ ወዲያና ወዲ ተበታትኖ በሚያምረው ፊቷ ላይ ሳይቀር ነስነስ ብሏል ፡ባለጭንብሉ ፡ትንፋሹ ፀጥ አለ ለረዥም ደቂቃ በመገረም አያት እናም ቀስእያለ ደመነፍሱን ተጠጋት ....ቀስስ እያለ እያለ.........
🔵ይቀጥላል,,,,,,,,,

✴️Share✴️ Share✴️ Share✴️
♥️ከወደዱት ሼር ያድርጉ♥️
@bewketuseyoum19
Log in to unlock more functionality.