Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ avatar
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™ avatar
MIKRE AIMRO | ምክረ-አዕምሮ™
22.04.202513:29
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
06.04.202518:17
ሙከራን ልመዱ!
፨፨፨////////፨፨፨
አዳዲስ ነገሮች ውስጥ ምን አለ? ከፍረሃታችሁ ጀርባ ምን የሚጠብቃችሁ ይመስላችኋል? ሃሳባችሁን እንዴት እውን ማድረግ ትችላላችሁ? ከተስፋና ከእምነት የትኛውን ይበልጥ ተግባራዊ ታደርጉታላችሁ? የአኗኗር ዘይቤ (lifestyle) በራሱ ህይወት ነው። የምንኖረው ህይወት እንደ ልማድ ከምናደርጋቸው ተግባሮች የተለየ አንድምታ የለውም። አብዝተን የምንገኝበት ስፍራ፣ ደጋግመን የምናደርገው ነገር፣ ረጅም ጊዜ አብረናቸው የምናሳልፋቸው ሰዎች፣ ብዙ ሰዓት የምናከናውነው ተግባር ህይወታችን ነው። ማናችንም ብንሆን እግዚአብሔር እስከፈቀደ ድረስ እንኖራለን፣ በፈጣሪ እገዛ ብዙ ከባድ ነገሮችን አልፈናል ወደፊትም እናልፋለን። የእያንዳንዱን የህይወት ስጦታዎች ጠዓም፣ የእያንዳንዱን አዲስ ተግባሮች ክብደት መለካት ደግሞ የሁላችንም ግዴታ ነው።

አዎ! ሙከራን ልመዱ! እራሳችሁን ለአደጋ ማጋለጥ ተለማመዱ፣ ለመውደቅ ደፋር ለመነሳትም ፈጣን ሁኑ። የምትኖሩትን ህይወት ከቁጪት ነፃ አድርጉት። የምንፈልገውን ህይወት ለመኖር በሰዓቱ የማያስደስተንንና የማይመቸንን ተግባር እንደምንወደውና እንደተመቸን አድርገን የመስራት ግዴታ አለብን። እራስን ምቾት መንሳት ደስ አይልም፣ እራስን ለአደጋ ማጋለጥ ያስፈራል፣ አውቆ እራስን መፈተን ያስጨንቃል ነገር ግን ከዚህ ቀደም ያልተገኘን ውጤት ያስገኛል፣ ከዚህ በፊት ያልተደረሰበት ስፍራ ያደርሳል፣ ታይቶ የማይታወቅ ዓለም ውስጥ ይከታል። አንድ ቦታ ቆማችሁ ከምትጨነቁ ሁሉን በመሞከር እራሳችሁን ግራ አጋቡ፣ በፍረሃታችሁ ታስራችሁ ከምትቀሩ በየደረጃው ፍራሃታችሁን ተጋፈጡት፣ ዘመናችሁን በሙሉ በስጋትና በማንአለብኝነት ከምታሳልፉ ለገዛ ህይወታችሁ ሃላፊነት ውሰዱ። ከእያንዳንዱ የህይወት ክስተቶቻችሁ ስትማሩ፣ ከየትኛውም ችግራችሁ ለመውጣት ስትሞክሩ እግረመንገዳችሁን እራሳችሁን እያሻሻላችሁና የሚያኮራ ማንነትን እየገነባችሁ ትመጣላችሁ።

አዎ! ጀግናዬ..! የበዪ ተመልካች አትሁን ተቀላቅለህ የሚበሉትን ብላ፣ የሚሞክሩትን ሞክር፣ የሚያደርጉትን አድርግ። ባለህበት ቆመህ የሚፈጠር ተዓምር የለም፣ በየአቅጣጫው ተንቀሳቀስ፣ እንዳቅምህ እራስህን ፈትነው፣ ተስፋህን ለመጨበጥ፣ እምነትህን ተግባራዊ ለማድረግ በትንሹ ወደፊት ተራመድ፣ በልክህ ጥረትህን ጨምር። ማድረግ እንደምትችል እያወክ ምንም ነገር ሳታደርገው እንዳያመልጥህ። ሁሉም ቦታ መገኘት፣ ሁሉንም መሞከር  ብክነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን በእቅድና በአለማ ሲፈፀም ግን ትልቁ ህይወት ቀያሪ ክስተት ይሆናል። አቅሙ እንዳለህ ታውቃለህ፣ የውስጥህን ፍላጎት ተረድተሃል፣ ምን ስታደርግ ምን እንደምታገኝ ግልፅ ነው። ካልሞከርክ ግን ዛሬም ነገም ውጤት አልባ እውቀት ተሸክመህ ትቀራለህ። ሙከራን የአኗኗር ዘይቤህ አንድ አካል አድርገው፣ አዲስ ነገርን የመጋፈጥን ድፍረት እንደ ግል አቋምህ አራምደው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
05.04.202510:30
ሰላሜ በዝቷል!
፨፨፨//////፨፨፨
ከራስ ጋር ንግግር፦ "በቀደመው ዘመን አንተ በሌለህበት ህይወት፣ አባትነትህን በሸሸውበት፣ ልጅነቴን በካድኩበት፣ ውለታህን በዘነጋውበት፣ ጥበቃህን ቸል ባልኩበት፣ አብሮነትህን ባልፈለኩበት በዛ ክፉ ዘመን አንተ ያው ሩህሩህ ጌታ ደግ አባት ነበርክ እኔ ግን እኔ አልነበርኩም። መታመኛዬ ዓለም ነበረች፣ መደበቂያዬ ዳንኪራው፣ ሱሱና ክፋቱ ነበር። የሆንኩልህን አላውቅም ያደረክልኝ ግዛ እጅግ ብዙ ነው፣ ያደረኩልህ ምንም ነው ያደረክልኝ ቁጥር ስፍር የለውም። እስከ ጥግ ወደሀኛል፣ እስከመጨረሻው ምረሀኛል፣ በይቅርታህ ጥፋቴን ሽረህልኛል፣ የጠፋው ልጅህን ወደቤትህ መልሰሀኛል፣ ዓለም የናቀችውን፣ ነውር ያረከሰውን፣ ጥፋት መገለጫው የሆነውን ባሪያህን ከከፋው አጥፍቶ ጠፊነት፣ መጨረሻ ከሌለው የስቃይ ህይወት ታድገሀዋል።

አዎ! ባንተ ሰላሜ በዝቷል፣ ባንተ ነፍሴ ተረጋግታለች፣ ባንተ ህይወቴ ሙሉ በርቷል፣ ባንተ ውስጤ ፈክቷል፣ ደምግባቴ ተመልሷል፣ ክብሬ ከፍ ብሏል፣ ባንተ ከድካሜ ሁሉ አረፍኩ፣ እንግልቴ ሁሉ ጠፋ፣ ንፁውን ፍፁም ደስታም ካንተ አገኘውት። አባትነትህ ምነኛ ፍፁም ነው? ርህራሔህ ምነኛ ድንበር አልባ ነው? መውደድህስ ቢሆን ምን ይሆን ገደቡ? ወደህ ፈቅደህ ወደእቅፍህ ጠርተሀኛል፣ ፈልገህ አለኝታ ሆነሀኛል፣ ሳትጠየፈኝ ዝቅ ብለህ አንስተሀኛል። አንድ ዘላለም የምኮራበት ነገር ቢኖር ያንተ የእግዚአብሔር አምላኬ ልጅ በመሆኔ ነው። ማንም በሌለበት በድቅድቁ ጨለማ አልያም በሃሩሩ በረሃ ብገኝ እንኳን አንተ አብረሀኝ እንዳለህ አውቃለሁና አንዳች አልፈራም፣ ፍቅርህ ከልቤ፣ ማዳንህም ከማንነቴ ተዋህዷልና ሁሌም ኩራቴ ነህ፣ ዘወትር መመኪያዬ መጠጊያዬም ነው። እወድህ ዘንድ የማንም ፍቃድ አልሻም፣ አክብሬህ እከብር ዘንድ መርጬህም እመረጥ ዘንድ አንዳች ግፊት አንዳች ግዴታ የለብኝ። አምላኬ እወድሃለሁ፤ አባቴ አከብርሃለሁ።"

አዎ! ጀግናዬ..! ከምድራዊ ህይወት እረፍትን መጠበቅ፣ ከዓለም ንብረትና ዝና እንዲሁ ከደካማው የሰው ልጅ ፍፁም ሰላምን መፈለግ ድክመት ነው። ከአባትህ ቤት መጥፋትህን አስብ፣ ከመገናኛችሁ መራቅህ ይታወቅህ፣ ከበረከቱ መጉደልህ ይግባህ። ስለምን ነገ የሚጠፋውን የዓለም ጌጥ ፍለጋ ያለእረፍት ትደክማለህ? ስለምን ቦሃላ በትሹ በሚሰበረው ሰውነትህ ትመካለህ? ስለምን ጊዜ በሚሰጥህ እግዚአብሔርም ባስረከበህ ስልጣን ልጆቹን ትበድላለህ? ስለምን ስህተትህን እንደ መልካም ስራ፣ ጥፋትህንም እንደ ጀብድ ትደጋግማለህ? ወደ ፈጣሪህ እቅፍ ተመለስ፣ ወደቤቱ ቅረብ፣ ዝቅ ብለህ ተማፀነው፣ ክብርን ከእርሱ አግኝ፣ ፍፁም ሰላምህን ከእርሱ ውሰድ። ፍቅሩን ተረዳ፣ ማዳኑን ተመልከት፣ እለት እለት ከበረከቱ ተካፈል፣ ውስጥህን አድስ፣ በመኖርህ ተደሰት።
ፍፁም ሰላማዊ ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
03.04.202518:31
ሁሉም አይሆንህም!
፨፨፨፨////////፨፨፨፨
ማንም ማስተማር የሚፈልግ ያስተምራል፣ ማንም ሃሳቡን ማጋራት የሚሻ ሃሳቡን ያጋራል። እንዲሁ እያንዳንዱ ሰው የራሱን ነገር ያጋራል፣ ሁሉም ሰው ስለገባው ያወራል፣ ማንም ስለሚያስደስተው ብቻ ይተነትናል። እናንተም የሚወራውን ሁሉ የምታምኑ ከሆነ፣ የተነገራችሁትን ሁሉ የምትቀበሉ ከሆነ፣ የተማራችሁትን ሁሉ ለመተግበር የምትጥሩ ከሆነ ከምኑም ሳትሆኑ እንደምትቀሩ እወቁ። መረጃ ማብዛት አዋቂ አያስብልም፣ ስለሁሉም ማውራትም እንዲሁ ተፅዕኖ ፈጣሪ አያደርግም። እናንተ አንድ እስከሆናችሁ ድረስ የሚሆናችሁም አስር ሳይሆን አንድ ብቻ ነው። ህይወታችሁን ለመቀየር እስከ ዛሬ የሰማችሁት ሳይሆን ዛሬ የሰማችሁት አንድ መረጃ በቂ ነው። ከሚነገራችሁ ሁሉ በጥበብ መምረጥ ካልቻላችሁ ጊዜም ሆነ አቅማችሁን እንደምታባክኑ አስተውሉ።

አዎ! ጀግናዬ..! ሁሉም አይሆንህም! ወርቅ ተብሎ የሚሰጥህ ሁሉ ወርቅ አይደለም፤ ላንተ ተብሎ የሚዘጋጅ በሙሉ ያንተ አይደለም። ከቀረበልህ ሁሉ የሚሆንህን የመምረጥ ጥበብ ያስፈልግሃል። ብዙ ሰው በመከተል የሚደረስበት ስፍራ አይኖርም፣ ለሚነገረው መረጃ ሁሉ ጆሮ እየሰጡም ሁሉን መተግበር አይቻልም። መዝናኛውም ያንተ፣ ፖሎቲካውም ያንተ፣ የትምህርት ስረዓቱም ያንተ፣ የማህበረሰቡ ችግርም ያንተ፣ ስፖርቱም ያንተ እንደሆነ እያሰብክ የትኛውንም በእጅህ ማስገባት አትችልም። የራስህን ነጥለህ ውሰድ የቀረውንም ለባለቤቱ አስረክብ። እራስህን በየአቅጣጫው በትነህ ለፈላጊውም አስቸጋሪ አትሁን። እስካሁን ባለህበት ቆመህ ከሆነ በላህ እውቀት ልክ በድፍረት ወደሚያዋጣህ ዘርፍ ተቀላቀል። ተጨማሪ እውቀት ቢመጣ ማጠናከሪያ እንጂ መሰረት ላይሆንህ እንደሚችል አስብ።

አዎ! ስላማረህ ብቻ የማትበላው ምግብ ይኖራል፣ በዘርፉ የተሳካላቸውን ሰዎች ስለተመለከትክ ብቻም አንተም እንደነሱ ስኬታማ የማትሆንበት አጋጣሚ ይኖራል። ማንም ልትሆን ትችላለህ፣ ምንም አይነት ሃሳብ ሊኖርህ ይችላል፣ የትኛውንም የተለመደ አካሔድ ልትከተል ትችላለህ፣ ከማንም የስኬት መንገዱን ልትኮርጅ ትችላለህ ነገር ግን ህይወትህ ከማንም ጋር አንድ አይንት ሊሆን አይችልም። ልዩነትህ በመልክህ፣ በቁመናህ ወይም በገቢህ ብቻ አይደለም ህይወትህ በሙሉ ከየትኛውም ሰው ህይወት የተለየ ነው። ለዚህም ነው ስዎች ስኬታማ የሆኑበት መንገድ በሙሉ ላንተም እንዲሰራልህ መጠበቅ የሌለብህ። ልብ ወዳደላበት፣ ንፍስህ ወደመረጠችው፣ ስሜት ወደሚሰጥህ፣ አቅሙ እንዳለህ ወደሚሰማህ አንድ ዘርፍ ጠቅልለህ ካልተቀላቀልክ ሁሌም ነዋሪ ሳትሆን አኗኗሪ፣ ተደናቂ ሳትሆን አድናቂ፣ አስከታይ ሳትሆን ተከታይ፣ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሳይሆን መካከለኛ ሰው ሆነህ ትቀራለህ። መረጃ በማሳደድ ጊዜህን አታጥፋ፣ በሁሉም አቅጣጫ ስኬትን አትፈልግ፣ ተረጋግተህ ፍላጎትህን ፈልገው፣ እራስህን ስጠው፣ እስከመጨረሻውም በፍቅር ኑረው።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
31.03.202518:55
አድራጊው ሁሌም ፍፁም ነው!
፨፨፨፨፨፨////////////፨፨፨፨፨፨
ሰወኛው ልብ እያንዳንዱን የአምላክ ተግባራት መርምሮ ማወቅ ይዳዳዋል፤ ለመፍረድ ይቸኩላል፤ ምክንያቱን ለማጣራት ይጣደፋል። ሁሉ በምክንያት መሆኑን ቢያውቅም ምክንያቱም እንደ ድርጊቱ በቶሎ እንዲገለጥ ይፈልጋል። አምላክ ግን ሰራው ረቂቅ ነው፤ ተግባሩም ፍፁም ነው። እንኳን ስህተት ሊሆን ቀርቶ ስህተት በእርሱ አይታሰብም። ተግባሩ፣ ስራው፣ ድርጊቱ በሙሉ ልክና እንከን አልባ ፍፁም ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! ሌላውን በትክክል ከውኖ ያንተ ህይወት ላይ ብቻ የሚሳሳት አምላክ አይደለም፤ አንተ ስለተጎዳህ፣ አንተ ስላዘንክ፣ አንተ ስለተጨነክ ብቻ የሚወቀስ አባት አይደለም። መዓት ሲመጣ፣ ጥፋት ሲከታተል፣ ሞት ሲበረታ በፍፁም ሃልዎቱ፣ መኖሩ የሚያጠራጥር ፈጠሪ አይደለም። በጥቂቱ ጥፋትና መከራ ማየሉ ይቅርና ምድር እንኳን ብትጠፋ አምላክ ልክ ነው፤ ስህተት አያውቀውም።

አዎ! ክርክር፣ ንትርክ፣ ሰጣገባ ከሰው ጋር እንጂ ከአምላክ ጋር አይደለም። አንተን ያስገኘ ጌታ ለማን ይከሰሳል? ለማንስ ይወቀሳል? ንብረቱ ነህና እንደፈለገው ቢያደርግህስ? ነፍስህን አውጥቶ ቢመልስስ? አንተንስ ቢወስድህ ማን ይጠይቀዋል? ማንስ ይከሰዋል? ማንም ለማንም አያደርገውም።

አዎ! አምላክ ሰራው ሁሉ እርማት አይፈልግም። መንፈሱ ስህተት የለውም፣ ተግባሩ የነፃ እንከን አልባ ነው። አድራጊው ሁሌም ፍፁም ነው። ምርመራን የሚያስችል፣ እውቀትን የሚገልፅ፣ ጥበብን የሚያሰርፅ እርሱ ደግ አምላክ፣ ድንቅ ፈጣሪ ብቻ ነው። በሰጠን እውቀት እራሱን ለመክሰሰል፣ ሰጪውን ለመወንጀል ከመጣደፍ ለሰጠን ማመስገንና በደረጃችን መራመድ ተገቢ ነው። አንተ ብትሳሳት፣ አንተ ብትስት አምላክ አይሳሳታም፤ አይስትም፤ አይሸወድም፤ አይታለልም። በልክህ የሚፈትንህ ስለሚያውቅህ፣ ስለሚወድህ ነው።

የስራው ልክነት፣ የተግባሩ ፍፁምነት አንተ ላይ ሲሆን እንዲሻር አትጠብቅ። የሆነውን እንደሆነው፣ እየሆነ ያለውንም እንዳለው በፀጋ ተቀበል። የሚሆነውም መልካም ይሆን ዘንዳ በሆነው እያመሰገንክ፣ ለሚሆነው እየተማፀንክ ቸር አምላክህን ጠብቅ። ህይወትህንም በተዓምራት እንዲሞላ እራስህን ስጠው፤ ነፍስህን አስገዛለት፤ ውስጥህን በእምነት አዘጋጅ። የተዓምራቱም ባለቤት ሁን።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
07.04.202519:06
💥📣 መፅሐፍ ከተወደደ አንባቢ ይጠፋል!
ምክንያቱም የመግዛት አቅም የለውምና!!

ይሄን መሰረት በማድረግ
የተለያዩ መፅሐፍ በ Pdf  ድርሰቶች አጫጭር ታሪኮችን የሚያዘጋጅ የቴሌግራም ቻናል
ልጠቁማችሁ!!!

ስሙ እንማር ይሰኛል !!
ቀኖትን እያረመ ማታዎትን እያደመቀ ምርጥ ምርጥ መፅሀፎች ይጋብዛቸዋል ።
100%ትወዱታላችሁ


https://t.me/Enmare1988
https://t.me/Enmare1988
06.04.202508:33
ማንም በሌለበት!
፨፨፨/////////፨፨፨
ማንም የለም፣ ማንም አይጠብቅህም፣ ማንም የምትደገፈው፣ ማንም የምትተማመንበት ሰው የለህም። ለራስህ እውታውን ንገረው። ሰውን ስትጠብቅ የባከኑ ውድ ጊዜህን አስታውስ። ብቻህን የምታደርገው ነገር፣ ለብቻህ የምትወስነው ውሳኔ፣ ማንም ሳያይህ የምታደርገው፣ ለማንም ሰይሆን ለእራስህ ብለህ የምትፈፅመው ጀብድ እርሱ ነው ከመሬት አንስቶ ከፍታ ላይ የሚያስቀምጥህ፣ እርሱ ነው ዋጋህን የሚጨምረው፣ እርሱ ነው የተለየ ሰው የሚያደርግህ። ብችህን ስትሆን ምን ታደርጋለህ? ማንም በሌለበት ደጋግመህ የምታከናውነው ተግባር ምንድነው? ተደብቀህ የት ትሔዳለህ፣ ምን ትሰራለህ? ምንስ ታያለህ?

አዎ! ጀግናዬ..! በዛ በጨለማ ማንም በሌለበት፣ ጠያቂ በማታገኝበት፣ አይዞህ ባይ አበርታች፣ በሃሳብም ሆነ በገንዘብ የሚደግፍህ በሌለህ ሰዓት ምን እያደረክ ነበር? ስለሆነብህ እያማረርክ ወይስ ምሬትህን ለመቀየር ጠንክረህ እየሰራህ? ብቸኝነትህን እየረገምከው ወይስ እራስህን ለመገንባት እንደ መልካም አጋጣሚ እየተጠቀምከው? እድለኛ እንዳልሆንክ እያሰብክ ወይስ ሁኔታውን ለመቀየር እየተፋለምክ? ብቻህን ስትሆን የሚኖርህ ማንነት ያንተ ትክክለኛው ማንነት ነው። አንተና ፈጣሪ ብቻ የምታውቁት የግል ሚስጥርህ ይኖራል። በገባህ ልክ እለት እለት ለብቻህ የምትፋለምለት ሃሳብ ይኖርሃል። "ብቻዬን ነኝ፣ ሰው የለኝም፣ የሚያግዘኝ አላገኘውም፣ የማደርገው ነገር በማንም ተቀባይነት አላገኘው፣ ማንም አላመነበትም።" ብለህ አታቆመውም።

አዎ! ብቻህን ስትሆን ስለምታደርገው እያንዳንዱ ነገር ተጠንቀቅ፣ ማንም በሌለበት ወደአዕምሮህ ስለሚመጣ ሃሳብ ደጋግመህ አስብ። በሰዎች መከበብ ትርፉ መዘናጋት እንደሆነ እወቅ፣ ከዚህም ከዛም በድጋፍም ሆነ በተቃውሞ ቃላት መዋከብ ትርፉ አጉል መኮፈስ ወይም ተሰብሮ መቅረት እንደሆነ አስታውስ። ከቻልክ ለብቻህ ስለራስህ ጊዜ ሰጥተህ አስብ፣ ስላለህበት ሁኔታ፣ ስለምትፈልገው፣ ስለአላማህ፣ ስለልማድህና ስለግል አቋምህ ጠንቅቀህ መርምር። በመዋከብ ጊዜ አታጥፋ፣ እዚም እዛም እየተገኘህ ዋጋህን አታሳንስ፣ በገዛ ፍቃድህ ብኩን አትሁን። ለራስህ ጊዜ ይኑርህ፣ ትኩረትህን እራስህ ላይ አድርግ፣ አንተ ሳትቀየር ውጪው እንዲቀየር መጠበቅ አቁም፣ ማንም ላይ አንድ ጣትህን ስትቀስር የቀሩት አራቱ ወዳንተ እንደሚያመለክቱ አስተውል። እራስህ ላይ ስራ፣ እራስህን አሻሽል የቀረው በጊዜው እንዲስተካከል ተወው።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
04.04.202518:02
እራስህን ገንባ!
፨፨፨//////፨፨፨
"ሌሎች ያላደረጉት ነገር አያሳስብህ።
ዋጋ ያለው አንተ የምታደርገው ነው።"
-Napoleon Hill

ብዙ ጊዜ የምትመለከታቸው ሰዎች የተግባር ሰዎች ላይሆኑ ይችላሉ፣ አካባቢህ ከስራ ወሬን በሚያስበልጡ ሰዎች ሊሞላ ይችላል፣ ያንተን ህይወት በእነርሱ ስንፍና ትለካውም ይሆናል ነገር ግን ሌሎች ያላደረጉት ነገር እኔም ባደረግው ለውጥ አያመጣም ከሚለው እሳቤ ውጣ። እነርሱ ስላላደረጉት ያጡት ነገር ይኖራል፣ እነርሱ የተግባር ሰው ባለመሆናቸው፣ ዋጋ ለመክፈል ባለመድፈራቸው፣ አደጋን በመፍራታቸው ምን እንደጎደላቸው አስተውል። ስኬቱንም ሆነ ውድቀቱን በቅርብህ ካሉ ሰዎች የምትማር ከሆነ ትርጉም ያለው ህይወት የማትኖርበት ምክንያት የለም።

አዎ! ጀግናዬ..! ማንም ያመነበትን ያደርጋል፤ አንተም እንዲሁ። ከማቀድ አለማቀድን፣ ካማድረግ አለማድረግን፣ ከመጀመር አለመጀመርን፣ ከመጨረስም አለመጨረስን ከሚመርጡ ሰዎች እራስህን ነጥል። የእነርሱ አለማድረግ፣ የእነርሱ አለመቀየር፣ የእነርሱ አዲስ ነገር አለመፍጠር፣ የእነርሱ ባሉበት መቆየት አንተን አያሳስብህ፤ ባንተ ህይወት ላይ አንዳች ነገር የሚጨምረው፦ የእነርሱ አለማድረግ ሳይሆን ያንተ ተሽሎ አድርጎ መገኘት ነው፤ የእነርሱ ጀምሮ ማቆም ሳይሆን ያንተ ጀምሮ መጨረስ ነው፤ የእነርሱ ተስፋ መቁረጥ ሳይሆን ያንተ በተስፋ መሞላት ነው፤ የእነርሱ በስንፍና መመላለስ ሳይሆን ያንተ በጥንካሬ መንቀሳቀስ ነው።

አዎ! ማንን እንደምትከተል ጠንቅቀህ እወቅ፣ በማን መርህ፣ በማን አቋም እንደምትመራ በሚገባ ለይ። በቅርበት የምታገኛቸው ሰዎች በራሳቸው መንገድ ይሰሩሃል፣ ረጅም ጊዜ አብረሃቸው የምታሳልፈው ሰዎች የህይወትህ መሪዎች ናቸው። ቁብነገር ያለው፣ ዋጋህን የሚጨምር፣ በለውጥና በእድገት የተቃኘ ህይወት ለመኖር ጥራት ያላቸው ብርቱና ጠንካራ ሰዎች ያስፈልጉሃል። ስለሃገሪቷ ተስፋ ማጣት እያወሩ ተስፋቢስ ከሚያደርጉህ፣ ስለስራቸው አለማስደሰት እየተነተኑ ለስራህ ያለህን ጥሩ አመለካከት ከሚቀይሩ፣ ተምረው ከማያስተምሩህ፣ ለራሳቸው ዋጋ ሰጥተው ያንተንም ዋጋ ከማይጨምሩ ሰዎች ራቅ፣ በተገነባ አካባቢ ውስጥም እራስህን ገንባ
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
03.04.202517:12
🔴 የተረጋጋ ሰው ሁኑ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/k-Y0j4cvTig?si=XdQKSfVfbOl2p3LT
01.04.202519:57
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
31.03.202517:52
🔴 ለሰው አትጨነቁ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/aM20DLsrrL4?si=RyjgoYNWzqjCm8ZV
07.04.202518:31
በስራህ አሳርፋቸው!
፨፨፨፨///////፨፨፨፨
በህይወትህ ሁለት ሰዎችን አትርሳ፣ በዘመንህ ሁሉ ሁለት ሰዎችን ችላ አትበል፣ በህይወት እስካለህ ለሁለት ሰዎች ፊትህን አታዙር፣ በእድሜህ ሁለት ሰዎች እንዲያዝኑብህ አታድርግ። አንዱ አንተ ታሸንፍ ዘንድ፣ አንተ ቀና ብለህ ትራመድ ዘንድ፣ አንተ ደረትህን እንድትነፋ፣ ከፍ ብለህ እንድትታይ፣ ከጓደኞችህ እንዳታንስ ሁሉ ነገሩን መሱዓት ያደረገው አባትህ ነው። ሁለት በህመምህ ወቅት፣ በችግርህ ጊዜ፣ ሰው በራቀህ፣ ወዳጅ ባጣህ ሰዓት አይዞህ ልጄ የምትልህን፣ የማያልቀውን ንፁ ፍቅሯን የምትመግብህን፣ ሁሌም እንደ ስስት ልጇ የምትመለከትህ እናትህ ነች። ማናችንም አንዴ ከሚሰጡን ቤተሰቦች በቀር ሌላ የለንም፣ አባት አንድ ነው እናትም አንድ ነች። በህይወት እያሉ ሊከበሩና ሊኮሩብን ይገባል። ምናልባት ከእኛ እርዳታን ላይፈልጉ ይችላሉ የእኛ እራስን ችሎ ጥሩ ቦታ መገኘት ግን ትልቁ ደስታቸው ነው።

አዎ! ጀግናዬ..! በስራህ አሳርፋቸው፣ አኩራቸው፣ ባንተ ደስ ይበላቸው፣ በምግባርህ፣ በማንነትህ ስማቸውን አስጠራ። ይኑራቸው አይኑራቸው፣ ያግኙ ይጡ፣ ይንደላቀቁ ይቸገሩ ቤተሰቦቻችን ሁሌም ቤተሰቦቻችን ናቸው፤ ስጋ ሁሌም ሰጋ ነው። ምንም ቢሆኑ ወደዚህ ዓለም የመምጫ መንገዳችን ናቸው። ማንም ቤተሰቡን መርጦ አልተወለደም፤ ማንም ፈልጎ ከቤተሰቡ አልተቀላቀለም። የመረጠልን የሚወደን ፈጣሪያችን እግዚአብሔር አምላክ ነው። ምንም እንኳን ነገሮች ሁሉ ባይመቹን፣ ምንም ያደረጉልን ነገር በቂ አይደለም ብለን ብናስብ፣ ምንም እንኳን ብዙ ነገር ፈልገን ባናገኝባቸው ቤተሰቦች ግን መቼም በልጆቻቸው ምክንያት እንዲሰበሩና ተስፋ እንዲቆርጡ ማድረግ አይገባም። ልጅ በረከት ነው፣ ልጅ ፀጋ ነው።

አዎ! አንደኛው ትልቁ መቼም በጀመርከው መንገድ ተስፋ የማትቆርጥበት ምክንያት፣ ለፈተናዎችህ እጅ የማትሰጥበት፣ እለት እለት የምትደክምበት፣ ሁሌም ሳትሰለች የምትደክምበት ምክንያት የቤተሰቦችህ ኩራትና ደስታ ነው። በአጭሩ ህይወት ለሚወዱት ሰው ብሎ አሸንፎ መገኘትን ትፈልጋለች። በድህነት ተቸግረው ላሳደጉህ ቤተሰቦችህ የመድረስ ግዴታ አለብህ፣ ላንተ ለዛሬ መብቃት ዋጋ የከፈሉ ሰዎችን የማስታወስ ሃላፊነት አለብህ። በተራብን ሰዓት ያጎረሱንን፣ በተጠማን ወቅት ያጠጡን፣ በለቅሷችን ጊዜ እንባችንን የጠረጉልንን እጆች አንረሳም፤ በከፋን፣ ሆድ በባሰን፣ ሰው ባጣን፣ በተሰበርን ሰዓት ከጎናችን የቆሙትን፣ አይዟችሁ ያሉንን ሰዎች በፍፁም ችላ አንልም። ማናችንም ዛሬ ላለንበት ለመድረሳችን እያንዳንዱ ወደ ህይወታችን የገባ ሰው የእራሱን አስተዋፅዖ አድርጓልና የትናንት ወዳጆቻችሁን አትርሱ፣ ውለታቸውን ባትመልሱ ውለታቸውን መስክሩ።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
04.04.202507:49
አንድ ነገር ከመጀመራችሁ በፊት!
፨፨፨፨፨፨///////////////፨፨፨፨፨፨
ከማንኛውም ሰው ጋር ባላችሁ ንክኪ ሊያሳባችሁና ጥንቃቄ ልትወስዱ የሚገባችሁ ነገር ቢኖር የአጀማመራችሁ ጉዳይ ነው፡፡ ሁኔታው የንግድ አጋርነት፣ የፍቅር ግንኙነት፣ ትዳር፣ የስራ ሁኔታም ሆነ ሌላ ማሕበራ ጉዳይ፣ የትክክለኛ አጀማመርን ሕግ ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት አንድን ነገር የጀመርንበት ሁኔታ በቀጣይነቱና በአጨራረሱ ላይ ትልቅ ተጽእኖ ስላለው ነው፡፡

አንድን ነገር ከመጀመራችሁ በፊት . . . 

1. ከፍጻሜው ተነሱ
ከፍጻሜው መነሳት ማለት የምትጀምሩትን ነገር እስከወዲያኛው በማሰብ ወደየት ልትወስዱት እንደምትፈልጉ፣ ምን ያህል ርቀት እንዲሄድ እንደምትፈልጉና ከነገሩ ምን ውጤት እንደምትጠብቁ በሚገባ በማሰብ መጀመር ማለት ነው፡፡ የቅርብ እይታ፣ አጭርና ስንኩል ጉዞን ይፈጥራል፤ ረጅም እይታ ደግሞ ረጅምና ስኬታማ ጉዞን ይሰጠናል፡፡

2. የመነሻ ሃሳባችሁን አስተካክሉ
የመነሻ ሃሳብን ማስተካከል ማለት ከአንድ ሰው ጋር አንድን ነገር ስትጀምሩ ያንን ነገር ለምን ለመጀመር እንደፈለጋችሁ የመነሻ ሃሳባችሁን ለይታችሁ በማወቅ ሃሳቡ ጤናማና ትክክለኛ መሆኑን ማወቅ ማለት ነው፡፡ አንድን ነገር የምትጀምሩት ለማይሆንና ለተዛባ ምክንያት ከሆነ ጅማሬው ላይ ምንም ያህል ተለሳልሳችሁና ተግባብታችሁ ብትቀራረቡም የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መበላሸቱ አይቀርም፡፡

3. የሚጠበቀውን ነገር ግልጽ አድርጉ
የሚጠበቀውን ነገር (Expectations) ግልጽ ማድረግ ማለት እናንተ ከሰዎቹ የምትጠብቁትን፣ እነሱ ደግሞ ከእናንተ የሚጠብቁትን ነገር በግለጽ መነጋገርና የጋራ ግንዛቤና ተግባቦት መፍጠር ማለት ነው፡፡ ትልቁ የሕብረተሰባችን አለመግባባትና መንስኤው አንዱ ከሌላው ምን እንደሚጠብቅ በግልጽ ከመነጋገር ይልቅ ሁኔታውን በስሜት ጀምሮ እግረ-መንገድ እየፈጠሩና ግራ እየተጋቡ የመሄድ ጉዳይ ነው፡፡
ዶ/ር ኢዮብ ማሞ
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
02.04.202518:26
መጀመር አለብን!
፨፨፨/////////፨፨፨
ሃሳባችን ምንም ይሁን ምን ሁሌም ወደ አዕምሯችን እየመጣ የሚያጨንቀን ከሆነ ማድረጉን መጀመር አለብን፤ ፋታ በወሰድን፣ የተወሰነ እራሳችንን ለማሳረፍ በሞከርን ቁጥር፣ ስለእራሳችን ባሰብን ቁጥር አዕምሯችን የሚወቅሰን ከሆነ የውስጥ ሃሳባችንን ወደ ምድር ማውረድ አለብን፤ በነጋ በመሸ ቁጥር ጭንቀት፣ ብሶትና ውስጣዊ ሰላም ማጣት የዘወትር ተግባራችን ከሆነ ያስጨነቀንን፣ ብሶት እንዲሰማን ያደረገንንና ሰላማችንን የነሳንን ጉዳይ ፊትለፊት በድፍረት ተጋፍጠን ከጭንቀታችን ነፃ መውጣት፣ ብሶታችንን መሻገርና የገዛ ሰላማችንን በእራሳችን ማረጋገጥ ይኖርብናል። አንዳንድ ሁኔታዎች የሚፈልጉት ተግባርን ብቻ ነው፤ አንዳንድ ሃሳቦች ምድር ላይ ካልወረዱ፣ ተጨባጭ እርምጃ ካልተካሔደባቸው የሚፋቱንና ሰላም የሚሰጡን አይደሉም። የመጨረሻ አማራጫችን መሞከር፣ ማድረግ ወይም ጀምሮ እራስን መገመት፣ እራስን መለካት ብቻ ከሆነ የተለየ ቀላልና አጭር መንገድ ከመፈለግ በላይ ቀጥታ ወደ ተግባር መግባት ይኖርብናል።

አዎ! ጀግናዬ..! መጀመር አለብን! ማድረግ አለብን፤ ልንሞክረው ይገባል። ማብቂያ የሌለው ሃሳባችን አስምጦ ከማስቀረቱ በፊት፣ ገደብ አልባው ፍላጎታችን ስሜታችንን ከመቆጣጠሩ በፊት፣ በየጊዜው የሚቀያየረው ምኞታችን መረጋጋታችን ከመቀማቱ በፊት በአንዱ ወሳኝ ሃሳብ ላይ ቆርጠን መነሳት ይኖርብናል፤ በአንዱ አስፈላጊ ምርጫችን ላይ እርምጃ መውሰድ ይጠበቅብናል። ተግባር ቀላል አይደለም፤ ሙከራ የዋዛ አይደለም፤ መጀመር እንዲሁ የሚሆንም አይደለም። ምናልባት አዕምሯዊና ቁሳዊ ዝግጁነት ሊያስፈልገው ይችላል። ነገር ግን ከሁሉም በላይ ባለን ነገር መጀመሩ ነገሮችን እያስተካከለ እንደሚመጣ ማመን በጣም አስፈላጊ ነው። የሃሳብ ሸክም የሚዛናዊነትህ ጠላት ነው፤ የምኞት ብዛት የጭንቀትህ መንስኤ ነው፤ የሚቀያየረው ፍላጎትህ የትግበራህ መሰናክል ነው።

አዎ! ምን እንደምታሳድድ ሳታውቅ ማሳደድህን አትጀምር፤ ፍላጎትህን አጥርተህ ሳታውቅ ወደ እርምጃ አትግባ። እራስህን በተረዳህ ልክ እንቅስቃሴ አድርግ፣ በምርጫህ አቅጣጫ እርምጃ ውሰድ፣ ለይተህ ባወጣሀው ፍላጎትህ ላይ ክህሎትህን አዳብር፣ ከልብህ በምትወደው ዘርፍ ላይ እራስህን ብቁ ለማድረግ ጣር። ያማረህን ሁሉ ብትከተል አንዱንም በእጅህ እንደማታስገባ እወቅ፤ ፍላጎትህን በሙሉ ለማሳካት ብትሯሯጥ ባክነህ እንደምትቀር ተገንዘብ። ውስጥህ ያለው ዓለም ከገሃዱ ዓለም የተለየ ቢሆንም በሂደት ወደ እርሱ መምጣት እንደምትችል እመን። ከጅማሬህ ቦሃላ ያለውን ስኬት አስብ፤ ከሙከራህ ቀጥሎ የሚመጣውን ውስጣዊ ሰላምና መረጋጋት አስብ፤ ወጥነት ካለው የማይቋረጥ ጥረትህ ቦሃላ የምትደርስበትን የተሻለ ስፍራ አስብ። ቁጭ ብሎ በማለም ከጭንቀት በቀር የምታተርፈው ነገር አይኖርም፤ አስሬ እራስን በመውቀስ በእራስህ ከማዘን በቀር የምታገኘው ነገር የለም። መጀመር ላለብህ ጉዳይ የማይገባውን ጊዜ አትስጠው፤ ፋታ ያሳጣህን ሃሳብ ሞክረህ ውጤቱን ተመልከት።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
01.04.202518:45
በጥላቻህ አትሰቃይ!
፨፨፨፨/////////፨፨፨፨
የበደለህንና ያስከፋህን ሰው በጠላሀው ልክ ባንተ ላይ ሀይል እንዲኖረው ታደርጋለህ፤ ያስከፋህንና የጎዳህን ሰው ለመበቀል በጣርክ ቁጥር የማትፈልገውን አይነት ማንነት በእራስህ ላይ መገንባት ትጀምራለህ። እልህ ውስጥ ስትገባ የማመዛዘን አቅምህን ታጣለህ፣ ንዴት ሲቆጣጠርህ አርቆ መመልከት ይሳንሃል፣ ብስጭትህን ልክ ሳታበጅለት ስትቀር የአቅም ውሱንነት ያጋጥምሃል። ሰዎች ከሚጎዱህ በላይ እራስህን ትጎዳለህ፣ ሰዎች ከበደሉህ በላይ እራስህን ትበድላለህ። ጥፋትን በጥፋት መሻር ብትፈልግ፣ ክፋትንም በክፋት ለመመለስ ብትሞክር ዳግም ጥፋትን ወደረሳስህ መሳብህ፣ ክፋትንም በእላይህ ላይ ማድረግህ አይቀርም። አተረፍኩ ብለሁ በጥላቻ አትታሰር፣ አገኘው ብለህ ከወዳጅህ አትራቅ፣ አቅሙ አለኝ፣ ምንም ማድረግ እችላለሁ ብለህም አቅምህን ለማሳየት አላስፈላጊ ግብግብ ውስጥ አትግባ።

አዎ! ጀግናዬ..!  በጥላቻህ አትሰቃይ፤ በያዝከው ቂም ውስጥህን አትረብሽ፤ ባነገብከው የተበዳይነት ስሜት መንፈስህን አታውክ፣ በተነገረህ አፈታሪክ ዛሬህን አታጨልም። ፍቅር ያሸንፋል መባሉን ከቃል በላይ በተግባር አሳይ፤ አንድነት ሃይል መሆኑን፣ ህብረትም የስኬት መሰረት መሆኑን በተግባር ተጠቀመው። ማንም ሰው ጠላቱ ሌላ ሰው እንደሆነ ቢያስብም ሁነኛው የገዛ ጠላቱ ግን እራሱ ነው። አንዴ የጎዳው ሰው አንዴ ጎድቶት ቢሄደም በልቡ ባዘለው ቂምና ጥላቻ ግን እራሱን ሲበድል ይከርማል። ይህም ባየውና ትዝ ባለው ቁጥር እንቅልፉን፣ ትኩረቱን፣ የደም ግፊቱን፣ ጤናውንና ባጠቃላይ ደስታውን እንዲቆጣጠር ይፈቅድለታል። በምርጫው ዳግም የጥቃት ሰለባ ይሆናል።

አዎ! በእርግጥ ለእራስህ የምታስብ ከሆነ ጥላቻህን አስወግድ፣ የምርም ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ፣ ውስጥህ እንዲረጋጋ፣ ትኩረትህን መሰብሰብና እያንዳንዱን ስራህን በጥራት መስራት የምትፈልግ ከሆነ በልብህ የያዝከውን ቂም፣ ሆድህን የሚቆርጥህን ነገርና እንቅልፍ የነሳህን የተጠቂነት ስሜት ልቀቀው። ተከፋው ብለህ ያስከፋህን ለማስከፋት መጣርህን አቁምና ለእራስህ መልካም በመሆን ለእራስህ ውለታ ዋል። በእራስህ ላይ ሙሉ ስልጣን ሊኖረው የሚገባው አንተና አንተ ብቻ ነህ። ይቅርታ ነፃ እንዲያወጣህ ፍቀድ፣ እራስህን አስቀድም፣ የገዛ ደስታህንም አሳልፈህ አትስጥ። የደረሰብህን በደልና ክፋት ማሰላሰል አቁምና ለእራስህ የተሻለ ማንነት ጀብድ ፈፅም፣ እርሱን እርሳውና እራስን ለላቀው ከፍታ የማብቃቱን የጀግንነት ጉዞህም ቀጥል።
ውብ ምሽት ይሁንልን! 🌘🌒💫⚡️
✍ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
31.03.202511:08
🔴 የማራኪ ሴት 6 ባህሪያት!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/ItMgB03jDRU?si=xVdUlpt3pSKU-zta
07.04.202516:39
🔴 አስፈሪ ሰው ሁኑ!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/4_QLKCtB93I?si=GvE-ymF02uQt38Js
05.04.202518:43
🔴 ከመኝታ በፊት አዳምጡት!

👍LIKE ✍️ COMMENT SUBSCRIBE  📣 SHARE 🙏

https://youtu.be/0TjPTYI3OQk?si=q7DLO_vnCcDMWsR3
03.04.202520:11
⭕️እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

✳️JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማረኛ ይማሩ✅


የቻናሉ Link👇👇

@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
@Learn_English_Language_USA
02.04.202505:36
በቀናት ታደሱ!
፨፨፨////፨፨፨
ትናንት ጥሩ ቀን ነበር፣ ዛሬ ግን እጅግ ድንቅ ቀን ነው፣ አዲስ ቀን ነው፣ የተለየ፣ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ፣ ተከስቶ የማያውቅ፣ እንዲሁ ፍፁም በህይወታችን ኖሮ የማያውቅ ቀን ነው። ዛሬያችሁን እንዴት ትቀበሉታላችሁ? አሁን ላላችሁበት ቀንና ሰዓት ምን አይነት አንድምታ ሰጥታችሁታል? ውድነቱ ሲያልፍ እንዲገባችሁ እየጠበቃችሁ ነው ወይስ አብሯችሁ እያለ ውድነቱ ገብቷችኋል? ምንም ለማድረግ የተመቻቸ ሌላ ቀን እየጠበቃችሁ ነው ወይስ በዛሬው ቀናችሁ ለመድመቅ፣ በአሁኑ ቅፅበታችሁ ለመፍካት አስባችኋል? በእግዚአብሔር ቸርነት፣ በእርሱ መልካም ፍቃድ እስከ ዛሬ ብዙ ዛሬዎችን፣ ብዙ አዲስ ቀናትን፣ ብዙ የተለዩ ሁነታትን መመልከት ችለናል። ይህ ሁሉ የሆነውም በህይወት በመኖራችን ነው። በመኖራችን ብቻ ከምንታደለው እጅግ ውድና ድንቅ ስጦታ ውስጥ ደግሞ አንዱ ዛሬያችን ነው፣ ወደ ህይወታችን የመጣው እኛም ተቀብለነው የምንኖርበት የተለየው ንጋታችን ነው።

አዎ! በቀናት ታደሱ፣ በአዲስ ብረሃን ፍቅርን ልበሱ፣ በተለየው ንጋት መኖራችሁን አንግሱ፣ ከፍ በሉበት፣ እደጉበት። የእያንዳንዱ የህይወት ስጦታችሁ ሚዛን የሚደፋውና ዋጋውን የሚጨምረው እናንተ በሰጣችሁት ልክ ነው። ምንም ውድ ነገር ቢሰጣችሁ እናንተ ካላስወደዳችሁት ሁሌም ርካሽ ነው። አለን ብለን ከምንኩራራባቸው የህይወታችን ገፀበረከቶች ውስጥ አንዱ ዛሬ ነው፤ እጅጉን ሃሴት ልናደርግበትና ደስተኛ ልንሆንበት ከሚገባ ነገር ውስጥ አንዱ አሁናዊ ቅፅበታችን ነው። ለዛሬ ባንደርስ፣ አሁን ውስጥ ባንገኝ እኛ የለንምና ምንም የሚፈጠር ነገር አይኖርም። ለማማረሩም ሆነ ለማመስገኑ፣ ለመደሰቱም ሆነ ለማዘኑ፣ ተስፈኛ ለመሆኑም ሆነ ተስፋ ለመቁረጡ ቀዳሚው የእኛ በህይወት መቆየት ነው። በቀናት ውስጥ ማለፍ፣ አዳዲስ ቀናትን ማየት በጣም ብዙ ነገር ያስመለክተናል።

አዎ! ጀግናዬ..! ዛሬ ስጦታህ ነች፤ አሁን ዋጋ የማታወጣለት በረከትህ ነው። ሁሌም በሰላም ማምሸቱ በጤና መንቃቱ ቀላል እንደሆነ የሚቀጥል እንዳይመስልህ። ቀላልና ዋጋ የሌላቸው የመሰሉን ነገሮች በጊዜያቸው ዋጋና ክብሩን ባለመስጠታችን አንድ ቀን ከረፈደ ቦሃላ ዋጋቸው ይገባናል። ብዙ ቀናት ሲያልፉ መመልከትን ሳይሆን በሚያልፉ ቀናት ውስጥ ያንተን ለውጥና እድገት በአፅንዖት ተመልከት፣ ለእያንዳንዱ ቀንህ የምትሰጠውን ዋጋ ተረዳ፣ ምንም የፈለከውን ባታደርግባቸውም በፍቅርና በደስታ ስለማሳለፍህ እርግጠኛ ሁን፤ አመስጋኝነትህን መዝን። ስላለው ለሚያመሰግነው ሁሌም ይጨመርለታል፣ ስለሌለው ለሚያማርረው ያለውም ይወሰድበታል። ሰጪም ነሺም፣ ጨማሪም ቀናሽም እግዚአብሔር ነው። ከምንናገረውና ከምናስመስለው በላይ ከልባችን የምንፈልገውን ነገር በሚገባ ያውቃል፣ ከሚገባን ጋር አስታርቆም በጊዜው ይሰጠናል። በዛሬህ ደስ ይበልህ፣ አሁን ላይ በመገኘትህ ነፍስህ ሃሴት ታድርግ።
ብሩህ ደማቅ ቀን ይሁንልን! 🌅🌞🏞
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
01.04.202511:16
ከገባበት ጉድፍ አይንህ ይበልጣል!
፨፨፨፨፨፨፨/////////////፨፨፨፨፨፨፨
በህይወትህ ያለህን ነገር መመልከት ከቻልክ ሁሉንም ነገር አለህ፤ እርሱን ማየት ካልቻልክ ግን መቼም በቂ ነገር ሊኖርህ አይችልም። ያለንን መቁጠር የሌለንን እንደመቁጠር ከባድ አይደለም። ትኩረታችን ያጣነውና የጎደለን ላይ ሆነ እንጂ ያለን ነገር ብዛቱ ከሌለው ጋር የሚነፃፀር አይደለም። ሙላትን ማሰብ ተራ ሆኖ ጉድለትን መቁጠር ሙሉ የሚያደርገን ይመስለናል፤ ሙገሳን ችላ ብሎ ነቀፋ ነገሮችን የሚያስተካክል ይመስለናል።

አዎ! ሁሌም ማጣትን ማጉላት ያለውን ይሸረሽረዋል፣ እንደሌለም ያስቆጥረዋል። በህይወታችን እኛ ላይም ሆነ ሌሎች ላይ ክፍተቶችንና ጉድለቶችን በፈለግን ቁጥር በግልፅ እናገኛቸዋለን፤ ለምሬት መንገድ እንከፍታለን፣ እራስን ለመወንጀል ሌሎችን ለመክሰስ እንበቃለን። ያለን የእራሳችንን በረከት መመልከት አለመቻል አንሶን የሌሎችን ክፍተት ለማጉላት እንሮጣለን።

አዎ! ጀግናዬ..! ከገባበት ጉድፍ አይንህ ይበልጣል። ካሉብህ ችግሮች ያንተ በህይወት መኖር በእጅጉ ይበልጣል። ዋናውን ተመልካቹን አይን ስላለህ ጉድፉ ገባብህ፤ አጥርተህ ለመመልከትም እርሱን የማውጣት፣ የማስወገድ ግዴታ አለብህ። በህይወትህም እንዲሁ ሰላም ያለው፣ የተረጋጋ፣ የሰከነ አስደሳች ህይወት ከፈለክ ስጦታዎችህ ላይ ተጣብቀው በረከቶችህን ከሚያስረሱህ ጥቃቅን የምሬትና የነቀፋ ምክንያቶች ተላቀቅ፤ እርግፍ አድርገህ ጣላቸው፣ ተዋቸው።

አዎ! ሁሌም ከሌለው ያለው ይበልጥብሃል። ገና ለገና በሚመጣው እደሰታለው፣ አርፋለው ስትል እጅህ ላይ ያለው እንዳይሾልክ ተጠንቀቅ። "ያለው ማማሩ የሌለው መማረሩ" እንዲል ንገርቱ ብዙ እያለህ እንኳን ስለጎደለችው ትንሽ ነገር ማሰብ ከጀመርክ ማማረርህ አይቀሬ ነው። ሰዎች ቢሄዱ በመሄዳቸው እናዝናለን፤ ከእነርሱ በፊት ብቻችንን እንደነበርን እንዘነጋዋለን። ቁስ ቢጎድል መተካቱን እነረሳዋለን፤ ገንዘብ ቢጠፋ ዳግም መምጣቱ አይታወሰንም። እኛ ከጠፋን ግን ሁሉም ያበቃል።

አዎ! ያለህ ላይ እንዲጨመር ምስጋናውን እወቅበት፣ መባረኩን ተለማመድ። ጉድለትን የማየት ልምድ ያለው ሰው በምንም ሁኔታ ሙሉና የተስተካከል ነገር ሊያጋጥመው አይችም። ፍፁም የሚጠባበቅ ሰው እንከን መቁጠሩ አይቀሬ ነው። ያለህን አለህ፣ የሌለህን የለህም፤ ያለህ ግን ከሌለህ እንደሚበልጥ አስተውል። ለምስጋናም እጅህን ለማንሳት አትስነፍ፤ ለመባረክም አትድከም።
ግሩም ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
✍️ (Epha A.)
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
31.03.202506:12
ሶስቱ ማንነቶቻችን!
፨፨፨፨//////፨፨፨፨
ከስነ-ልቦና እይታ አንጻር ሶስት አይነት ማንነት እንዳሉን ማሰብ እንችላለን፡-

1. ራሴ “እንዲህ ነኝ” ብዬ የማስበው

እኔ በራሴ ላይ ያለኝ ተጽእኖ እጅግ ታላቅ ነው፡፡ ይህ ከሆነበት ምክንያቶች ዋነኛው ብዙውን ጊዜ ከራሴ ጋር ስለማሳልፍና ብዙ ነገሮችን ለራሴ የመናገር እድሉ ስላለኝ ነው፡፡ ይህ ልቀይረውና ሌላ አማራጭ ልፈልግለት የማልችለው እውነታ በመሆኑ በሚገባ ላስብበት ይገባኛል፡፡ በራሴ ላይ ያለኝ አመለካከት ራሴው በእኔው ላይ ከለጠፍኩበት ዋጋ አልፎ በመዝለቅ ወደ ትክክለኛው መስመር እስከሚገባ ድረስ ትክክለኛ መለኪያን እንዳላዳበርኩ አመልካች ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የሰውነቴ ዋጋ የማይለዋወጥ እንደሆነና እኔው በፈቃዴ ግን የተለያዩ የዋጋ ተመኖች እንዲለጠፉብኝ መፍቀድ እንደምችል ማስታወስ የግድ ነው፡፡

2. ሰዎችና ሁኔታዎች “እንዲህ ነህ” ብለው የሚነግሩኝ

ሰዎች ካለማቋረጥ መልእክትን ወደ እኛ ይልካሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በቃል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ በሁኔታ፡፡ በተለይም የመደብ ልዩነት ከባህሉ ጋር ተገምዶ በሚገኝበት እንደኛው አይነት ማሕበረሰብ ውስጥ ጀርባችንን፣ የወቅቱ ሁኔታችንን፣ ያለንና የሌለንን በመደመርና በመቀነስ ካለማቋረጥ ማንነታችን ላይ ተመን ይለጥፋሉ፡፡ ይህ ዋጋ ደግሞ አንዴ ከፍ ይላል፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ዝቅ ይላል፡፡ ይህንን ሁኔታ በተገቢው ሚዛናዊነት የማስተናገዱ ግዴታ እኔው ላይ ነው ያለው፡፡ ሰዎች በእኔ ላይ የሚለጣጥፉት የዋጋ ውጣ ውረድ በማንነቴ ላይ ተጽእኖ የሚያመጣው እኔው ራሴ ስፈቅድለት ብቻ እንደሆነ ማስታወስ የግድ ነው፡፡ 

3. እውነተኛውና ትክክለኛው ማንነቴ

እውነተኛው ማንነቴ ማለት እኔው በራሴ ላይ ወይም ደግሞ ሌሎች ሰዎች የለጠፉብኝ ተመን (Price) ሳይሆን ሰው በመሆኔ ከፈጣሪ የተሰጠኝ ዋጋ (Value) ነው፡፡ ይህ የመጨረሻ ስልጣን ያለውና ሁሉንም ትቼ ላምነው፣ ላሰላስለውና ልለማመደው የሚገባኝ እውነት ነው፡፡ ይህ የማንነቴ ዋጋ በምንም ሁኔታ ሊቀንስም ሆነ ሊጨምር አይችልም፡፡ ይህንን ዋጋ በጥረቴ ልጨምረውም ሆነ ላሳድገው አልችልም፡፡ ለዚያ ሊቀነስም ሆነ ሊጨመር ለማይችለው ከፈጣሪዬ ለተቀበልኩት የከበረ ዋጋ ላለው ማንነቴ የሚመጥን አመለካከትና የኑሮ ዘይቤ የመከተሌ ሁኔታ ግን የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡

እንግዲህ አንድ ሰው በራሱ ማንነት ላይ ያለው ዋጋ የተዛባ መሆኑን ለማወቅ ካሉን መመዘኛዎች መካከል አንዱ በችግሮቹ ላይ ያለውን አመለካከት በማጤን ነው፡፡ የተቃኘና ትክክለኛ ራስ-በራስ ምልከታ ያለው ሰው እለት በእለት በሚገጥመው ችግሩ ላይ ያለውም ምልከታ ሚዛናዊና አዎንታዊ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ችግር ሲገጥመው የወደቀ አመለካከት ያለው ሰው በቅድሚያ በራሱ ላይ ያለው አመለካከት አለመስተካከሉን አመልካች ነው፡፡

የኑሯችሁ ሁኔታ በተለዋወጠ ቁጥር በማንነታችሁ ላይ ያለችሁን አመለካከትና ለራሳችሁ የምትሰጡትን ግምት አትለዋውጡ፡፡ በምንም ሁኔታ ውስጥ ብታልፉም የማንነታችሁ ዋጋ ያው ነው!
/የማንነትህ መለኪያ መጽሐፍ/
ግሩም ቀን ይሁንልን! 🏞🌞🌅
ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
#SHARE እንዳይረሳ ቤተሰቦች!

YouTube አማራጭ ይቀላቀሉን!
🔺🔻 SUBSCRIBE NOW
https://www.youtube.com/channel/UCIZv4h3iDx2C7CGbv9WIkVg?sub_confirmation=1
ምክረ-አዕምሮ/ @mikre_aimro 😊 💪
Shown 1 - 24 of 414
Log in to unlock more functionality.