Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
በዝሙት አንዘምን 🚫 avatar

በዝሙት አንዘምን 🚫

የተለያዩ ባለንበት ተጨባጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንመካከር እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል ቻናሉ ውስጥ ገብተው ሁሉንም ያምብቡ።
ከሃራም መንገድ(ፍቅር)መውጣት ለምትፈልጉ
በውስጥ መስመር እንመካከር
👉 @Jezakellah
ሙሂዲን ሰኢድ

ጆይን ግሩፕ👉 @bezemut_anzemn
كنتم خير أمة أخرجت للناس تأمرون
بالمعروف و تنهون عن المنكر
Рэйтынг TGlist
0
0
ТыпПублічны
Вертыфікацыя
Не вертыфікаваны
Надзейнасць
Не надзейны
Размяшчэнне
МоваІншая
Дата стварэння каналаMar 13, 2021
Дадана ў TGlist
Mar 19, 2025
Прыкрепленая група

Рэкорды

23.04.202523:59
13KПадпісчыкаў
24.03.202523:59
100Індэкс цытавання
18.03.202518:44
1.9KАхоп 1 паста
18.03.202518:44
1.9KАхоп рэкламнага паста
28.03.202517:44
4.35%ER
18.03.202518:44
15.21%ERR

Развіццё

Падпісчыкаў
Індэкс цытавання
Ахоп 1 паста
Ахоп рэкламнага паста
ER
ERR
MAR '25MAR '25MAR '25APR '25APR '25APR '25

Папулярныя публікацыі በዝሙት አንዘምን 🚫

24.03.202522:46
ከሷሊሆች አንዱ ለይል ለመስገድ ተነሳ በሶላቱ ውስጥም ይሄን የቁርዐን አያ እየደጋገመ እየቀራ ያለቅሳል ቁርዓኑ እንዲህ ይላል

وَسَارِعُوٓا۟ إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا ٱلسَّمَٰوَٰتُ وَٱلْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ

ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ጀነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ(ተሽቀዳደሙ)።

ከዛም ጡሃት ሲያለቅስ የሰማው ሰው እንዲህ አለው የማታስለቅስ አያ አስለቀሰችህሳ እሷኮ ጀነት ረጅም ሲፊ መሆኗን ነው ምትናገረው አለው ሰውየውም እንዲህ አለው እኔ ከስፋቷ ምን አለኝ አንድ እግሬን እንኳ የማስቀምጥበት ቦታ ከለለኝ ብሎ መለሰለት❗️

አስተንትናችሁታል? እኔ ከስፋቷ ምን አለኝ አንድ እግሬን እንኳ የማስቀምጥበት ቦታ ከሌለኝ!?

አላሁ አክበር አስቡት ጀነትን ምን ያክል እንደተረዳት።
ያ አላህ! አትከልከለን ውዷን ሃገርህን መልካም ስራዎችንም አግራለን፣ ከወንጀልም አርቀን።

እንንቃ ጀነት ውድ ናት ውድ ዋጋም ሊከፈልባት ይገባል።!

 እንዴት ጀነትን ፈላጊ ሁነን እናንቀላፋለን!?


በመልካም ዱዓ አንረሳሳ

መልዕክቱን ሼር በማድረግ ሌሎችንም እናንቃቸው❗️


በዝሙት አንዘምን!👇👍
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
07.04.202503:15
ክፍል ሁለት(2)

ሃላል ስራ ለሁሉም!

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
በተለይ አብዘሃኛው ሴቱም ወንዱም ሙስሊም(ወጣቶች)የተዘፍቁበት ስራ የኦላይን ስራ ነው። በጣም የሚገርመው ስለ ሃራምና ሃላልነቱ ጠይቃችኋል ወይ ሲባሉ አልጠየኩም ነው የሚሉት። ስለ ዲናችን ሲሆን አንጠይቅም ለዱንያዊ ኪሳራ የፍራንበት ጉዳይ ሲኖር ግን እንጠይቃለን። በጣም ነው ሚያሳፍረው። በቃ ብሩ ይምጣንጂ ከየትም በየትም ይምጣ እያሳሰብን አይደለም። ይሄ ትልቅ አደጋ ነው።!

የኦላይን ስራዎችን አስመልክቶ ራሳችንን እንድንጠይቅ ጠቅለል ያለ ጥያቂያዊ ሃሳብ ላንሳላችሁ ያው እንደምናውቀው ባለንበት ጊዜ በተለያዩ መንገዶች ኦላይን ላይ ብር ይሰራሉ። ስራዎችም የሆነ ቪዲዩ ወይም ፎቶ ማለት እንዲሁም አፕልኬሽኖችን ላይክ ማድረግ ሊሆን ይችላል ወይም ለሆነ ያክል ጊዜ ሊንኩ ውስጥ ገብቶ መውጣት ሊሆን ይችላል። ብዙ አይነት ናቸው ተዘርዝረው ላያልቁ ይችላሉ። እዚህጋም የሚሰሩ ልጆች ምንችግር አለው ማየት አይደል ወይም ገብቶ መውጣት አይደል ይላሉ ነገር ግን የኔ ጥያቄ ያን በማድረጋችን ያ ድርጅት ምንድን ነው የሚጠቀመው!?፣ ያን በማድረጋችን ምን አይነት አላማ ያለውን ድርጅት እያሳደግን ያለው!? እንዲሁም ምን አይነት አላማ ያለው ድርጅት ነው አባል እየሆን ያለው? ለዚህ ጥያቄ ሁላቸውም ማለት ይቻላል መልስ የላቸውም። ታዲያ ይሄ ለሙስሊም የማያሳስብ ጉዳይ ሁኖ ነው።? ከዛ ነገር ውስጥ ስንገባ ያን ድርጅት እያሳደግን፣ ተስፋም እየሰጠን፣ እያስተዋውቅን መሆኑ ጥፍቶን ነው? ታዲያ የዛን ድርጅት አላማ ሳናውቅ እንዴት ዝምብለን እንገባለን? መቸም ድርጅቱ አላማ የለውም ብር መስጠት ብቻ ነው እንደማትሉኝ ተስፋ አድርጋለሁ። ሲቀጥል አላማው እንኳ ጥሩ ነው ቢሉን በውስጡ ምን አይነት አላማ ያለው ድርጅት መሆኑን እንዴት እናውቃለን? መቸም መጥፎ አላማ ቢኖረው ያንን እንዲነግሩን አንጠብቅም። የውጮችም አላማ አብዘሃኛው ይታወቃል በተለይ ኢስላምን ለማጥፋት እቅድ ማይኖረው ድርጅት የለም ማለት ይቻላል። ታዲያ እኛ ብር ስላስገቡልን ብቻ ያሉንን ሁሉ መስራታች ነገ አላህ ዘንድ አያስጠይቀንም።? ስለ ገንዘባችን አመጣጥ አንጠየቅም ምን ልንመልስ ነው።? ይሄንንም ነገር ማስተዋል ያስፍልጋል።

አንዳንዶቻችን ደግሞ ስለዚህ ነገር አሰራሩም መረጃውም የማያውቁትን ኡስታዞች ለነሱ ሃላል በሚሆን መልኩ ይጠይቁና እከሌ ሸይህ ችግር የለውም ብሏል ይላሉ። አላህን እንፍራ ራሳችንን ነው የምንጎዳው። አላህን መሸወድ አንችልም። የገንዘብ አመጣጥ ጉዳይ ቀላል ነገር አይደለም። ጥንቃቄ እናድርግ። በመሆኑም በኦላይን ከሚመጡ ስራዎች እንራቅ እላለሁ። ወላሁ አእለም

ለጓደኞቻችን ሼር እናድርገው ባረከላሁ ፊኩም

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ

በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል
👇👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
13.04.202513:35
ቁጥር ስምንት(8)
  📌 ካለፉት እንማር

  🎁 አስደናቂው ሪዝቅ!
       🧲 ክፍል አንድ

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
አንዳንድ ሙስሊም የሆኑ እህቶች ሰዎች በሃራም መንገድ ሂደው ከመተኛትም አልፈው የዝሙት ልጅ ታቅፈው ወደ ትዳር ሲገቡ ሲመለከቱ ግራ የሚጋቡ እህቶች አሉ። ይሄ መንገድ ልክ ነውንዴ ትዳር ካገኘሁ ለምን እኔም አልሞክረውም የሚል ሃሳብ ሸይጧን እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል። ይሄም የኢማን መድከምና በአላህ ላይ ያለን ተወኩል የመጥፋት ምልክት ነው።አዎ በኢማናችን ደካማ ከሆንና አላህን ካላወቅነው በዚህ ደረጃ ነው ሸይጧን የሚጫወትብን። አንዷ እህታችንም ምታውቃት ልጅ በዚህ መንገድ የዝሙት ልጅ ይዛ ተጋብታ ስታይ ግራ ተጋባሁ አለችን ያው ከላይ እንደነገርካችሁ እውነተኛ መንገድ መስሏት።

ጉዳዩንም ወደናንተ ያመጣሁት በዚህ አስተሳሰብ ያሉ ብዙ እህቶች ስላሉ እንድትነቁ ነው። ትዳር ፈልገው ግን በዙርያቸው ያሉ ወንዶች ከትዳር በፊት ሃራምን(ዝሙትን)ይጠቋቸዋል። አላህ ያላዘነላቸውም ተስፋ ቆርጠው ያንን ቆሻሻ ሃራም የሚሰሩ አሉ። ግን የሚያሳዝነው ታግለው ታግለው በመጨረሻ ሶብር ያጣሉ።! አላህ ያዘናላቸው ግን በሃራም ከሚተኙ ቁሞ መቅረትን ይመኛሉ። አዎ! ውድ እህቴ ወላሂ በሃራም ከምተኚ ወይም ዝሙት ከምትሰሪ ቁመሽ ብትቀሪ ይሻልሻል። ይሄን ስልሽ በዚህ መንገድ ካላሳለፍሽ ስሜቱን ላትረጅው ትችያለሽ ነገር ግን እኔ የምነግርሽ በዚህ ሃራም መንገድ ያለፉ እህቶች የሚሰማቸውን ስሜት ነው። ከዝሙት በኃላ አላህ የሚለቅባቸውን ጭንቀት ሲቀምሱትና እንቅልፍ ሲያሳጣቸው ምን አለ ቢቀርብኝ ይላሉ። እውነታው ይሄ ነው ከደም ስራችን ማይወጣ ጭንቀት ነው የሚለቅብን። ሲጀመርም ትክክለኛ ለትዳር ከፈለግሽ እንደዛ አይነት ቆሻሻ ነገር አይጠይቅሽም።

ሃራም ስርታ ትዳር ይዛ ከላይ ፈገግ እያለች ስታያት ደስተኛ ልትመስልሽ ትችላለች ነገር ግን የውሸት ፈገግታ ነው ውስጧ ሰላም መረጋጋት የለውም።! አንዳንዴ በጣም ከፍቶን ነገር ግን ሰዎች ፊት ፈገግ እንል አይደል የነሱም ህይወት እንደዛ ነው። በነዚህ አይነት ሰዎች መቸም እንዳትቀኝ። በክብርሽ መቸም እንዳትደራደሪ። በዚህ መንድም አልፈሽ ከሆነም ወደ አላህ ተመልሰሽ ተውበትሽንም አጥብቀሽ ያዢ። ከወንጀል የተመለስ ልክ ወንጀል እንደሌለበት ነው።!

በትኩረት ተከተሉኝ ይሄ ለሂወታችን ትልቅ ምክር ነው። ማንም ቢሆን ከሪዝቁ ውጭ የሚያገኝ የለም።! ወላሂ ሪዝቃችን ከአንበሳ አፍ ላይ እንኳ ቢሆን ተመልሶ ይመጣል። ሪዝቃችን የኛ ካልሆነ ግን በእጃችን የተቀበልነው ነገር እንኳ ቢሆን ተመሶ ይሄዳል በዚህ እንዳትጠራጠሩ።! አንድ ሌባ ሰው ሲሰርቅ ያ የሰረቀው ነገር የራሱ ሪዝቅ ነው ነገር ግን ቸኮለና በሃራም መንገድ ወሰደው። እንጂ ትዕግስት ቢያደርግ በሃላል ይመጣለት ነበር። የሚያጭበረብርም ሰው እንዲሁም ጉቦ የሚበላ ሰው ሪዝቃቸውን ነው የወሰዱት ነገር ግን ሶብር አጡና በሃራም መንገድ ወሰዱት ቢታገሱ በሃላለ ይመጣላቸው ነበር። አላሁ አክበር! ይሄ የሚገርም ነገር ነው። እንደዚሁም በሃራም መንገድ ሂዳ ትዳርን የያዘች ልጅ ልጁን ማግባቷ ሪዝቋ ስለሆነ ነው። ነገር ግን በችኮላ በሃራም መንገድ አደረገችውና ትልቅ ወንጀል ውስጥ ገባች። በትታገስ በሃላል መንገድ እንደሚመጣላት ምንም ጥርጥር የለውም።  የሷም ካልሆነም አስረግዞት ይጠፋል እንጂ መቸም ልታገባው አትችልም ነበር መቸም።! ሪዝቅ ልክ እንደ ሞት የተፃፍ ነገር ነው ማንም ሊሸሸው አይችልም። ስለዚህ ነፍሳችንን እናሳርፋት፣ ከአላህ መንገድ አንውጣ፣ አላህን አስቆጥተን ሪዝቃችንን አንፈልግ፣ ከሃራም መንገዶች ርቀን ሶብር እናድርግ። አላህም በትክክለኛው ሰአት በሃላሉ መንገድ የተሻለ ይሰጠናል። (አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

ስሙ ይሄን ታሪክ አንዴ የሆነ ሰው አንሸራቶት ጉድጓድ ውስጥ ገባ ከዛም...
በቀጣይ ይጠብቁን  #ይ_ቀ_ጥ_ላ_ል

ሁላችንም ስልካችን ላሉት እህት ወንድሞች ሼር እናድርገው! ባረከላሁ ፊኩም

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ

በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል
ተቀላቅለው ይከታተሉን 👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
04.04.202516:18
ክፍል አምስት(5)

📌ለትዳር የመጠባበቅ መስፈርትና አደጋዎቹ!

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ

በዚህ መንገድ ያለፉ ብዙ ናቸው ማለትም ከትዳር በፊት በጣም ተላምደው መጨረሻው ትዳር ሳይሆን ቀርቶ የተለያዩ በዛም ምክንያት የሚጎዱና የሚሰቃዩ ይሄም እጃችን በሰራው ወንጀል የመጣብን ፈተና ነው። ስለዚህ ይሄ አላህን የምናምፅበት መንገድ መጨረሻው ራስን መጉዳት ነውና ለራሳችን ብለን መንገዱን እንራቅ። የሃራም መንገድ ሪዝቃችንን አያሰፋውም አያፋጥነውም። ነገር ግን በአላህ ላይ ያለን ተወኩል ደካማ ሲሆን በሃራም መንገድ የምንሰጣጠው ፍቅር የወደፊት ህይወታችንን የሚያሳምረውና የሚያግባባን ይመስለናል። ነገር ግን ውሸት ነው! ሸይጧን ነው ቃል እንደገባው እንደዛ እንድናስብና ወንጀሉን አሳምሮ እንድናየው የሚያደርገን። አላማውም ተሳክቶለት ለትዳር በሚል በመጠባበቅ ሰበብ ብዙዎችን ለዝሙት ማጥመድ ችሏል።

በድጋሚ ለማስታወስም ያክል እንጠባበቅ ብለን የምናስብና አሁን ላይ ተጋብተን አብረን መኖር ካልቻልን በመጀመሪያ የሁለታችሁም ቤተሰብ ማወቅ አለባቸው እሱም ለወንድም ለእህት ሳይሆን የምናሳውቀው ለእናትና አባቶቻችን ነው ማሳወቅ ያለብን። ከዛም ቤተሰብ ፍቃደኛ ከሆነና ልጁ እምነት የሚጣልበት አይነት ከሆነ ልጁ ለመኖር ሚያስችለውን ነገር እስኪያመቻች ኒካህ ታስሮላችሁ ቤተሰብጋ ሁናችሁ እንድትቆዩ ጥያቄ አቅርቡ። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በዚህ ሃሳብ የሴት ቤተሰብ ስለማይስማሙና ፍቃደኛ ላይሆኑ ይችላሉ ማለትም ኒካህ ከታሰረላት ይዟት እንዲሄድ ነው የሚፈልጉት። ስለዚህ ከተሳካ ጥሩ ነው። ካልተሳካ ግን ለመጠባበቅ እሷን ማስተዳደር ሲችል እንደሚሰጡት ፍቃደኛ መሆን አለባቸው። ያም ሁኖ ግን በሁለታቸው መሃል ምንም አይነት የስልክም ሆነ የፁሁፍ ግኑኝነትና ወሬ ሳይኖር ነው ሊጠባበቁ የሚችሉት። እንጂ አሁን ላይ እንዳለው ቤተሰብ ሳያውቅ በተለያዩ አጋጣሚዎች ተገናኝተው አሁን ላይ ማግባት አልችልምና እንጠባበቅ ተባብለው በራሳችን የምንወስነውና የምንጠባበቀው መንገድ የሃራም ግኑኝነት ወይም ፍቅረኛ ማለት ነው። ምንም የሚቀይረውና የተለየ ነገር የለውም እኛ እንጋባለን ብለን ብናሳምረውም እንኳ።

በመሆኑም እንደ ወንድም የምመክረው ነገር በሰአቱ ኒካህ ማሰር ካልቻልን እንጠባበቅ ከሚል አስተሳሰብ እንውጣ። ካልሆነ ከላይ ያስታወስኳችሁን መስፈርት ልንጠብቅ ይገባል። ነገር ግን ያን መስፈርት ጠብቀንም ቢሆንም ከአመት በላይ ከሆነ እቅዳችሁ ቢቀርባችሁ ነው የምመክረው። ርእሱን ለማሳጠር ያክል እንጂ ይሄ መንገድ ከአላህ ጋር ያለንን ጉኑኝነት ያዳክመዋል፣ ወደ ኢባዳ እንዳንነሳሳና እንዲሁም የኢባዳችንን ጥፍጥና እንዳናገኝ ትልቅ ሰበብ ይሆናል። ስለዚህ ከዚህ ነገር እንወጣ ሰላም እናገኛለን። ራሳችንን አላህ የሚወደው አይነት ባሪያዎች እናድርግ፣ አላህጋር እንተዋውቅ ቂርአታችንን እንቅራ፣ አለባበሳችንንም እናስተካክል፣ከመጥፎ ጓደኞች እንራቅ፣ የትዳር መስፈርታችንንም ሸሪአው በመከረን አይነት መንገድ ይሁን አላህም በትክክለኛው ሰአት በሃላል መንገድ ጥሩውን እንደሚሰጠን ቃል ገብቶልናል። ወላሁ አእለም
        📌 ይ ቀ ጥ ላ ል

ሁላችንም ለጓደኞቻችን በሌሎችም መንገዶች ሼር እናድርገው አላህ የሚወደውን ይመራበታል።

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ
@jezakellah

ይህ በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ነው!
ተቀላቅለው ይከታተሉን ካለፉት እንማር
     👇👇👍 👍 👍👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
05.04.202511:59
የሸዋል ትንሹ ኢድ!?

ቢስሚላህ አልሃምደሊላህ
አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የሸዋል ስድስቱ ፆም ሲያልቅ እንደ ኢድ ሲያከብሩ ይስተዋላል እንደሰማሁትም ከሆነ የነገሩ አመጣት ልጆችን እንዲፆሙ ለማነሳሳት ከፆማችሁ በኃላ ይሄን እናድርግላችኋለን እንደሚባሉና ያች ነገር አድጋ ቀኑ እስኪ ከበር እንደበቃ ነው። የሽርክንም አመጣጥ አስተውላችሁት ከሆነ ይሄው ነው።ሸይጣን ለረጅም ጊዜ እንዲሳካ ነው የሚያቅደው በመጀመሪያ ቀብሩ ላይ ቤት እንዲሰራ ያደርጋል ከዛ በቆይታ ሰዎች ይሄ የሆነውማ ሰውየው የተለየ ነገር ቢኖረው ነው ብለው በማሰብ ምንም ማያውቁትን ሰው ቀብር ሲያመልኩትና ሲለምኑት ይስተዋላል። ይሄም የቢድዓ ተግባር እንደዛው ሸይጧን እንደተሳካለት የሚያሳይ ነው።

በመሆኑም ምን አልባት በዚህ ተግባር ላይ ያለን እህት ወንድሞቻችን የቢድዓን አድገኝነት ልንረዳ ይገባል። በዲን ላይ ማስረጃ የሌለው አንድን ስራ ስንሰራ አላህ ያልደነገገውን ነገር መደንገግ ማለት ነው። ይሄ ደግሞ እጅግ በጣም ከባድ ወንጀል ነው። ከዝሙት፣ ሰው ከመግደልም የበለጠ ነው። ስለዚህ ለራሳችን ብለን ራሳችንን ቁጥብ እናድርግ ሰዎች እንደነዚህ አይነት ነገሮችንም በሚያስታውሱን ሰአት እልህ ውስጥ ልንገባ አይገባም ምክንያቱም ምንጎዳው ራሳችንን ነው። ሃቅ ከሆነ ለምን አልቀበለውም ብለን ነው ማሰብ ያለብን ሃቅን ደግሞ ምንመዝነው ቁርአንና ሃዲስን በሶሃቦች አረዳድ በማየት ነው። ሲጀመርም ወደ አላህ መቃረብና ጀነትን ፈልገን ከሆነ በግልፅ የመጡልን ትዕዛዞች በቂ ናቸው። ምንም እንኳ ያልቀራንና በራሳችን መረጃዎችን አገላብጠን ማየት ባንችል እንኳ ፈጠራ ወይም በዲን ላይ አዲስ የሆኑ ነገሮች ግልፅ ናቸው። ማስታወሻው ለሸዋል ኢድ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ በዲናችን ላይ በሌሉ ነገሮች ላይ ራሳችንን ቁጥብ እንድናደርግ እንዲሁም ቤተሰቦቻችንን እንድናስታውስ ነው። ወላሁ አእለም

ከቻልን ሼር እናድርገው!

ከወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ

  የቀድምቶች መንገድ
የቴሌግራም ቻናል 👇👇
ይህ አዲስ ቻናል የአቂዳና ሽርክ እንዲሁም የቢድዓ ተግባሮችን ምንተዋወስበት ቻናል ነው። ተቀላቅለው ይከታተሉን👇
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah

ይሄን ቻናል ለመክፈት ያነሳሳኝ፦
① የዲን መሰረታዊ እውቀቶችና ሰዎች ከእሳት ድነው ጀነትን የሚወርሱበት በሆነው ጥቅል የአህሉስ-ሱንና ወል-ጀማዐህ እምነት ላይ ትኩረት ይሰጣል።

② በሺርክና በቢድዐህ የተበከለውን የሙስሊሞች ዐቂዳ በማስተካከሉ ዘርፍ ላይ የጎላ ሚና ይኖረዋል።

③ ሙስሊሞችን ወደ ቁርኣንና ወደ ነብዩﷺ ሱንና እንዲመለስ

ፊ ዓቂደቲ አሰለፊ አስሷሊሕ(አህሊ'ስ ሱንነቲ ወ'ል- ጀማዕህ)
በቅርቡ ከመጡልኝ አንድ ሁለት ጥያቄዎች ለሁላችንን ስለሚጠቅመን እንመካከርባቸው

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
አንደኛው፦ ሳትፈልግ ለቤተሰብ ብላ ያገባች ሴት ከገባች በኋላ ካልወደደችው ፍች መጠየቅ ትችላለች የሚል ነው። ባጭሩ በዚህ ሰበብ ፍች መጠየቅ አይቻልም። ይሄ ምክንያት አይሆንም። ፍቅራችሁን የሚጨምሩ መንገዶችን እየተጠቀማችሁ ውዴታ እንዲኖራችሁ ሰበቡን አድርሱ። "እናንተ ምጠሉት ነገር ኸይር ሊሆን ይችላል በተቃራኒውም የወደዳችሁት ወይም የፈለጋችሁት ነገር ለናንተ መጥፎ ሊሆን ይችላል"ብሎናል አላህ(ሱብሃነ ወተዓላ)። እና ሶብር እናድርግ ችግርም ካለ በግልፅ ተነጋግራችሁ ለመፍታት ሞክሩ። ለባለ ትዳሮች ውድ ምክር የሚልም ከዚህ በፊት የጀመርኩት ተከታታይ ፅሁፍ አለ እሱን ላኩላቸው። እስካሁን የተለቀቁትንም ከታች በሊንክ እለቅላችኋላለሁ ቀሪዎችም ይቀጥላሉ። ኢንሻ አላህ

እንዲሁም ከሁለት ውጭ ከሚኖሩ እህቶች ባሌ ራቁትሽን ፎቶ ላኪልኝ እያለኝ ነው። ፍች መጠየቅ እችላለሁ? ምንስ ነው ማድረግ ያለብኝ የሚል ነው። እዚሁምጋ ፍች ለመጠየቅ ሰበብ አይሆንም። ነገር ግን እሱ ይሄን ካላደረጋችሁ እፍታለሁ ካለ መፍታት ይችላል። ቤተሰብን፣ ባልን አላህን በማመፅ ላይ መታዘዝ አይቻልም። ተግባሩ አላህ ማይወደው ስለሆነ አልክም በሉ እንጂ ይሄን ሰበብ በማድረግ ፍች መጠየቅ አትችሉም።

ለባለ ትዳሮች ውድ ምክር
ክፍል አንድ👇
https://t.me/latekrebu_zina/2585
ክፍል ሁለት 👇
https://t.me/latekrebu_zina/2589
ክፍል ሶስት 👇
https://t.me/latekrebu_zina/2591
ኢንሻ አላህ ሌሎችንም ክፍሎች እለቅላችኃለሁ።

🎁 ክፍል ሶስት የቴሌግራምና ሌሎችም ግሩፕ ባለቤቶች ማወቅ ያሉብን አደጋዎችና ጥንቃቄዎች! ኢንሻ አላህ ማታ አራት ሰአት ይለቀቃል።

🩸በዝሙት አንዘምን❗️
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.