20.04.202515:17
✳️ ከትንሳኤ እሑድ በኋላ የሚውሉ ዕለታት ስያሜ
✍ሰኞ ማዕዶት ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር ማለፍ ማለት ነው በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን ከሞት ወደ ሕይወት ከሲኦል ወደ ገነት ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን::
✍ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል ዮሐ. 20፡27-29::
✍ ረቡዕ አልአዛር ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን::
✍ሐሙስ አዳም ሐሙስ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን::
✍አርብ ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ይሰበካል ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ነስቶ ስለመመስረቷ እንዳከበራት ይነገራል ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና::
✍ ቅዳሜ ቅዱሳት አንስት ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል::
✍ እሑድ ዳግም ትንሣኤ ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል::
🙏† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †🙏
01.04.202517:44
♡ ተክለ ሃይማኖት ጻድቅ ♡
ስጋዬ ታሞብኝ ተጨንቃ ሕይወቴ
በስምህ ታመንኩኝ ተክለ አብ አባቴ
ከቤቴ ሳልወጣ ገዳምክን ሳስበው
መከራው አልፎልኝ በአይኔ አይቻለሁ
ስፍገመገም ልወድቅ በዝቶ ፈተናዬ
ደገፍከኝ አባቴ መተህ መመኪያዬ
ተስፋዬ ተሟጦ አይኔን እንባ ሞልቶ
ጸበልህ ሲነካኝ አገኘሁኝ ድህነት
በተስፋ ሞልተኸኝ ስመጣ ከደጅህ
የበዛው ሕመሜ ሸፈንከው በጽድቅህ
ሞኝ ነው ይሉኛል ሳያውቁ አባቴ
መሰከርኩ ልጅህ በርትቶ ጉልበቴ
ከችግር ከሐዘን ያመነህ ይወጣል
አይኑ ተከፍቶለት አብርቶ ይታያል
በሰው እጅ የመጣ ነበር ይሆን እና
ድኖ ይመለሳል በጽድቅህ ገናና
የደብረ አስቦቱ የኢቲሳው አባት
መሰከረች ዛሬ ጽላልሽ በእውነት
ክንፍን የተሸለምክ የምሕረት አባት
ዳቢሎስ አፈረ ስትታይ በዳሞት
ዘማሪ ዲ/በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
ተክለሃይማኖት ጻድቅ
ስምህ ያድናል ከመውደቅ
ተክለሃይማኖት ጻድቅ
ስምህ ያድናል ከመድቀቅ
ቅኔ ልቀኝልህ ልዘምር በደስታ
አይቻለሁ በአንተ ችግሬ ሲፈታ[፪]
ስጋዬ ታሞብኝ ተጨንቃ ሕይወቴ
በስምህ ታመንኩኝ ተክለ አብ አባቴ
ከቤቴ ሳልወጣ ገዳምክን ሳስበው
መከራው አልፎልኝ በአይኔ አይቻለሁ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
አገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት
ስፍገመገም ልወድቅ በዝቶ ፈተናዬ
ደገፍከኝ አባቴ መተህ መመኪያዬ
ተስፋዬ ተሟጦ አይኔን እንባ ሞልቶ
ጸበልህ ሲነካኝ አገኘሁኝ ድህነት
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት
በተስፋ ሞልተኸኝ ስመጣ ከደጅህ
የበዛው ሕመሜ ሸፈንከው በጽድቅህ
ሞኝ ነው ይሉኛል ሳያውቁ አባቴ
መሰከርኩ ልጅህ በርትቶ ጉልበቴ
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት
ከችግር ከሐዘን ያመነህ ይወጣል
አይኑ ተከፍቶለት አብርቶ ይታያል
በሰው እጅ የመጣ ነበር ይሆን እና
ድኖ ይመለሳል በጽድቅህ ገናና
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት
የደብረ አስቦቱ የኢቲሳው አባት
መሰከረች ዛሬ ጽላልሽ በእውነት
ክንፍን የተሸለምክ የምሕረት አባት
ዳቢሎስ አፈረ ስትታይ በዳሞት
ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ተክለሃይማኖት
ሀገሬ ትፈወስ ይታሰር አጋንንት
ዘማሪ ዲ/በሱፍቃድ አንዳርጋቸው
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
28.03.202518:13
♡ አልዓዛር ይነሳ ♡
የበደል እስራት መግነዙን ፍቱለት
ህይወትን ያገኛት ጽድቅን ይኑርበት
ሞት መሻሩን አውቆ ከሞት በላይ ይቁም
በእግዚአብሔር ቸርነት ልቦናው ይታመን
በደሉ ቢበዛ ልቦናው ቢከብድም
ከአምላኩ ቸርነት በሚዛን አይበልጥም
ኃጢአቱን ተናዞ ንስሀ እንዲገባ
መጽአትን አሳዩት የፍቅርን እንባ
የሚያስደንቅ ብርህን አይቶ ይመላለስ
አዲሲቷን ምድር በንስሀ ይውረስ
ካህናት አጽናኑ ህዝብን በፍቅር ቃል
ሞት እውነት አይደለም በቃሉ ተሽሯል
በአምላክ ብርሀን ይመላለስ አይቶ
ንስሀ ይጠበው እንዲታይ አብርቶ
ንጹህ ልብስ አልብሱት ነብሱ ሀሴት ታድርግ
እሱም ህያው ይሁን በሰዎች መአረግ
ከመቃብር ይውጣ ጌታ የጠራው ነው
ከህይወት እንጀራ ማን ነው የሚያግደው
ብርሀን ክርስቶስ ለሱ ተሰውቷል
ስጋው ለእርሱ እኮ ነው ማን ይመገበዋል
ብርሀን ክርስቶስ አላዛር ይለዋል
መቃብሩን ሺሮ አዲስ ፍጥረት ሆኗል
ማን ነው ሙት የሚለው ከእንግዲህ በኋላ
ተጠርቷል በጌታ ወደ ፍጹም ተድላ
ሊቀ መዘመራን ይልማ ኃይሉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አልዓዛር ይነሳ መግንነዙን ፍቱለት
በጽድቅ አደባባይ ይመላለስበት
ተስፋ ላለው ህይውት ልቡ ይነቃቃ
ነብሱ እንዳትወሰድ በአጋንንት ተሰርቃ
የበደል እስራት መግነዙን ፍቱለት
ህይወትን ያገኛት ጽድቅን ይኑርበት
ሞት መሻሩን አውቆ ከሞት በላይ ይቁም
በእግዚአብሔር ቸርነት ልቦናው ይታመን
አዝ= = = = =
በደሉ ቢበዛ ልቦናው ቢከብድም
ከአምላኩ ቸርነት በሚዛን አይበልጥም
ኃጢአቱን ተናዞ ንስሀ እንዲገባ
መጽአትን አሳዩት የፍቅርን እንባ
አዝ= = = = =
የሚያስደንቅ ብርህን አይቶ ይመላለስ
አዲሲቷን ምድር በንስሀ ይውረስ
ካህናት አጽናኑ ህዝብን በፍቅር ቃል
ሞት እውነት አይደለም በቃሉ ተሽሯል
አዝ= = = = =
በአምላክ ብርሀን ይመላለስ አይቶ
ንስሀ ይጠበው እንዲታይ አብርቶ
ንጹህ ልብስ አልብሱት ነብሱ ሀሴት ታድርግ
እሱም ህያው ይሁን በሰዎች መአረግ
አዝ= = = = =
ከመቃብር ይውጣ ጌታ የጠራው ነው
ከህይወት እንጀራ ማን ነው የሚያግደው
ብርሀን ክርስቶስ ለሱ ተሰውቷል
ስጋው ለእርሱ እኮ ነው ማን ይመገበዋል
አዝ= = = = =
ብርሀን ክርስቶስ አላዛር ይለዋል
መቃብሩን ሺሮ አዲስ ፍጥረት ሆኗል
ማን ነው ሙት የሚለው ከእንግዲህ በኋላ
ተጠርቷል በጌታ ወደ ፍጹም ተድላ
ሊቀ መዘመራን ይልማ ኃይሉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
28.03.202504:56
✞ አብሰራ ገብርኤል ✞
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
ወይቤላ (፪) ትወልዲ ወልድ
ሚካኤል መላዕክ በክነፍ ፆራ
መንጦላዕት ደመና ሰወራ
ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ተወልደ ወልድ እምኔሐ
ገብርኤል ማርያም አበሰራት አበሰራት
ወንድ ልጅም ትወልጃለሺ አላት
ሚካኤል መላዕክ በክንፋ ከለላት
የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም
ወልዳልናለችና
አዳም በጥፋቱ ከገነት ሲባረር
በሚካኤል ክንፎች ቀድሞ አይቶሽ ነበር
ሔዋንን ሲጠራት ሕይወቴ ነሽ አላት
እንደሚድን አውቆ ድንግል በአንች ምክንያት
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
እግዚአብሔር የላከው የከበረው መላዕክ
ድንግል ሆይ ለክብርሽ ዐየን ሲንበረከክ
በፍቅር በትህትና በፍፁም ሰላምታ
የጌታ ሰው መሆን የነገረሽ በደስታ
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
ደስተኛዬቷ ሆይ ደስ ይበልሽ ድንግል
የአብ ቃል ክርስቶስ ሥጋሽን ይለብሳል
አንቺም ትይዋለሽ ስሙን ኢየሱስ
መድኋኒት ነውና ለሥጋ ወነፍስ
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ
አንደ ዘኬርያስ ሳትጠራጠሪ
ይሁነኒ ብለሽ ቃልን ተቀበልሽ
ከፍጥረት ማነው አንቺ የሚመስልሽ
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልና
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አብሰራ ገብርኤል ለማርያም
ወይቤላ (፪) ትወልዲ ወልድ
ሚካኤል መላዕክ በክነፍ ፆራ
መንጦላዕት ደመና ሰወራ
ንፅህት በድንግልና አልባቲ ሙስና
ተወልደ ወልድ እምኔሐ
ገብርኤል ማርያም አበሰራት አበሰራት
ወንድ ልጅም ትወልጃለሺ አላት
ሚካኤል መላዕክ በክንፋ ከለላት
የሰማይ መጋረጃውን ሸፈናት
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም
ወልዳልናለችና
አዳም በጥፋቱ ከገነት ሲባረር
በሚካኤል ክንፎች ቀድሞ አይቶሽ ነበር
ሔዋንን ሲጠራት ሕይወቴ ነሽ አላት
እንደሚድን አውቆ ድንግል በአንች ምክንያት
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
እግዚአብሔር የላከው የከበረው መላዕክ
ድንግል ሆይ ለክብርሽ ዐየን ሲንበረከክ
በፍቅር በትህትና በፍፁም ሰላምታ
የጌታ ሰው መሆን የነገረሽ በደስታ
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
ደስተኛዬቷ ሆይ ደስ ይበልሽ ድንግል
የአብ ቃል ክርስቶስ ሥጋሽን ይለብሳል
አንቺም ትይዋለሽ ስሙን ኢየሱስ
መድኋኒት ነውና ለሥጋ ወነፍስ
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልናለችና
አንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ
አንደ ዘኬርያስ ሳትጠራጠሪ
ይሁነኒ ብለሽ ቃልን ተቀበልሽ
ከፍጥረት ማነው አንቺ የሚመስልሽ
ንፅህት ናትና በድንግልና (፪)
ጥፋት የለባትምና ወንድ ልጅም ወልዳልና
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


24.03.202518:03
❣️🌹❣️...........❶➏🕯
❶➏...ኪዳነ ምሕረት እናቴ አለው ትበላችሁ ❣️
..........................................................
ልጆችሽ ስለሆን፥ እናቴ እንላለን፤
እስከ ዘለዓለም፥ ገና እንወድሻለን።
ከወዴት ይገኛል፥ እንዳንቺ ያለ እናት፤
ዘውትር እንላለን፥ ኪዳነ ምሕረት።
❶➏...ኪዳነ ምሕረት እናቴ አለው ትበላችሁ ❣️
..........................................................
20.04.202510:30
♡ ይኸው ተነሳ ደስ ይበለን ♡
ኃያል ነው እርሱ ዘላዓለማዊ
የሁሉ ጌታ ሞትን የዋጠው
ድልን ያወጀው የማይረታ
ይኸው ተነሳ ደስ ይበለን ❤️
.
.
.
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
ኃያል ነው እርሱ ዘላዓለማዊ
የሁሉ ጌታ ሞትን የዋጠው
ድልን ያወጀው የማይረታ
ይኸው ተነሳ ደስ ይበለን ❤️
.
.
.
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
31.03.202514:40
ፀሐይ ዘልዳ ኮከብ ዘልዳ ዘልዳ ንጉሥ ነዓ ጊዮርጊስ
እምነ ሠናያት ኩሎ እለ ውስተ ባሕር ወየብስ
ሶበ ነጸርኩ በሃሢሥ ዘከማከ አልቦ ጊዮርጊስ
♡ ፀሐይ ዘልዳ ♡
እምነ ሠናያት ኩሎ እለ ውስተ ባሕር ወየብስ(፪)
ሶበ ነጸርኩ በሃሢሥ ዘከማከ አልቦ ጊዮርጊስ(፪)
የመከራ ገፈት ቀምሳ ለሰጠችህ
ልጅ ሆነሃልና ለማርያም እናትህ
ስምዐ ክርስቶስ አርአያ ሰማዕታት
ሆነህ የተሰየምክ የሰማዕታት አባት
አዝ= = = = =
የገድልህን ነገር ጆሮአችን ሲሰማ
ልባችን ይቀልጣል ለጽናትህ ዜና
የጌታህን ትዕግሥት ቀራንዮን እያሰብክ
በወጣትነትህ ተጋድሎህን ፈጸምክ
አዝ= = = = =
በጭንቅ በመከራ ጽናትህ ሲፈተን
ከአምላክ ተምረህ ቁጣን ሳትናገር
ሁሉን ስለ ጌታ ችለህ ታግሰሃል
የብርሃን አክሊልን በሰማይ ደፍተሃል
አዝ= = = = =
ስዕለ ገጽህን ዘወትር እያየን
ነገረ ገድልህን ሁልጊዜ እያደነቅን
ፍቅርህ በልባችን ስለተሳለብን
ይኸው አንዘምራለን ጊዮርጊስ እያልን
መዝሙር
ደብረብርሃን ሰ/ት/ቤት
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gtmoch
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
27.03.202504:19
♡ አምላኬ መቅደስህን ♡
አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ
በውስጡ ለመኖር እናፍቃለሁ
ሰላም እንድሆን በቤት በደጄ
ወደ ማደርያህ ልምጣ ማልጄ
ተመለሰልኝ ደስታ ሰላሜ
ቤትህ መጥቼ በመሳለሜ
ስጋዬም ዳነ ታደሰች ነፍሴ
ወደ ማደርያህ በመግስገሴ
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
የሰማይ ዜማ የሚሰማባት
ሰዎች ከሀዘን የሚጽናኑባት
የጸሎት ስፍራ የአምልኮት ቦታ
ቤተክርስትያን ውድዋ ስጦታ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አምላኬ መቅደስህን እወደዋለሁ
በውስጡ ለመኖር እናፍቃለሁ
ሰላም እንድሆን በቤት በደጄ
ወደ ማደርያህ ልምጣ ማልጄ
እንድሰለጥን በመላእክት ዜማ
የሕወትን ቃል ከአፍህ ልስማ
እንዲቀል ሸክሜ ከትክሻዬ
ወደ ዙፋንህ ልቅረብ ጌታዬ
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
ተመለሰልኝ ደስታ ሰላሜ
ቤትህ መጥቼ በመሳለሜ
ስጋዬም ዳነ ታደሰች ነፍሴ
ወደ ማደርያህ በመግስገሴ
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
የተማርኩባት የሰላም ቅኔ
የተባረከው እድሜ ዘመኔ
የተለወጠው ሞቴ በሕይወት
እኔ እናፍቃለሁ የእግዚያብሔርን ቤት
መልካም በሚልዋት በመቅደስህ
ሳመልክህ ልኑር ስማጸንህ
የሰማይ ዜማ የሚሰማባት
ሰዎች ከሀዘን የሚጽናኑባት
የጸሎት ስፍራ የአምልኮት ቦታ
ቤተክርስትያን ውድዋ ስጦታ
ዘማሪ ገ/ዮሐንስ ገ/ማርያም
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
24.03.202514:26
✞ አልረሳውም ያንን ዕለት ✞
ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝ እህት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
በቅረዜ ሲጨልም ስጓዝ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝምብዬ አለቅሳለሁ
አይኔን አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዋዊ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው እረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠመኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳኩኝ ከመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ
መዝሙር
ዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አልረሳውም ያንን ዕለት
አልዘነጋው ያን ደግነት
እናቴ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
እምዬ ሆይ ምልሽ ኪዳነ ምሕረት
ስላለኝ ነው ምክንያት/፪/
ለሠው ተናግሬ ያልተረዳኝ ሰው
ዕንባዬ በምሬት ከዓይኔ የሚፈሰው
የቤቴን ገመና ሁሉን ስነግርሽ
አዛኝ እህት ነሽና እራራልኝ ልብሽ
አረሳው መቼም የአንቺን ደግነት/፪/
ውለታ አለብኝ ኪዳነ ምሕረት
አዝ= = = = =
ልቤ በሐዘን ጠቁሮ ውስጤ እየደማ
በቅረዜ ሲጨልም ስጓዝ በጨለማ
በራፌን ዘግቼ ዝምብዬ አለቅሳለሁ
አይኔን አቀርቅሬ እናቴ እልሻለሁ
ዘንበል አልሽልኝ ሠምተሽ ፆሎቴን/፪/
አልተጸየፍሽም ብቸኝነቴን
አዝ= = = = =
እናት የለኝ ብዬ ከቶም አልከፋ
እኔስ አይቻለሁ ስትሞይኝ በተስፋ
ምድራዋዊ እናቴ ለጊዜው ነው ፍቅሯ
ያንቺስ ግን ልዩ ነው እረ ስንቱን ላውራ
ማርያም ማርያም ብል አልሠለችሽ/፪/
በልቤ ጽላት ስለ ታተምሽ
አዝ= = = = =
ሲረበኝ መጥተሻል ሲጠመኝ ደርሰሻል
ለጎደለው ቤቴ በረከት ሆነሻል
ጭንቄም ቀለለልኝ ሐዘኔም ራቀ
ያስጨነቀኝ ጠላት ራሱ ተጨነቀ
መዳኒት ወልደሽ ዳኩኝ ከመሜ/፪/
ይኸው ዘመርኩኝ በምልጃሽ ቆሜ
መዝሙር
ዘማሪ ዲ/ን ሙሉቀን ከበደ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


19.04.202515:15
❣️❣️❣️
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''
ውድ የመዝሙር ግጥሞች ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
ሚያዚያ 11/2017 ዓ.ም
''ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ▸ በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ፤ አሰሮ ለሰይጣን አግአዞ ለአዳም ፤ ሰላም ▸ እምይእዜሰ ፤ ኮነ ▸ ፍስሐ ወሰላም''
''ክርስቶስ በታላቅ በኃይልና ስልጣን ከሙታን ተነሳ ፤ ሰይጣንን አሰረው አዳምንም ነጻ አወጣው ፤ ስለዚህም ከእንግዲህ ወዲህ ፍፁም ሰላም እና ደስታ ሆነ''
ውድ የመዝሙር ግጥሞች ቻናል ቤተሰቦች በሙሉ ፥ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የአንድነት በዓል ይሁንልን አሜን።
ሚያዚያ 11/2017 ዓ.ም
01.04.202517:45
♡ አባ ተክለሃይማኖት ♡
ለእውነት የመነነ ጽኑ ተጋዳይ
የጸጋ እንጀራ የማያልቅ ሲሳይ
በረከተ ብዙ የደሃ ድልባቸው
ቢበሉት ቢጠጡት የማያልቅባቸው
ከምድር እስከ ሰማይ የተተከለ ዐምድ
ሥላሴ ዘንድ ቀርቦ ለእውነት የሚማልድ
ቅዱስ ተክለሃይማኖት በሁሉ የሚወደድ
ጥግ ላደረጉት ሞገስ የዓለም ዘውድ
በተዋህዶ አምኖ ተዋህደን የኖረ
የምድራችን ብርሃን ጨለማን ያስቀረ
ዳግማዊ መቃርስ ለጽድቅ የጀገነ
ኢትዮጲያን አድኖ ለዓለም ጨው የሆነ
ሰይጣን ክህደትን መንቆሮ ያጠፋ
በኪዳኑ የሚያኖር የድኩማን ተሰፋ
የዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁ
የዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁ
መዝሙር
መምህር ፍስሀፅዮን ካሳ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
የእምነት ገበሬ መልካም ዘር የዘራ
በአምላኩ ታምኖ መቶ እጥፍ ያፈራ
አባ ተክለሃይማኖት የነፍሳችን ጌጥ
በጸና ኪዳኑ ምሕረትን የሚያሰጥ/2/
ለእውነት የመነነ ጽኑ ተጋዳይ
የጸጋ እንጀራ የማያልቅ ሲሳይ
በረከተ ብዙ የደሃ ድልባቸው
ቢበሉት ቢጠጡት የማያልቅባቸው
አዝ= = = = =
ከምድር እስከ ሰማይ የተተከለ ዐምድ
ሥላሴ ዘንድ ቀርቦ ለእውነት የሚማልድ
ቅዱስ ተክለሃይማኖት በሁሉ የሚወደድ
ጥግ ላደረጉት ሞገስ የዓለም ዘውድ
አዝ= = = = =
በተዋህዶ አምኖ ተዋህደን የኖረ
የምድራችን ብርሃን ጨለማን ያስቀረ
ዳግማዊ መቃርስ ለጽድቅ የጀገነ
ኢትዮጲያን አድኖ ለዓለም ጨው የሆነ
አዝ= = = = =
ሰይጣን ክህደትን መንቆሮ ያጠፋ
በኪዳኑ የሚያኖር የድኩማን ተሰፋ
የዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁ
የዓለም ፀሐይ ነው የተመረጠ ዕንቁ
መዝሙር
መምህር ፍስሀፅዮን ካሳ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


30.03.202514:44
🌷እንኳን ለዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት ገብር ኄር እግዚአብሔር አምላክ በሰላም አደረሰን። መልካም ዕለት ሰንበት (ገብር ኄር)ና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@yemezmur_gtmoch
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
፨🌸፨🌸፨🌸፨🌸፨🌸፨🌸፨
28.03.202505:12
♡ ከሚነደው እሳት ♡
ናቡከደነፆር መንፈሱ ታውኳል
ህልሙን የሚፈታ ባለ ራዕይ ሽቷል
የከለዳውያን አስማት ተዘለፈ
በሰማዩ ሚስጥር ገብርኤል ህይወቴን ከሞት አተረፈ/፪/
ጠላት የለኮሰው የፈተናው ችቦ
በነብሴ አላለፈም ስጋዬን ለብልቦ
ከባቢሎን ባህር ተርፋለች ህይወቴ
የጌታ ባለሟል በምልጃው ጠላትን ከልሎኝ አባቴ/፪/
ዘማሪት መቅደስ ማርዬ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
ከሚነደው እሳት ነበልባል /፪/
ያወጣኝ እርሱ ነው የታደገኝ ፈጥኖ ገብርኤል/፪/
ናቡከደነፆር መንፈሱ ታውኳል
ህልሙን የሚፈታ ባለ ራዕይ ሽቷል
የከለዳውያን አስማት ተዘለፈ
በሰማዩ ሚስጥር ገብርኤል ህይወቴን ከሞት አተረፈ/፪/
የእስረኞቹ አለቃ አስፋኒስ ተገርሞ
ሽብሸባዬን አየ ከሳቱ ዳር ቆሞ
የአማልክትን ልጅም አይለይም ንጉሱ
አምላከ ሰብ መልአክ ከቶኑ ሀያሉ ታድጎኛል እሱ/፪/
ጠላት የለኮሰው የፈተናው ችቦ
በነብሴ አላለፈም ስጋዬን ለብልቦ
ከባቢሎን ባህር ተርፋለች ህይወቴ
የጌታ ባለሟል በምልጃው ጠላትን ከልሎኝ አባቴ/፪/
የውሀው መፍለቅለቅ ልቤን አያዝለም
አለም መዳን ቢሆን እምነቴን አይንድም
ቂርቆስ እየሉጣን ከፍል እንዳዳነ
ደመናን ሰንጥቆ ገብርኤል ከጥፈት ሊያድነኝ ፈጠነ/፪/
ዘማሪት መቅደስ ማርዬ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


26.03.202504:42
“እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም” አላቸው። ዮሐንስ 8:12
🌸እንደምን አደራችሁ መልካም ቀን ይሁንልን።
24.03.202514:20
♡ ኪዳነ ምሕረት ♡
የከበረ ሆነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለስምሽ ዘምሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በሰማይሽ ፀሐይ
ስለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሰሰ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሰ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በልጅሽ ነው የነፍሴ ጽናቱ(፪)
ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያለአንቺ እናቴ
ተዋብኩብሽ ገጼ በአንቺ አበራ
አንደበቴ ስምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫዬ ከፈርዖን ቀንበር
ከእንግዲህማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ(፪)
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @maedot_ze_orthodox
💛 @maedot_ze_orthodox
❤️ @maedot_ze_orthodox
ኪዳነምህረት የእረፍቴ እናት
ሰላም ሆነ ባንቺ አማላጅነት
ንጽህት ድንኳን በእምነት ያጌጥኩብሽ
ሰላም ሆነ በአማኑኤል ልጅሽ (፪)
የብርሃን ዝናር ባይኖረኝም
በንጉሥ ፊት ተሸልሜ ብቆም
በልጅሽ ነው ውበቴ ማማሩ
በምልጃሽ ነው ስሜ መቀየሩ
በልቤ ላይ ተነበበ ልጅሽ
አሁን ስሜ ተጠርቷል በልጅሽ
ከታች በምድር እስከ ሰማይ ደረስ
ድርሻዬ ነው ስምሽን ማወደስ(፪)
አዝ= = = = =
የከበረ ሆነሽ ንግግሬ
ቅኔ አነሳሁ ለስምሽ ዘምሬ
እንደ ዝግባ ከፍ ብዬ ብታይ
ወጥቶልኝ ነው በሰማይሽ ፀሐይ
ስለ ምልጃሽ ዘይቱ ፈሰሰ
አንቺን ይዤ ሙሽራው ደረሰ
ቀንዲሌ ነሽ ድንግል አዛኝቱ
በልጅሽ ነው የነፍሴ ጽናቱ(፪)
አዝ= = = = =
ከኤልያብ ቢደምቅ ደም ግባቴ
ማን ሊመርጠኝ ያለአንቺ እናቴ
ተዋብኩብሽ ገጼ በአንቺ አበራ
አንደበቴ ስምሽን ሲጠራ
እንደ ሙሴ እንደ አሮን በትር
ማምለጫዬ ከፈርዖን ቀንበር
ከእንግዲህማ እኔ እንዴት አዝናለሁ
አማላጄ አንቺን ይዤሻለሁ(፪)
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
💚 @maedot_ze_orthodox
💛 @maedot_ze_orthodox
❤️ @maedot_ze_orthodox
15.04.202519:50
♡ ቀራኒዮ አየሁት ♡
ቁስሉ ፈውሶኝ ጌታዬ
ንጹህ ደሙ ነው ዋጋዬ
የኔ አይደለሁም የራሴ
ለዋጀኝ አለኝ ውዳሴ
አዝ =====
ልብሴ ነው ለኔ እርቃኑ
ደስታን የሰጠኝ ማዳኑ
የኔን መሰደድ ተሰዶ
በክብር አስጌጠኝ ተዋርዶ
አዝ ======
የተቀበለው መከራ
የኔን ጨለማ አበራ
እንባየን ገድቦት ደሙ
በልቤ ሞልቷል ሰላሙ
አዝ =====
ፍቅር ያደከመው ኃይለኛ
ይጠብቀኛል ሳይተኛ
ቀድሞ እየወጣ በሰልፌ
ዛሬም አለሁኝ አትርፌ
አዝ ======
በምድረ በዳ መንጭቶ
ውሃ ሆነልኝ ተጠምቶ
ስፍራ አዘጋጄ በሰማይ
ጩኸቴን ጨኸ መስቀል ላይ
አዝ ======
ሰርጓጉት ሸለቆ ሞልቷል
አጥፊውም ሳይነካኝ አልፏል
ቀራንዮ ላይ ብቃቴን
አግኝቸዋለሁ ንጋቴን
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
ቀራንዮ አየሁት ቀራንዮ አየሁት
የተጠማሁት ጌታን አገኘሁት
እረፍት ሆኖልኛል ሸክሜን ተሸክሞ
ሕይወቱን በሰጠኝ የኔን ሕይወት ታሞ
ቁስሉ ፈውሶኝ ጌታዬ
ንጹህ ደሙ ነው ዋጋዬ
የኔ አይደለሁም የራሴ
ለዋጀኝ አለኝ ውዳሴ
አዝ =====
ልብሴ ነው ለኔ እርቃኑ
ደስታን የሰጠኝ ማዳኑ
የኔን መሰደድ ተሰዶ
በክብር አስጌጠኝ ተዋርዶ
አዝ ======
የተቀበለው መከራ
የኔን ጨለማ አበራ
እንባየን ገድቦት ደሙ
በልቤ ሞልቷል ሰላሙ
አዝ =====
ፍቅር ያደከመው ኃይለኛ
ይጠብቀኛል ሳይተኛ
ቀድሞ እየወጣ በሰልፌ
ዛሬም አለሁኝ አትርፌ
አዝ ======
በምድረ በዳ መንጭቶ
ውሃ ሆነልኝ ተጠምቶ
ስፍራ አዘጋጄ በሰማይ
ጩኸቴን ጨኸ መስቀል ላይ
አዝ ======
ሰርጓጉት ሸለቆ ሞልቷል
አጥፊውም ሳይነካኝ አልፏል
ቀራንዮ ላይ ብቃቴን
አግኝቸዋለሁ ንጋቴን
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
01.04.202517:45
♡ አረሳት ኢትዮጵያን ♡
ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠ ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ
ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት
ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ
ሊቀ መዘመራን ይልማ ኃይሉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አረሳት ኢትዮጲያን በእርፈ መስቀል
አባ ተክለሃይማኖት ሰባኪ ወንጌል
የእግዚአብሔር ሰው ነው ተወዳጅ በ ሰማይ
የተረማመደ በጽድቅ አደባባይ
ፈውስና ጸሎቱ ቃሉ የተሰማ
ወንጌል የሰበከ በገጠ ከተማ
የእቲሳው ኮከብ የደብረ አስቦቱ
ለወንጌል ተዋጋች ንጽህት ሕይወቱ
አዝ= = = = =
ፋናው እስከ ዛሬ ሲያበራ የኖረ
የእቲሳው አባት ፍስሐጽዮን
እግዚአርያ እናቱ ማህፀነ ብሩክ
ወለደች ኮከብን ሲኦልን የሚያውክ
አዝ= = = = =
ዲያቢሎስ እስካሁን ስሙ ሲጠራበት
ሲረገጥ ይኖራል በእሳት ሰንሰለት
አዲስ ሐዋርያ የኢትዮጵያ አባት
ደጋ ና ቆላውን በመስቀል ባረካት
አዝ= = = = =
ምንጩና ፏፏቴው ተራራው ቅዱስ ነው
የአባታችን መስቀል ጽኑ ስለነካው
የተራመደበት የዳሰሰው ሁሉ
ድውይ ይፈውሳል ሳርና ቅጠሉ
ሊቀ መዘመራን ይልማ ኃይሉ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


28.03.202520:26
🌷መጋቢት [20] እንኳን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛርን ከሞት ላስነሳበት ደግ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። የጌታችን ቸርነቱ ፡ የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን።
❤️:::::::::::✝️:::::::::::❤️
28.03.202505:09
♡ ገብርኤል ነው እሱ ♡
ቂርቆስ ኢየሉጣ ከእሳት ሲጣሉ
ውሃ ሆነ ጠፋ ነበልባሉ /፪/
ሠለስቱ ደቂቅም ከእሳት ሲጣሉ
ውሃ ሆነ ጠፋ ነበልባሉ /፪/
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
ገብርኤል ነው እሱ አስደሳች መልአክ
አብሳሪሃ ለእመ አምላክ /፪/
ቂርቆስ ኢየሉጣ ከእሳት ሲጣሉ
ውሃ ሆነ ጠፋ ነበልባሉ /፪/
ቤተ መቅደስ ስትኖር ድንግል እመቤት
አበሰራት የአምላክን ልደት /፪/
ሠለስቱ ደቂቅም ከእሳት ሲጣሉ
ውሃ ሆነ ጠፋ ነበልባሉ /፪/
ሠለስቱ ደቂቅን ከእሳት ያዳነ
ገብርኤል ዛሬም ያድህነነ /፪/
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
26.03.202504:22
♡ አትንገሩት ያውቀኛል ♡
ፊልጶስ ሳይጠራኝ ገና ሳልቆም ፊቱ
ከበለስ ስር ሳለው ያውቀኛል ከጥንቱ
መካሪ አያሻውም ሁሉን ያውቃልና
ከሳሽ ሆይ ተመለስ ድንጋዩን ጣልና
ታናሹ ተቀባ ታላቆቹ ሳሉ
ለምን እንዲህ ሆነ ስህተት ነው አትበሉ
ለክብር የጠራኝ ከባህር ዳር ቆሞ
ሶስቴ እንደምክደው ያውቃል አስቀድሞ
ሀጢያተኟነቱን ሳያውቅ ገባ ቤቱ
ብላችሁ አትሙት በዝቶ ነው ምህረቱ
የአባቴን ንብረት ባባክን ፈጽሜ
እንዴት ልጅ ይሆናል አትበል ወንድሜ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አትንገሩት ያውቀኛል/4/
ስራዬ በፊቱ መቼ ተሰውሯል
አትንገሩት ያውቀኛል
ፊልጶስ ሳይጠራኝ ገና ሳልቆም ፊቱ
ከበለስ ስር ሳለው ያውቀኛል ከጥንቱ
መካሪ አያሻውም ሁሉን ያውቃልና
ከሳሽ ሆይ ተመለስ ድንጋዩን ጣልና
ታናሹ ተቀባ ታላቆቹ ሳሉ
ለምን እንዲህ ሆነ ስህተት ነው አትበሉ
ለክብር የጠራኝ ከባህር ዳር ቆሞ
ሶስቴ እንደምክደው ያውቃል አስቀድሞ
ሀጢያተኟነቱን ሳያውቅ ገባ ቤቱ
ብላችሁ አትሙት በዝቶ ነው ምህረቱ
የአባቴን ንብረት ባባክን ፈጽሜ
እንዴት ልጅ ይሆናል አትበል ወንድሜ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
24.03.202504:44
♡ አኑሮኛል ቸርነትህ ♡
ያቺ ፈዋሽ አዳኝ እጅህ
ዛሬም ለኔ ተዘርግታ
በሐጢያት ርቄ እንዳልጓዝ
አስረኸኛል በውለታ
ደግሞስ ህይወት ምርጫ ቢሆን
ካንተ ወደማን ይኬዳል
አባቴ ፍቅርህ እኮ
ጌታዬ ፍቅርህ እኮ
አለምን ያስክዳል
መቅደስህን ተጠግቼ
አይቻለሁ ብዙ ነገር
በልቤ ውስጥ ያስቀመጥኩት
እንዲህ ለሰው ማይነገር
ግን የሆነው ሁሉም ሆኖ
የለም ዛሬ ያላረፈ
የመከራው እሳት
የፈተናው እሳት
ባንተ እየታለፈ
ስነፈርቅ ሳለቅስብህ
እሺ እያልከኝ ሁሉም ሆነ
ማይሆንለት ነገር የለም
ለካስ ባንተ የታመነ
መቸኮሌ መጣደፌ
አምላኬ ሆይ በከንቱ ነው
መፈፀሙ ላይቀር/2/
ጌታዬ አንተ ያልከው
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
አኑሮኛል ቸርነትህ ልክ የሌለው ደግነትህ
እንዳንተ አይነት ከየት ይገኛል
ሁሉም ነገር ትዝ ይለኛል/2/
ያቺ ፈዋሽ አዳኝ እጅህ
ዛሬም ለኔ ተዘርግታ
በሐጢያት ርቄ እንዳልጓዝ
አስረኸኛል በውለታ
ደግሞስ ህይወት ምርጫ ቢሆን
ካንተ ወደማን ይኬዳል
አባቴ ፍቅርህ እኮ
ጌታዬ ፍቅርህ እኮ
አለምን ያስክዳል
ሞቼ ነበር ተቀብሬ
ጌታ ወደ እኔ ባትመጣ
አንተ ሞቴን ባትሞትልኝ
ወዴት ነበር የእኔ እጣ
ከንቱ ነበር ማንነቴ
ተሽናፊ ለዚች ዓለም
ግን አንተ የያዝከው
አባቴ የያዝከው
ይኖራል ዘላለም
መቅደስህን ተጠግቼ
አይቻለሁ ብዙ ነገር
በልቤ ውስጥ ያስቀመጥኩት
እንዲህ ለሰው ማይነገር
ግን የሆነው ሁሉም ሆኖ
የለም ዛሬ ያላረፈ
የመከራው እሳት
የፈተናው እሳት
ባንተ እየታለፈ
አይጠፋኝም ያ ፈገግታ
ልጄ ብለህ ያሳየህኝ
አመፀኛ መጥፎም ሆኜ
በትክሻህ ላይ ያኖርከኝ
እንዲህም አይነት ወዳጅ አለ
እየጠሉት የሚያፈቅር
ስሙም ኢየሱስ ነው/2/
የፅድቃችን ሚስጥር
ስነፈርቅ ሳለቅስብህ
እሺ እያልከኝ ሁሉም ሆነ
ማይሆንለት ነገር የለም
ለካስ ባንተ የታመነ
መቸኮሌ መጣደፌ
አምላኬ ሆይ በከንቱ ነው
መፈፀሙ ላይቀር/2/
ጌታዬ አንተ ያልከው
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
Паказана 1 - 24 з 62
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.