Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
💞መንታ ልቦች💞 avatar

💞መንታ ልቦች💞

♥️ይህ ነው ለእኔ ፍቅር 💟 ማለት፤
➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
➣ በንፁህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
➣ ይህ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
➤ ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴘʀᴏᴍᴏᴛɪᴏɴ ᴀɴᴅ ᴀᴅᴠᴇʀᴛɪsɪɴɢ 📩
@mihret_123
Рэйтынг TGlist
0
0
ТыпПрыватны
Вертыфікацыя
Не вертыфікаваны
Надзейнасць
Не надзейны
Размяшчэнне
МоваІншая
Дата стварэння каналаFeb 25, 2025
Дадана ў TGlist
Feb 06, 2025
Прыкрепленая група

Апошнія публікацыі ў групе "💞መንታ ልቦች💞"

የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው

1⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ
2⃣ ለወጣ  250 ብር ካርድ
3⃣ ለወጣ  100 ብር ካርድ

👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
Wallpaper ወይስ Profile ይፈልጋሉ? 😍
Выдалена20.04.202519:10
Пераслаў з:
LE
Learn English
➡️ እንግሊዝኛን በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ❔

👍 አዎን እፈልጋለሁ ካሉ
👌 እንግዲያውስ አሪፍ ቻናል ልጋብዛችሁ
❤️ ያለ ምንም ጥርጥር
ትወዱታለችሁ💯

📝 JOIN አድርጉና እንግሊዝኛን በአማርኛ ይማሩ።

የቻናሉ Link👇👇

t.me/English_Ethiopian/14946
t.me/English_Ethiopian/14946
t.me/English_Ethiopian/14946
Выдалена20.04.202519:10
የምትወዳትን ልጅ ስታገኝ የምታወራው ይጠፋብሀል ⁉️


👉ከስር ነበብ ነበብ አርገህ ፍጠንባት‼️

⚜ወንድ እስከሆንክ ድረስ ቀልጠፍ ማለት አለብህ‼️


😋 ከስር view የሚለውን በመጫን ያገኙታል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የቻናላችን ተከታታይ ለሆናችሁ እንዲሁም ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ❤️🙏

❤️መልካም የፋሲካ በዓል ❤️
@MENTA_LIBOCHE
@MENTA_LIBOCHE
Выдалена20.04.202518:18
😂😂ሁሌ ሳቅ😂😂
Выдалена20.04.202518:18
እንዴዴዴዴዴዴዴ ኧረ ፍጠኑ ጥያቄና መልስ ጀምረናል🔥🔥

✔️ ቀድሞ ለመለሱ 5 ሰዎች የካርድ ሽልማት አለ Request to Join ያድርጉ

  🚛 የአለማችን ብዙ ህዝብ ያላት ሀገር ማን ነች?
Выдалена20.04.202518:18
Пераслаў з:
Ei Du 💃 avatar
Ei Du 💃
🥰ለፕሮፋይል የሚሆኑ ገራሚ ገራሚ ፎቶዎችን ለማግኘት ከስር ጆይን ያድርጉ የፈለጉትን አይነት ያገኛሉ ይ🀄️ላ🀄️ሉን!👇

https://t.me/+UqU8zCoHqyw2NzQ0
❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል ሀያ (20)

.
ድሬ እውነተኛ ፍቅር እና መቻቻል የሚንፀባረቅባት ውብ ከተማ ነች። ሀገሬው ጭንቅ አይወድም። ጭንቀትም በአየሯ ላይ ቦታ የለውም በፈገግታና ፍቅር እየተባረረ ድንበሯን ጥሶ ይጠፋል።
ገና ከተማዋ ስገባ መንፈሱ የደስ ደስ ይሰጠኝ ጀምሯል።
ድሬ ፍቅር ፍቅር ትሸታለች።
.
ሁለት ሳምንታት ድሬን ዞርኩ ምንም ጠብ ያለ ነገር አላገኘውም። ወደ ጅማ መመለስ አልፈለግኩም።
ፍሌሜን አየዋት የሚለኝ ሰው አጣው።
ጀማ ሆኜ ሳስብ እንዲህም ተንከራትቼ የማጣት አልመሰለኝም ነበር። የበላት ጅብ አልጮህ ቢል ልቤ ቀቢፀ ተስፋውን ወደ መጥራቱ እያዘነበለ በነበረበት ሰሞን የሆነ ባለሱቅ ጋር ስለፍሌም ና ስለእኔ በደንብ አወጋን እሱም አሰብ አድርጎ ፍሌምን እንደሚያውቃት ነገር ግን ከቅርብ ወራት በፊት በድንገተኛ የመኪና አደጋ እንደሞተች እና እናትየው በህይወት እንዳሉ ነገረኝ።
ይህን ሲለኝ ሰማይ የተደፋብኝ ያህል ዞረብኝ የሰማውት ነገር ቅዠት እንጂ እውነት አልመስልህ አለኝ።
ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሆኜ ራሴን ጠላውት። ዛሬውኑ ድሬን ለቅቄ ለመሄድ ወሰንኩ። ግን ከዚህ ወዲህ ፍሌምን አጥቶ እንዴት ይኖራል? ዋ!!!
ግን ይሄ ሁላ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ፍሌም እናቷ ካልሞቱ እንዴት ደክመዋል ተብሎ ሲቀጥልም ሞተዋል ብለው ጠሯት? ' እያልኩ ስብሰከሰክ ድሬ ከገባሁ ወዲህ የተዋወቅኩት አንድ ጫታም እየተንከወከወ መጥቶ የሆነ ሽማግሌ ጋ ወሰደኝ።
ሽማግሌው ወንድምየው ታሞበት እያስታመመ መሆኑን እና እውነተኛዋ እኔ የምፈልጋት ፍሌም እዚሁ ጊቢው ውስጥ እንዳለች ነግሮኝ ፍሌሜን ሊያሳየኝ ወደ ጊቢው ይዞኝ ገባ።
ፍሌም አለች የተባለችበት ሰርቢስ ውስጥ ነበር።
ስገባ ቤቱ ጭልምልም ብሏል። እሷን የሚመስሉ አሮጊት ሴትዮ ወደ አልጋው ትራስጌ ቆመዋል።
አልጋው ላይ ፍሌም ተኝታለች። ቀረብ ብዬ ተመለከትኳት።መልኳ ገርጥቷል።ፍሌሜን አሟታል፤,የድሮ መልኳ ተለውጧል።
ገና ስታየኝ እያቃሰተች ተጣጥራ አቀፈችኝ ፤ እምባዋን አዘራች።
አምርሬ አለቀስኩ ከፈጣሪዬም ጋር ተዋቀስኩ። በእጅጉ አለም እንደከዳችኝ ገባኝ።
ሳለቅስ ሽማግሌው የታመመ ወንድምየው እንዳይረበሽ ለቅሶዬን አስቁሞ ያፅናናኝ ገባ።
የማየው ነገር ሁሉ እውነት አልመስልህ አለኝ።
.... እንደዋዛ ከፍሌም ጋር ለሶስት ቀናት ቆየው። ከሚያስታምሟት እናቷ ጋር ሆነን የማይገፉ ሶስት ቀናትን የዘላለም ያህል እየከበደኝ ገፋሁት።
ፍሌሜም እኔ ፊት ደስተኛ ሆና ለመታየት ፈገግ ትላለች። ያ ውብ ዲንፕሏ ድምቀቱ ጠፍቶ የበርባሮስ ጉድጓድ መስሏል።

​​✎ ክፍል ሀያ አንድ (21) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
old GROUP መግዛት የሚፈልግ INBOX 📩@mihret_123
📩For spam:-
@Menta_liboche_bot
Выдалена19.04.202519:44
Пераслаў з:
BE
betting
🙏ከፍቶኛል🙏
Выдалена19.04.202519:44
Выдалена19.04.202500:03
Пераслаў з:
BE
betting
ሃናንን በጣም እወዳት ነበር እሷም እንደዛው ለዛ ነው ትምህርት ላይ እያለን ኒካህ ያሰርነው።ከኔ ይበልጥ የሷ ፍቅር ከፍ ይል ስለነበር ነፃነቴን አሳጣቺኝ በ ቀን ከ 10ጊዜ በላይ ትደውላለች ምሳ ፣ ቁርስ ፣ እራት ፣ መክሰስ ጭምር መብላቴን ታረጋግጣለች። ሰለቸኝ!!

አንድ ቀን እንቅልፌን ልተኛ እየተዘጋጀው እያለ ስልኬ ላይ መልዕክት ገባ ሃናን ነበረች ቀን ስላወራን መልዕክቱን ሳልከፍተው ተኛው።
ጠዋት ስነሳ እናቴ እያለቀሰች ትቀሰቅሰኛለች ምን እንደሆነች ስጠይቃት የ ሃናን እናት ደውላ እንደነበር እና ማታ ...read more

📍ሙሉ ለማንበብ  📥 ይጫኑ
Выдалена19.04.202500:03
የምትወዳትን ልጅ ስታገኝ የምታወራው ይጠፋብሀል ⁉️


👉ከስር ነበብ ነበብ አርገህ ፍጠንባት‼️

⚜ወንድ እስከሆንክ ድረስ ቀልጠፍ ማለት አለብህ‼️


😋 ከስር view የሚለውን በመጫን ያገኙታል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ ዘጠኝ (19)
.
.... ብላ ልትቀጥል ስትል እምባ ተናነቃት። አምቃ የያዘቸውን ለቅሶ አፈነዳችው። እየተንሰቀሰቀች ወጥታ ሄደች....
እናቴ ግራ ገባት። ልትቆጣኝ አልወደደችም። እንድደነግጥ አልፈለገችም።
"የእኔ ጌታ ትንሽ ምግብ አትበላም?"አለች አይኗን ቡዝዝ አድርጋ እየተመለከተችኝ። በግምባሯ ላይ የተጋደሙትን እጥፋቶች ስመለከት በትልልቅ ችግር ውስጥ አላሳልፍ ብሎ የተጋደመ ትልቅ ግንድ ያየው መሰለኝ።
በረጅሙ ተንፍሼ እመባዬን እያበስኩ "በቃኝ እማ!" አልኳት።
"ግሩም ልጄ ምነው አሳቀቅከን ምነው ስቃዬን በቃሽ ብትለኝ ?
እህትህንም ሰላም አልሰጣሃትም! ተሰቃየች እኮ ጌታዬ እኔስ ባማጥኩህ በወለድኩህ ልጎዳ እህትን ምነው ልጄ!?
የኔ ጌታ ፈተናህን ተወው ይቅር ግን አንዴ ብቻ ተጣጥበህ ልብስህን ለውጠህ ምግብ ብላልኝ! ልጄ ባጠባውህ ጡት ይዤሃለው እባክህ እባክህ!" አለች እናቴ እምባዋን እያዘራች።
የለበሰችው ቢጃማ በላይዋ ላይ አድፏል። ስለእኔ ማሰቡ ክስት አድርጓታል። የድሮ ወዟን አጥታ አመዷ ቡን ብሏል። ይባስ ብሎ አባቴ ከሶስት ወራት በፊት ለአንድ ወር ከወጣበት የመስክ ስራ ሲመለስ ሰርቦ በተባለች የጅማ አዋሳኝ ትንሽዬ ከተማ ውስጥ ህፃን ልጅ ገጭቶ ከታሰረ ወዲህ እናቴ እንቅልፍ የላትም ትርሃሴም እንደቆዘመች ትውላለች። ታድራለች። በቤታችን ሰማይ ስር መከራ ጥቁር ጥላውን አጥልቷብናል።
ይሄን ፈተና ተፈትኖ ፍሌሜን ድሬዳዋ ሄጄ ልፈልጋት አሰብኩኝ። ትርሃሴን እና እናቴን ደስ እንዲላቸው ጠዋት ወጥቼ ማታ እገባለሁ።
ሀደኮ መጥታ ታየኛለች ብቻዬን ስታየኝ ውሃውን ሳትቀዳ ተመልሳ ትገባለች። ከፍሌም ጋር ፀሀይን የምናጠልቅበት ከጀምበር መጥለቂያ ላይ አንዳንዴ እሄዳለሁ ግን ምን ያደርጋል። ትዝታ ብቻ። ህይወት ለዛዋ ጠፍቶ ቀለም አልባ ትሆንብኛለች።
የጎዳናው ዳር ፣ የሲኒማው ቤት ፣ የመናፈሻ እና የሬስቶራንቶች ደስታው እና ፌሽታው ልጆችዋን እንደተራበች ወፍ በረው ጠፍተዋል።

         .......     .......

እንደምንም አንድ ወሬን ባጅቼ ፈተናዬን አጠናቅቄ ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ ተነሳሁ። ትርሃሴ አብሬህ ካልሄድኩ ብላ አስጨነቀችኝ በስንት ውትወታ አስቀረዋት። ከሶስት ቀናት በኃላ " የበረሃዋ ንግስት "  ወደምትሰኘው ታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ድሬ ከተማ ገባሁ።
ድሬ እውነተኛ ፍቅር እና መቻቻል የሚንፀባረቅባት ውብ ከተማ ነች። ሀገሬው ጭንቅ አይወድም። ጭንቀትም በአየሯ ላይ ቦታ የለውም በፈገግታና ፍቅር እየተባረረ ድንበሯን ጥሶ ይጠፋል።
ገና ከተማዋ ስገባ መንፈሱ የደስ ደስ ይሰጠኝ ጀምሯል።
ድሬ ፍቅር ፍቅር ትሸታለች።......

​​✎ ክፍል ሀያ (20) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜

Рэкорды

12.04.202519:35
131.9KПадпісчыкаў
24.01.202505:45
100Індэкс цытавання
08.03.202507:47
48.6KАхоп 1 паста
14.04.202518:50
2.9KАхоп рэкламнага паста
19.04.202518:31
500.00%ER
08.03.202511:04
37.54%ERR

Развіццё

Падпісчыкаў
Індэкс цытавання
Ахоп 1 паста
Ахоп рэкламнага паста
ER
ERR
MAR '25APR '25

Папулярныя публікацыі 💞መንታ ልቦች💞

17.04.202518:00
❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ ዘጠኝ (19)
.
.... ብላ ልትቀጥል ስትል እምባ ተናነቃት። አምቃ የያዘቸውን ለቅሶ አፈነዳችው። እየተንሰቀሰቀች ወጥታ ሄደች....
እናቴ ግራ ገባት። ልትቆጣኝ አልወደደችም። እንድደነግጥ አልፈለገችም።
"የእኔ ጌታ ትንሽ ምግብ አትበላም?"አለች አይኗን ቡዝዝ አድርጋ እየተመለከተችኝ። በግምባሯ ላይ የተጋደሙትን እጥፋቶች ስመለከት በትልልቅ ችግር ውስጥ አላሳልፍ ብሎ የተጋደመ ትልቅ ግንድ ያየው መሰለኝ።
በረጅሙ ተንፍሼ እመባዬን እያበስኩ "በቃኝ እማ!" አልኳት።
"ግሩም ልጄ ምነው አሳቀቅከን ምነው ስቃዬን በቃሽ ብትለኝ ?
እህትህንም ሰላም አልሰጣሃትም! ተሰቃየች እኮ ጌታዬ እኔስ ባማጥኩህ በወለድኩህ ልጎዳ እህትን ምነው ልጄ!?
የኔ ጌታ ፈተናህን ተወው ይቅር ግን አንዴ ብቻ ተጣጥበህ ልብስህን ለውጠህ ምግብ ብላልኝ! ልጄ ባጠባውህ ጡት ይዤሃለው እባክህ እባክህ!" አለች እናቴ እምባዋን እያዘራች።
የለበሰችው ቢጃማ በላይዋ ላይ አድፏል። ስለእኔ ማሰቡ ክስት አድርጓታል። የድሮ ወዟን አጥታ አመዷ ቡን ብሏል። ይባስ ብሎ አባቴ ከሶስት ወራት በፊት ለአንድ ወር ከወጣበት የመስክ ስራ ሲመለስ ሰርቦ በተባለች የጅማ አዋሳኝ ትንሽዬ ከተማ ውስጥ ህፃን ልጅ ገጭቶ ከታሰረ ወዲህ እናቴ እንቅልፍ የላትም ትርሃሴም እንደቆዘመች ትውላለች። ታድራለች። በቤታችን ሰማይ ስር መከራ ጥቁር ጥላውን አጥልቷብናል።
ይሄን ፈተና ተፈትኖ ፍሌሜን ድሬዳዋ ሄጄ ልፈልጋት አሰብኩኝ። ትርሃሴን እና እናቴን ደስ እንዲላቸው ጠዋት ወጥቼ ማታ እገባለሁ።
ሀደኮ መጥታ ታየኛለች ብቻዬን ስታየኝ ውሃውን ሳትቀዳ ተመልሳ ትገባለች። ከፍሌም ጋር ፀሀይን የምናጠልቅበት ከጀምበር መጥለቂያ ላይ አንዳንዴ እሄዳለሁ ግን ምን ያደርጋል። ትዝታ ብቻ። ህይወት ለዛዋ ጠፍቶ ቀለም አልባ ትሆንብኛለች።
የጎዳናው ዳር ፣ የሲኒማው ቤት ፣ የመናፈሻ እና የሬስቶራንቶች ደስታው እና ፌሽታው ልጆችዋን እንደተራበች ወፍ በረው ጠፍተዋል።

         .......     .......

እንደምንም አንድ ወሬን ባጅቼ ፈተናዬን አጠናቅቄ ወደ ድሬዳዋ ለመሄድ ተነሳሁ። ትርሃሴ አብሬህ ካልሄድኩ ብላ አስጨነቀችኝ በስንት ውትወታ አስቀረዋት። ከሶስት ቀናት በኃላ " የበረሃዋ ንግስት "  ወደምትሰኘው ታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ድሬ ከተማ ገባሁ።
ድሬ እውነተኛ ፍቅር እና መቻቻል የሚንፀባረቅባት ውብ ከተማ ነች። ሀገሬው ጭንቅ አይወድም። ጭንቀትም በአየሯ ላይ ቦታ የለውም በፈገግታና ፍቅር እየተባረረ ድንበሯን ጥሶ ይጠፋል።
ገና ከተማዋ ስገባ መንፈሱ የደስ ደስ ይሰጠኝ ጀምሯል።
ድሬ ፍቅር ፍቅር ትሸታለች።......

​​✎ ክፍል ሀያ (20) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
15.04.202516:58
❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ ስምንት (18)


ከወዲያኛው የስልኩ ጫፍ
"ግሩሜ በፍጥነት ቤት ና እፈልግሃለው " የሚል የፍሌሜን ድምፅ እንደሰማው ስልኩ ተዘጋ።
ግራ ገባኝ ተነስቼ ከነፍኩ።
የትርሃስ ስድብና ንጭንጭ እስክወጣ እየተከተለኝ ነበር።
        ➲➲➲➲➲➲➲➲➲➲➲
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተንጋልያለሁ ትርሃስ አልጋው ጫፍ ላይ ሆና ታፋዋ ላይ አስተኝታኝ ጣቶቿን በፀጉሬ ውስጥ ታርመሰምሳለች። ፍዝዝ ብላለች ትክዝ ብያለሁ
"ግሩሜ " አለች ቅዝቅዝ ባለ ድምፀት
ዝም አልኩ!
"ለምን እንዲህ ትሆናለህ የኔ ጌታ! እራስህን እየጎዳህ እኮ ነው ግሩሜ ቢያንስ እናታችንን አስባት እስኪ ምን ያህል እንደተጎሳቆለች። ፈተናህም አንድ ወር ነው የቀረው። በዛ ላይ ፍሌም ከሄደች ይኸው ድፍግ አምስት ወር ሆናት አይደል እንዴ!" አባታችንስ ከታሰረ ሶስት ወር ሆነው አይደል? እሷስ ብትሆን የእውነት ከወደደችህ እና ካፈቀረችህ እንዴት ይህን ያህል ጊዜ ትተውሃለች?!" አለችኝ። እምባ በአይኗ እየቀረረ ሳግ እየተናነቃት።
ትመጣለች! እናቷ ሞተው ታዲያ በዚህ ፍጥነት .....እምባ አነቀኝ።እልህ ጉሮሮዬን ፈጥርቆ ያዘው።ትኩስ እምባዬ ጉንጬን እንደሳማ እየለበለበኝ እርግፍ እርግፍ ሲል ይታወቀኛል።
ፍሌም ናፈቀችኝ በዛች የተረገመች ቀን ጠርታኝ እናቷ እንደደከሙ እና አሁኑኑ መሄድ እንዳለባት እየተርበተበተች የነገረችኝ ነገር ሁኔታው በአይነ ህሊናዬ ውልብ አለ።
ከሄደች ጀምሮ በሽተኛ ሆኛለሁ። አልጋ ላይ ሆኜ እምባዬ አለከልካይ በጉንጮቼ ሲንፎለፎል ትርሃስ ጭንቅላቴን ወርውራ ተነሳች።
"ቆይ አንተ ምንድነው ፍላጎትህ.."እኔ አላሳዝንህም ? እማዬ አታሳዝንህም ? ቅዱሴን እንኳን ተመልከተው ግሩሜ! እኔ እህትህ እኮ ደስታህን እፈልገዋለሁ ቆይ ከፍትህ አልጋ ላይ ስትውል የማይከፋኝ ይመስልሃል ? ምን ስሆን ማየት ነው የምትፈልገው?.."
"ምንድነው ምን ሆናችሁ ሚሚዬ "እናቴ ከውጭ ገባች።
እማ እኔ ግሩሜ በዚሁ እየቀጠለ የሚኖር ከሆነ ከእኔም ሆነ ከቅዱሴ ምንም ነገር አትጠብቂ እንደውም እኔ እህቱ አይደለሁም! እማ ተመልከቺው እስኪ ምግብ በስርዓቱ የበላው መች ነው? ይሄን ልብስ ከቀየረው ስንት ጊዜው ነው?  እኔና አንቺን መች አይቶን ያውቃል? የታሰረ አባቱን ከጠየቀው ስንት ጊዜ ነው? እማ በእግዚአብሔር ጠይቂው ጨነቀኝ እንደድሮ አያናድደኝም ስድቤ አይናፍቀውም እማ የድሮው ግሩም ናፈቀኝ... !" ብላ ልትቀጥል ስትል እምባ ተናነቃት። አምቃ የያዘቸውን ለቅሶ አፈነዳችው። እየተንሰቀሰቀች ወጥታ ሄደች.....

​​✎ ክፍል አስራ ዘጠኝ (19) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
19.04.202514:49
❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል ሀያ (20)

.
ድሬ እውነተኛ ፍቅር እና መቻቻል የሚንፀባረቅባት ውብ ከተማ ነች። ሀገሬው ጭንቅ አይወድም። ጭንቀትም በአየሯ ላይ ቦታ የለውም በፈገግታና ፍቅር እየተባረረ ድንበሯን ጥሶ ይጠፋል።
ገና ከተማዋ ስገባ መንፈሱ የደስ ደስ ይሰጠኝ ጀምሯል።
ድሬ ፍቅር ፍቅር ትሸታለች።
.
ሁለት ሳምንታት ድሬን ዞርኩ ምንም ጠብ ያለ ነገር አላገኘውም። ወደ ጅማ መመለስ አልፈለግኩም።
ፍሌሜን አየዋት የሚለኝ ሰው አጣው።
ጀማ ሆኜ ሳስብ እንዲህም ተንከራትቼ የማጣት አልመሰለኝም ነበር። የበላት ጅብ አልጮህ ቢል ልቤ ቀቢፀ ተስፋውን ወደ መጥራቱ እያዘነበለ በነበረበት ሰሞን የሆነ ባለሱቅ ጋር ስለፍሌም ና ስለእኔ በደንብ አወጋን እሱም አሰብ አድርጎ ፍሌምን እንደሚያውቃት ነገር ግን ከቅርብ ወራት በፊት በድንገተኛ የመኪና አደጋ እንደሞተች እና እናትየው በህይወት እንዳሉ ነገረኝ።
ይህን ሲለኝ ሰማይ የተደፋብኝ ያህል ዞረብኝ የሰማውት ነገር ቅዠት እንጂ እውነት አልመስልህ አለኝ።
ግራ በተጋባ ስሜት ውስጥ ሆኜ ራሴን ጠላውት። ዛሬውኑ ድሬን ለቅቄ ለመሄድ ወሰንኩ። ግን ከዚህ ወዲህ ፍሌምን አጥቶ እንዴት ይኖራል? ዋ!!!
ግን ይሄ ሁላ እንዴት ሊሆን ቻለ?
ፍሌም እናቷ ካልሞቱ እንዴት ደክመዋል ተብሎ ሲቀጥልም ሞተዋል ብለው ጠሯት? ' እያልኩ ስብሰከሰክ ድሬ ከገባሁ ወዲህ የተዋወቅኩት አንድ ጫታም እየተንከወከወ መጥቶ የሆነ ሽማግሌ ጋ ወሰደኝ።
ሽማግሌው ወንድምየው ታሞበት እያስታመመ መሆኑን እና እውነተኛዋ እኔ የምፈልጋት ፍሌም እዚሁ ጊቢው ውስጥ እንዳለች ነግሮኝ ፍሌሜን ሊያሳየኝ ወደ ጊቢው ይዞኝ ገባ።
ፍሌም አለች የተባለችበት ሰርቢስ ውስጥ ነበር።
ስገባ ቤቱ ጭልምልም ብሏል። እሷን የሚመስሉ አሮጊት ሴትዮ ወደ አልጋው ትራስጌ ቆመዋል።
አልጋው ላይ ፍሌም ተኝታለች። ቀረብ ብዬ ተመለከትኳት።መልኳ ገርጥቷል።ፍሌሜን አሟታል፤,የድሮ መልኳ ተለውጧል።
ገና ስታየኝ እያቃሰተች ተጣጥራ አቀፈችኝ ፤ እምባዋን አዘራች።
አምርሬ አለቀስኩ ከፈጣሪዬም ጋር ተዋቀስኩ። በእጅጉ አለም እንደከዳችኝ ገባኝ።
ሳለቅስ ሽማግሌው የታመመ ወንድምየው እንዳይረበሽ ለቅሶዬን አስቁሞ ያፅናናኝ ገባ።
የማየው ነገር ሁሉ እውነት አልመስልህ አለኝ።
.... እንደዋዛ ከፍሌም ጋር ለሶስት ቀናት ቆየው። ከሚያስታምሟት እናቷ ጋር ሆነን የማይገፉ ሶስት ቀናትን የዘላለም ያህል እየከበደኝ ገፋሁት።
ፍሌሜም እኔ ፊት ደስተኛ ሆና ለመታየት ፈገግ ትላለች። ያ ውብ ዲንፕሏ ድምቀቱ ጠፍቶ የበርባሮስ ጉድጓድ መስሏል።

​​✎ ክፍል ሀያ አንድ (21) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
29.03.202514:58
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል ስምንት (8)


ጥቁሩ ዞማ ፀጉሯ በፊቷ ላይ ተበታትኗል።
ፈገግ አለች። ጎትቼ እቅፌ ውስጥ ወሸቅኳት። እንደተራራ የተገተሩ አጎጠጎጤ ጡቶችዋ ደረቴን እንደ አድዋ ጦር ወግተው በሰራ አካላቴ ላይ ሙቀት ለቀቁብኝ።
በጥፍሯ ተንጠራርታ ግምባሬን ሳመችኝ።አፀፋውን ለመመለስ ጉንጭ እና ጉንጯን አጥብቄ ይዤ ከንፈሯን ጎረስኩት። ቀና ብላ አይታኝ አይኗን በሀፍረት ሰበር አድርጋ በፊቷ ላይ ላይ የወደቁትን የፀጉሯን ዘለላዎች እየሰበሰበች ወደቤት ገባች።ተከተልኳት። ክፍሌ እንድትገባ ፈልጌያለሁ። ተንኮል ፈለግኩ። ሳሎኑን አልፋ በኮሪደሩ ወደ ቀኝ ታጥፋ ወደ ትርሃስ ክፍል ስትገሰግስ እጇን ያዝ አድርጌ " ትርሃሴን ዛሬ አሟት ተኝታለች" አልኳት በለሆሳስ።
"ልብሴን ልለውጥ ነው አልረብሻትም" አለች አይኗን በአይኔ ላይ ተክላ።
"ግድ የለሽም እኔ ክፍል ግቢ እኔ  ይዤልሽ ልምጣ " አልኳት ዞማ ፀኑሯን እየሰበሰብኩኝ።
"የኔ ቆንጆ የትርሃሴን ነገር ታውቂው የለ ከተነሳች ንጭንጯን አልችለውም!" አልኳት ደግሜ በልመና አኳኋን።አይኗን በአይኔ ላይ እያንከራተተች በእሺታ አንገቷን ነቅንቃ ወደ ክፍሌ ገባች።
ትርሃስ ክፍል ስገባ አጣጥፋ ያስቀመጠቻቸውን ምርጥ ምረጥ ልብሶቿን ትራስጌዋ ላይ አገኘውት።
ፀጉሯን በትና ግራና ቀኝ እጆቿን ወዲያና ወዲህ ወርውራ ተኝታለች። አስተኛኘቷ አስቀናኝ በጥልቅ ስሜት ውጥ ተዘፍቃ እንቅልፏን ትለጥጠዋለች።
በመስኮት በኩል የከሰዓቱ የደመና ግርዶሽ እየተቀደደ ፀሀይ እየወጣች ስለመሆኑ ጮራው በመስኮቷ በኩል አልፎ ኮመዲኖዋ ላይ አርፏል።
የሲሳይ ንጉሱ ሰመመ ፣ የአቤ ጉበኛ አልወለድም ፣ የይስማዕከ ወርቁ ተከርቸም መፅሀፍቶች አንዱ በአንዱ ላይ ተደራርቦ ተቀምጧል።
የከሰዓቱ ድባብ ቤቱን ወርፎታል።
ከትርሃስ ክፍል ወጥቼ ወደ ክፍሌ አቀናው ፍሌም ከክፍሌ ደቡባዊ ጫፍ ላይ ቆማለች። አይኔን ከአይኗ ላይ ሳልነቅል ያመጣሁላትን ልብስ አልጋው ላይ ወርውሬ ተጠጋዋት።
እጄን ትከሻዋ ላይ አድርጌ ጎትቼ ከንፈሬን ከከንፈሯ ጋር አዋሃድኩት።
ትንፋሽ እና ትንፋሻችን ጠፋ። ህይወት ዳናዋን አጥፍታ በህቡዕ መሰስ እያለች የምትበረው ይህን ጊዜ መሰለኝ።
ሰመመን በመሰለ የህይወት ጉዞ አለከልካይ በጥልቅ ተመስጥኦ ከደፉ ወረደን ወደ ጥልቁ ህይወት ዘለቅን።
በዚህ ጥልቅ ረቂቅ አለም ተስፋ እንጂ ውድቀት ፤ ገነት እንጂ ገሀነም አይታይም። ፍሌሜ ሁለቱ እጇቿን በአንገቴ ላይ አቆላልፋየጎመራ ፖም በሚመስለው ስስ ከንፈሯ ትመጠምጠኝ ገብታለች።
ሁለታችንም ራሳችንን ውጠን ለሌላ አለም ለመውለድ የምናምጥ ተስፈኞች ነን ስል አሰብኩ።.......

​​✎ ክፍል ዘጠኝ (9) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
13.04.202515:05
⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ ሰባት (17)


እማ ምነው ትርሃሴ ቆየች!? " አልኳት ቻርጀሩ መቀበል አለመቀበሉን እያረጋገጥኩ።
"አሁን ትመጣልህ የለ!" ብላኝ ሳትጨርስ
"እማ እንዴት ነሽልኝ እናቴ !" እያለች ገባች። ከመቅበጥበጧ የተነሳ የምትዘፍን ነበር የምትመስለው።
"ሚሚዬ እንዴት ዋልሽ ልጄ?"
"አለውልሽ ኡፍፍፍ ደክሞኛል እማ ውሃ ስጪኝ በማሪያም?"
"እሺ እሺ ወንድምሽን ሰላም አትዪውም እንዴ? ምነው ትርሃሴ?" አለች
ባክሽ እኔ የማንንም ሽንኩርታም ሰላም ስል ጊዜዬን አላቃጥልም! You know time is the gold"አለች በጎሪጥ እየተመለከተችኝ።
"ማንን ነው አንቺ? አይጥ!"አልኳት ኮስተር ለማለት እየታገልኩ።
"እኔ ግሩም ብዬ ጠርቼሃለው ሽንኩርታም!" አለች ጀነን እንዳለች።
ሚሚዬ እግዚአብሔርን ይሄን ሽንኩርት አበላሻለሁ! ጥጋብሽን ቀንሺ "አልኳት።
"ወንድ ነኻ ዝም ስልህ የፈራሁህ መሰለህ? አመዳም! ግምባራም! ሂሽ ሽንኩርታም!!" አለች።
ከምከትፈው ሽንኩርት ላይ በእጄ ዘግኜ ወስጄ ላበላት ታስታገል ጮኸች።
"ግሩሜ በእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ግሩሜ የኔ ወንድም በእግዚአብሔር አዪዪዪ እማ ተው በይው እንጂ ኧረ በማሪያም እማ?!" አለች እየታገለችኝ
"አንቺ ማን ነገር ፈልጊው አለሽ እና ነው?" አለች እናቴ
"ኧረ እማ አበላኝ እኮ በእግዚአብሔር ቱ ምን አይነት ገገማ ነው በእግዚአብሔር " አለች ፊቷን ጭፍግግ አድርጋ ያበላዋትን ሽንኩርት እየተፋች
"አሁንም እንዳላበላሽ ዋ!"
"ሂድ ወደዛ ሽንኩርታም! ወንድ ነህ ግሩሜ አሁንማ"አለች ወደ እናቴ እየርጠች። እናቴን መሃል አድርገን ተያየን።
"ምነው ጌታዬ ብትተዉ ሽንኩርቱንም በትናችሁ ጨረሳችሁት እኮ አዬ ልጅነት"አለች ወደ እኔ ዞራ።
"አንቺም እረፊ ተሞጣሙጠሽ ስታበቂ እኔን አትጥሪኝ ደቃቃ" አለቻት በፍቅር ቁጣ
"እማ ግን ሁል ጊዜ እኔ ላይ ነው አይደል የምትጮሂው? እንዴ......" ትርሃስ እየተነጫነጨች ስልኬ ጮኸ።አነሳሁት።
"አቤት ፍሌሜ!" አልኩኝ
ከወዲያኛው የስልኩ ጫፍ
"ግሩሜ በፍጥነት ቤት ና እፈልግሃለው " የሚል የፍሌሜን ድምፅ እንደሰማው ስልኩ ተዘጋ።
ግራ ገባኝ ተነስቼ ከነፍኩ።
የትርሃስ ስድብና ንጭንጭ እስክወጣ እየተከተለኝ ነበር።

​​✎ ክፍል አስራ ስምንት (18) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
11.04.202517:45
⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ ስድስት (16)


.
ትርሃስ ዘንድሮ የ10 ክፍል የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ስለሆነች ከእኔም ሆነ ከፍሌም ጋር የመገናኘታችን እድል የጠበበ ነበር።
አንድ ቅዳሜ ጠዋት ህይወታችንን ያመሰቃቀለ ነገር ተፈጠረ።
ቀኑ ቅዳሜ ጠዋት ነበር። እስከ አምስት ሰዓት ተምረን ቤት ስገባ ቤቱ ጭር ብሏል። እየተጣራው ገባሁ። ቤት ስገባ ደስ ብሎኝ ነበር የገባሁት እኔና ፍሌም የሁለተኛ መንፈቅ አመት ከጀመሩ  በፊት ባለችው የእረፍት ጊዜ ድሬ እንደምትወስደኝ እና ከእናት አባቷ ጋር እንደምታስተዋውቀኝ ከክፍል ስወጣ ነግራኝ ነበር።
ደስ ብሏታል። ስለእኔም ብዙ ነገር እንደነገረቻቸው ጨምራ አውግታኛለች።
ፍትት ብዬ እናቴን እየጠራዋት ኩሽና ስገባ እናቴ ሽንኩርት እየላጠች ነበር።
" እማ እንዴት ዋልሽ?" አልኳት ጉንጯን አጥብቄ እየሳምኩ።
" እንዴት ዋልክ ጌቱ!" ብላ በተራዋ ግንባሬን ሳመችኝ። (ጌታዬ ጌቱ የኔ ጌታ እያለች ነው የምትጠራኝ።) የኤሌክትሪክ ምድጃውን ለኩሳ ውሃ እስክትጥድ ሽንኩርቱን እከትፍላት ጀመር።
"እማ! ሚሚዬ የት ነች ?" አልኳት ሽንኩርቱ እያቃጠለኝ ከአይኔ የሚወጣውን እምባ በአይበሉባዬ እየጠረግኩ።
"መቼ ከትምህር ቤት መጣች ብለህ ነው ጌታዬ!?" አለች። ለወጥ የሚሆን ቲማቲም እየመረጠች።
"ናፈቀችኝ እኮ እማ ! አይ ትርሃሴ" አልኳት
"ምን ጭቅጭቋ ነው የሚናፍቅህ አይ እናንተ! እንደው ጌታዬ እናንተ ባትኖሩ ምን እሆን ነበር ቸሩ መድሃኒያለም ጥሎ አልጣለኝም ቤቴን በፌሽታ ሞላችሁት እኮ!" አለች በእናታዊ የመንሰፍሰፍ ሀዘኔታ ባለው ድምፅ ቲማቲሙን አምጥታ ከፊት ለፊቴ እያስቀመጠች።
"እማ ዛሬ ደስ ብሎኛል የሆነ የምነግርሽ ነገር አለኝ። አንቺም ደስ እንደሚልሽ አልጠራጠርም!" አልኳት።
"አድርጎት ነው የኔ ጌታ አንተ ብቻ ደስተኛ ሁንልኝ እንጂ ደስ ያለህ ነገር እኔንም ደስ ያሰኘኛል።"ብላ መጥታ በስስት ጉንጬን ሳመችኝ።
ስልኬ ላይ የሆነ ነገር ላሳያት ብዬ ስልኬ እኔ ጋ እንዳልሆነ ኪሴን ዳብሼ ስረዳ ከደብተሬ ጋር ሳሎን እንደተውኩት ገባኝና እናቴን "መጣው እማ!" ብዬያት ወደ ሳሎን አቀናው።
ስልኬን ይዤ ልመጣ ስል ባትሪ ዘግቶል። ከቻርጀር ጋር  ኩሽና ሰክቼ ከእናቴ ጋር ማውራቴን ቀጠልኩ።
"እማ ምነው ትርሃሴ ቆየች!? " አልኳት ቻርጀሩ መቀበል አለመቀበሉን እያረጋገጥኩ።


​​✎ ክፍል አስራ ሰባት (17) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
31.03.202516:37
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል ዘጠኝ (9)



   ✍ ፍሌሜ ሁለቱ እጇቿን በአንገቴ ላይ አቆላልፋየጎመራ ፖም በሚመስለው ስስ ከንፈሯ ትመጠምጠኝ ገብታለች።
ሁለታችንም ራሳችንን ውጠን ለሌላ አለም ለመውለድ የምናምጥ ተስፈኞች ነን ስል አሰብኩ።
እጆቿ አንገቴን ለቀው በፀጉሬ ዘለላዎች ውስጥ ይርመሰመሱ ጀመር። ጦርነቱ መጀመሩ ነው።
እኔም እጄ ስራ አላስፈታሁትም። እንደ እንቁሉል በስስት ይዣት እንደ ጣፋጭ ማንጎ ከናፍሯን መጠጥኩት። አየር ለመሳብ ብለን እረፍት አደረግን ትንፋሻችን እንደ ሲኦል ወላፈን ይጋረፋል።አንገቷ ስር ገብቼ እየሳምኳት በጆሮዋ ውስጥ አንሾካሾኩ።
እሷም ከጥልቁ ስሜት አፋፍ ላይ ሆና አንሾካሾከች።
ጊዜ ሳላጠፋ ወደ ከንፈሯ ተመልሼ እያካለብኩ ወደ አልጋው ላይ ጣልኳት። አብሬያትም ወደቅኩ።
እጆቼን በመላው አካላቷ ላይ አርመሰመስኩት እንደ ተራራ ተቀስሮ ሲወጋኝ የነበረው ጡቷን አለከልካይ እንደፈትል ፈተልኩት።
የትንፋሿን ሙቀት አልቻልኩም። ተነስቼ በሩን ቆልፌ ወደቅኩባት።ከዛ እንጃ ዙሩ ከረረ።
የሆነ ሰመመን ውርር አደረገኝ።ፍሌም ስታቃስት በጆሮዬ ስታንሾካሹክ ይታወቀኝ ነበር።
የሆነ ብቅ ጥልቅ የሚል ባህር ላይ ተጥለን የምንዋኝ አላዋቂ ዋናተኞች እንደሆንም ይሰማኝ ነበር።
......ደስስስ የሚል የስቃይ አለም....
በመሰንበት እና በመንቃት ወሰን የታጠረ ሽቦ።
የፍሌም ማቃሰት እየበዛ እየበረታ ሄዶ ብቅ ጥልቅ የሚለው ባህር ማዕበሉን አናውፆ ፀጥ አለ።ረጭ።
እየተንቀለቀለች የነበረች መከረኛ ነፍሴ ሰከነች።
ፍሌሜም እርግት አለች።አለምን በግዛቴ ስር ያኖርኳት ያህል እርካታ ተሰማኝ።አለሜን ሸመትኳት ፤ ህይወትን ከረጋ ምንጯ ተጎነጨዋት።
የባህሩ ተናውጦ እኛ ዋናተኞቹን ወደ ዳር ሲያወጣን ጨፍኜ እርካታዬን እያጣጣምኩ ነበር። አይኔን ገለጥኩኝ ፍሌሜ ክንዴን ተንተርሳ በጎን ደረቴ ላይ ተንታለች።
ስስ አልጋ ልብስ ለብሰናል። ፍሌምም ሆንን ባዶ ራቁታችን ነን። እቅፍ አድርጌ ሳምኳት። አጥብቃ አቀፈችኝ።
በዚህ ሰዓት በሩ በሀይል ተንኳኳ በድንጋጤ የምገባበት ጠፋ ፍሌም አይኗ ፈጠጠ።
"ማነው?" አልኩኝ ድንጋጤ በሸበበው ድምፀት።
"ግሩሜ ማነው ያስቀመጥኩትን ልብስ የወሰደው? ቆይ በእግዚአብሔር እዚህ ቤት የሚረዳኝ የለም ማለት ነው?"አለች ትርሃስ ንጭንጯን ጀመራት አልኩኝ በልቤ።
"የምን ልብስ ነው ማለቴ ምን የሚደረግ?" አልኳት ድንጋጤው አለቀቀኝም።......

​​✎ ክፍል አስር(10) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
09.04.202517:31
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ አምስት (15)


"ብቻሽን ነበርሻ! ይህን ሁሉ ጊዜ?..."አልኳት።
" ታዲያ ምን ምርጫ አለኝ ደጋግሜ ቤት አንተጋ ብመጣ የለም ይሉኛል። መሄጃ ሲጠፋኝ ተኝቼ እውላለሁ!" አለች ትክዝ እንዳለች።
በነገረችኝ ነገር በእራሴ አዘንኩ የራሴን ስሜት እየሰማሁ ለካስ ፍሌሜን ጎድቻታለሁ ብዬ ተፀፀትኩ። ግን ፍሌም ይህን ያህል አድርጌያትም አልተለወጠችብኝም።
ምንም በልቧ የለም። ንፁህ ነች። ልቧን አደነቅኩላት ፤ ይበልጥ ስወዳት ተሰማኝ።
ይህቺ ፍካት ህይወቴን አጥርታ እኔነቴን አፈካችው። ልቤ ወገግ ሲል ይሰማኛል።
ፍሌም የሰው ወርቅ!
በድብስብስ ቀን ያገኘዋት ፀሀይ በድብስብስ አለም የታደልኳት ጎህ ፍሌም።
የብቻዬ ነች ብዬ ለልቤ ነገርኩት።
ሰማይና ምድሬ ነች።
ቀኑ ደንገዝገዝ እያለ ነበር በአዌቱ ውሃ እንደ ህፃን ልጅ ፊቷን አጥቤ ወደቤት ወሰድኳት።
................. #########..................
እንደዋዛ ትምህርት ተጀምሮ መንፈቅ አመት ሊሆነው ምንም አልቀረም። እኔና ፍሌም ያለውን ነገር ተነጋግረን እዚህ ለመማር ከወሰነች ወዲህ መንቲና በሚገኘው የጅማ ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት እሷ 11ኛ እኔ የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሆነን እየተማርን ነው።
ዘውትር ተሳስበን እና ተዋደን ነው የምንኖረው። ትምህርት ቤት ስንሄድም ሆነ ስንመጣ አብረን ነን ተነጣጥለን አናውቅም።
እሁድ እሁድ ሁሌም ማምሻውን በጀምበር መጥለቂያ ደርብ ላይ ወጥተን ጀምበርን እያጠለቅን እናወጋለን።
በየካፌውና ሬስቶራንቶች ላይ እየተዟዟርን በትምህርት በኑሮ የተጨናነቀ መንፈሳችንን እናድሳለን። እኔም ሆንኩኝ ፍሌም በእጅጉ ደስተኞች ነን።
ትርሃስ ዘንድሮ የ10 ክፍል የሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ተፈታኝ ስለሆነች ከእኔም ሆነ ከፍሌም ጋር የመገናኘታችን እድል የጠበበ ነበር።

​​✎ ክፍል አስራ ስድስት (16) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
07.04.202514:22
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ አራት (14)


     🔅 ከእሷ በቀር በወጉ የሚረዳኝ ሰው እንደሌለ ውስጤ ያውቃል።
"ግሩሜ ፍሌም እኮ ነኝ ለምን የሆንከውን አትነግረኝም"አለችኝ ወደ አንገቷ ስር ጎትታ እያቀፈችኝ።
"የኔ ጌታ ከምልህ በላይ ናፍቀኸኛል። እየሸሸከኝ እንደሆነ ይሰማኛል። ግሩሜ እንደምታፈቅረኝ አልጠራጠርም። እኔ በጣም ነው የምወድህ። እኔ የማስበው ፍቅር ለመስጠት እንጂ ለመቀበል ቦታ እንደሌለው ነው። ለዚህም ነው አንተን አጥሮ ያገደኝን የስሜትህን ኬላ አፍርሼ የምወተውትህ። አንተን ስለማፍቀሬ እንጂ አንተ ለእኔ ስለምትሆንልኝ ነገር እየተነበይኩ ልረብሽህ አልሻም። ዛሬ ይህን ያህል ጊዜ ስንራራቅ ለምን አልፈለግከኝም ብዬ ማኩረፍ ነበረብኝ። ግን ማፍቀሬ ስለመስጠት እንጂ ስለመቀበል አላደላም።

ግሩሜ የኔ የፍቅር ስሌት
1+1 = 2 ሳይሆን 1+1= 1ነው።

ምክኒያቱም የኔ እና የአንተ ፍቅር ተደምሮ ሁለት የሚባል ፍቅርን አይሰጠንም። ግሩሜ መቀበልን ስታስብ ነው 1+1=2 የሚሆነው።
አንተ እንዲደመር መስጠት እንጂ ድምሩ ሁለት ሆኖ ካላየሁ ብለህ ግብግብ መግጠም የለብህም። አንድ ቀን ሳታስበው በውጤቱ ትደሰታለህ።"
አለችኝ ይህን ስትለኝ አልቻልኩም ሆድ ባሰኝ ከእቅፏ ውስጥ ተሸሽጌ ተንሰቀሰቅኩኝ። ገና ልነግራት የፈለግኩትን ነገር ቀድማ ትነግረኛለች። በግልፅነቷ ብቸኝነቴን ታሸሽብኛለች። ከሰው በቀደመ አድማስ ሰፊነቷ ጭንቀቴን ታባርልኛለች። ፍሌም የሰው ወርቅ! ሰው የመሆን ልክ!
ለፍሌም የሆንኩትን ሁሉ ፍርሃቴን ሳይቀር በግልፅ ምንም ሳልደብቅ ሁሉንም ነገር ነገርኳት ፍሌም ደስ አላት። ከቁዘማ አለሟ ወጥታ ተፍነከነከች።
ይሄ ደስታዋን እናቴ እንድታይ ተመኘሁ።"ፍሌሜ ለምን እናቴ ጋ ቤት ሄደን ትንሽ ተጫውተን አትሄጂም?" አልኳት የአፍንጫዋን ጫፍ በእጄ ጎተት ጎተት እያደረግኩ።
"እሺ እዛ ቤት ሁሉም ሰው ነው የናፈቀኝ። በተለይ የትርሃስ ንጭንጭ።" አለች "እሺ አላቆይሽም ቶሎ እሸኝሻለሁ" አልኳት።
"ፈቅደውልኝ እንኳን አብሬያችሁ ባደርኩ!"
"እ..ህ አጎትሽስ?" አልኳት
"ፊልድ ከወጣ ሁለት ሳምንቱ ነው። እኔ እና አንተ ከተጠፋፋን ጀምሮ እንደሄደ አልመጣም" አለች ቅር እያላት። "ብቻሽን ነበርሻ! ይህን ሁሉ ጊዜ?"አልኳት።
ታዲያ ምን ምርጫ አለኝ ደጋግሜ ቤት አንተጋ ብመጣ የለም ይሉኛል።መሄጃ ሲጠፋኝ ተኝቼ እውላለሁ!" አለች ትክዝ እንዳለች።

​​✎ ክፍል አስራ አምስት (15) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
02.04.202516:38
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ አንድ(11)


ከድር ሰተቴን የመሳሰሉ እልፍ ሀቀኛ ዶሰኞች ለእውነት ሟች የሆኑ ጀግኖች የበቀሉባት በዘመናችንም እነ አህመዲን ጀበልን እነ ዶ.ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮን እና ሌሎች እልፍ ጀግኖችን ያበቀለች ከተማ ነች ጅማ ወይም ገሙ።....
ፍሌም ክንዴን እየጎተተች፤
"ግሩሜ ፍቅር ማለት ለአንተ ምን ማለት ነው?" አለችኝ
"እኔ እንጃ! ሲወራ እራሱ ይከብደኛል የሆነ ቀፋፊ ነገር ነው።" አልኳት ፊቴን ጨምደድ አድርጌ እንግሽግሽ እያደረግኩ።
"አትቀልድ ግሩሜ!"አለች ቆም ብላ ጎንተል እያደረገችኝ።
የሆነ ጊዜ ክፍል ውስጥ ቤዛዬ የምላት ቅመም የሆነች ልጅ ነበረች እና ስትነግረኝ 'ፍቅር ማለት አንድ ሴት እና ወንድ የሚሰክሱት ሳክስ ነው' ብላኝ ነበር።እሷንም ከፌስ ቡክ ላይ መንትፋት ነው!" አልኳት እና ፈገግ አልኩ።
"ደረቅ ነህ ግሩሜ ሙት። ምን አለበት ብትነግረኝ ለምሳሌ ፊልሙ ላይ እየወደደችው እና እያፈቀረችው ጨክና መለየቷ ጨካኝ እንጂ አፍቃሪ ያሰኛታል? ፍቅር የልባችንን ሀገር መፈለጊያ ነው ትካዜያችንን መሸሸጊያ?
የልባችን መሻት እንዲሳካ እና ከተፈጥሮ ጋር እንድንታረቅ እኛ ነን ወደ ፍቅር የምምቀርበው ወይስ እሱ ነው ያለንበት ድረስ የሚመጣው?" አለች።ፍሌም ስታመር እፈራታለሁ አነጋገሯ ይከብደኛል።ለህይወት ያላት ግንዛቤ እና ትርጉም ይደንቀኛል።
አሁን እየተናገረች ያለው ነገር ልቤን ወጋኝ።
"የኔ ቆንጆ ፍቅር እኮ በአፋችን እንደቀለለ የአፍ እዳ አይደለም። ይልቅ ይልቅ የልብ እውነት ነው። ፍቅር እኮ ጥበብ ነው በግርድፍ አማን እና አርነት ያልታበየ ህቡዕ አማን!
ፍሌሜ ስለፍቅር ተዘፍኗል ፣ ተገጥሟል ፣ በመፅሀፍ ተፅፏል ግን ከንቱ ነው። ልብን አሙቆ ከማቀዝቀዝ ባለፈ ምንም ፋይዳ የለውም።
በእብሪት ከአጠላን መንፈስ ጋር ተፋተን በሰከነ እኛነታችን እኛነታችንን አጭተን እና ድረን ካልሆነ ፍቅር በልባችን አይገባም። እኛም ከወደቅንበት አንነሳም።
ስለክርስቶስ በመስቀል ላይ ለፍቅር ስለመሰቀል በአንደበታችን ያወራነውን ያህል በልባችን መች ኖረነው እናውቃለን?
ሰው ስለፍቅር ይህን አደረገ ያን አደረገ እያሉ ፊልም ይሰራሉ መፅሀፍ ይፅፋሉ ሙዚቃ ይዘፍናሉ። ታዲያ ሰው ለፍቅር መሰዋዕት ካልሆነ ለምን መሰዋዕት ሊሆን ነው?
ፍቅር እኮ የእያንዳንዳችን የምሉዕነት መለኪያ ነው። በፍቅር ቤት የጎደለ በምንም ቤት ምሉዕ ሊሆን አይችልም።
እነዚያ እገሌ ለፍቅር እንዲህ ሆነ እንዲያ ሆነ እያሉ የሚሰብኩት ከንቱ ውዳሴ የትም አያደርሰንም።ፍቅር ኑረት ነው ሊያውም እንደ አለት በጠነከረ ቃፊር የታጠረ ኑረት።
አንዳንዴ ሰው መሆናችን በራሱ እያወቅን እየመሰለን የሚያደድበን አባዜ አለው።.....

​​✎ ክፍል አስራ ሁለት(11) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
01.04.202516:44
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስር (10)



"ማነው?" አልኩኝ ድንጋጤ በሸበበው ድምፀት።
"ግሩሜ ማነው ያስቀመጥኩትን ልብስ የወሰደው? ቆይ በእግዚአብሔር እዚህ ቤት የሚረዳኝ የለም ማለት ነው?"አለች ትርሃስ ንጭንጯን ጀመራት አልኩኝ በልቤ።
"የምን ልብስ ነው ማለቴ ምን የሚደረግ?" አልኳት ድንጋጤው አለቀቀኝም።
"የሚጠጣ ልብስ ምን አይነት ገገማ ልጅ ነው በእግዚአብሔር አንተ አመዳም ማነው ክፍሌ የገባው?"አለች። ትንሃስ በምትሰድበኝ ስድብ ፍሌም ትስቃለች።
"አንቺ ቆይ ግሩም በትርፍ ጊዜው የትርሃስን ልብስ ይለብሳል አሉሽ እንዴ? በቃ እኔ አላውቅም ያቺ ፍሌም መጥታ ነበር እሷ ቀይራ ይሆናል አልኳት።ፍሌም ድምፅ እንዳታወጣ እያስጠነቀቅኳት።
"ቆይ ይህቺ አይጥ የሆነች ልጅን ምን አባቴ ባደርጋት ነው የምትተወኝ ኧረ በእግዚአብሔር ታዲያ ምን ለብሼ ልሄድ ነው?" አለች ምርር ብሏታል።
"እኔጋ የግምበኞች ቱታ አለ። አተመቸሽ ላውስሽ ንፁህ ነው!።"አልኳት ካላናደድኳት ስትነጫነጭብኝ ነው የምትውለው።
"አንተ አመዳም ድሮስ ከአንተ ምን ይገኛል ኡፍ!....."እያጉረመረመች ሄደች።
ድምጿ እየራቀ እየራቀ ጠፋ ትንሽ ቆይተን ትርሃስ ስትወጣ ሰራተኛችን መጣች። ቤቱን ለሰራተኛዋ ትተን ሲኒማ ገባን።
....ከሲኒማ ስንወጣ መንገዱ በከተማ መብራቶች አሸብርቋል። የከድር ሰተቴ ሀገር ጅማ በሰፊው ሜዳ ላይ የበቀለች የአደይ አበባ ማሳ መስላለች።
ጅማ በጥንቱ ዘመን ገሙ ተብላ ትጠራ ነበር። ጅማ በ1960ዎቹ አከባቢ በንግድ የጦፈች ከተማ ነበረች። እንዲህ ባላደገች ጊዜ ፈረንጆች ተቆፍራ የወጣች ሀገር ናት ይሏት ነበር። ጣሊያን ሊለውጣት ብዙ ለፍቷል።ትንሿ ሮም እያለ ይጠራትም ነበር። በብዙ የጅማ ክፍሎች አይረሴ አሻራውን ጥሎባት ሄዷል ማለት ይቻላል። በተለይም በፈረንጅ አራዳ ፣ በመንቲና እና በፉርስታሌ ሰፈሮች።
ጅማ ብዙ ታሪክ ያላት ጥንታዊት ከተማ ከመሆኗም ባሻገር አባ ጅፋርን የመሰሉ ለአፍሪካ ስለ Relation ship ያርታወቁ እና ያስተማሩ ቀደምት እና ታላቅ ንጉስ የበቀለባት ፣ ከድር ሰተቴን የመሳሰሉ እልፍ ሀቀኛ ዶሰኞች ለእውነት ሟች የሆኑ ጀግኖች የበቀሉባት በዘመናችንም እነ አህመዲን ጀበልን እነ ዶ.ር ኤልያስ ገብሩ አእምሮን እና ሌሎች እልፍ ጀግኖችን ያበቀለች ከተማ ነች ጅማ ወይም ገሙ።....

​​✎ ክፍል አስራ አንድ(11) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
27.03.202514:21
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል ሰባት (7)

ያን ሰሞን ቁዘማ ስራዬ ሆነ። ቤት ውስጥ ንጭንጭ አበዛለው ብቻዬን መዋል ማደርን አዘወትራለው። ፍሌም ስታስጠራኝም የለም አስብል ጀምሬያለሁ።
ስትሄድ ደግሞ ይከፋኛል። ውስጤ ፍሌሜን ይራባል።ትኩስ እምባዬ እንደሳማ ጉንጬን እየለበለበኝ ይወርዳል። ምን መወሰን እንዳለብኝ ግራ ገባኝ የማዋየው ጓደኛም ሆነ ወዳጅ የለኝም። የነበሩትንም ክረምቱ ወስዷቸዋል።
ከፍሌም አንደበት 'እዬዳለሁ አልሄድም 'የሚሉትን አቁሳይ ፈዋሽ ቃላቶችን ከአንደበቷ ሳልሰማ ልቤ፤ ልቤ ከራሱ ጋር ግብግብ ገጥሞ ሰርክ ያስጨንቀኝ ጀምሯል።
ማንን የውስጤን አዋይቼው ከልቤ ሀገር ዘልቆ ባማለደኝ እላለሁ። ግን ማለት ብቻ ነው። ወኔ እንደ ኳስ ተጫዋች ቁምጣ ካጠረኝ ሰነባብቷል።
ቤት ውስጥ ጠዋቱን ቁርስ ሳልበላ ስቆዝም እውላለሁ። በእናቴ ልመና እና ግዝት ትንሽ ነገር ቀማምሼ ፍሌሜን ብዙ ነገር ወዳዋየሁባት የጋራ ቦታችን እሄዳለሁ።
ጅማ ፉርስታሌ ሰፈር አዌቱ ወንዝ ዳር ዋርካው ስር ተቀምጬ በመሬቱ ላይ እየተጥመለመለ ሲሄድ በልዩ ፍቅር የማየውን የአዌቱን ወንዝ እየተመለከትኩ ፍሌሜን በጥልቅ ተመስጦ እና ጥልቀት የሀሳብ ባህር ውስጥ ሆኜ አሰላስላታለሁ።
በማሰላሰሌ ውስጥ አንድ ሃሳብ ከተፍ አለልኝና የቁዘማዬን ልጓም ከአዌቱ ዳር ካለው ዋርካ ሸብ አድርጌ በትዝታ ሰረገላ ተሳፍሬ አድማሱን እየቀደድኩ ነጎድኩኝ።
     
ቀኑ አንድ እሁድ ከሰዓት ነው።
የአዌቱ ወንዝ ዳር እና ከባቢው ጭር ብሏል። ውሃው እና ድንጋዮቹ ተጋጭተው ከሚፈጥሩት ድምፅ በቀር ምንም የሚሰማ ነገር የለም።
እኔ ግዙፉን የአዌቱን ዳር ዋርካ ተደግፌ የሆነ ወቅት ከፍሌም ጋር ሲኒማ አይተን ስላየነው ሲኒማ የተጠያየቅነው ነገር ትዝ አለኝ።
........ ቀኑ ደመናማ ነበር። ማንም በቤት ውስጥ የለም አልነበረም። እናቴ ሰርግ ብላ ጠዋት እንደወጣች አልተመለሰችም። ቅዱስ መንደር ሊጫወት ሄዷል። ትርሃስ ክፍሏ ተኝታለች። ፍሌም ቤቷ ደብሯት እኛ ጋ ልትጫወት መጣች። እኔ ትርሃስ የተከለቻቸውን አበባዎች እየነቀልኩላት ነበር። የቤታችን ድባብ ጭር እንዳለ ነው። ፍሌሜ ሰላም ብላኝ ደረጃዎቹ ላይ ተቀመጠች። ከቧንቧው ላይ በቱቦ ውሃው ቀድቼ እያጠጣሁኝ ተንኮል አስቤ ፍሌሜን ጠራዋት መጣች። በቱቦ ውስጥ እየተንፎለፎለ የሚመጣውን ውሃ ወደ እሷ መልሼ ዝም አልኩ። ውሃው ሲነካት ፍሌም ጮኸች።
ልታስቆመኝ ታገለች። ውሃው ሁለታችንም ላይ ወረደ ተረጫጨን ሁለታችንም በሰበስን ኃላ ላይ ፍሌሜን ሳያት ደስ ብሏታል። ጥቁሩ ዞማ ፀጉሯ በፊቷ ላይ ተበታትኗል።
ፈገግ አለች። ጎትቼ እቅፌ ውስጥ ወሸቅኳት። እንደተራራ የተገተሩ አጎጠጎጤ ጡቶችዋ ደረቴን እንደ አድዋ ጦር ወግተው በሰራ አካላቴ ላይ ሙቀት ለቀቁብኝ።........

​​✎ ክፍል ስምንት (8) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
03.04.202514:16
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አስራ ሁለት (12)


ፍቅር ኑረት ነው ሊያውም እንደ አለት በጠነከረ ቃፊር የታጠረ ኑረት።
አንዳንዴ ሰው መሆናችን በራሱ እያወቅን እየመሰለን የሚያደድበን አባዜ አለው።
ቆይ እኔ ያየሁትን ካላያችሁ እሞታለሁ ብሎ መደስኮር ምኑ ነው ጉብዝና???
ስለ ክርስቶስ መሰዋዕትነት ዘመንን ሙሉ መደስኮር ጀግንነት አይደለም። ይልቁንም ከክርስቶስ ባልተናነሰ መንገድ ስለፍቅር መሰዋዕት መሆኑ ነው ጀግንነት።
ክርስቶስማ የህይወት አሸናፊ ድርብርብ ጀግና ነው። ስለክርስቶስ አላወራሽም ማለት ፍቅርን አታውቂም ማለት አይደለም።ስለክርስቶስ ሁሌ አወራሽ ማለትም ፍቅርን ታውቂያለሽ ማለት አይደለም። አመንም አላመንም ከክርስቶስ መሰዋእትነት ባልተናነሰ መልኩ በሁላችንም ልብ ውስጥ ታላቅ ፍቅር አለ። አንደበታችን ሊገልፀው የማይችለው ትልቅ እውነት! ግድንግድ ሀቅ።
በእኛና በልባችን መካከል የወደቀው ዋርካ አላሻግር አለን እንጂ።
ፍሌሜ ይሄ በእኛና በልባችን መካከል የወደቀው ዋርካ መቆየቱ ሲበረታ አረም እያረባ አላስፈላጊ ፍሬ አፍርቶ የልባችንን ሀገር ጋርዶታል።
እኛም አረሙን ከመንቀል ይልቅ ተስማምቶን እየኖርን ነው።
የኔ ፍሌም ፍቅር እኮ የሞት መድሃኒት ናት። ሰው የሞት ሞቱን የሚሞተው ነብስ እና ስጋው ስትለያይ ሳይሆን ፍቅርን ሲያጣ ነው።"አልኳት አይኗን ቡዝዝ አድርጋ በፅሞና ስታዳምጠኝ ከቆየች በኃላ እምባ በአይኗ ሞልቶ የአይን ሽፋሏን አረጠበው።
"ግሩሜ እዚህ የሚደርስ ፍቅር አለኝ ብዬ አስቤ አላውቅም! እወድሃለሁ ግሩሜ"አለች።
ከትርሃስ ጋር ሁሌ የምንነታረካት ነገር ዛሬ ቦታዋን አገኘች አልኩኝ በልቤ። አባብያት መንገዳችንን ቀጠልን።
,,,,,,,,,,,,,, ►►►►►►►►►►►►► ,,,,,,,,,,,,

የሰው ኮቴ ዳና እና ኮሽታ ሰምቼ ዘወር ስል ፍሌም ናት። በዚህ ሰዓት እዚህ ወንዝ ዳር ትመጣለች ብዬ አልገመትኩም።ተነስቼ ቆምኩ ሰላምም ሳትለኝ ዋርካው ስር አጠገቤ ቁጭ አለች።
ድብርብር ብሏታል። ሳቋ እንደ ጉም በኗል። ፍዝዝ ብላለች።ከፍሌም ጋር ሁሌም ዋርካው ስር ስንቀመጥ "ሀደኮ" የምንላት የልጅ እናት ሁሌም እኛ በተቀመጥንበት ቀጥታ መጥታ ውኃ ትቀዳለች።
ውኃ እየቀዳች አይኗን ሰበር አድርጋ ትመለከተናለች። ደስ እንዲላት ፍሌሜን እስማታላሁ። ደስ እያላት አይኗን ሰበር አድርጋ በሀፍረት እጇን በአፏ ጭና እየሳቀች ትሄዳለች።
ሁሌም መጥተን እንደተቀመጥን ትመጣለች። እድስማት እየደጋገመች ታየናለች እስማታለሁ።እጇን በአፏ ጭና እየሳቀች ትሄዳለች።
ዛሬም ልክ ፍሌም ተክዛ መጥታ አጠገቤ ቁጭ እንዳለች መጣች። ውሃውን እየቀዳች ተመለከተችን።....

​​✎ ክፍል አስራ ሶስት (13) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
22.03.202517:40
═•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል አምስት (5)



    ......➲ በስልኬ በሻሸመኔ እና በሀዋሳ ከተማ መካከል ጥቁር ውኃ ተብላ በምትጠራበት ቦታ የበቀለውን ተወዳጁን የሙዚቃ ንጉስ የድምፃዊ ታምራት ደስታን ውብ ትዝታ እየሰማሁ ወደ መናፈሻው ተቃረብኩ።
የሙዚቃው ስሜት በለሆሳስ በውስጤ እየተርመሰመሰ ከንፋሱ ጋር በትዝታ ሰረገላ ላይ በደመና ክምር ውስጥ ይዞኝ እየነጎደ ነው።
ድምፁ በልጅነታችን በተረት የምናውቃትን የተረት ከተማ ኩልል አድርጎ ያስቃኛል። የግጥም እና የዜማው ቁርኝት የልቤን በር ከፍቶ አንድን ሰው እንዳስብ እያደረገኝ ነው።በሌላ በኩል ክረምቱንም በግጥሙ ከትቦታል።
.......🎶 የደጃፌን መዝጊያ ክፍት አድርጌው ነበር
ዛሬም አልተዘጋም ሳትመለስ ስትቀር
አይኔ በእምባ ጭጋግ እንደተጋረደ
ስንት ሰኔ ጠብቶ ስንት ክረምት ሄደ
🎶
እየቆረቆረኝ እያሰረኝ ከእግር እስከ ራሴ
አጎዛው ሊጥለኝ ሲታገለኝ ተረበሸች ነፍሴ..🎶
🎶
እያለ ይቀኛል።ግጥም እና ዜማው እንደ ድር እና ማግ ከድምፁ ጋር ተሰፍቷል ማለት ይቻላል። ሙዚቃውን እናጣጣምኩኝ መናፈሻው ጋ ደረስኩኝ። ሁሌም መናፈሻው ጋር ስደርስ ማዘውተሪያው ፊት ለፊት የድንች ጥብስ ከሚሸጡት ሰዎች ድንች ገዝቶ እየበሉ መሄድ ወደቤት መመለስ ልምዴ ነው። ሙዚቃው ከስሜቴ ጋር ዘለአለማዊ ህያው ምጥቀትን ያላበሰኝ ያህል ከደም ዝውውሬ ጋር የተዋሃደ መሰለኝ።
...🎶 አንቺው ጋር ይቀመጥ እባክሺ የፍቅሬ ትዝታ
የማትመጪ እንደሆን ምን አጥቼ እኔ ልንገላታ 🎶
🎶
ማዘውተሪያውን ተሻግሬ የጅማ ሙዚየሙ በር አከባቢ ስደርስ ከፊት ለፊቴ ያየውትን ማመን አቃተኝ። ልቤ በደስታ ይሁን በድንጋጤ ቶሎ ቶሎ ትመታ ጀመር። ጭንቀት የመከነበት ፤ ደስታ የተንጠፈጠፈበት ፊት አስተዋልኩ። ስታየኝ ፈገግ አለች። እኔም ፈገግኩ። ፍሌም ናት።
በዚህ የመልዓከ ሞት ፈረስ መጋለቢያ ሜዳ በመሰለው ጭጋጋም ምሽት እሷን ማግኘት መታደል ነው ስል አሰብኩኝ።
አንዳች ደስታ ውርር ሲያደርገኝ ይሰማኛል።
የፍሌም ፀዓዳ መሳይ ቀይ ፊቷ እና የሲኦል የፍም ገላ የመሰለው ከንፈሯ ሸሽቶ ጥርስዋ ብቅ ሲል ጉራማይሌዋ በምሽቱ ጭላንጭል ብርሃን ሲታየኝ አለማንም ከልካይ ተንደርድሬ ሄጄ አቀፍኳት። ምንም አላለችም ይልቁንም አፀፋዋን በማቀፍ መለሰች።
"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።..............


✎ ክፍል ስድስት (6) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
25.03.202514:55
•⊰❂ ♥ ተከታታይ ልቦለድ ♥ ❂⊱• ══ ❦ 

                      ♥ ፍሌም ♥
               ✅ ክፍል ስድስት (6)


"ግሩሜ እንዴት ነህ?" አለችኝ ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይረጋ ከለበሰችው ኮት ጋር ትልቅ ሰው መስላለች።
"ደህና ነኝ ከየት ነው በዚህ ሰዓት?"አልኳት
"ባሌ ሰለቸሽኝ ሲለኝ ለአንዷ ሰጥቼው መመለሴ ነው አልገርምም?" አለችኝ ይበልጥ ፈገግ እያለች፤ ፈገግታዋ ልብ ያሞቃል በዚህ ብርዳም ምሽት እሷን በማግኘቴ ተደሰትኩ።
"ይገርምሻል እኔም ሚስቴ የሆነ ሰውዬ ጋ አየናት ያውም የሆነች ቆንጅዬ ሴት ናት አሉ 'ባሌን ውሰጂው ብላ የሰጠችው' ብለውኝ እኮ ጉድ ብዬ ስልኬን ስዘጋ ተገናኘን ወይ መገጣጠም!" አልኳት።
ከት ብላ ስቃ ስታበቃ "አቦ በአላህ ደስ ትላለህ አሳከኝ!" አለች በልስልስ ጥዑም አንደበቷ።
"ይልቅ ከየት ነሽ?" አልኳት ውብ አይኗ ላይ አይኔን ተክዬ
"አጎቴ ከጉዋደኞቹ ጋር አስተዋውቆኝ እቆያለሁ አንቺ ብሎኝ መመለሴ ነው። አንተስ ግሩሜ?" አለች።
አይ እኔማ ወክ እያደረኩ ነበር ካልቸኮልሽ ለምን ተቀምጠን አናወራም ?"  አልኳት የመናፈሻውን ግቢ በአይኔ እየጠቆምኳት።
ጭንቅላቷን በመነቅነቅ እሺታዋን ገለፀችልኝና ገብተን የመናፈሻው ወንበር ላይ ተቀምጠን ስለብዙ ነገር አወራን። ወሬያችን ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ፍሌም በሳቅ ትንከተከት እንደነበር አስታውሳለሁ!።
ጥቂት የማይባል ጊዜ እንዳወራን  የሰዓቱን መንጎድ ተመልክታ እንድንሄድ ጠየቀችኝ። ተያይዘን ከመናፈሻው ቅፅር ግቢ ስንወጣ ሰዓቱ ሁለት ሰዓት ከሰላሳን አጋምሶ ለሶስት ሰዓት ግስገሳውን አፍጥኖታል።
ታክሲም ሆነ ባጃጅ ጥድፊያ ነው። በእግራችን አዘገምን በጉዞአችን በበረደኝ ሰበብ ከፍሌሜ ጋር እየተጠጋጋን እየተጠጋጋን በስተመጨረሻ ተቃቅፈን ጉዞአችንን ባጀነው።
የእሷ መታጠፊያ ጋ ስንደርስ ይበልጥ ተቃቅፈን ትንሽ ከቆየን በኃላ "ደህና እደር ግሩሜ " አለችኝ "ደህና እደሪልኝ" ብዬ አፀፋውን መልሼ ወደ ቤት  አዘገምኩ።
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተንጋልዬ ያፈራነውን እያመሰኳሁ እንቅልፍ ይዞኝ ሄደ።


ከዛች ምሽት ወዲህ ከፍሌም ጋር በሰፊው መገናኘት መቀራረብ ቻልን። ፍሌም ከድሬ በበለጠ እዚህ ከመጣች ወዲህ ደስታዋ እንደጨመረ ዘውትር ታወሳኛለች። አጎቷ ለፊልድ ወጣ ካለ መናፈሻው አይቀረን ሲኒማው አይቀረን የወንዝ ዳር ደፎች አይቀሩን ፣ በየመንገዱ ላይ ስንፈስ ነው የምንውል የምናመሸው!?።
እንዲህ እንዲህ እያልን ክረምቱን ለመባጀት ተቃረብን ሀምሌን ሸኝተን ነሀሴን አጋምሰነዋል። ይሄኔ እኔ ክፉኛ ጨነቀኝ ፍሌሜን ማጣት አልፈለኩም እሷን ማጣት ሞትን የመቀበል ያህል ከበደኝ። ስቀርባት እንደምትርቀኝ አልታወቀኝም ነበር መሰል።
ያን ሰሞን ቁዘማ ስራዬ ሆነ። ቤት ውስጥ ንጭንጭ አበዛለው ብቻዬን መዋል ማደርን አዘወትራለው። ፍሌም ስታስጠራኝም የለም አስብል ጀምሬያለሁ።


​​✎ ክፍል ሰባት (7) ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like &  Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
          ┄┄┉┉✽‌✽‌✽‌ ┄┄┉┉
         ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
                 💗💗------💗💗------
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
💛
@MENTA_LIBOCHE 💜
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.