Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
ibnu_ibrahim(ابن إبراهيم) avatar
ibnu_ibrahim(ابن إبراهيم)
ibnu_ibrahim(ابن إبراهيم) avatar
ibnu_ibrahim(ابن إبراهيم)
21.04.202517:13
ራሱን መግዛት የማይችል ሁላ እየተነሳ <የራሴ ግዛት ቢኖረኝ ኖሮ ሳቅሽን ብሄራዊ መዝሙር አደርገዉ ነበር እማ የኔ እናት> እያለ ይበጠረቃል

መጀመሪያ እስቲ እዚያዉ ባለህበት እናትህን አግዛቸዉ... ከዛ በኃላ ወደ ራስህ ግዛት እንመጣለን ➢ ፕሮፋይል በለጠፈኮ አይደለም። በጥራቂት አንቺንም ይመለከታል
20.04.202503:42
አርቴፊሻል መቀመጫ ፣ አርቴፊሻል ጥፍር ፣ አርቴፊሻል ደረት ( ሁለት ሶስት ብራ ደርበው እየለበሱ ) ፣ አርቴፊሻል የፊት ከለር ( እጃቸውና ፊታቸው ያለው ልዩነት ) ፣ አርቴፊሻል ፀጉር ( ሙስሊሞቹም… አንዳንዶቹ ጋቢ የሚያህል የፀጉር ማስያዣ እያደረጉ ) ፣ አርቴፊሻል የሰውነት ቅርፅ ( በ spanx ሼፐር ቦርጭ ለመደበቅ ኩላሊታቸውን እና ጉበታቸውን አጣብቀው ) …. ያሉ ሴቶች አርቴፊሻል ማንነት እንደማይኖራቸው ትጠራጠራለህ ? ደግሞ አርቴፊሻል ፀባይ እና ድምፅም አላቸው ። የሚስለመለሙት ነገር ። ለማንኛውም ዐይንህን ሰብረህ መንቀሳቀስ ይኖርብሃል ያ ካልገራህ ግን የምታየው እውነት እንዳልሆነ እወቅ በየሄድክበት ልብህ አይሸፍት ።

ካነበብኩት
18.04.202512:05
ዛኪር ማለት ልቡ ወንጀል ላይ እየዘወተረ ሱብሃነልሏህ አልሐምዱ ሊላህ  የሚል አይደለም።
ዛኪር የሚባለውማ ወንጀል ለመስራት ሲያስብ ድብቅ ሚስጥሮችን አዋቂው አላህ ፊት መቆሙን የሚያስታውስ ነው።

📚 ተዝኪራ/ኢብኑል-ጀውዚ

ቻናል፦
https://t.me/ibnu_ibrahim11
17.04.202515:33
🎯አህባቢ ፊላህ በቀጣይ በምን እርእስ ፁፍ ይዘጋጅ ትላላቹ እስቲ በናተ ምርጫ ላርገው

በዚ አሳውቁኝ➢
@mustefa123

ወይም በዚ በቦት➢
@Mustefa1233bot

ሌላም ስለ ቻናሌ የምትሉኝ ሀሳብ አስቴትም እቀበላለሁ ወጀዛአኩመላሂ ኸይር🌹
16.04.202517:22
ደስ የሚል እንቅልፍ ለመተኛት ወይም በትንሹ ሞት ለመርካት አልጋህንና ትራስህን እንደምታመቻቸው በትልቁ ሞትም እንድትረካና እንድትደሰት ከወንጀልህ ተውባ አድርገህ ወደ አላህ ተመለስ
15.04.202510:37
🎯ምኞትህን ሁሉ ሱጅድ ላይ አስቀምጠው:ጌታህ ዝቅ ብሎ የለመነውን ባሪያውን በባዶ አይመልስም🌹
20.04.202508:45
«አምላክ ሰውን ለማዳን የግድ ሰው መሆን አለበት ብሎ ማለት፥ አንድ የእንስሳት ዶ/ር ከብት ለማከም የግድ ከብት መሆን አለበት እንደማለት ነው።»

አገናቹኝ ሀሳቤ👍
19.04.202520:58
📖
     ከቁርኣን ተኣምራት…………

የሙእሚን ነፍስ ስትወጣ ለምን:
   {ወደ ጌታሽ ተመለሺ} እንጂ ወደ "ጌታሽ ሂጂ" አትባልም?


የመሄድ እና የመመለስ ልዩነታቸው ምንድን ነው?

መሄድ ማለት………
    መዘውተሪያ ከሆነው ቦታ ጊዜያዊ ወደሆነው ቦታ የሚደረግ ጉዞ ሲሆን

መመለስ ማለት………
   ጊዜያዊ ከሆነው ቦታ መዘውተሪያ ወደሆነው ቦታ የሚደረግ ጉዞ ነው።

ለምሳሌ፦
"ወደ ሱቅ ሄጃለሁ", "ወደ ቤት ተመልሻለሁ" ትላለህ።
ግን
  "ወደ ሱቅ ተመልሻለሁ", "ወደ ቤት ሄጃለሁ" አትልም።

ለዚህም ነው ነብዩላህ ሱለይማንﷺ መልእክተኛውን በላከ ጊዜ እንዲህ ያለው፦
📖{اذْهَب بِّكِتَابِي هَذَا فَأَلْقِهْ إِلَيْهِمْ}
{ይህንን ደብዳቤዬ ይዘህ
ሂድ: ወደ እነርሱም ጣለው።}
    [አል_ነምል:28]

  ከንግስቷ ወደ ሱለይማን ተልኮ ለነበረው መልእክተኛ ሲመልስ ግን እንዲህ አለው፦
📖{ارْجِعْ إِلَيْهِمْ}
{ወደ እነርሱ
ተመለስ።}
    [አል_ነምል:37]


ስለሆነም አንድ ሙእሚን በሚሞት ጊዜ አላህ ለነፍሱ
📖{ارْجِعِي إِلَى رَبِّكِ رَاضِيَةً مَّرْضِيَّةً}
  {ወዳጅም ተወዳጅም ሆነሽ ወደ ጌታሽ
ተመለሺ።} ይላታል
  [አል_ፈጅር:28]

  {ወደ ጌታሽ ተመለሺ} እንጅ "ወደ ጌታሽ ሂጂ" አይላትም።
ምክንያቱም፦ ዱንያ ለአንድ ሙእሚን ጊዜያዊ መቆያው እንጅ ዘላለም መዘውተሪያው አይደለችም።

  ዘላለም መዘውተሪያ አላህ ዘንድ ያለው አኼራ ላይ ብቻ ነው። አላህ በሌላ ቦታ እንደገለፀው፦

📖{وَاتَّقُوا يَوْمًا تُرْجَعُونَ فِيهِ إِلَى اللَّهِ}
{በእሱ ውስጥ ወደ አላህ የምትመለሱበተን ቀን ተጠንቀቁ።}

    [አል_በቀራ:281]

እዚህ ቦታም ላይ {ወደ አላህ የምትመለሱበት} እንጅ "የምትሄዱበት" አላለም።

ምክንያቱም፦
  መዘውተሪያችን አኼራ ሲሆን: እቺ ዱንያ ግን ጊዜያዊ መቆያ ብቻ ናት።


📖ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል!!

ኢሻአላህ ይቀጥላል......

ቻናል፦
https://t.me/ibnu_ibrahim11
18.04.202506:36
🎧🌹ቁርዓን🌹🎧
🎧🌹የልቤ 🌹🎧 ሱረቱል-ከህፍ
🎧🌹ብርሃን🌹🎧 ተጋበዙልኝ


የጁምዓ ሱናዎች :-👇

👉ገላን መታጠብ
👉ከሌላ ግዜው የተሻለ ቆንጆ ልብስ መልበስ
👉ሽቶ መቀባት
👉ሱረቱል ከህፍን መቅራት
👉በግዜ ወደ መስጅድ መግባት
👉ዱዓ ማብዛት
👉በነቢዩ ﷺ ላይ ሶለዋት ማብዛት
👉መስጅድ ከገቡ ቡሃላ በሁለት ሰዎች ትከሻ አለመረማመድ ሰውን አዛ አለ ማድረግ

ማሳሳቢያ:- ሽቶ መቀባት የተባለው ለወንዶች ብቻ ነው። ሴት ልጅ ሽቶ ተቀብታ ከቤት መውጣት ሀራም ነው ኡኽቲ ተጠንቀቂ‼️

اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد🌸🌺
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد🌸🌺
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد🌸🌸
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد🌺🌸
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد🌸🌺
اللهم صلِّ وسلم على نبينا محمد🌸🌺

አደራ ምላቹህ ነገር ቢኖር የፍልስጤም ወንድም እህቶቻችንን በዱዓ አንርሳቸው
በቁማቸው እያቃጠሏቸው ነው አሏህ ነስሩን ቅርብ ያድርግላቸው ከነፍሳ በላ የሰው አውሬዎች ጭካኔ ይሰውራቸው በቃቹህ ይበላቸው ደስታቸውን ያሳየን أللهم آمين يارب العالمين🤲🤲
17.04.202514:58
ይጣረሳልን (is it Contradict) ?

የክርስቲያኖች ብዥታ :- "ዘይነብ ቢንት አል'ሃሪስ ተገድላለች ምክንያቱም ነብዩን በመርዝ ለመግደል ስለሞከረች እንዲሁም ዘገባው ይጣረሳል"

▣ መልስ :- ነብዩን ለመግደል ስለሞከረች አልተገደለችም እንዲሁም የሀዲስ ዘገባዎቹ በፍፁም የሚጣረሱ አይደሉም! በቅድሚያ ልናውቀው የሚገባው ነገር ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ ዐረፍተ-ነገሮች ፣ መዛግብት ፣ አናቅጽት ፣ ዜናዎች ...ወ.ዘ.ተ ይጣረሳሉ ከማለት በፊት የህገ-ቅራኔ ቅድመ-መስፈርቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ ይኖርብናል።

➣ ህገ-ቅራኔ (The law of contradiction)

1. በተመሳሳይ ሁኔት (T𝔥𝔢 𝔰𝔞𝔪𝔢 situation)
2. በተመሳሳይ ጊዜ (T𝔥𝔢 𝔰𝔞𝔪𝔢 time)
3. በተመሳሳይ የቃላት ትርጉም አጠቃቀም (𝖈𝖔𝖓𝖙𝖗𝖆𝖉𝖎𝖈𝖙 word)

በተወሰነ መልኩ ከላይ የተወሱት 3 መስፈርቶች (Conditions) ከተሟሉ መዛግብት ፣ አንቀፆች ፣ ዜናዎችን ፣ ሀሳቦችን ...ወ.ዘ.ተ ይቃረናሉ (Contradict) ለማለት ያመቸናል።

ለምሳሌ

1. ፉኣድ ሀብታም ነው።
2. ፉኣድ ድሀ ነው።

እነዚህ ሁለቱ ገለፃዎች የማይጣረሱ (የማይቃረኑ) ሊሆኑ ይችላል።

1ኛ. ተመሳሳይ ሁኔታ ላይሆን ይችላል የሚናገረው ስለ ሁለት የተለያዩ ፉኣዶች (ሰዎች) ከሆነ አይቃረንም።

2ኛ. ስለ አንድ ፉኣድ እንኳ ቢሆንም በተመሳሳይ ጊዜ ላይሆን ይችላልና ድሮ ሀብት የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ድሀ ቢሆን አይቃረንም (አይጣረስም)።

3ኛ. ስለ አንድ አካል (ፉኣድ) ተመሳሳይ ጊዜና ሁኔታም ቢሆንም ለገለፃ የገቡ ቃላቶች በተመሳሳይ (የሚጣረሱ) የቃላት ትርጉም አጠቃቀም ላይሆን ይችላልና ላይጣረሱ ይችላሉ። ፉኣድ ሀብታም ነው ሲባል የገንዘብ ሀብታም ቢሆንና ድሀ የተባለው ግን የመንፈስ ድሀ ቢኾን በፍፁም አይጣረስም።

ህገ-ቅራኔን በደንብ ከተረዳን ሙስሊም ላይ የተዘገበው  (the Companion's of the Holy Prophet) said: Should we not kill her? Thereupon he said: No. 

  "አንገድላትምን?" ብሎ ሲጠይቋቸው 《በፍፁም አይሆንም》 በማለት መልስ ሰጡ። 📚 ሙስሊም 2190 a

በመርዝ ከመረዘችው ምግብ ከሷቸው ጋር የበላው ሰሀቢይ ቢሺር ብን አል'በራእ በዛን ሰዓት (immediately) በመርዙ ምክንያት አልሞተም ነበር ።

• ነገር ግን ከትንሽ ቆይታ በኋላ ቢሺር ስለሞተ ሰዉንም ሆን ብላ በመርዝ መርዛ ስለገደለች
በዚህ ምክንያት ሸሪዓዊ ፍርድ ተወሰነባት።

Exodus - ዘጸአት - 21:12-17

12: “ሰው ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ እርሱ ፈጽሞ ይገደል።
15: አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ፈጽሞ ይገደል።
17: አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ ፈጽሞ ይገደል።

➣ በባይብል ሰዉን ሆን ብሎ የገደለ ይቅርና የቤት እንስሳህ ሰዉ ቢገድል ትገደላለህ።
Exodus 21 አማ - ዘጸአት
29: በሬው ግን አስቀድሞ ተዋጊ ቢሆን፥ ሰዎችም ለባለቤቱ ቢመሰክሩለት ባይጠብቀውም፥ ወንድንም ወይም ሴትን ቢገድል፥ በሬው ይወገር፥ ባለቤቱ ደግሞ ይገደል።

አስተንትኖት

ነብዩን ለመግደል ምግብ በመርዝ መርዛ አብልታቸው እሷቸው አልሞቱም ከመሆኑም ጋር የግዲያ ሙከራ ተደረገብኝ ብለው ትገደል አላሉም! ይልቁንም አትገደልም በማለት ተከላከሉላት! የትኛው መሪ ነው እንዲህ አይነት ባህሪይ ያለው?!

- ዘይነብ ቢንተ አል'ሃሪስ ኢብን ሰላም ነብዩ ይቅርታ ማድረጋቸዉን ባየች ጊዜ ሰለመች ከዛ በኋላ ነው ሰሀቢዩን በመግደሏ የተገደለችው ሰሃቢያ ሁና ሞተች። 📚 ሙስነፍ ዐብዲረዛቅ ገፅ 8/470 ፣  ፈትሁል ባሪ ገፅ 9/348

➣ "አላህም ከሰዎች ይጠብቅሃል፡፡"
معناه 《يعصمك من القتل》
ትርጉሙም መልዕክትን ሙሉ እስከ ምታደርስ ድረስ《ከመገደል ይጠብቀሀል።》

۞ يَا أَيُّهَا الرَّسُولُ بَلِّغْ مَا أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ ۖ وَإِن لَّمْ تَفْعَلْ فَمَا بَلَّغْتَ رِسَالَتَهُ ۚ وَاللَّهُ يَعْصِمُكَ مِنَ النَّاسِ ۗ إِنَّ اللَّهَ لَا يَهْدِي الْقَوْمَ الْكَافِرِينَ
አንተ መልክተኛ ሆይ! ከጌታህ ወዳንተ የተወረደውን አድርስ፡፡ ባትሠራም መልክቱን አላደረስክም፡፡ አላህም ከሰዎች ይጠብቅሃል፡፡ አላህ ከሓዲዎችን ሕዝቦች አያቀናምና፡፡ 📗 ቁርአን ሱረቱል ማኢዳ 5:67

- ነብዩ ሙሀመድ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እውነተኛ ነብይ መሆናቸውን ስላረጋገጠች ሰለመች። አቢ ኑዓይም አል'አስበሃኒይ 📚ደላኢሉ አን'ኑቡወህ ገፅ 1/197 ፣  ደላኢሉ አን'ኑቡወህ ገፅ 4/259 (አል'በይሃቂይ)

የነብዩን ባህሪን ከተረዳችሁልን አይቀር እናንተ "አምላካችን" የምትሉት ልብሳችሁን ሽጣችሁ ሰይፍ ግዙ ይላል። “እርሱም፦ አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይውሰድ፥ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ።”   — ሉቃስ 22፥36


ቻናል፦
https://t.me/ibnu_ibrahim11
16.04.202510:29
እኤንን ሁላቹም ስሙት👂

ፁፍ ስፅፈው ምክያያቴ እና እዲ ማለት የፈለኩበት ምክንያቴ ጭምር ቁጭ አርጌያለሁ

ከአህባሺዮች ጋር በነበረኝ ውይይት የገጠመኝን ተተርሼ እደፅፍኩት ጭምር

ቢቻ አዳምጡት ሙሉ መልሱ አለ

በንግግሬ ስህተት ካለብኝ አርሙኝ በዚ➢
@mustefa123
🎙ሰለምቴው ወድም ሙስጠፋ ነኝ
14.04.202519:47
ከጀነት ውጪ ያለ ፀጋ ሁሉ አላቂ ነዉ:ከእሳት ዉጪ የሆነ መከራ ሁሉ አላፊ ነዉ
20.04.202507:13
🚧 ጥንቃቄ  🚧

➠ በተለያዩ ዌብሳይቶች ለሀዲሶች  የእንግሊዝኛ ትርጉም የምትጠቀሙ እየተጠነቀቃችሁ።
የሚመረጠው አረብኛውን መጠቀም ወይም አረብኛ በሚችሉ ታማኝ ኡስታዞች ማስተርጎም አለባችሁ።
-- ዌብሳይቶቹ በጣም ብዙ ስህተት አለባቸው
እንደምሳሌ ሁለት ስህተቶችን  ልጥቀስላችሁ
🎯 ስህተት 01
💥 በ أدب الممفرد حديث ٧٠٠  [adab lmufarad hadith 700]
በተዘገበው ሀዲስ ላይ ነቢያችን ዱዓ ሲያደርጉ ያደርጉት የነበረው ዱዓ ላይ" لا إله إلا الله" ላኢላሃ ኢላሏህ (ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) የሚለውን
💥ከላይ ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ሲተረጉሙት በጣም በጣም ከባድ ስህተት ተሳስተዋል።
ሲተረጉሙት there is no god but prophet( ከነቢዩ በቀር እውነተኛ አምላክ የለም)😢 ብለው ተርጉመውታል። ከባድ ስህተት

🎯ስህተት 02
💥 በ سنن أبي داود 3080  [sunan abi dawud 3080]
በተዘገበው ሀዲስ ላይ የነቢያችን ሚስት የነቢዩን ፀጉር ታበጥርላቸው ነበር أنها كانت تفلي شعر رسول الله
የሚለውን ከነቢዩ  ፀጉር ቅማል ትቀምል ነበር። በሚል ተርጉመውታል። ስህተት ነው። ሀዲሱ ላይ የለም። ቅማል በአረብኛ قمل ቁመል ነው ሚባለው። قمل የሚል ቃል ሀዲሱ ላይ የለም።
➵ ከላይ በምትመለከቱት የእንግሊዝኛ ትርጉም ኪታብ ላይም ታበጥር ነበር እንጂ ትቀምል ነበር የሚል የለም።

🎯እና ጥንቃቄ አድርጉ
ካፊሮች በብዛት የሚያመጧቸው ጥያቄዎች እነዚህን ስህተቶች በመያዝ ነው።

ይህ ስላችሁ ሙሉ ለሙሉ ስህተት ነው ማለቴ አይደለም።
ለማንኛውም ጥንቃቄ እያደረጋችሁ 🙌

ቻናል፦
https://t.me/ibnu_ibrahim11
19.04.202514:26
➢#የንፅፅር_ትምህርት እና #በእስልምና ላይ #ለሚነሱ_ትችቶች መልስ የሚሰጥበት #ቻናል ልጦቅማቹ

➢#ተቀላቀሉ የሚለው #በመንካት ይቀላቀሉ👇👇
18.04.202506:04
↩️ قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين

🌼የአላህ መልዕክተኛ ነብያችን ﷺእንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል።))
📚 صحيح الجامع - رقم : (6470)

⏮لقولهﷺ أكثروا من الصلاة عليَّ ليلة الجمعة وىوم الجمعة فإنَّ صلاتكم معروضة عليَّ

🌼 እንዲሁም ብለዋል ﷺ የጁመዕ ሌሊትና  ቀኑ ለይ በኔ ሰለዋትን  አብዙ። ሶለዋታችሁ እኮ ለኔ ይቀርብልኛል።
اللَّهُــمَّ صَلِّ وَسَـــلِّمْ وَبَارِكْ على نَبِيِّنَـــا مُحمَّد


ቻናል፦
https://t.me/ibnu_ibrahim11
15.04.202518:10
መሃይም ካጋጠመህ ከመሃይም
ጋር እኩል መሃይም መሆን አለብህ
እንጂ መሃይምን በእውቀት ልታሸንፈው አትችልም


እውነት👍ሀሰት👎
እስቲ የተመቻቹ🌹👍

▣አባቶቻችን አላህ ይጠብቅልን እረጅም እድሜ ከጤና ጋር እና በተውሒድ ኑሮ በተውሒድ ከሚሞቱት ያርጋቸው አላሁመ አሚንን 🤲🤲

🎯ወደ አኤራ የተሻገሩ አባቶቻችን ደሞ የላቀው እና የተከበረው አላህ አዘ ወጀል ፊርደውሰን አህላ ይወፍቃቸው አላሁመ አሚንንን🤲🤲

ኢስላም  የነቢያት  ሀይማኖት
20.04.202507:13
19.04.202507:15
" ላጤ ሁናችሁ ለቅርብ ጓደኛችሁ ባሌ ባልሽ የምትሉ ሴቶች ካገባችሁ በኋላ ብናወራ አይሻልም ?! ስታገቡ ገደል ግቢ ከኔ አፍ አልወጣም እኔ አላልኩም ልትሉ አሁን የምታወሩ እረፉ ¡
17.04.202517:27
"እሥልምናን" መቀበል "መሰናከል" "ሳይሆን "መስተካከል" ነው።

✍ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
17.04.202505:35
የትክክለኛ ፍቅር መነሻው ኒካህ

መድረሻው ደግሞ ጀነት ነው።
15.04.202511:15
ፈታዋ ኑር ዐላ አድ-ደርብ

ኢማም ሱዩጢ (አላህ ይዘንላቸውና) የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወላጆች (ከጀሀነም) እንደሚድኑ፣ ከሞቱ በኋላ አላህ ህይወትን እንደመለሰላቸውና በእርሳቸው እንዳመኑ የሚል አመለካከት ነበራቸው።

ይህ አመለካከት እነዚያን የሚያመለክቱ ሐዲሶች የተፈበረኩ (መውዱዕ) ወይም በጣም ደካማ (ደዒፍ ጂዳን) ናቸው ብለው በፈረዱ አብዛኞቹ ምሁራን ውድቅ ተደርጓል።

‘አውን አል-መዕቡድ’ ላይ እንዲህ ይላል፡-
የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወላጆች ህይወት እንደተመለሰላቸውና በእርሳቸው እንዳመኑና እንደዳኑ የሚገልጹ አብዛኛዎቹ ዘገባዎች የተፈበረኩና ሐሰት ናቸው። አንዳንዶቹ በጣም ደካማ ናቸው እና በምንም አይነት ሁኔታ ሰሂህ ሊሆኑ አይችሉም፣ የሐዲስ ኢማሞች እንደ ዳራቁጥኒ፣ ጀውዘቃኒ፣ ኢብኑ ሻሂን፣ ኸጢብ፣ ኢብኑ ዓሳኪር፣ ኢብኑ ናሲር፣ ኢብኑል ጀውዚ፣ ሱሃይሊ፣ ቁርጡቢ፣ ሙሂብ፣ ጠበሪ፣ ፈትህ አድ-ዲን ኢብኑ ሰይድ አን-ናስ፣ ኢብራሂም አል-ሐለቢ እና ሌሎችም በአንድ ድምፅ የተፈበረኩ እንደሆኑ ስለተስማሙ። ምሁሩ ኢብራሂም አል-ሐለቢ የነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወላጆች ከጀሀነም እንዳልዳኑ በተለየ ጽሑፍ በስፋት አስረድተዋል፣ እንዲሁም ዓሊ አል-ቃሪ በሸርህ አል-ፊቅህ አል-አክበር እና በተለየ ጽሑፍ አስረድተዋል።

የዚህ አስተያየት መሰረት የዚህ ሐዲስ ("አባቴም የአንተም አባት በጀሀነም ናቸው") ትክክለኛነት ነው። ሸይኽ ጀላሉዲን ሱዩጢ ከሐፊዞች እና ምሁራን ተቃውመው እንዳመኑ እና እንደዳኑ አረጋግጠዋል፣ እናም በዚህ ርዕስ ላይ በርካታ ጽሑፎችን ጽፈዋል፣ ከነዚህም መካከል አል-ተዕዚም ወል-ሚናህ ፊ አና አበወይ ረሱል-ኢላህ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ፊል-ጀናህ ይገኝበታል።

ሸይኽ አል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (አላህ ይዘንላቸውና) ተጠየቁ፡- የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወላጆቻቸውን ሙስሊም እንዲሆኑ አላህ ህይወትን እንደመለሰላቸው፣ ከዚያም (እንደገና) እንደሞቱ የሚገልጽ ሰሂህ ዘገባ አለን?

እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ፡- ከሐዲስ ሊቃውንት በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም አይነት ሰሂህ ዘገባ የለም። ይልቁንም ምሁራኑ ይህ የፈጠራ ውሸት እንደሆነ በአንድ ድምፅ ይስማማሉ... ይህ እጅግ በጣም ግልጽ ከሆኑ የፈጠራ ስራዎች አንዱ እንደሆነ ምሁራን መካከል ምንም አይነት አለመግባባት የለም፣ እውቀት ያላቸው ሰዎች እንደተናገሩት።

ይህ በሰሂህ፣ በሱነን፣ በሙስነድ ወይም በሌሎች ታዋቂ የሐዲስ መጽሃፍት ውስጥ ባሉ አስተማማኝ የሐዲስ መጽሃፍት ውስጥ አይታይም። ደካማ (ደዒፍ) ዘገባዎችን ከሰሂህ (ትክክለኛ) ዘገባዎች ጋር ቢያወሩም የመጋዚ ወይም የተፍሲር መጽሃፍት ደራሲዎች እንኳን አልጠቀሱትም።

ይህ ውሸት መሆኑ ለማንኛውም የሃይማኖት እውቀት ላለው ሰው ግልጽ ነው። እንደዚህ ያለ ነገር ተከስቶ ቢሆን ኖሮ እሱን ለማስተላለፍ ከፍተኛ ተነሳሽነት ይኖር ነበር፣ ምክንያቱም በሁለት ጉዳዮች ላይ ያልተለመደ ነገር ነውና፡ ሙታንን ማሳደግ እና ከሞት በኋላ ማመን። እንደዚህ ያለ ነገር ከሌላ ከማንኛውም ነገር በላይ ለመተላለፍ ይበልጥ የሚገባው ነበር። ምንም አይነት የታመነ ዘጋቢ ስላላስተላለፈው ይህ ውሸት እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

ከዚህም በላይ ይህ ቁርኣን እና ሰሂህ ሱና እንዲሁም የምሁራንን ስምምነት ይቃረናል።

ኢሻአላህ ክፍል❸ ይቀጥላል...
..

ቻናል፦
https://t.me/ibnu_ibrahim11
14.04.202517:20
➢ውድና የተከበራቹ የ➢ኢስላም የነቢያት ሀይማኖት ቤተሰቦች አድ ነገር አሰብኩ👇

🎯በዚ ቻናል ግድም ውድድር ላዘጋጅ ቢዬ አሰብኩ

➢ውድድሩ የሚሆነው ግጥም ነው

ግጥሙ ስለ እናት ነው


🎯ሽልማቹ የሚሆነው #በላይክ👍ብዛት   ነው ከ 1 እስከ 5 ለወጡ የካርድ ይሸለማት አላቸው

▣መወዳደሬያ ግጥማቹ በዚ➢@mustefa123 ላኩ

⚠️ማሳሰበያ የምልኩት ግጥም ስለ እናት ቢቻ ነው ከዛ ውጪ አልቀበልም ሳህ

መወዳደር የምፈልጉ በዚ ላኩ ➢@mustefa123

ውድድሩ የሚካኤድበት ቻናል 👇👇👇
https://t.me/+ea9yXKVmoa1mZjg0
https://t.me/+ea9yXKVmoa1mZjg0
Паказана 1 - 24 з 316
Увайдзіце, каб разблакаваць больш функцый.