Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Мир сегодня с "Юрий Подоляка"
Труха⚡️Україна
Труха⚡️Україна
Николаевский Ванёк
Николаевский Ванёк
💞አውደ💞 ቃል 💞💖 avatar
💞አውደ💞 ቃል 💞💖
💞አውደ💞 ቃል 💞💖 avatar
💞አውደ💞 ቃል 💞💖
05.05.202520:46
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
Deleted04.05.202519:41
🔥👏 ተከፈተ ተከፈተ ተከፈተ 👏🔥

🥳 አስደሳች ዜና 🥳

🔴ለአርሴናል እና ለማንቺስተር ዩናይትድ 🔴 ደጋፊዎች አዲስና ለየት ያለ ቻናል የዘነላችሁ መጥተናል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የአርሴናልና የማንችስተር ዩናይትድ ቻናል ነው መረጃዎችን በአንድ ቦታ በአንድ ቻናል ለየት ባለ ሁኔታ የዘነላችሁ መጥተናል ከናንተ የሚጠበቀው ቻናሉን join በማረግ ቤተሰብ ማሆን ብቻ ነው ::
✞ ማክሰኞ- ቶማስ ይባላል፡-

በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ "ጌታዬና አምላኬ" ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ.፳፥፳፯-፳፱

                 🌹🌹
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
                 🌷🌷
20.04.202506:07
#እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤ አደረሳችሁ

            ✨ «ትንሣኤ» ✨
የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡ መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡
«ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡
«ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡
          አከፋፈል
✨አንደኛው «ትንሣኤ» ኅሊና ነው፡፡ ይህም ማለት ተዘክሮተ እግዚአብሔር ነው፡፡

✨ሁለተኛውም «ትንሣኤ» ልቡና ነው፡፡ የዚህም ምስጢሩ ቃለ እግዘብሔርን መስማትና በንስሐ እየታደሱ በሕይወት መኖር ነው፡፡

✨ሦስተኛው «ትንሣኤ» ለጊዜው የሙታን በሥጋ መነሣት ይሆናል፡፡ ነገር ግን ድጋሚ ሞት ይከተለዋል፡፡

✨አራተኛው «ትንሣኤ» የክርስቶስ በገዛ የባሕርይ ሥልጣኑ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት ነው፡፡ የእርሰ ትምህርታችንም መሠረት ይኸው እንደሆነ ይታወሳል፡፡

✨አምስተኛውና የመጨረሻው «የትንሣኤ» ደረጃም የባሕርይ አምላክ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን «ትንሣኤ» መሠረት ያደረገ «ትንሣኤ ዘጉባኤ» ነው፡፡ ይህም ከዓለም ኅልፈት በኋላ ሰው ሁሉ እንደየሥራው ለክብርና ለውርደት፣ ለጽድቅና ለኩነኔ በአንድነት የሚነሣው የዘለዓለም ትንሣኤ ይሆናል፡፡

☦#የትንሣኤ በዓል በቃሉም ምስጢር በይዘቱም ስለሚመሳሰሉ ጥላው ምሳሌውም፣ ስለሆነ «ፋሲካ» ተብሎ ይጠራል፡፡ «ፋሲካ» ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ «ፌሳሕ» በጽርእ በግሪክኛው «ስኻ» ይባላል፡፡ ይህም ወደ እኛው ግእዝና ዐማርኛ ቋንቋችን ሲመለስ ፍሥሕ ዕድወት = ማዕዶት፣ በዓለ ናእት = የቂጣ በዓል፣ እየተቸኮለ የሚበላ #መሥዋዕት፣ #መሻገር #መሸጋገር ማለት ነው፡፡

☦#ታሪካዊ መልእክቱ በዘመነ ኦሪት ይከበር የነበረው በዓለ ፋሲካ እስራኤል ዘሥጋ ከግብጽ የባርነት ቀንበር ወደነፃነት የተላለፉበት፣ ከከባድ ሐዘን ወደ ፍጹም ደሰታ፣ የተሸጋገሩበት በዓል ነበር፡፡ በዚህ ኦሪታዊ ምሳሌ በዓል አሁን አማናዊው በዓል «ትንሣኤ» ተተክቶበታል፡፡

☦#ፋሲካ፣ በዓለ ትንሣኤ በዘመነ ሐዲስ እስራኤል ዘነፍስ የሆኑት ምእመናነ ክርስቶስ ትንሣኤውን የሚያከብሩበት ዕለት ሆኖ በእርሱ ትንሣኤ #ከኀጢአት ወደ ጽድቅ፣ ከኀሳር = ከውርደት ወደክብር፣#ከጠላት ሰይጣን አገዛዝ ወደ #ዘለዓለማዊ ነፃነት፣ #ከአደፈ፣ #ከጐሰቆለ አሮጌ ሕይወት ወደ ሐዲስ ሕይወት የተሻገሩበት ታላቅ መንፈሳዊ የነፃነት በዓል ነው፡፡

☦#ክርስቲያኖች የትንሣኤን በዓል በታላቅ ደስታና መንፈሳዊ ስሜት ያከብሩታል፡፡ ስለዚህም ከበዓላት ሁሉ የበለጠ ሆኖ ይታያል፡፡
          #ባህሉስ
ከትንሣኤ እሑድ ጀምሮ እስከ ዳግም ትንሣኤ ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ «እንኳን ጾመ ልጓሙን ፈታላችሁ» እየተባባለ በመጠራራት ዐብሮ ሲበላ ሲጠጣ ልዩ ልዩ ጨዋታ ሲጨዋወት ለንስሐ አባትና ለሽማግሌዎች ለወዳጅ ዘመድም የአክፋይ ዳቦ፣ ወይም የሥጋ ወጥ ግፍልፍል ሲወስድ ይሰነብታል፡

አገልግሎቱን መደገፍ መርዳት ለምትፈልጉ ሃሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላችሁ  በዚህ በኩል ያናግሩን!


@emebtemariyam21bot

📲 @mezmurortodox21📱
📲 @mezmurortodox21📱
15.04.202518:46
የሰሙነ ሕማማት
ሦስተኛው ቀን
#ምክረ አይሁድ
#የመልካም መዓዛ
#የእንባ ቀን




@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
04.05.202519:03
ሰላም ቤተሰብ ዛሬ ከ social media ላይ ያገኘውትን ታሪክ ላካፍላችሁ ነው።ተከታተሉ!!!!!!!!!!


አንድ ዘመኑን በሀጥያት ያሰለፈ ወጣት ንስሀ ለመግባት ይፈልግና ወደ ቤተክርስቲያን ሂዶ የንስሀ አባት ይዞ ንስሀ ይገባል።አባቱም ከ ንስሀው በጨማሪ ሁሌም መፅሀፍ ቅዱስ እንዲያነብ እና ቶሎ ጨርሶ እንዲያስረዱት ነግረው ላኩት።ልጁም እያነበበ እያነበበ አልገባ አልረዳህ ሲለው ወደ አባቱ ሂዶ አባ አቅቶኛል አላቸው።እሺ ልጄ ሌላ ልዘዝህ አሉና የከሰል ማዳበሪያ ይዘው መተው በዚህ ማዳበሪያ ከሀይቅ ውሀ እያመላለስክ ያንን በርሚል ሙላ ይሉታል።ልጁም ተቀብሎ ሲመላለስ ዋለ ነገር ግን ማዳበሪያ ውሀ አይዝምና ሳያደርሰው አፍሶ እየለቀቀ መሙላት አልቻለም።አባቱንም አባቴ ማዳበሪያው እኮ ውሀ አይዝም አላቸው።እሳቸውም አየህ ልጄ ያላስተዋልከው ነገር ማዳበሪያው በከሰል የቆሸሸ ነበር አሁን ግን ፀድቷል አላቸው።ስለዚህ ልጄ መፅሀፍ ቅዱሱንም ስታነብ እግዚአብሔር እንደዚህ ውስጥህን ያፀዳዋል።።አላቸው ይባላል።።።።

እናም ሁልጊዜም መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ ይልመድብን ወደ እግዚአብሔር ያቀርበናልና።።።።

መልካም ምሽት😊😊

@tsedi12m

@yetbebaleme
@yetbebaleme
@yetbebaleme
እረ join እያረጋችሁ አበረታቱን❤
27.04.202518:32
እንኳን ለዳግም ትንሣኤ በሰላም አደረሳችሁ 🙏

               🌹🌹
@AWDEKALAT_2112
                 🌷🌷
25.04.202520:45
✞ ሐሙስ- አዳም ሐሙስ ይባላል፡-

በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡


@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
23.04.202522:20
✝ከትንሳኤ በኋላ ያሉት ቀናት ስያሜ✝

ሰኞ- ማዕዶት ይባላል፡-

ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡


                 🌹🌹
@AWDEKALAT_2112
                 🌷🌷
​​​​ ቅዳሜ
፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧



➦ ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦

ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
➦ ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።



➦ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-

ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።



     ✨🌷 እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን 🌷✨
            ፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧፧



@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
15.04.202504:16
#ሰሙነ ሕማማት

ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ።

በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው።
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦

            📖ሰኞ

መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል፦
በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል።

አንጽሖተ ቤተመቅደስ ይባላል፡-
ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና።

      📖ማክሰኞ

የጥያቄ ቀን ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።

የትምህርት ቀን ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

      📖ረቡዕ

ምክረ አይሁድ ይባላል፦
ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል።

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል፡-
ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል።

የእንባ ቀን ይባላል፡-
ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል።

       📖ሐሙስ

ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፦
ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል።

የምስጢር ቀን ይባላል፡-
ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል።

የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡-
መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድህነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል።

የነጻነት ሐሙስ ይባላል፡-
ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል።

             📖ዓርብ

የስቅለት ዓርብ ይባላል፦
ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል።

መልካሙ ዓርብ ይባላል፡-
ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል።

          📖ቅዳሜ

ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦
ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።

ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-
ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

    @AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
Deleted04.05.202519:41
02.05.202506:16
📥 wave 📥  መግባት የምትፈልጉ 
      
◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦◦
➺ Above  ➣  1k subscribers
➺ Above  ➣  2k+ subscribers
➺ Above  ➣  3k+ subscribers


ከዛም በታች ያላቹ እንዳትመጡ!!  ቦታው ሳይሞላ አፍጥኑት

🅘🅝🅑🅞🅧 @king_negn

FOLDER LINK https://t.me/addlist/_PHX8J2JOmBiYmVk
✞ ቅዳሜ- ቅዱሳት አንስት ይባላል፡-

በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112



🙏🙏🙏
24.04.202518:59
ምናልባት
ወ ደ ፊ ት!
<strike>~</strike>~~~
እኔም ትልቅ ሆኜ
እሄ ትንሽ ልቤ አድጎ ከተገኘ
በ ትላልቅ ሀሳብ ቅኔ ከተቀኘ
~~~~
ዛሬ አሰባስቤ
ያስቀመጥኳቸውን የበደል ጥሪቶች በደሜ መዝግቤ
- - - ነገ በተራዬ
አስረክበዋለው ውስጤን ላቆሰለው ምስጋና ደርቤ

ለምን ቢባልማ

ክፉ ለቸረኝ ሰው ክፋት አላወርስም
ቂም በቀል አልይዝም
ምክንያቱም
- - - **እንኳን እኔ ፍጡሯ
ፈጣሪም ራሱ ምህረት ነው እንጅ ቅጣት አያውጅም!
             
𝕃𝕚𝕜𝕖❤️  𝑆ℎ𝑒𝑟💌  𝗝𝗼𝗶𝗻📥 🙏
     

         @AWDEKALAT_2112   🥇
23.04.202512:16
ፍቅር ይሆን እንዴ ?
___

  አይንሽ
ለማየት የምርበደበደው
ድምፅሽን ስሰማ ባንዴ የምርደው
ስምሽን ሲጠሩት ከተቀምጥኩበት የምነሳው ባንዴ
እኔምን አውቃለሁ ወድጄሽ ነው እንዴ ?

ፍቅር አይመስለኝም ብቻ ናፍቀሺኛል
አብረሺኝ ከሌለሽ  ያቁነጠንጠኛል
ያመኛል ያመኛል
ስጨነቅ ያየ ሰው ፍቅር ነው ይለኛል

ፍቅር ይሆን እንዴ
                ያከሳኝ ሰሞኑን
እንዴት ነው የማውቀው
              አፍቅሬሽ መሆኑን

ስራመድ በድንገት አንቺን እያስታወስኩ
ምኑንም ሳላውቀው ይሀው ቤትሽ ደረስኩ

ላንኳኳ ነበረ እጄ ቦታው ጠፋኝ
ወደቤት ተመለስኩ እንዲያ እንደከፋኝ
አፍቅሬሽ ከሆነ  አልፈልግም በቃኝ 😫



👇🏾👇🏾👇🏾
@AWDEKALAT_2112


""""""""""""""""""""
15.04.202519:49
(...)

የምኞት መጨለም
የትዝታ መናድ
በወዳጅ መጠላት
ባመኑት ሰው መካድ
ሲኖሩት አይደለም
ሲያስቡት ነው ከባድ ።


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ


@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
መርገመ በለስ

የሰሙነ ሕማማት የመጀመሪያው ዕለት ዕለተ ሰኑይ መርገመ በለስ ይባላል፡፡

ጌታችን የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግስቱ ከቢታንያ ሲወጣ ተራበ፤ በመንገድም ሲያልፍ ቅጠል ያላት በለስን ከሩቁ ተመለከተ፡፡ ወደ በለሲቱም በቀረበ ጊዜ ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ያንጊዜም ‹‹ከእንግዲህ ወዲህ ለዘለዓለም ከአንቺ ፍሬ የሚበላ አይኑር›› ሲል በለሲቱን ረገማት፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ይህንን ሰሙት፡፡ በዚህም ምክንያት ይህች ዕለት በለሲቱ የተረገመችባት ቀን ናትና መርገመ በለስ ተብላ ትጠራለች፡፡ (ማር.፲፩፥፲፩-፲፬)

በዚህ አገላለጽ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ስትሆን ፍሬ የተባለ ደግሞ ሃይማኖትና ምግባር ነው፡፡ መድኃኒታችን ክርስቶስ ከእስራኤል ፍቅርን፣ ሃይማኖትን፣ ምግባርን ፈልጎ አላገኘባቸውም፡፡ እስራኤል፦ ሕዝበ እግዚአብሔር፣ የአብርሃም ዘር መባልን እንጂ የአብርሃምን ሥራ በመሥራት በምግባር በሃይማኖት ጸንተው መኖር አይፈልጉምና ደግ ሰው አልተገኘባቸውም፡፡

ከዚህም ባሻገር በለስ የተባለች ኃጢአት ናት፡፡ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አግኝቷታል፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሠሩት ለጊዜው ደስ ያሰኛል ኋላ ግን ያሳዝናል፡፡ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም በአንቺ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ሲል ነው፡፡ በለሲቱ ስትረገም ፈጥና መድረቋም በአዳም ምክንያት ያገኘን በደል በእርሱ እንደጠፋልን ለመግለጽ ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
💚 @Mahdere_tewahedo 💚
💛  @Mahdere_tewahedo 💛
❤️ @Mahdere_tewahedo ❤️
01.05.202519:24
አንቺን አገኝ ብዬ
:
ሴትን የመማረክ ቁልፍ ሚስጥራቶች
ሃያ አራቱ ድብቅ የመግባቢያ ስልቶች
ሰባቱ ታላላቅ የፍቅር መንገዶች
ዘጠና ዘጠኙ ግሩም አባባሎች
አራቱ የሴት ልጅ፣ ያልተቃኙ ቅፆች
ሁለቱ የፍቅር፣ ተለዋዋጭ ገፆች
:
:
ብለው የተፃፉ
ወ.ዘ.ተ  መፅሐፍትን እንደሸመደድኩት
ሳነብ ስታትር፣ ውዬ እንዳደርኩት!
አታውቂም!

አንቺን አገኝ ብዬ
:
እንደሚያገባ ሰው ሽርክርክ ብዬ
ጀነን ኮራ እያልኩ ከደጃፍሽ ውዬ
አመሻሽ መመለስ በብስጭት በቂም
የዘውትር ተግባሬ መሆኑን አታውቂም።

አንቺን አገኝ ብዬ
:
ጓደኞቼን ልኬ፣ ገፍተው እንዲነኩሽ
እራሴው መጥቼ፣ የውሸት ያዳንኩሽ
ስታመሰግኝኝ በደስታ ስትስቂም
ለፍቅርሽ ውለታ መሆኑን አታውቂም።
:
አንቺ አገኝ ብዬ
የጥንዱን ቤት ሳይቀር እንደመረመርኩኝ
ገፃቸውን ሁሉ ፎሎ እንዳረኩኝ
አታውቂም!
:
አንቺን አገኝ ብዬ
የልቤን አርግቤ ናፍቆቴን ባልቆርጥም
ለፍቅርሽ ስጦታ የፃፍኩልሽ ግጥም
ዛሬ ካንቺ ጋራ በልቤ ውስጥ አድጎ
እዛው እንዳስቀረኝ ገጣሚ አድርጎ
አታውቂም!
:
አንቺን አገኝ ብዬ
ፍልስፍናን ግቼ ስለፍቅር መንገድ
ጓዝ ጥቅልሉ ሳይቀር ቢኖረው ብዬ ገድ
ሳነበው... ስፅፈው፣ ዘመን እንደፈጀው
የፍቅር ፈላስፋ ሆኜ እንዳረጀው።
አታውቂም!




@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112



        ✨......✨......✨
         ✨......⭐️........✨

  ——¯_✨—⭐️—_—✨¯_
✞ አርብ- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይባላል፡-

በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡



@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112

         🦋🦋🦋
✞ ረቡዕ- አልአዛር ይባላል፡-

በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥና የባህርይ አምላክ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡


                 🌹🌹
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
                 🌷🌷
""" ሕያዉን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ ?  ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም።"""  ሉቃ ፪፬ ÷  ፭
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤
አሰሮ ለሰይጣን፤
አግዐዞ ለአዳም፤
ሠላም ፤
እምይዕዜሰ ፤
ኮነ፤
ፍስሐ ወሠላም፡፡”
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤ በአል በሰላም አደረሳቹ😊

💙💙💙 መልካም በዓል 💙💙💙

@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
15.04.202519:49
የሰሙነ ሕማማት
ሦስተኛው ቀን
#ምክረ አይሁድ
#የመልካም መዓዛ
#የእንባ ቀን




@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
ሆሳዕና በአርያም 🌿🌿🌿🌿


እንኳን ለ ሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🌿🌿🌿🌿

@AWDEKALAT_2112
@AWDEKALAT_2112
Shown 1 - 24 of 38
Log in to unlock more functionality.